TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ፔካ ሐቪስቶ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።

By : www.ethiopiainsider.com

የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የፊንላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሐቪስቶ “በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተለይ የትግራይ ክልል ቀውስ እና በቀጠናው ባለው አንድምታ ላይ ለመወያየት” በድጋሚ ወደ አ/አ እንደሚያቀኑ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል

ሚኒስትሩ ከሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ፤ የተመለከቷቸውን ጉዳዮች የያዘ ሪፖርት በሚቀጥለው ወር ለሚካሔደው የአውሮፓ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያቀርባሉ ተብሏል።

የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ፤ ሐቪስቶ “ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተገናኝተው የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም ያለውን ስጋት” ያስረዳሉ።

በዚሁ ጉዟቸው “ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እና የስደተኞች መብቶች ጥበቃ ህግጋት እንዲያከብሩ እንዲሁም ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ገለልተኛ ምርመራ እንዲከናወን እንዲፈቅዱ ” ጥሪ እንደሚያቀርቡ በመግለጫው ተመልክቷል።

ሐቪስቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሚያነሱት ሌላው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት የተመለከተ እንደሆነ መግለጫው ላይ ጠቅሷል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Attention😷

በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓት 21 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 8,392 የላብራቶሪ ምርመራ 1,997 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 1,297 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 213,311 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,936 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 161,226 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 818 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ግልገልበለስ ከተማ እንቅስቃሴ ቆሟል።

የግልገልበለስ ቲክቫህ አባላት በአካባቢያቸው ስላለወቅታዊ ሁኔታ ሪፖርት ልከዋል።

ከትላንት ጀምሮ ገልገልበለስ ጭር እንዳለች መሆኑን ገልፀዋል ፤ አልፎ አልፎ ከሚታይ የሞተር እንቅስቃሴ ውጭ ፤ የንግድ ተቋማት ዝግ ናቸው ፣ገበያ የለም ቆሟል ፣ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ የለም፣ ከከተማ የሚወጣ ሆነ የሚገባ የህዝብ ትራንስፖርት የለም ፤ ክፍት የስራ ቦታም የለም በአጠቃላይ የከተማዋ እንቅስቃሴ ቆሟል።

ባንክ ቤቶች ስጋት ስላለባቸው ተዘግተዋል ፤ ATM አገልግሎት ግን አልቆመም።

ነዋሪው እንቅስቃሴ ያቆመው ጥያቄ ስላለው ነው ያሉት የግልገልበለስ አባላት ፥ "ሞት በቃን፣ ስደት በቃን፣ ግድያ በቃ፣ የሰላም እጦት በቃን ዘላቂ መፍትሄ ይፈለግልን" የሚል ነው።

በዚህ እንቅስቃሴ ማቆም ዋነኛው ማህበረሰቡ ማስተላለፍ የፈለገው እየተፈፀሙ ያሉ ግድያዎች አለመቆማቸው፣ በሰላም ወጥቶ ለመግባት ፈተና መሆኑ፣ እንደዜጋ የመከበር እና በሰላም የመኖር ጉዳይ ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳሰብ እንደሆነ የግልገልበለስ አባላት ገልፀዋል።

ከግልገልበለስ አባላት መካከል በስልክ ያገኘናቸው አባል ፥ "ጥያቄያችን ሰላማዊ ነው ፥ ስለምን ሞት ፣ ግድያ ፣ መፈናቀል አይበቃም ? ለዚህ ሰላማዊ ጥያቄያችን ደግሞ መልስ እንፈልጋለን ፤ ዛሬ አንዳንድ ተቋማትን የፀጥታ ኃይሎች በኃይል ለማስከፈት ሞክረው ነበር ግን ነዋሪው ጥያቄውን የሚመለከተው አካል ተረድቶት መፍትሄ እንዲሰጠው ይፈልጋል" ብለዋል።

ከላይ የተያያዙት 3 ፎቶዎች የዛሬውን የግልገል በለስ ውሎ የሚያሳዩ ሲሆን በአባላችን BR ተነስተው በ @tikvahethiopiaBOT የተቀመጡ ናቸው።

@tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የG7 ሀገራት መግለጫ ፡ የካናዳ ፣ ፈረንሳይ ፣ ጀርመን ፣ ጣልያን ፣ ጃፓን ፣ ዩናይትድ ኪንግደም እና ዩኤስኤ የሚገኙበት የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እንዲሁም የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ የትግራይን ወቅታዊ ጉዳይ በተመለከተ የጋራ መግለጫ አወጡ። በመግለጫው የቡድን 7 ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች እና የአውሮፓ ህብረት ከፍተኛ ተወካይ ፣ በቅርቡ ሪፖርት የተደረጉ በትግራይ የተፈፀሙ…
የኢፊድሪ መንግስት ለG 7 መግለጫ ምላሽ ሰጠ !

