ለትግራይ ጊዜው ያለፈበት ዘይት እና ዱቄት ተልኳል ?
በትግራይ ጦርነት ምክንያት ተፈናቅለው መቐለ "ማይወይኒ" መጠለያ የሚገኙ ዜጎች ከቀናት በፊት የመጠቀሚያ ጊዜው ያለፈበት የስንዴ ዱቄትና የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበት ቀን የታተመበት አጠራጣሪ ዘይት 'ቀይ መስቀል' አቅርቧል በሚል እንደማይጠቀሙ ገልፀው ነበር።
የቀይ መስቀል ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዶ/ር ሰለሞን አሊ ፥ በመቐለም ሆነ በሌላ የትኛውም አካባቢ የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት ምግብ እንደላቀርቡ እና እንደማያቀርቡ ገልፀዋል።
የጥርጣሬው መነሻ የሀገሪቱ ስንዴ አምራች ኩባንያዎች የመጠቀሚያ ጊዜ የሚያልፍበትን ጊዜ ማሸጊያው ላይ የሚያትም ዘመናዊ አሰራር ስለሌላቸው መሆኑን አስረድተዋል።
ቀይ መስቀል ያቀረበው ስንዴ እና ዘይት የመጠቀሚያው ጊዜ ያለፈበት አይደለም ብለዋል።
ዶ/ር ሰለሞን #ለቪኦኤ ፦
"የምግብ ቁጥጥር ባለስልጣን በአ/አ እና መቐለ ባለው ተረጋግጧል። እነዚህ ምልክቶች በወረቀት ተለጥፈው ነው የሚሄዱት እነዚህ ምልክቶች የሚያሳስቱ መስሏቸው ስለተጠራጠሩ አንወስድም ፤ ይሄ ተለጥፎ ነው የመጣው፤ ቀኑም ልክ አይደልም ብለዋል።
የእኛ ሀገር ዱቄት ይሄን ሁሉ መንገድ አጓጉዘን፤ ዱቄቶቹ ከቃጫ የሚሰሩ ናቸው ከማሌዢያ ወይም ከፊሊፒንስ የሚመጡ አይደለም ፤ እነዚህን ሲያዩ አንዳንድ ተፈናቃይ ወገኖቻችን እነዚህን ነገሮች ተጠራጥረዋል።
መጠራጠራቸውን ትክክል ነው ፤ እነዚህ ነገሮች ይታዩ ፤ ይፈተሹ ተባለ ፤ ናሙናው ተወስዶ ታዩ ዱቄቱ በሙሉ ንፁህ ነው ፤ ለምግብነት መዋል ይችላል የሚል የፅሁፍ ማረገገጫ ነው ያገኘነው።
ዘይቶቹ ለሚቀጥሉት 3 ዓመታት የሚያገለግሉ ዘይቶች ናቸው። ነገር ግን ምርመራ ሲደረግ የአዮዲን መጠናቸውን አነስተኛ ሆነው ነው የተገኘው"
ያንብቡ : telegra.ph/ERCS-05-05
@tikvahethiopia

#Tigray
ከትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚነት የተነሱት ዶክተር ሙሉ ነጋ በድጋሚ የሳይንስ እና ከፍተኛ ትምሕርት ሚኒስትር ዲኤታ ሆነው ተሹመዋል።
የዶ/ር አብርሃም በላይ የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው መሾማቸውን የጠ/ሚ ፅህፈት ቤት በይፋ አሳውቋል።
ሹመቱ ከሚያዝያ 28 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጠ መሆኑም ተገልጿል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ።
5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡
ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ህወሓት)" እና "ሸኔ" በሽብርተኝነት እንዲሰየሙ የሚኒስትሮች ምክር ቤት ያቀረበውን የውሳኔ ሃሳብ ም/ቤቱ በአንድ ደምፅ ተአቅቦ በአብላጫ ድምፅ አጹድቋል፡፡
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
የG7 ስብሰባ ዛሬ ተጀመረ። የG7 ስብሰባ በኢትዮጵያ የትግራይ ክልል ቀውስን ጨምሮ በሌሎችም ጉዳዮች ይመክራል። የG7 ሀገራት ማለትም ፦ 🇺🇸አሜሪካ 🇯🇵 ጃፓን 🇬🇧ዩኬ 🇮🇹ጣልያን 🇫🇷 ፈረንሳይ 🇨🇦ካናዳ 🇩🇪ጀርመን የዉጪ ጉዳይ ሚንስትሮች የሁለት ቀናት ስብሰባቸዉን ዛሬ ሎንዶን ዉስጥ ነው የጀመሩት። ሚንስትሮቹ ከሩሲያ ፣ ከቻይና እና ከኢራን ጋር የገጠሙትን ውዝግብ በኢትዮጵያ የትግራይ ቀውስ ፣…
G7_Foreign_and_Development_Ministers’_Meeting_Communiqué,_London.PDF
142 KB
የG7 ስብሰባ በኢትዮጵያ ጉዳይ ምን አለ ?
