TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
* Update ኦሮሚያ ክልል አሊደሮ በተባለው አካባቢ በ14/09/2013 ዓ.ም ምሽት ላይ በደረሰው የመኪና መቃጠልና በሰዎች ላይ በደረሰ አደጋ ምክንያት ከአማራ ክልል ወደ አዲስ አበባ የሚደረግ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ በ15/09/2013 ዓ.ም ከጠዋቱ 12 ሰዓት ጀምሮ መቋረጡን የደጀን ወረዳ ኮሚኒኬሽን አስታውቋል። @tikvahethiopia
"...የሾፌሮችን እንቅስቃሴ ከስጋት ነጻ ለመድረግ ከኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገርን ነው" - ኮማንደር ቢምረው አሰፋ

በአሽከርካሪዎች ላይ የሚደርሰውን ግድያ እና የንብረት ዘረፋ መንግስት ባለማስቆሙ ለስራቸው አስቸጋሪ እንደሆነባቸው በምስራቅ ጎጃም ዞን ደጀን ከተማ የሚገኙ እና ከተለያዩ አካባቢዎች የመጡ አሽከርካሪዎች ለወረዳው ኮሚኒኬሽን ቢሮ ተናግረዋል።

በኦሮሚያ ክልል በተለይ ደግሞ "አሊ ዶሮ" ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በተደጋጋሚ በታጠቁ ሀይሎች በሾፌሮች ላይ ግድያና የንብረት ዘረፋ እየተፈጸመ መንግስት አልታደገንም ሲሉ ያለውን አስቸጋሪ ሁኔታ በምሬት አስረድተዋል።

እነዚሁ ሾፌሮች እንደሚሉት መንግስት ባለበት ሀገር የስጋት ቦታዎችን ለይቶ መቆጣጠር ባለመቻሉ ከቀን ወደ ቀን በመንገዱ ለመንቀሳቀስ አሳሳቢ ሆኖብናል ብለዋል፡፡

የደጀን ወረዳ ፖሊስ ጽ/ቤት ሃላፊ ኮማንደር ቢምረው አሰፋ ስለጉዳዩ ተጠይቀው ምላብ ሰጥተዋል።

ኮማንደሩ ፥ ችግሩ እንዳለ ገልጸው ዘላቂ መፍትሄ ለማጣትና የሾፌሮችን እንቅስቃሴ ከስጋት ነጻ ለመድረግ ከኦሮሚያ ክልል ሃላፊዎች ጋር እየተነጋገሩ እንደሆነ አብራርተዋል፡፡

ከተለያዩ የአማራ ክልል ከተሞች ወደ አዲስ አበባ በመጓዝ ላይ የነበሩ አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎች የመንገዱን የጸጥታ ስጋት በመፍራት ደጀን ከተማ ላይ እየተጉላሉ እንደሚገኙ የደጀን ወረዳ አሳውቋል።

@tikvahethiopia
ታጣቂዎች በፈፀሙት ጥቃት 1 የመንግስት ባለስልጣን ጨምሮ 7 ሰዎች ተገደሉ።

በምዕራብ ጉጂ ዞን ገላና ወረዳ በተፈጸመ ጥቃት የወረዳው ጸጥታ እና አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊን ጨምሮ 7 ሰዎች ተገደሉ።

ጥቃቱን የፈፀሙት የ "ሸኔ ታጣቂዎች" መሆናቸውን የወረዳው ፖሊስ ጽ/ቤት አስታውቋል።

የፖሊስ ጽህፈት ቤቱ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ኦብሳ ሁንዴሳ፥ "የአሸባሪው ሸኔ ታጣቂዎች ግድያውን የፈጸሙት ትናንት አመሻሽ 11:00 ሰዓት አካባቢ በወረዳው ሾሮ ጫልቤሳ ቀበሌ ነው" ብለዋል።

የወረዳው አመራሮች የልማት ስራዎች እየጎበኙ ባሉበት ወቅት በሸኔ ታጣቂዎች የደፈጣ ጥቃት እንደተፈጸመባቸው ኮማንደር ኦብሳ ገልፀዋል።

በጥቃቱ የወረዳው ጸጥታ እና አስተደደር ጽህፈት ቤት ሃላፊን ጨምሮ 7 ሰዎች ተሰውተው በሌሎች 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሷል ሲሉ አስረድተዋል።