የትግራይ ክልልን አስመልክቶ በቡድን ሰባት አባል ሀገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የወጣው መግለጫ መንግስት እየወሰዳቸው ያሉ ጉልህ እርምጃዎችን ያላገናዘበ መሆኑን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ ትላንት ባወጣው መግለጫ መንግስት በክልሉ የተከሰተውን ችግር ሙሉ በሙሉ ለመቅረፍ በርካታ እርምጃዎች እየወሰደ መሆኑን አመላክቷል፡፡

ሆኖም የቡድን 7 አባል ሃገራት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች የተሰጠው ማግለጫ ይህን ከግንዛቤ ሊያስገባ አልቻለም ነው ያለው ሚኒስቴሩ፡፡

ሚኒስቴሩ ፣ “ባለፈው ሳምንት እንደተገለጸው በሕወሓት ቀስቃሽነት ድንበር አቋርጠው የገቡት የኤርትራ ወታደሮች አሁን ለቀው መውጣት የጀመሩ ሲሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይል ብሔራዊ ድንበሩን በመቆጣጠር ላይ ይገኛል” ብሏል፡፡

መንግስት የሚዲያ ተቋማትን ጭምሮ ለሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በትግራይ ክልል ያለተገደብ እንቅስቃሴ ፈቃድ ቢሰጥም ከአለም አቀፉ ማሕበረሰብ እየቀረበ ያለው እርዳታ በጣም ዝቅተኛ መሆኑን ሚኒስቴሩ በመግለጫው አመልክቷል፡፡

በክልሉ ተፈጽሟል ስለተባለው የሰብዓዊ መብት ጥሰት አለም ዓቀፍ የሰብዓዊ መብት ባለሙያዎች ምርመራ እነዲያደርጉ ፈቃድ የተሰጣቸው ሲሆን ሥራቸውን በቅርቡ እንደሚጀምሩ ሚኒስቴሩ በመግለጫው አስፍሯል፡፡

እንዲሁም መንግስት ከ4.2 ሚሊየን በላይ ለሆኑ ተረጂዎች እረዳታ ማቅረቡን ያስታወሰው መግለጫው ከዚህ ውስጥ ከአለም አቀፍ ማሕበረሰብ የተገኘው የዕርዳት መጠን ከአንድ ሶስተኛ በታች መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም በክልሉ ያለው ችግር ሙሉ በሙሉ እና በወቅቱ እንዲቀረፍ ከተፈለገ በቂ የእርዳታ አቅርቦትን ማሰባሰበ ላይ ቅድሚያ ሊሰጠው እንደሚገባ መግለጫው ማመልከቱን ኤፍ ቢ ሲ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT
የተማሪዎችን ቅበላ እና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጀቱን የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ አስታውቋል !

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት ማዘጋጅቱን ገልጿል።

የኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ ዋና ዳይሬክተር ተሻለ በሬቻ ለኢፕድ እንደገለፁት፣ ዩንቨርሲቲው የተማሪዎችን ቅበላና ድልደላ የሚያስተዳድርበት ሥርዓት አዘጋጀቶ ለኢፊድሪ ሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እንዲፀድቅ አቅርቧል።

በዚህም በቅርቡ ፀድቆ ዩንቨርሲቲው ተማሪዎችን መቀበል እንደሚጀምር ገልጿል።

እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ ፤ ዩንቨርሲቲ መግቢያ ውጤት ያመጡ ተማሪዎችን መቀበል የሚጀምር ሲሆን ተማሪዎቹ በኢትዮጵያ ቴክኒካል ዩኒቨርሲቲ የሚሰጥ የመግብያ ፈተናም እንደሚሰጣቸው ገልፀዋል።

