TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የፌደራል መንግሥት የ2013 ዓ/ም ተጨማሪ በጀት ሆኖ የፀደቀውን 26 ቢሊዮን ብር ከሀገር ውስጥ ባንክ በብድር መውሰድ እንዲችል የቀረበለትን የውሳኔ ሀሳብ በሙሉ ድምፅ አፀደቀ፡፡

ተጨማሪ በጀቱ በድርቅ የተጎዱ እና በግጭት የተፈናቀሉ ዜጎችን ለመደገፍ እንዲሁም ኮቪድ-19 ያስከተለውን የኢኮኖሚ ተፅእኖ ለመቋቋም እና ለተለያዩ ተግባራት የሚውል መሆኑ ተገልጿል፡፡ #ኢብኮ

@tikvahethiopia
#ምርጫ2013

“... ምርጫው ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት ተደርጓል” - አቶ ተመስገን ጥሩነህ

ኢትዮጵያ የምታካሂደው ሀገራዊ ምርጫ በሰላም እንዲጠናቀቅ የፌዴራል እና የክልል የደህንነትና የፀጥታ መዋቅር በቂ ዝግጅት ማድረጋቸው ተገለፀ።

ይህን የገለፁት የብሔራዊ ደህንነትና መረጃ አገልግሎት ዳይሬክተር ጀነራል አቶ ተመስገን ጥሩነህ ናቸው።

የፌዴራል እና የክልል የደህንነት እና የፀጥታ አካላታ ግብረሐይል በወቅታዊ የሀገሪቷን ደህንነት የሚገመግም እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን የሚያስቀምጥ ውይይት እያደረጉ ይገኛሉ።

በዚሁ ወቅት አቶ ተመስገን ጥሩነህ ቀጣዩ የምርጫና ድህረ ምርጫ ሰላማዊ እንዲሆን በቂ ዝግጅት መደረጉን ተናግረዋል።

የፌዴራል እና ክልል የፀጥታ እና ደህንነት አካላት የጋራ ግብረ ሀይል የሀገረቷን ወቅታዊ የደህንነት ሁኔታ በመገምገም ቀጣይ አቅጣጫዎችን ያስቀምጣሉ ተብሏል። #ኢብኮ

@tikvahethiopia
የአረብ ሊግ ስብሰባ እና የኢትዮጵያ ምላሽ :

የዐረብ ሊግ የተመድ ጸጥታው ም/ቤት ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየገነባች ባለችው ታላቁ የሕዳሴ ግድብ ዙሪያ ስንብሰባ እንዲያደርግ ትላንት ባደረገው ስበባ ጠይቋል።

የሊጉ አባል አገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ባደረጉት ሰብሰባ የሁሉንም አካላት ፍላጎት የሚያሳካ አስገዳጅ ስምምነት ላይ መደረስ እንዳለበት አንስተዋል።

የዐረብ ሊግ አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች በአፍሪካ ህብረት አስተባባሪነት እየተካሄደ ያለውን ድርድር አዝጋሚ ነው ሲል ገልጾታል።

ሚኒስትሮቹ በኳታር መዲና ዶኃ ባደረጉት ስብሰባ በአፍሪካ ሕብረት ስር እየተካሄደ ያለው ድርድር አዝጋሚ በመሆኑ የጸጥታው ም/ቤት በግድቡ ዙሪያ ስብሰባ እንዲያደርግ ጥሪ አቅርበዋል።

የሊጉ ዋና ፀሀፊ አህመድ አብዱል ጌት እንዳሉት የግብፅና የሱዳን የውሃ ደህንነት ጉዳይ የዐረብ ሀገራት ደህንነት አካል መሆኑን መግባባት ላይ መደረሱን አስታውቀዋል።

የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ የዐረብ ሊግ ለሱዳን እና ለግብፅ ድጋፍ እንዳለውም ዋና ጸሐፊው ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ የአረብ ሊግ የህዳሴው ግድብን በተመለከተ በኳታር ተወያይቶ ያሳለፈው ውሳኔ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል አሳውቃለች።

የአረብ ሊግ የግብጽ እና የሱዳንን መሰረተ ቢስ ውንጀላ ላይ ሳይመሰረት በህዳሴ ግድቡ ድርድር ዙሪያ ገንቢ ሚና መጫወት ሲገባው ሚዛናዊነት የጎደለው እና ወደ አንድ ወገን ያደለ ውሳኔ መወሰኑ ተቀባይነት እንደሌለው ገልጻለች።

ውሳኔው በቀጠናው የአባይን ወንዝ በትብብርና በዘላቂነት ለመጠቅም የሚያስችል መንገድ አለመሆኑንም አሳውቃለች።

የአርብ ሊግ አባል ሀገራት የአባይ ወንዝን አጠቃቀም እና የኢትዮጵያን ነባር አቋም በሚገባ ሊያውቁ ይገባቸዋልም ብላለች።

#ኢብኮ #አልዓይን

@tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ሪጅን የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎትን አሰጀመረ !

በደቡብ ሪጅን የተጀመረው የ4ጂ አድቫንስድ አገልግሎት ሀዋሳ፣ ሻሸመኔ እና ቡሌ ሆራን ጨምሮ 12 ከተሞችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሏል።

አገልግሎቱ የኢንተርኔት እና ሌሎች በኩባንያው የሚቀርቡ አገልግሎቶች በተሻለ ፍጥነት ለማግኘት ያስችላልም ነው የተባለው።

ኩባንያው ከፍተኛ የኢንተርኔት አጠቃቀም በሚታይባቸው 103 ከተሞች የ4ጂ .ኤል.ቲ.ኢ አገልሎትን ለማሰፋፋት እየሠራ የሚገኝ ሲሆን እሰከአሁን ባደረጋቸው የኔትወርክ ማስፋፊያ ስራዎች 65 ከተሞችን ተጠቃሚ አድርጓል።

የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ሰራ አሰፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ በአዲስ አበባ ከተማ ተወሰኖ የቆየውን የ4ጂ አገልግሎት ወደ ክልሎች በማስፋፋት ለሀገሪዊ ጥቅል ዕድገት እንዲያግዝ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የ4ጂ ኤል.ቲ.ኢ አድቫንስድ አገልግሎት ከ3ጂ አንፃር በ14 እጥፍ በተሻለ ፍጥነት አገልሎት ለማገኘት የሚያሰችል እንደሚሆን ተናግረዋል።

127 ዓመት እድሜ ያለው ኢትዮ ቴሌኮም በርካታ ማሻሻያዎች በማድረግ ለደንበኞች የተሻለ አገልግሎት ለማቅረብ እየሠራ ይገኛል ብለዋል።

ኩባንያው በአጠቃላይ በመላ ሀገሪቱ 55 ነጥብ 4 ሚሊዮን ደንበኞች ሲኖሩት ከዚህ ውስጥ 25 ነጥብ 5 ሚሊዮን ያህሉ የኢንተርኔት ተጠቃሚ መሆናቸው ተገልጿል።

#ኢብኮ

@tikvahethiopia