TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 
#USAID #OCHA

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) አሳስቧል።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በሌላ መረጃ ፦ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም USAID/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር የትግራይ ግጭት እጅግ የከበደ ረሃብ እያስከተለ እንደሆነ እና ከ5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል።

ሳምንታ ፓዎር "የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቅኝታችን አጣዳፊ የምግብ ችግር መኖሩን ይጠቁማል" ያሉ ሲሆን ችግሩ እጅግ አስከፊው ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጲያ መንግሥት ግጭቱን ለማቆም እንዲሁም የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ እንዲችሉ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ ገልፀዋል። #VOA

@tikvahethiopia
"... እስራኤል ራሷን ከጥቃት መከላከል መብቷ ነው " - አንቶኒ ብሊንከን

የኤሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንተኒ ብሊንከን እስራኤል እና ሃማስ ባለፈው ሳምንት ያደረጉትን የተኩስ አቁም ሥምምነት ለማጎልበት ወደመካከለኛው ምስራቅ ይገኛሉ።

ትላንት ማክሰኞ በእየሩሳሌም ጉብኝታቸው፣ እስራኤል ራሷን ከጥቃት መከላከል መብቷ መሆኑን አጥብቀው ሲናገሩ ተደምጠዋል።

ብሊንከን ከእስራኤል ጠ/ሚር ቢኒያሚን ኔታንያሁ ጋር ሆነው በሰጡት መግለጫ በውጊያው እስራኤልም ፍልስጥኤማውያንም ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል ብለዋል።

ለመጻኢው ጊዜ ተስፋ፣ መከባበር እና መተማመንን ለማስፈን ብዙ ሥራ መሰራት ይኖርበታል ሲሉ አሳስበዋል።

ሰው ላይ የሚደርሱ ጉዳቶች ብዙውን ጊዜ በቁጥር ደረጃ ዝቅ ተደርገው የሚገለጹ ቢሆንም በእያንዳንዷ ቁጥር የሚገለጸው አባት፣ እናት፣ ልጅ፣ አያት፣ ጓደኛ ሰብዓዊ ፍጡር ነው።

ጥንታዊው የአይሁድ ሃይማኖታዊ ህግ እንደሚያስተምረውም፣ ህይወት ሲጠፋ የእስራኤላዊም ይሁን የፍልሥዔማዊ ህይወት መጥፋት ከመላው ዓለም መጥፋት የሚቆጠር ነው ብለዋል።

አሜሪካ ሃማስ በማይጠቀምበት መንገድ ጋዛን መልሶ ለመገንባት ዓለም አቀፍ ድጋፍ ለማሰባሰብ ትሰራለች ሲሉም ተደምጠዋል።

ብሊንከን ፥ በጋዛ እና በዌስት ባንክ ለሚኖሩ ፍልስጤማውያን የኢኮኖሚ ዕድሎችን ለማጎልበት እንሰራለን ሲሉ ቃል የገቡንሲሆን እስራኤልንም ፍልስጥኤሞችንም የሚጠቅም የተረጋጋ ድባብ ሊያመጣ ይችላል ብለዋል።

አንቶኒ ብሊንከን ከፍልስጤም ፕሬዚደንት ማህሙድ አባስ እና ከጠ/ሚ ማሃማድ ሲታዬህ ጋር በራማላህ ተገናኝተው አሜሪካ የምታሰጠውን እርዳታ ይፋ አድርገዋል። #VOA

@tikvahethiopia