- አሁንም በትግራይ ያለው ሁኔታ ፣ የቀጠለው ግጭት እና የሰብዓዊ መብትና የሰብዓዊ ድጋፍ ቀውስ በእጅጉ ያሳስበናል ብለዋል።
- የሲቪሎች/የሰላማዊ ሰዎች ግድያ ፣ የሴቶች አስገድዶ መደፈር ፣ የወሲባዊ ብዝበዛ ሌሎችም ፆታ ላይ የተመሰረቱ ጥቃቶችን አውግዘዋል።
- የሃይማኖታዊ እና ባህላዊ ቅርሶችን መውደም እና መዘረፍ አውግዘዋል።
- በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የትግራይ ተወላጆች እና የኤርትራ ስደተኞችን በግዳጅ ማፈናቀልን አውግዘዋል።
- በኢሰመኮ እና በUN የሰብዓዊ መብት ከፍተኛ ኮሚሽነር መካከል የተፈፀሙት የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን ለማጣራት የተደረገውን ስምምነት በደስታ ተቀብለዋል።
- ሁሉም ወገኖች በፍጥነት ግጭት እንዲያቆሙ፣ የዜጎችን ደህንነት እንዲያረጋግጡ፣ የሰብዓዊ መብቶችንና ዓለም አቀፍ ህጎችንና የሚዲያ ነፃነት እና ተደራሽነትን እንዲያከብሩ ጥሪ አቅርበዋል።
- የሰብዓዊ ጥሰት እና ፆታዊ ጥቃቶችን የፈፀሙ ተጠያቂ እንዲሆኑ ጥሪ አቅርበዋል።
- የውጭ ሀይሎች በትግራይ መኖራቸውን እጅግ የሚረብሽና መረጋጋት የሚያሳጣ መሆኑን ገልፀዋል።
- የኤርትራ ኃይሎችን ከትግራይ ለማስወጣት የኢትዮጵያ እና የኤርትራ መንግስታት የሰጡትን መግለጫ እንደሚቀበሉ ገልፀው፤ ነገር ግን ማስወጣቱ ገና አለመጀመሩ እንዳሰጋቸው ገልፀዋል። የኤርትራ ወታደሮችን የማስወጣት ሂደቱ መፋጠን አለበት ብለዋል።
- በትግራይ ክልል ሁሉን አቀፍ ግልፅ የሆነ የፖለቲካ ሂደት እንዲፈጠር ጥሪ አቅርበዋል።
- ዛሬም ለኢትዮጵያ አንድነት/የግዛት አንድነት ቁርጠኛ መሆናችንን እናረጋግጣለን ብለዋል።
- በመጨረሻም፦ በኢትዮጵያ ተአማኒ ምርጫና ብሄራዊ እርቅ እንዲኖር ለማስቻል ሁሉን አቀፍ የፖለቲካ ሂደት እንዲኖር ጥሪ አቅርበዋል።
* መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት 'ህወሓት' እና ሸኔ' ን በሽብርተኝነት ፈረጀ። 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 13ኛው መደበኛ ስብሰባ በመካሄድ ላይ ነው፡፡ ም/ቤቱ ዛሬ በጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት የመሰብሰቢያ አዳራሽ በሚያካሄደው 13ኛ መደበኛ ስብሰባ "ህዝባዊ…
'ሸኔ' ማንነው ?
በርካቶች 'ሸኔ' እያለ እራሱን የሚጠራ ድርጅት በሌለበት እንዴት አሸባሪ ተብሎ ይሰየማል ሲሉ ይጠይቃሉ። ይህ ስያሜ አንዳች ነገር ለመሸፈን ተፈልጎ ነው በሚል ጥርጣሬያቸውን የሚገልፁ ምሁራንም አልጠፉም።
ለመሆኑ 'ሸኔ' ማነው ?