በአሁኑ ወቅት ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ዲላ ሪፈራል ሆስፒታል የህክምና እርዳታ እየተደረገላቸው እንደሚገኝም ጠቁመዋል።

ጥቃት ያደረሱ አሸባሪዎችን የማደኑ ስራ በጸጥታ አካላት በቅንጅት እየተከናወነ እንደሚገኝ አዛዡ አስታውቀዋል።

የጥፋት ቡድኑን ከወረዳው ነጻ ለማድረግ የተጀመረው ዘመቻ እንዲሳካ ህብረተሰቡ ለመንግስት ያለውን ድጋፍና ትብብር ያጠናክር ሲሉም ጥሪ አቅርበዋል።

የገላና ወረዳ መንግስት ኮሙኒኬሽን ሃላፊ አቶ ገበየሁ ያደቴ የወረዳውን ህዝብ በተለይ ጥቃቱ የተፈጸመበትን የሾሮ ጫልቤሳ ነዋሪዎችን በማረጋጋት አካባቢው ወደ ቀድሞ ሰላሙ እንዲመለስ እየተሰራ መሆኑን አስታውቀዋል።

"የተሰዉ አመራሮችን በክብር ለመቅበር ዝግጅት እየተደረገ ይገኛል" ሲሉ መናገራቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,376 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 293 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነው ተገኝተዋል፤ ይህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 269,194 አድርሶታል።

በ24 ሰዓት ውስጥ የስምንት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,076 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,655,244 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia
አሜሪካ ፦

- በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት ፣ በወታደራዊና የደህንነት ሹማምንት፣

- በአማራ ክልል አስተዳደርና የፀጥታ መዋቅር መሪዎች፣

- በወንጀል የተሳተፉ የሕወሓት (TPLF) መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች።

አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የኢኮኖሚ ማበረታቻ እና የፀጥታ ድጋፍ ታቋርጣለች።

የስብዓዊ ዕርዳታ እንዲሁም ለትምህርት፣ ግብርናና ጤና ለመሳሰሉት የሚደረገው የልማት ዕርዳታ ግን ይቀጥላል።

አሜሪካ ማዕቀቡን ለመጣል የወሰነችው የትግራዩ ጦርነት እንዲቆምና የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ እንዲወጡ ፣ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት እንዲሻሻል እንዲሁም ተፋላሚ ወገኖች ወደ ድርድር እንዲመጡ ያቀረብኩት ሀሳብ ተቀባይነት አላገኘም በሚል ነው።

የጉዞ ማዕቀቡ የትኞቹን ባለስልጣናት እንደሚመለከት መግለጫው አልዘረዘረም።

በኢትዮጵያ ሆነ በኤርትራ ባለስልጣናትና በሕወሓት አንዳንድ አባላት ላይ የተጣለው እገዳ የጠቀሰው ደንብ ቁጥር (Section 212a) ሲሆን በዚህ ደንብ መሰረት የማዕቀቡ ዒላማ የሆኑት ባለስልጣናትን ስም ለህዝብ ይፋ ማድረግን አይጠይቅም።

በተለምዶ ለከፋ የስብዓዊ መብት ረገጣና ሙስና ጉዳዮች ስራ ላይ የሚውለው የማዕቀብ አይነት (Section 7031c) ሲሆን ማዕቀቡ የሚመለከታቸው ባለስልጣናትና ግለሰቦች ስም ዝርዝር በአሜሪካ የውጪ ጉዳይ መ/ቤት በኩል ለህዝብ ይፋ እንዲደረግ ያዛል።

በሰብዓዊ መብት ጥሰት ግድያና መሰል ወንጀሎች የተሳተፉ ወገኖችን ኢትዮጵያም ሆነች ኤርትራ ለፍርድ እንዲያቀርቡ የአሜሪካ መግለጫ ይጠይቃል።

ባለፈው ሳምንት የአሜሪካ የህግ መወሰኛ ም/ ቤት በትግራይ ጦርነት የሚሳተፉ ወገኖች ላይ የጉዞና የኢኮኖሚ ማዕቀብ እንዲደረግ የሚጠይቅ ውሳኔ አሳልፎ ነበር።

ምንጭ፦ www.wazemaradio.com

@tikvahethiopia
የቴሌግራፍ ሪፖርትና የመንግስት ምላሽ:

