TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.1K photos
1.5K videos
211 files
4.09K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Tokyo2020

የ12 ዓመቷ ሶሪያዊ ታዳጊ በቶኪዮ ኦሎምፒክ !

በዘንድሮው የቶኪዮ 2020 ኦሎምፒክ ከሚሳተፉ ሀገራት መካከል ሶርያ ትገኝበታለች።

በውድድሩ ላይ በእድሜ ትንሿን ተወዳዳሪ የምታሳትፈው ሶርያ ስትሆን ተወዳዳሪዋ የ12 ዓመቷ ሄንድ ዛዛ ናት ፤ ዛዛ በጠረጴዛ ቴኒስ ነው ሀገሯን ሶሪያ ወክላ በዓለም አቀፉ ውድድር የሚትፋለመው።

የቶኪዮ በእድሜ ትንሿ ተወዳዳሪ ሄንድ ዛዛ በ ኦሎምፒክ የ መጀመሪያ ጨዋታዋ ብትሸነፍም ሌሎች ሕፃናት “ ሕልማቸውን እንዲከተሉ ” ታበረታታለች።

በልጅነቷ በሀገሯ በጦርነት የተጎዳችው ዛዛ ወደ ውድድሩ ለመድረስ “ብዙ የተለያዩ ችግሮችን” ማለፍ እንደነበረባት ተናግራለች።

የቶኪዮ መረጃዎችን ይከታተሉ : @tikvahethsport
#Tokyo2020

ታዳጊዋ ለሀገሯ ወርቅ አስገኘች !

የ13 ዓመቷ ጃፓናዊት የ #SkateBoard ተወዳዳሪ ሞሚጂ ኒሺያ ለሀገሯ ጃፓን በውድድር ዘርፉ የመጀመሪያውን ወርቅ አስገኝታለች።

ሞሚጂ ኒሺያ በ ታሪክ ለ ሀገሯ ወርቅ ያስገኘች በ እድሜ ትንሿ ተወዳዳሪም ለመሆን በቅታለች ።

@tikvahethsport
#Ethiopia 🇪🇹 #Tokyo2020

ኢትዮጵያ በቶኪዮ ኦሎምፒክ የመጀመሪያውን ዲፕሎማ አግኝታለች።

በወርልድ ቴኳንዶ የመጀመሪያ ተሳትፎን በኦሎምፒክ ያደረገው ሰለሞን ቱፋ 7ኛ ደረጃን በ መያዝ ዲፕሎማውን መረከቡን #EOC አሳውቋል።

Via @tikvahethsport
#ETHIOPIA 🇪🇹 #Tokyo2020

ዛሬ ሌሊት ከ9፡00 ሰዓት ጀምሮ በሚደረጉ የአትሌቲክስ ውድድሮች ላይ የአለም አትሌቲክስ ባወጣው የተወዳዳሪዎች ዝርዝር መሰረት ከዚህ በታች የተገለፁ የሀገራችን አትሌቶች ውድድሮቻቸውን የሚያካሂዱ ይሆናል።

በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ ፦
- ሀብታም አለሙ
- ነፃነት ደስታ
- ወርቅውሃ ጌታቸው

በ3000 ሜትር መሰናክል ወንዶች ማጣሪያ ፦
- ጌትነት ዋለ
- ለሜቻ ግርማ
- ታደሰ ታከለ

ድል ለሀገራችን🇪🇹ኢትዮጵያ !

@tikvahethsport
#Tokyo2020 🇪🇹 #ETHIOPIA

ሰለሞን ባረጋ ወርቁን አጥልቋል !

በትላንትናው ዕለት ለኢትዮጵያ የመጀመሪያው ወርቅ ያስገኘው ሰለሞን ባረጋ ከደቂቃዎች በፊት ከቀድሞው የኬንያ አትሌት እና ከአሁኑ የ ኬንያ ኦሎምፒክ ኮሚቴ ፕሬዝዳንት ፖል ቴርጋት ወርቁን ተረክቦ አጥልቋል።

ኢትዮጵያ በሜዳሊያ ሰንጠረዡ ከዓለም ሰላሳ ሰባተኛ ላይ ስትቀመጥ ከአፍሪካ በሜዳሊያ ዝርዝር ውስጥ ከደቡብ አፍሪካ እና ቱኒዚያ በመቀጠል ሶስተኛ ላይ ተቀምጣለች።

@tikvahethsport