በዚህ ጉዳይ ላይ በዛሬው ዕለት የተጠየቁት የፌዴራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቲዮስ ተከታዩን ማብራሪያ ሰጥተዋል ፦
"በተለምዶ 'ሸኔ' የሚባለው እራሱን ደግሞ 'የኦሮሞ ነፃነት ሰራዊት' ብሎ የሚጠራው ቡድን ነው። በምዕራብ ኦሮሚያ ፣ በሌሎችም ክልሎች እየተንቀሳቀሰ ጥቃት የሚያደርስ ድርጅት ነው።
እራሱ ለእራሱ የሰጠውን ስያሜ ግን እኛ የምናፀድቅበት ምክንያት የለንም ፤ ተገቢም አይሆንም ብለን እናምናለን።
ይህ ቡድን ከዚህ በፊት እንደ 'ህወሓት' ተመዝግቦ ፣ ህጋዊ እውቅና ፣ ህጋዊ ሰውነት እና ሰርተፊኬት ኖሮት የሚያውቅ አይደለም ፤ ስለዚህ ስያሜው እሱ እራሱን በአንድ ስያሜ ይሰይማል ፤ አንዳንዶች በሌላ ስም ይጠሩታል በተለምዶ 'ኦነግ ሸኔ' ይባል ነበር ስለዚህ በተለምዶ ከሚጠራበት 'ኦነግ ሸኔ' / 'ሸኔ' ከሚባለው 'ሸኔ' የሚለውን መርጠናል።
እዚህ ጋር ግልፅ መሆን ያለበት በአዋጁ አንቀፅ 23 መሰረት ስያሜውን ብትለዋውጥ ያው ቡድን ያው ስብስብ እስከሆነ ድረስ በውሳኔ ሀሳቡ የተገለፀው ስብስብ እስከሆነ ድረስ ስያሜ መለዋወጥ የሚያመጣው ለውጥ የለም፤ ውሳኔ ሀሳቡ ተፈፃሚ ይሆንበታል።
አይ እኔ እራሴን የምጠራው እንዲህ ብዬ ነው ፤ እንዲያ ብዬ ነው የሚለው ማምለጫ ሊሆን አይችልም።
ይሄ ተመዝግቦ ፣ ሰርተፊኬት ተሰጥቶት ፣ ህጋዊ ሰውነት ኖሮት በዚህ ስም ነው የሚጠራው ይባል የነበረ እንደ ህወሓት የለውም።
ያንብቡ : telegra.ph/Dr-Gedion-Timothewos-05-06

#Update የኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነስርዓት ነገ ይፈፀማል። በነገዉ ዕለት የቀብር ስነስራዓቱን አስመልክቶና ሙሉ ዝግጅቱ በድሮዉ ጊዮን ሆቴል አደባባይ ከተከናወነ በኃላ በካቴድራል ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ስርዓተ ቀብራቸው የሚፈመፅ መሆኑን የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ፥ የባህር ዳር ፖሊስ መምሪያ ያሰራጨው "የሀዘን ጥሪ" መልዕክት ያስረዳል። የቀድሞው የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር ትላንት…
#Update
የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ባህርዳር ገባ።
በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል።
በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር አለም አቀፍ ኤርፖርት አየገባ ይገኛል።
በስፍራው ፦
- የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር
- የጠ /ሚኒስትሩ የደህንነት አማካሪ አቶ ገዱ አንዳርጋቸው
- ከፍተኛ የፌደራል እና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች
- አዲሱ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ተኮላ አይፎክሩ
- ከፍተኛ የፖሊስ መኮንኖች መገኘታቸውን ከአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

በኦሮሚያ_ክልል_ውስጥ_በሚገኙ_21_ፖሊስ_ጣቢያዎች_ላይ_የተደረገ_የክትትል_ሪፖርት_.pdf
364.4 KB
#Oromiya