ትላንት ቴሌግራፍ የተባለው ጋዜጣ ባወጣው ሪፖርት በሰሜን ኢትዮጵያ (ትግራይ) የሚገኙ ሲቪሎች ከ 'ነጭ ፎስፈረስ' ጋር ተመሳሳይ የሆነ አሰቃቂ የቃጠሎ አደጋ ደርሶባቸዋል ፥ ይህም የጦር ወንጀል ሊሆን ይችላል ብሏል።

ቴሌግራፍ ጋዜጣ ከትግራይ ተገኙ ባላቸው ምስክሮች ፣ ተጎጂዎች እና ልዩ ምስሎች የኢትዮጵያ እና የኤርትራ ጦር በሲቪል አከባቢዎች ኃይለኛ የሆነና በከፍተኛ ሁኔታ የሚነድ መሳሪያ ተጠቅመው ሊሆን ይችላል ሲል ገልጿል።

አናገርኳቸው ያላቸው የኬሚካል የጦር መሣሪያ ባለሞያዎች ከትግራይ ተቀረፀው የወጡት ምስሎች በዓለም አቀፍ ሕግ በሰው ዒላማዎች ላይ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ከሚከለከለው ከ 'ነጭ ፎስፈረስ' ጋር ተመሳሳይነት ያለው ነው ስለማለታቸው አስነብቧል።

ከተጎጂዎቹ መካከል በማዕከላዊ ትግራይ የ 'አዲአይቆሮ' መንደር ነዋሪ የሆነች የ13 ዓመት ታዳጊ ኪሳነት ገብረሚካኤል የምትገኝበት ሲሆን ሚያዚያ 20 ቤቷ ጥቃት ሲሰነዘርበት ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶባታል ብሏል።

ሌላኛው ተጎጂ፥ በምስራቅ ትግራይ አዲዎልዎ መንደር ነዋሪ የሆነው የ18 ዓመት ወጣት የማነ ወልደሚካኤል ሲሆን እሱም በተመሳሳይ ከፍተኛ ቃጠሎ ደርሶበታል።

የቴሌግራፍ ዘገባ 👇
telegraph.co.uk/news/2021/05/23/exclusive-ethiopians-suffer-horrific-burns-suspected-white-phosphorus/amp/

የኢትዮጵያ መንግስት ምላሽ ?

የኢፌዴሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በትግራይ 'የኬሚካል ጦር መሳሪያ' አጠቃቀም አስመልክቶ 'ቴሌግራፍ' ያወጣውን ዘገባ መመልከቱን ገልጿል።

የቀረበውን ክስም ውድቅ አድርጓል። ኢትዮጵያ የታገዱ መሳሪያዎችን አልተጠቀመችም በጭራሽ አትጠቀምም ብሏል።

ያንብቡ: telegra.ph/Tikvah-05-24

@tikvahethiopia
#AmbassadorTayeAtskeSelassie

በተመድ (UN) የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ አምባሳደር ታዬ አጽቀስላሴ ፥ ኢትዮጵያን ለማዳከምና አንድነቷን ለማናጋት ከየትኛውም የውስጥም ሆነ የውጭ አካል የሚሰነዘር ትንኮሳና ጫናን በአንድነት መመከት እንደሚገባ ተናገሩ።

አምባሳደሩ ይህን ያሉት በተ.መ.ድ የኢፌዴሪ ቋሚ መልዕክተኛ ፅ/ቤት አስተባባሪነት በአሜሪካ ኒውዮርክ፣ ኮኔክትከት እንዲሁም በሌሎች ስቴቶች የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያዊያን ጋር በተደረገ የኦንላይን ውይይት ነው።

አምባሳደሩ ፥ ምዕራባዊያን በኢትዮጵያ ላይ እያሳዩት ያለው ያልተገባ ጣልቃ ገብነት ምን ይዘት እንዳለው በተለይ ሰሞኑን የአሜሪካ ሴኔት ያወጣውን ሪዞልሽን ምንነት፣ እንዲሁም በተመድ በፀጥታው ም/ቤት ይቀርቡ የነበሩትን ጉዳዮች በዝርዝር አስረድተዋል፡፡

በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ የሚቀርቡትን የተሳሳቱ አመለካከቶች እና እንቅስቃሴዎችን መመከት እንደሚያስፈልግ አንስተዋል።

ዳያስፖራው ባለበት አካባቢ የሚገኙ ፦ ተፅእኖ ፈጣሪ የሆኑ ግለሰቦችን፣ የፓርላማ አባላትንና የሚዲያ ተቋማትን አግኝቶ ኢትዮጵያን በተመለከተ እውነታውን የማስረዳት እና ማስገንዘብ የሚጠበቅ ተግባር መሆኑን በማስገንዘብ ከዚህ አንጻር የተጀመሩ ስራዎች ተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው አሳስበዋል።

