TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#GERD #EGYPT #ETHIOPIA #SUDAN

የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሳሜሕ ሽኩሪ በካይሮ የሚገኙ የአፍሪካ አገራት አምባሳደሮችን አነጋገሩ። ግብፅ በኅዳሴ ግድብ ጉዳይ "ትክክለኛና ሚዛናዊ ስምምነት" ላይ ለመድረስ ቁርጠኛ መሆኗን እንደተናገሩ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል-አቀባይ ገልጸዋል።

#EsheteBekele
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EGYPT

ግብፅ ኢትዮጵያ የአረብ ሊግን አቋም ለመቃወም ባወጣችው መግለጫ ድርጅቱን እና አባል አገራቱን ዘልፋለች ስትል ከሰሰች። ኢትዮጵያ የአረብ ሊግና አባላቱ ከአፍሪካውያን ስለሚኖራቸው ግንኙነት ማብራሪያ የመስጠት መብት የላትም ብላለች።

ኢትዮጵያ በታላቁ የኅዳሴ ግድብ ጉዳይ ከስምምነት ለመድረስ ፖለቲካዊ ቁርጠኝነት የላትም፤ ድርድሩን ለውስጥ ፖለቲካ ፍጆታ ለማዋል ሞክራለች ሲል የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በዛሬው ዕለት ባወጣው መግለጫ ወንጅሏል።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ እሸት በቀለ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EGYPT

በግብፅ በትላንትናው ዕለት 358 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መያዛቸውን #egypttoday ዘግቧል፡፡ ይህም በሀገሪቱ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎችን ቁጥር 5 ሺህ 895 አድርሶታል፡፡

የጤና ሚንስቴር ቃል አቀባይ ካሊድ መጋህድ እንደገለጹት በ24 ሰዓታቱ 14 ታማሚዎች ሕይወት አልፏል ፤ ይህም በግብፅ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሞቱትን ሰዎች ቁጥር 406 አድርሶታል ብለዋል፡፡ በአንጻሩ ደግሞ 79 ሰዎች ማገገማቸውና ከሆስፒታል መውጣታቸው ነው የተነገረው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Egypt #Ethiopia #Sudan

በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው ድርድር በሚቀጥለው #እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል።

አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ነው።

ከታላቁ ህዳሴው ግድብ ድርድር ራሷን አግልላ የነበረችው #ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል፡፡

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሰጡት መግለጫ ላይ ያነሷቸውን ሌሎች ጉዳዮች በዚህ ማግኘት ትችላላችሁ : telegra.ph/ALAIN-12-29 (መረጃውን አዘጋጅቶ ያሰራጨው አል ዓይን ኒውስ ነው)

@TIKVAHETHIOPIA @TIKVAHETHIOPIABOT
TIKVAH-ETHIOPIA
#Egypt #Ethiopia #Sudan በሕዳሴ ግድብ ዙሪያ በኢትዮጵያ፣ ሱዳን እና ግብፅ መካከል የሚደረገው ድርድር በሚቀጥለው #እሁድ ታህሳስ 25 ቀን 2013 ዓ.ም እንደሚቀጥልም አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ገልፀዋል። አምባሳደሩ ይህን የገለፁት በሰጡት ሳምንታዊ መግለጫ ላይ ነው። ከታላቁ ህዳሴው ግድብ ድርድር ራሷን አግልላ የነበረችው #ሱዳን ወደ ድርድሩ እንደምትመለስ በቅርቡ ይፋ ማድረጓ ይታወቃል፡፡…
#Egypt #Ethiopia

አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ባለፈው ማክሰኞ በሰጡት መግለጫ ፥ “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ” ማለታቸውን ተከትሎ ግብጽ በኩል ቅሬታዎች እየመጡ ነው፡፡