"ሕግን የማስከበር እርምጃ ሕግን የተከተለ መሆን አለበት" - ኢሰመኮ
የኢትዮጵያ ሰብአዊ መብቶች ኮሚሽን በኦሮሚያ ክልል ያለው የእስረኞች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እንደሚያሳስበው ገለጸ።
ኮሚሽኑ ከህዳር 11 ቀን 2013 ዓ.ም. እስከ ጥር 04 ቀን 2013 ዓ.ም. ባለው ጊዜ ውስጥ በክልሉ ያለውን የእስረኞችን አያያዝ ሁኔታ በተመለከተ በተለይም የአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በቁጥጥር የዋሉ ተጠርጣሪዎችን ጨምሮ ሌሎችም “በወቅታዊ ሁኔታ” (“haala yeroo”) የተያዙ የሚባሉ ብዛት ያላቸው እስረኞች ከሚገኙባቸውና ተደጋጋሚ ቅሬታዎች ከሚቀርቡባቸው መካከል በ21 የተመረጡ ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ማድረጉን ገልጿል።
በክትትሉ ከእስረኞች እና የፖሊስ ጣቢያዎቹ ኃላፊዎች ጋር መወያየቱን፤ እንዲሁም የክትትሉን ግኝቶች ጉዳዩ ለሚመለከታቸው የክልሉ የሕግ አስከባሪ እና የአስተዳደር አካላት በማሳወቅ ምላሽ እንዲሰጥባቸው እንደጠየቀ አሳውቋል።
ኮሚሽኑ በጎበኛቸው የፖሊስ ጣቢያዎች በእስር ላይ የሚገኙ ሰዎች ሰብአዊ መብቶች አያያዝ ሁኔታ እጅግ አሳሳቢ እና በአፋጣኝ ሊሻሻል የሚገባው ነው ብሏል።
* የኢሰመኮ ሙሉ ሪፖርት ከላይ ተያይዟል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

ከኢሰመኮ ሪፖርት የተወሰዱ፦
- ኦሮሚያ ክልል ውስጥ በ21 ፖሊስ ጣቢያዎች ላይ ክትትል ተደርጓል
- ክትትል ከተደረገባቸው ፖሊስ ጣቢያዎች መካከል ከሚገኙ እስረኞች መካካል የተወሰኑት በፖሊሶች በሚያዙበት ወቅት (በተለይ በኦሮሚያ ልዩ ኃይል) እንዲሁም በፖሊስ ጣቢያ ውስጥ በተለያየ ምክንያት ድብደባ የተፈፀመባቸው መሆኑን ገልፀዋል።
- እስረኞ በተፈፀመባቸው ድብደባ ጭንቅላታቸው፣ ፊታቸው ፣ አፍንጫቸው፣ ሆዳቸው ፣ እግራቸው፣ ጥርሳቸው ...ላይ ጉዳት ደርሶባቸዋል፤ ገና ያልዳነ ቁስል፣ ስብራት ወይም ደም በሰውነታቸው ላይ የሚታይና ለጊዜያዊ እና ቋሚ የአካል ጉዳት የተዳረጉ እስረኞች አሉ።
- በተወሰኑ ቦታዎች 'ኦነግ ሸኔ' አባል ወይም ደጋፊ በሚል የሚፈለጉ "ልጆቻችሁን አቅርቡ" በማለት አባት ወይም እናት ማሰር፣ "ባልሽን አቅርቢ" በማለት ሚስትን ማሰር ፣ ሰዎችን ያለአግባብ በማሰር "ኦነግ በሸኔ" አባል ናችሁ ብለን እንሰካሰል በማለት በማስፈራራት ገንዘብ የመጠየቅ ሁኔታዎች መኖራቸውን እስረኞች ተናግረዋል።
- በሁሉም ፖሊስ ጣቢያዎች ሴት እስረኞች አሉ፤ከነዚህ ውስጥ በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩ ወይም ሌላ በወንጀል የሚፈለግ የተሰወረ የቤተሰብ አካል አቅርቡ ተብለው የታሰሩ ይገኙበታል፤ ከነዚህ ሴቶች የተወሰኑት ከ5 ወር እስከ 10 ዓመት የሚሆናቸውን ህፃናት ልጀች ይዘው የታሰሩ ናቸው።
- በተለያዩ ፖሊስ ጣቢያዎች በወንጀል ጉዳይ ተሳታፊናቸው በሚ የታሰሩ እድሜያቸው ከ9 እስከ 18 ዓመት የሚሆናቸው ህፃናት አካለ መጠን ከደረሱ ሰዎች ጋር ተቀላቅለው በእስር ላይ ይገኛሉ።
- አብዛኛዎቹ ፖሊስ ጣቢያዎች ያሉት የማረፍያ ክፍሎች በእስረኞች የተጣበቡ ናቸው። የተወሰኑ እስር ቤቶች የከፋ መጨናነቅ በመኖሩ ቀን ውጭ በረንዳ ላይ ውለው ማታ ደግሞ በተራ ይተኛሉ።

Photo
የድሬዳዋ የሰዎች ህይወት አለፈ።
