TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዘ ዊኬንድ ለትግራይ ድጋፍ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር አበረከተ።

አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ የሚውል የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማደረጉን WFP USA አሳውቋል።

More : https://t.co/9vS6PfQQFj

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Attention😷

ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 6,962 የላብራቶሪ ምርመራ 1,878 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 742 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 215,189 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,963 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 161,968 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 742 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NewsAlert

በሙርሌ ጎሳ አባላት ታግተው ከተወሰዱት ዜጎቻችን መካከል 5ቱ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ከነበሩ ህፃናትና ሴቶች መካከል አምስቱ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታውቀዋል።

አቶ ኡሞድ እንዳሉት፥ ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ 275 ህፃናት በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች እንደተወሰዱ ጠቁመው በወቅቱም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን 208 ህፃናት ማስመለስ እንደተቻለ አስታውሰዋል።

በ2012 ዓ.ም ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ጋር በተደረገው መልካም ግንኙነት 13 ህፃናት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት 3 ህፃናትና 2 ሴቶች በድምሩ 5 ዜጎቻችን መመለሳቸውን በመግለጽ ቀሪ ያልተመለሱትን ህፃናት ለማስመለስ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ መግለፃቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከመጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች :

- መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

- ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

- ግዛው ተስፋዬ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ዘ ዊኬንድ ለትግራይ ድጋፍ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር አበረከተ። አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ የሚውል የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማደረጉን WFP USA አሳውቋል። More : https://t.co/9vS6PfQQFj @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#TheWeeknd #WFP_USA

WFP USA በትግራይ ሰብዓዊ ድጋፍ ለሚሰራው ስራ የዘ ዊኬንድን በጎ ተግባር ሌሎችም እንዲቀላቀሉ ጥሪ እያቀረበ ይገኛል።

የWFP USA ፕሬዜዳንት እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ባሮን ሴጋር ዘ ዊኬንድ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ለሚሰራው ስራ የአንድ ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ስላደረገ ምስጋና አቅርበውለታል።

ዘ ዊኬንድ የአንድ ሚሊዮን ድጋፍ ከማድረግ ባለፈም በይፋዊ የትስስር ገፆቹ ላይ ሌሎችም ድጋፍ እንዲሰጡ (https://secure.wfpusa.org/donate/save-lives-giving-food-today-donate-now-107) አበረታቷል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
* update

የኢፌዴሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ህግ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለመከላከል ባለፉት ሳምንታት ከወጣው መመሪያ ጋር በተያያዘ መሰረታዊ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

ማብራሪያ የሰጠባቸው ጉዳዮች ስብሰባዎችን የተመለከቱ፣ ከፓርቲዎች የምርጫ ቅስቀሳ ጋር በተያያዘ፣ መመሪያው በመንግስት ተቋማት ላይ ተፈጻሚነት ያለው ስለመሆኑ እና ቅጣቶችን ያካተተ ነው፡፡

* ሙሉ ማብራሪያው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምዝገባ ጀመሩ።

የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ወስደው አዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሌጂ እና አዲስ አበባ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች በፈተና ለመግባት ለሚፈልጉ ምዝገባው መጀመሩ ተገልጿል።

የመመዝገቢያ መስፈርቶች ፦

ተዳጊ ክልሎች (አፋር፣ ሱማሌ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ) ፦

- ኢንጂነሪንግ : ወንድ 415 እና በላይ ፤ ሴት 410 እና በላይ
- አፕላይድ ሳይንስ : ወንድ 400 እና በላይ ፤ ሴት 395 እና በላይ

ሌሎች ክልሎች ፦

- ኢንጂነሪንግ : ወንድ 420 እና በላይ ፤ ሴት 415 እና በላይ
- አፕላይድ ሳይንስ : ወንድ 405 እና በላይ ፤ ሴት 400 እና በላይ

የምዝገባ ጊዜ ፡- ከመጋቢት 26/2013 ዓ.ም እስከ ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ሲሆን ምዝገባው ሚያዝያ 02 ቀን 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 6፡00 ሰዓት ላይ ይጠናቀቃል።

ለምዝገባ የወጣውን መስፈርር የሚያሟሉ አመልካቾች በማንኛውም ስፍራ በኢንተርኔት (online) በ www.astu.edu.et / www.aastu.edu.et/ ድህረ ገፅ በመጠቀም መመዝገብ ይችላሉ፡፡

ፈተናው የሚሰጥበት ቀን ሚያዚያ 8 ቀን 2013 ዓ.ም (ከጠዋቱ 1፡30 እስከ 6፡00 ፣ ከሰዓት ከ8፡00 እስከ 11፡00 ድረስ ይሆናል) ተብሏል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"... በምስራቅ የኢትዮጵያ 2.1 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል" - UN OCHA