ከዚህም በተጨማሪ አምባሳደሩ ታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ሁለተኛ ዙር ሙሌት ሂደትንና መጭው 6ኛው ሀገራዊ ምርጫን በተመለከተ መልዕክት ማስተላለፋቸውን ኢፕድ አስነብቧል።

@tikvahethiopia
የቤንች ሸኮ ዞን ም/ቤት አስቸኳይ ጉባኤውን ዛሬ ያካሂዳል።

ምክር ቤቱ 4ኛ ዙር 8ተኛ ዓመት የሥራ ዘመን 3ተኛ አስቸኳይ ጉባኤውን ነው የሚያካሂደው።

በወጣው መርሃ ግብር መሰረትም የዞኑ ወቅታዊ ሰላምና ፀጥታ ሁኔታ ላይ እና የሚዛን አማን አውሮፕላን ማረፊያ ግንባታን በተመለከተ ምክር ቤቱ መክሮበት አቅጣጫ ያስቀምጣል ተብሎ ነው የሚጠበቀው።

መረጃው የዞን ኮሚኒኬሽን ቢሮ ነው።

@tikvahethiopia
#ማስታወሻ

በ2012 ዓ/ም የትምህርት ዘመን የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ወስደዉ ቅሬታ ያቀረቡ ተማሪዎች ዳግም ምደባ ከዛሬ ግንቦት 16 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ በበየነ መረብ መመልከት ይችላሉ።

@tikvahethiopia
#NEAEA

የ2013 የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ግንቦት 29 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚሰጥ በአንዳንድ የማህበራዊ ትስስር ገፆች እየተሰራጨ ያለው መረጃ ትክክለኛ አይደለም ተብሏል።

ፈተናው መቼ እንደሚሰጥ ገና #አለመወሰኑን የሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ ለቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ @tikvahuniversity አረጋግጧል።

የኤጀንሲው የሕዝብ ግንኙነት እና ኮሚዩኒኬሽን ዳይሬክተር ረዲ ሽፋ ፈተናው የሚሰጥበት ቀን አሁንም ገና እንዳልተወሰነ ገልፀዋል።

ኤጀንሲው የመጨረሻ ውሳኔ ላይ ሲደረስ ይፋዊ የሆነ መግለጫ እንደሚሰጥ ተናግረዋል።

Tikvah-University t.iss.one/joinchat/RYD_4tbNBwRoKR2h

@tikvahuniversity @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
አሜሪካ ፦ - በኢትዮጵያና በኤርትራ ባለስልጣናት ፣ በወታደራዊና የደህንነት ሹማምንት፣ - በአማራ ክልል አስተዳደርና የፀጥታ መዋቅር መሪዎች፣ - በወንጀል የተሳተፉ የሕወሓት (TPLF) መሪዎች ላይ የጉዞ ማዕቀብ ጣለች። አሜሪካ ለኢትዮጵያ ትሰጥ የነበረውን የኢኮኖሚ ማበረታቻ እና የፀጥታ ድጋፍ ታቋርጣለች። የስብዓዊ ዕርዳታ እንዲሁም ለትምህርት፣ ግብርናና ጤና ለመሳሰሉት የሚደረገው የልማት ዕርዳታ…
"...የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር ያሳለፈው የቪዛ ክልከላ አግባብነት የሌለውና አሳዛኝ" - የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር

(ኤፍ ቢ ሲ)

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የፕሬዜዳንት ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ላይ ያሳለፈው የቪዛ ክልከላ ውሳኔ አግባብነት የሌለው መሆኑን አስታወቀ፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ የስራ ሃላፊዎች ላይ የቪዛ ክልከላ ውሳኔ ማሳለፉ ታወሳል፡፡

ሚኒስቴሩ ፥ የባይደን አስተዳደር በኢትዮጵያ ላይ አላስፈላጊ ጫና ለመፍጠር ያሳለፈው የቪዛ ክልከላ አግባብነት የሌለውና አሳዛኝ መሆኑን ገልጿል፡፡

አሁን የተላለፈው ውሳኔ ኢትዮጵያ ከአሜሪካ ጋር በጋራ በሆኑ ጉዳዮች ላይ አወንታዊና ገንቢ በሆነ መልኩ መስራት በጀመረበት ወቅት መሆኑን አንስቷል፡፡