በድሬደዋ ትላንት በጣለው ከባድ ዝናብ ሳቢያ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ግንብ ፈርሶ በመኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ የሶስት ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን በመብረቅ አደጋ የአንድ ሰው ህይወት ማለፉ ተገልጿል።
በቀበሌ 08 ልዩ ስሙ "ለገሃሬ ከመንገድ በላይ" ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ከለሊቱ ዘጠኝ ሰአት ጀምሮ በድሬዳዋ ከተማ በጣለው ከባድ ዝናብ የአንድ መኖሪያ ቤት አጥር ተደርምሶ በአቅራቢያው ባለው መኖሪያ ቤት ላይ በመውደቁ በቤቱ ውስጥ ተኝተው የነበሩ የአንድ ቤተሰብ አባላት የሆኑ 3 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
ህይወታቸው ያለፈው የ12 አመት ፤ የ3 አመት እና የ2 ወር ህጻን ልጅ ሲሆን የልጆቹ ወላጅ እናት እና አንድ ወንድ ልጃቸው ላይ ከባድ የአካል ጉዳት ደርሶባቸው ድሬዳዋ ድልጮራ ሪፈራል ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ።
በልጆቹ አባት ላይ ቀላል የአካል ጉዳት ደርሷል።
በሌላ በኩል በቀበሌ 01 "መልካ ጀብዱ" ከቀኑ በዘጠኝ ሰአት በጣለው መብረቅ የኢትዮ- ጅቡቲ ምድር ባቡር ግቢ ውስጥ በስራ ላይ በነበሩ ሁለት ግለሰቦች ላይ መብረቅ በመውደቁ በአንደኛው ግለሰብ ላይ የሞት አደጋ ሲያስከትል በሌላው ግለሰብ ላይ የአካል ጉዳት በመድረሱ በማርያም ወርቅ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛል፡፡
ባሳለፍነው ሚያዝያ 24 በድሬዳዋ የአንድ ድርጅት አጥር ፈርሶ በአደጋው የዘጠኝ ሰው ህይወት ማለፉ አይዘነጋም።
በቀጣይ ቀናት ዝናብ ጥሎ የጎርፍ አደጋ ሊደርስ ስለሚችል ህብረተሰቡ ተገቢው ጥንቃቄ ሊደረግ ይገባል ተብሏል።
ምንጭ፦ ድሬ ፖሊስ

#Update የኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስከሬን ባህርዳር ገባ። በድንገተኛ ህመም ህይወታቸው እንዳለፈ የተገለፀው የቀድሞ የአማራ ክልል ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ አስክሬን ለተጨማሪ ምርመራ ወደ አዲስ አበባ ተልኮ እንደነበር ይታወሳል። በአሁኑ ሰዓት ከአዲስ አበባ ወደ ባህርዳር አለም አቀፍ ኤርፖርት አየገባ ይገኛል። በስፍራው ፦ - የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አገኘው ተሻገር - የጠ /ሚኒስትሩ…
#Update
የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርአት በባህር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን መፈፀሙን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የቀድሞ የአማራ ፖሊስ ኮሚሽነር አበረ አዳሙ የቀብር ስነ ስርአት በባህር ዳር ፈለገ ገነት ቅዱስ ጊዮርጊስ ካቴድራል ቤተክርስቲያን መፈፀሙን የአማራ ፖሊስ ኮሚሽን አሳውቋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ስቴም ፓወር ፣ ቪዛ እና ቲክቫህ ኢትዮጵያ በመተባበር ባዘጋጁት የሥራ ፈጠራ ክህሎት እና መሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ የተሳተፉ የመጀመሪያ ዙር ሰልጣኞች የምርቃ መርኃግብር ተካሂዷል።