BY : AL AIN NEWS & CGTN

በምስራቅ የኢትዮጵያ 2.1 ሚሊየን ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ እንደሚያስፈልገቸው በተመድ የሰብአዊ ጉዳዮች ማስተባበሪያ አስታውቋል።

ማስተባበሪያው ይህን ያሳወቀው ትላንት ባወጣው ሳምንታዊ መግለጫ ነው።

UN OCHA ባህላዊ የውሃ ምንጮች መድረቅ እና ከጉድጓድ ውሃ የሚወጡ የውሃ አቅርቦቶች ውስንነት ክፍተኛ ችግር እያስከተለ መሆኑን በመግለጽ ፤ በክልሉ በአፋጣኝ የዉሃ ማጓጓዣ ተሸከርካሪዎች አቅርቦት እንደሚያስፈልግ አስታውቋል።

በክልሉ በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተጋለጡ ወደ 2 ነጥብ 1 ሚሊየን ገደማ የሚጠጉ ሰዎች የምግብ እና ምግብ ነክ ያልሆኑ አስቸኳይ ድጋፍ ያስፈልጋል ብላል።

በክልሉ በድርቅ ምክንያት ለችግር ለተዳረጉ ዜጎች ለመድረስ 65. 5 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር እንደሚያስፈልገው የሰብአዊ አስታውቋል።

ግጭቶች ፣ ድርቅ እና በየወቅቱ የሚደርሱ የጎርፍ አደጋዎች የሶማሌ ክልልን ጨምሮ በሌሎች የኢትዮጵያ ክፍሎች የተለያዩ ሰብዓዊ ቀውሶችን ሲያስከትል መቆየቱንና የሰብአዊ ድጋፍ የሚስፈልጋቸው ሰዎች እንዲያሻቅብ ማድረጉን ድርጅቱ አስታውሷል።

ከዚህ በተጨማሪ በኢትዮጵያ ያለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ስርጭት ሰብዓዊ ድጋፍ የሚስፈልጋቸው ሰዎች ቁጥር እንዲጨምር ምክንያት መሆኑን UN OCHA በመግለጫው አስታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Update

የሚያዚያ ወር የነዳጅ ምርቶች የችርችሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት ይቀጥላል።

የንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር ከመጋቢት 26 እስከ ሚያዚያ 30 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ ተግባራዊ የሚሆን የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋን አስመልክቶ መግለጫ አውጥቷል።

ሚኒስቴሩ በመግለጫው፥ ከአውሮፕላን ነዳጅ ውጪ የሌሎች የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ባለበት እንዲቀጥል ወስኗል።

ሚያዚያ ወር የአውሮፕላን ነዳጅ ዋጋ በሊትር 43 ብር ከ70 ሳንቲም እንዲሸጥ የተወሰነ ሲሆን በመጋቢት ወር ሲሸጥበት ከነበረበት ዋጋ የ5 ብር ከ5 ሳንቲም ጭማሪ እንዳለው አስታውቋል። #ENA

@tikvahethiopia
ከ1.8 ሚሊዮን ብር በላይ ንብረት ያወደመው የእሳት ቃጠሎ ፦

BY : ENA

በደብረ ብርሀን ከተማ በንግድ ሱቅ ውስጥ የተነሳ የእሳት ቃጠሎ ከአንድ ነጥብ 8 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት ንብረት መውደሙን ፖሊስ አስታወቀ።

አደጋው በሰው ህይወት ላይ ያደረሰው ጉዳት እንደሌለ ተመልክቷል።

በከተማው የሁለተኛ ፖሊስ ጣቢያ ሃላፊ ኮማንደር ጥበበ ሙላቱ እንደተናገሩት ፤ የእሳት ቃጠሎው የተነሳው ትናንት ምሽት ሶስት ሰዓት ተኩል አካባቢ  በቀበሌ ዘጠኝ ቀጠና ሁለት ሰፈረ ሰላም ባሉ የንግድ ሱቆች ውስጥ  ነው።

በአደጋው  በስድስት የንግድ ሱቆች ውስጥ የሚገኙ የወረቀት ማባዥ ማሽኖች፣ የመዋቢያ ቅባቶችና ሽቶዎች ፣ኮምፒውተሮችና ሌሎችም ንብረቶች መውደማቸውን አስታውቀዋል።

