TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
 
#USAID #OCHA

በትግራይ የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች ችግር ላይ ያሉ ማህበረሰቦችን ለመድረስ በሚያደርጉት እንቅስቃሴዎች ላይ የሚገጥማቸው መሰናክል ተባብሷል ሲል የተመድ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ (OCHA) አሳስቧል።

አጣዳፊ የምግብ እርዳታ ከሚያስፈልገው 5.2 ሚሊዮን ህዝብ ውስጥ ከመጋቢት ወር መጨረሻ ወዲህ ለመድረስ የተቻለው 1.8 ሚሊዮኑን ብቻ ነው ብሏል።

በክልሉ አሁን ካለው የከፋ የተመጣጠነ ምግብ ዕጥረት እንዳይከሰት አስቸኳይ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያስፈልግ ያስታወቀው ኦቻ እርዳታ ለሚያስፈልጋቸው ሁሉ እስከዚህ የአውሮፓ 2021 ማብቂያ ድረስ በቂ እርዳታ ለማቅረብ 853 ሚሊዮን ዶላር እስከፊታችን ሃምሌ መጨረሻ ደግሞ 200 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ያስፈልጋል ብሏል።

በሌላ መረጃ ፦ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ልማት ተራድዖ ድርጅት ወይም USAID/ አስተዳዳሪ ሳማንታ ፓወር የትግራይ ግጭት እጅግ የከበደ ረሃብ እያስከተለ እንደሆነ እና ከ5 ሚሊዮን የሚበልጥ ህዝብ እርዳታ የሚያስፈልገው መሆኑን አሳስበዋል።

ሳምንታ ፓዎር "የቅድመ ማስጠንቀቂያ ቅኝታችን አጣዳፊ የምግብ ችግር መኖሩን ይጠቁማል" ያሉ ሲሆን ችግሩ እጅግ አስከፊው ደረጃ ላይ ደርሷል ብለዋል።

የኢትዮጲያ መንግሥት ግጭቱን ለማቆም እንዲሁም የሰብዓዊ ረድዔት ሠራተኞች የተቸገረውን ህዝብ ለመድረስ እንዲችሉ አሁኑኑ እርምጃ መውሰድ አለበት ሲሉ ገልፀዋል። #VOA

@tikvahethiopia