ከዚህ ባለፈም በሃገሪቱ አዲስ የፖለቲካ ትሩፋቶችን ያመጣል ተብሎ የሚጠበቀው ሃገራዊ ምርጫ ሊካሄድ በተቃረበበት ወቅት የተወሰነ የተሳሳተ ውሳኔ መሆኑንም ጠቅሷል፡፡

6ኛው ሃገራዊ ምርጫ አካታች ለሆነ ፖለቲካዊ ውይይት ምቹ ሁኔታን ይፈጥራል ያለው መግለጫው፥ ከዚህ አንጻር የኢትዮጵያ መንግስት ድጋፍ እንጅ አላስፈላጊ የሆነና በምርጫው ላይ ጥላ የሚያጠላ ውሳኔን አይጠብቅምም ነው ያለው፡፡

ኢትዮጵያ በፈተና ጊዜ አጋሯ ከሆነችውና ከወዳጅ ሃገር አሜሪካ ጋር ያላትን የረጅም ጊዜ ግንኙነት ያነሳው ሚኒስቴሩ፥ የቪዛ ክልከላውን ጨምሮ መሰል እርምጃዎች የሃገራቱን የረጅም ጊዜ ታሪካዊ ግንኙነት ሊጎዳው እንደሚችልም ነው የገለጸው፡፡

ከዚህ ባለፈ ግን የኢትዮጵያን መንግስት ከ "አሸባሪው ህወሓት" ጋር በእኩል አይን ለማየት የተሞከረበት መንገድ እጅግ አሳዝኖኛል ሲል ሚኒስቴሩ ገልጿል፡፡

ያንብቡ : telegra.ph/MoF-05-24

@tikvahethiopia
#BREAKING

የባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ /ባልደራስ/ ከፍተኛ አመራሮች የሆኑት ፕሬዚዳንት አቶ እስክንድር ነጋ ጨምሮ ፣ አስቴር ስዩም ፣ ስንታየሁ ቸኮል እና አስካለ ደምሌ በመጪው ምርጫ በዕጩነት እንዲመዘገቡ ፤የፌዴራል ጠቅላይ ፍ/ቤት 2ኛ ሰበር ሰሚ ችሎት ውሳኔ መስጠቱን ፤የባልደራስ የሕግና የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች ኃላፊ አቶ ሔኖክ አክሊሉ ገልጸዋል ።

ምንጭ፦ ባልደራስ ፓርቲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ ነገ ይጀምራል።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርሰቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ ነገ ግንቦት 17 ቀን 2013 ዓ/ም ከቀኑ በ10:00 ሰዓት በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም በሚያካሂድ የጸሎት ሥነሥርዓት ይጀምራል።

ነገ በሚያካሂደው ጉባኤ ቋሚ ሲኖዶሱ በምልአተ ጉባኤው መታየት ይገባቸዋል በማለት ያዘጋጃቸው አጀንዳዎች ምልአተ ጉባኤው በሚሰይማቸው ብጹአን አባቶች እንዲታዩ ካደረገ በኋላ መካተት ያለባቸው አጀንዳዎች ለይቶ ለቅዱስ ሲኖዶስ ምልአተ ጉባኤ በማቅረብ የሚያጸድቅ ይሆናል።

በጉባኤው የጸደቁት አጀንዳዎች መሰረት በማድረግና በቅደም ተከተል በመወያት ውሳኔ እንደሚያስተላልፍ ይጠበቃል።

ብጹዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአክሱም ወእጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የጉባኤውን መከፈት በማስመልከት የመክፈቻ መልዕክት ያስተላልፋሉ።

መረጃው የቅዱስ ሲኖዶስ ጽህፈት ቤት/የኢኦተቤ የህዝብ ግንኙነት መምሪያ ነው።

@tikvahethiopia
#Ethiopia #COVID19

ኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ካደረገችው 4,106 የኮቪድ19 የላብራቶሪ ምርመራ 306 ሰዎች ለቫይረሱ ተጋላጭ ሆነ ተገኝተዋል ፤ በዚህም አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 269,500 ደርሰዋል።

በ24 ሰዓት ውስጥ የ8 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 4,084 ደርሷል።

የኮቪድ-19 ክትባት የተከተቡ ዜጎች 1,684,450 ደርሰዋል።

@tikvahethiopia