እሳቱ አንድ ሱቅ ውስጥ የተያያዘ ከሰል የነበሩ ሰዎች ሳያጠፉ በመሄዳቸው እንደተነሳ ያስረዱት ኮማንደሩ ጊዜው ምሽት በመሆኑና ሱቆቹ በመቆለፋቸው ንብረቶቹን ማዳን እንዳልተቻለ ገልጸዋል።

የአካባቢው ማህበረሰብና ፖሊስ ፣ እንዲሁም የእሳት አደጋ መከላከያ ተሽከርካሪዎች ባደረጉት ርብርብ የእሳት ቃጠሎ ወደ  መኖሪያ ቤቶች ሳይዛመት መቆጣጠር መቻሉን ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

ግብፅ በኪንሳሻ የተጀመረው የታላቁ ህዳሴ ግድብ ውይይት ሁለተኛው ዙር የውሃ ሙሌት ከመደረጉ በፊት ስምምነት ላይ ለመድረስ የመጨረሻው እድል ሊሆን ይችላል ብላለች።

ግብፅ ይህን ያለቸው ግብፅ ፣ ኢትዮጵያና ሱዳን በታላቁ የህዳሴ ግድብ ዙሪያ እየተደረገ የሚገኘውን ውይይት አስመልክታ ባወጣችው መግለጫ ነው።

ዛሬ ሰኞ እንደሚጠናቀቅ በሚጠበቀው ውይይቱ 3ቱ ሃገራት በዕድሉ ተጠቅመው ከመጪው ክረምት በፊት ከአንዳች ስምምነት እንዲደርሱ ፍላጎታቸው መሆኑን የግብጽ ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ባወጣው መግለጫ አሳእቋል።

ሶስቱን ሃገራት የማደራደር ሃላፊነቱን የተረከቡት የኮንጎ ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ፕሬዚዳንት እና የወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ሊቀመንበር ፍሌክስ ሺሴኬዲ «ሃገራቱ አንድ አልያም በርካታ የተስፋ በሮችን ይከፍቱ ዘንድ አዲስ ጅማሬ እንዲያሳዩ እጋብዛለሁ » ብለዋል።

በእሁዱ ውይይት ስለተነሱ ሀሳቦች ሆነ ስለተደረሰ ስምምነት የተባለ ምንም ነገር የለም።

የግብጹ ፕሬዚዳንት አብደልፈታህ አልሲሲ ባለፈው ሳምንት የግብጽ የውሃ ድርሻ ከተነካ «በቀጣናው አለመረጋጋት ሊያስከትል ይችላል።» ብለው ነበር።

ምንም እንኳ ግብጽ እና ሱዳን ሁለተኛው ዙር የውኃ ሙሌት እንዲራዘም ቢፈልጉም ኢትዮጵያ ሁለተኛውን ዙር የግድቡን ውኃ ሙሌት የፊታችን የክረምት ወራት የመሙላት ዕቅድ እንዳላት ቀደም ብላ አስታውቃለች።

ምንጭ፦ Reuters እና DW

@tikvahethiopia @tikvahethiopia
በአንድ ቀን 37 ሰዎች በኮቪድ-19 ሞቱ፥ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥርም 3 ሺህ ደረሰ !

ባለፉት 24 ሰዓት 37 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 9,038 የላብራቶሪ ምርመራ 2,138 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,054 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 217,327 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 3,000 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 163,022 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 862 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን ከሱዳን ጠ/ሚ ዶ/ር አብደላ ሃምዶክ ጋር በስልክ ተወያይተዋል ፤ በውይይታቸው ፦

- አሜሪካ በሲቪሉ ለሚመራው የሱዳን የሽግግር መንግስት ስለምታደርገው ድጋፍ ተወያተዋል (የሰላም ሂደቱን ስለማስቀጠል፤ ኢኮኖሚያዊ፣ ቀጠናዊ ጉዳዮች እንዲሁም የፖለቲካ ሪፎርም)

- በቅርቡ ከሱዳን ህዝብ ነፃነት ንቅናቄ - ሰሜን (SPLM-N) አል-ሂሉ ጋር የተደረገውን ስምምነት አንቶኒ ብሊንከን በደስታ ተቀብለዋል ፤ በመላ ሱዳን የዜጎችን ደህንነት ማረጋገጥ አስፈላጊ መሆኑን አስገንዝበዋል።

- በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ዙሪያ ስለሚደረገው ድርድር ተወያይተዋል።

- በሱዳን እና ኢትዮጵያ በድንበር (አልፋሽጋ አካባቢ) ያለውን ውጥረት ስለማርገብ አስፈላጊነትና ችግሩ በውይይት እንዲፈታ ተወያይተዋል።

በስቴት ዲፓርትመንት የወጣው መግለጫ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia