TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#AntonioGuterres #DrAbiyAhmed

የተመድ ዋና ጸኃፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በዛሬው ዕለት ከጠ/ሚ ዶ/ር ዐቢይ አሕመድ ጋር መነጋገራቸውን የዋና ፀኃፊው ቃል አቀባይ ስቴፋን ጁዣሪች ገልጸዋል፡፡

አንቶኒዮ ጉተሬዝ :
- የህግ የበላይነትን በፍጥነት ማስፈን፣
- ለሰብአዊ መብቶች ሙሉ በሙሉ እንዲከበሩ ማድረግ ፣
- ማህበራዊ ትስስርን ማስፈን ፣
- ሁሉን አቀፍ እርቅ መፈጸም ፣
- የህዝብ አገልግሎቶችን አቅርቦት እንደገና መጀመር እና ያልተገደበ ሰብዓዊ ተደራሽነት ማረጋገጥ እንደሚያስፈልግ አንስተዋል፡፡

ተመድ የአፍሪካ ህብረትን ተነሳሽነት ለመደገፍ ሙሉ በሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም ነው ዋና ጸኃፊው ገልፀዋል፡፡

በትግራይ ክልል ያለው ሁኔታ እንዳሳሰባቸው የገለጹ ሲሆን ድርጅቱ ለስደተኞች ፣ ለተፈናቀሉ ዜጎች እና በችግር ላይ ለሚገኙ ሰዎች ሁሉ ሰብአዊ ድጋፍ ለመስጠት ሙሉ ቁርጠኛ መሆኑንም አረጋግጠዋል፡፡ (AlAIN)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#DrAbiyAhmed

ዛሬ መጋቢት 24 ዶ/ር አብይ አህመድ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው የተሰየሙበት ቀን ነው።

ልክ በዛሬው ቀን የዛሬ 3 ዓመት ነው የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ዶክተር አብይ አህመድን (በዛን ወቅት የኢህአዴግ ሊቀመንበር) ጠቅላይ ሚኒስትር አድርጎ የሰየመው።

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ እንደሚታየው ጠ/ሚሩ ወደስልጣን ከመጡበት ጊዜ ያሳኳቸውን፣ የተገበሯቸውን ተግባራት በማንሳት የሚደግፏቸው ፤ በአንፃሩ ያሉ ጉድለቶችን በማንሳትም የሚቃወሟቸው በርካቶች ናቸው።

@tikvahethiopia