ስልጠናውን ከተከታተሉ 200 ሰልጣኞች ውስጥ በአጠቃላይ 70 የሚሆኑ ፕሮጀክቶች የቀረቡ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ ለመጨረሻው ዙር ከደረሱ 20 ፕሮጀክቶች በአራት ዘርፎች ለአራት አሸናፊዎች የ25,000 ብር በድምሩ የ100,000 ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
አሸናፊዎቹ በግብርና፣ በጤና፣ በኢንጂነሪንግና በአገልግሎት ዘርፍ የተመረጡ ሲሆን በጤናው ዘርፍ ኢሶፕ የተሰኘ የፈጠራ ሃሳብ፤ በግብርናው ዘርፍ ደግሞ ፖሊተሪ ፋርሚንግ ላይ የቀረበ ፕሮጀክት አሸናፊ ሆኗል።
በኢንጅነሪንግ ዘርፍ የፕላስቲክ ኮዳን ወደ ፋይበር ፕላስቲክ የሚለውጥ እንዲሁም በአገልግሎት ዘርፍ ደግሞ ሎሃ የተሰኘ የኦንላይን ትምህርት አገልግሎት አሸናፊዎች ሆነዋል።
የስቴም ፓወር ሥራ አሥኪያጅና ቅድስት ገብረአምላክ አሸናፊዎቹ ከተበረከተላቸው ሽልማት በተጨማሪ ወደ አገልግሎት እስኪገቡ ድረስ በቀጣይ አንድ ዓመት ስቴም ፓወር ሙሉ የቴክኒክና የሞያ ድጋፍ እንደሚያደርግ ገልጸዋል።
በሥራ ፈጠራ ክህሎት እና በመሰረታዊ የፋይናንስ ትምህርት ላይ ያተኮረው ሁለተኛው ዙር ስልጠና በቀጣይ ሳምንታት ይጀምራል። ቲክቫህ ኢትዮጵያም በቀጣይ የሚኖሩ ሁነቶችን ወደ እናንተ የሚያደርስ ይሆናል።

የብሔራዊ የአደጋ ስጋት ስራ አመራር ኮሚሽን ኮሚሽነር አቶ ምትኩ ካሳ መግለጫ ፦
- መንግስት ከዚህ በኋላ ከትግራይ አጠቃላይ የቆዳ ስፋት ውስጥ በ14 በመቶው ብቻ ድጋፍ ያደርጋል ፤ ቀሪው 86 በመቶው የዓለም ምግብ ፕሮግራምን ጨምሮ በሌሎች ዓለም አቀፍ እርዳታ ሰጭ ተቋማት ይሸፈናል። ከዚህ ቀደም 70% ሲሸፈን የነበረው በኢትዮጵያ መንግስት ብቻ ነበር።
- ተፈናቃዮችን ወደቀያቸው ለመመለስ በ3 መንገድ እየተሰራ ነው።
ሶስቱ መንገዶች ፦
• ሰላም በተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ህዝቡን በማወያየት መመለስ፣
• ሙሉ ሰላም ያልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ላይ ስነልቦናዊ ችግሮችን ለማቅለል ወደዘመድ እንዲሄዱ መርዳት
• ሰላም ካልተረጋገጠባቸው ቦታዎች ለተፈናቀሉት ደግሞ ጊዜያዊ መጠለያን ማዘጋጀት የሚሉ ናቸው።
- ለሰብዓዊ ድጋፍ አቅርቦት ተጨማሪ 4 ተቋማት ፈቃድ አግኝተዋል፡፡
- ሰብዓዊ ድጋፎችን ለማድረግ አልተቻለም በሚል የሚቀርቡ ክሶችና ወቀሳዎች ከአሁን በኋላ ተቀባይነት የላቸውም።
- እርዳታዎችን ለማድረግ የሚያስችሉ ሁኔታዎች ሙሉ በሙሉ ተከፍተዋል።
- “በረሀብ የሞተ ሰው የለም”፤ ነገር ግን ዓለም አቀፍ ተቋማት “እርዳታ ለማግኘት ሲሉ ጉዳዩን እያስጮሁት” ነው። “ልክ እንደ የመን እና ሶሪያ እርዳታ ለማግኘት ጉዳዩን እየተደረገ ያለ ሩጫ ነው።
በሌላ በኩል ፦
በሀገሪቱ ያለው የተፈናቃይ ብዛት 2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ሲሆን 40 በመቶ ያህሉን ለመመለስ መታሰቡን ተጠቁሟል።
አጣየ በተመለከተ፦ አማራ ክልል ውስጥ ለ50ሺ ተረጂዎች ድጋፍ እንዲደረግ ችግሩ በተፈጠረበት ወቅት ወዲያውኑ መጠየቁን ተከትሎ ድጋፉ በማግስቱ (ቅዳሜ ተጠይቆ እሁድ) እንዲደርስ ተደርጓል።
ምንጭ፦ አል ዓይን