“የሱዳንን ሰፊ መሬትን የያዙ አሉ፤ ግን ለሱዳን ተቆርቋሪ እየመሰሉ ይረብሻሉ” ያሉት አምባሳደር ዲና “ስማቸውን መናገር ግን አልፈልግም ፤ እናንተው ታውቋቸዋላችሁ” ሲሉ ማንነታቸውን በግልጽ ሳይጠቅሱ ማለፋቸው ይታወሳል፡፡

የግብፅ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ዛሬ ባወጣው መግለጫ “የኢትዮጵያ ውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት ቃል አቀባይ በግብጽ የውስጥ ጉዳይ ላይ አስተያየት መስጠታቸው ተገቢ አይደለም” ብሏል፡፡

“አምባሳደር ዲና ሙፍቲ ግብጽን በተመለከተ ኃላፊነት የጎደለው አስተያየት ሰጥተዋል” ያሉት የግብፅ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር አሕመድ ሀፊዝ “ግብፅ የግድቡን ግንባታ የምትቃወመው በሀገሪቱ ያለባትን ቀውስ ለማቀዝቀዝ ነው ማለታቸው ተገቢ አስተያየት አይደለም” ሲሉም ነው የገለጹት፡፡ 

አምባሳደር ዲና “የአፍሪካ ቀንድና ምስራቅ አፍሪካ አካባቢ እንዲተራመስ የሚፈልጉ አካላት አሉ ነው ያልነው ፣ ነገር ግን ሌባ እናት ልጇን ስለማታምን ይህንን የምናደርገው እኛ ነን ካሉ ምንም ማድረግ አንችልም” ብለዋል።

ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Egypt #Sudan

በግብፅ እና ሱዳን ጉብኝት ለማድረግ ወደ አፍሪካ የገቡት የአሜሪካው የግምጃ ቤት ኃላፊ ስቴቨን ምኑቺን ካርቱም መግባታቸውን የሱዳን ዜና አገልግሎት ዘግቧል፡፡

ስቴቨን ምኑቺን ካርቱም ሲደርሱ በሱዳን የገንዘበና ኢኮኖሚ ዕቅድ ሚኒስትር ዶ/ር ሂባ መሐመድ አሊ እና በሱዳን የአሜሪካ አምባሳደር አቀባበል እንደተረገላቸው ተገልጿል፡፡

ምኑቺን ትናንት ከግብፁ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር በካይሮ ተወያይተዋል።

በካርቱም ቆይታቸው ከሉዓላዊ የሽግግር ምክር ቤት ሊቀ መንበር አብዱል ፋታህ አል ቡርሃን እና ከጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሃምዶክ (ዶ/ር ) ጋር እንደሚወያዩ ይጠበቃል፡፡

ምኑቺን ትናንት በግብፅ ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት አብዱል ፋታህ አልሲሲ ጋር ኢትዮጵያ በዓባይ ወንዝ ላይ እየሰራችው ባለው የሕዳሴ ግድብ ሰሞነኛ ጉዳዮች ዙሪያ መወያየታቸውን የፕሬዚዳንቱ ጽ/ቤት ገልጿል።

ምኑቺን በሱዳን ቆይታቸውም እንዲሁ በግብፅ እንዳደረጉት ሁሉ ስለ ሕዳሴ ግድብ ድርድርና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ እንደሚወያዩ ተገልጿል፡፡

በተጨማሪም የሱዳንን ወቅታዊ ሁኔታ በተመለከተ ውይይት እንደሚኖራቸው ይጠበቃል፡፡

ስቴቨን ምኑቺን የሕዳሴ ግድብ ድርድር በአሜሪካ ሲደረግ ፣ ከታዛቢነት ሚናቸው አልፈው ፣ ድርድሩን በሦስተኛ ወገንነት ሲመሩ እንደነበር የሚታወቅ ነው፡፡

በአሜሪካ ግምጃ ቤት የተዘጋጀውን ሰነድም ኢትዮጵያ እና ሱዳን አንፈርምም ማለታቸው ይታወሳል፡፡ ~ ኣል ዓይን ኒውስ

@tikvahethiopia