በቀጣዩ ዓመት ጥቅምት ወር ላይ በመቶዎች የሚቆጠሩ ተማሪዎችን ተቀብሎ በመጀመሪያ ዲግሪ እንደሚያስተምርም ዳይሬክተሩ ገልፀዋል። #EPA

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
TIKVAH-ETHIOPIA
ዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ዛሬ ማምሻውን በላከልን መልዕክት ነባር ተማሪዎቹ ከመጋቢት 28-30/2013 ድረስ ወደዩኒቨርስቲው እንዲገቡ ጥሪ አድርጓል። ለዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ነባር ተማሪዎች በሙሉ ፦ የዩኒቨርስቲው ተማሪዎች የሆናችሁ በሙሉ ተቋርጦ የነበረው የመማር ማስተማር ሂደት ለማስጀመር ዩኒቨርሲቲው በወሰነው መሰረት የመግብያ ቀን መጋቢት 28-30/2013 ዓ/ም መሆኑ ኣውቃችሁ በተጠቀሰው ቀን በዩኒቨርሲቲው…
የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ መግቢያ ተራዘመ።

የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ተማሪዎች የመግቢያ ቀን በ1 ሳምንት መራዘሙን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል።

ዩኒቨርሲቲው መግቢያው የተራዘመው ፥ "አንዳንድ ያልተሟሉ ግብዓቶችን በበቂ ለማቅረብ ሲባል" ነው ብሏል።

መጋቢት 28-30 የነበረው ወደ ዩኒቨርስቲው የመግቢያ ቀን ወደ ሚያዝያ 5-7/2013 ነው የተራዘመው።

መረጀው የዓዲግራት ዩኒቨርስቲ ረጂስትራር እና MoSHE ነው።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ለጋዜጠኞች ስለምርጫ አዘጋገብ የተሰጠው ስልጠና :

የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎች ማህበር አዘጋጅነት ለ2 ቀናት በአዲስ አበባ የተካሄደው የጋዜጠኞች የምርጫ አዘጋገብ ስልጠና ጋዜጠኞች በምርጫ ወቅት መረጃ ለህዝብ በሚያደርሱበት ጊዜ ስለ ምርጫ ስለሚኖራቸው የተሻለ ግንዛቤ ያተኮረ ነው።

ከዚህም በተጨማሪ አሁን አሁን እየተባባሰ የመጣውን የጥላቻ ንግግር በማስወግድና ሀቅን በማንጠር ጋዜጠኞች ለዜጎች ትክክለኛ መረጃ ማድረስ እንደሚገባቸው በመድረኩ ተነስቷል።

የማህበሩ ፕሬዜዳንት ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በምርጫ ወቅት ብዙ አጀንዳዎች ወደ ህዝቡ ይቀርባሉ ፤ የሚቀርቡት አጀንዳዎች በመንግስት አካላትም ሆበ በተቃዋሚ ጎራ ሊሆን ይችላል መረጃውን የሚያቀርቡት ጋዜጠኞች እራሳቸውን ከዜናው ውስጥ በማውጣት ሁሉንም ባማከለ መልኩ መረጃዎችን በማመዛዘን ማቅረብ አለባቸው ብለዋል።

ጋዜጠኛ ኤልያስ ፥ "ለአንድ ጋዜጠኛ ትልቁ አለቃው ኤዲተሩ ወይም የሚሰራበት ሚዲያ ባለቤት አይደለም፤ እውነት ነው መሆን ያለበት በተለይ እንደምርጫ ባለ ጉዳይ የሀሰተኛ መረጃ ስርጭቱ ፣ የጥላቻ ንግግሩ የተለያዩ ፕሮፖጋንዳዎች የሚንፀባረቁበት ነው አሁንም እያየን ነው ያለነው ፥ ስለዚህ ከፍተኛ የፕሮፌሽናሊስም ስታንዳርድ ጋዜጠኞች መከተል አለባቸው" ሲሉ ተናግረዋል።

አክለው ፥ ጋዜጠኞች የራሳቸውን አስተያየት፣ የሚደግፉት የሚከተሉት አቋም ሊኖር ቢችልም ነገር ግን ከዛ ውስጥ እራሳቸውን አውጥተው በማሰብ ሁሉንም ባማከለ መንገድ ፣ በገለልተኝነት ዜናዎችን መስራት አለባቸው ብለዋል።

More : https://telegra.ph/EMMPA-04-04

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አውቶብስ ተራ በትንሹ መናኸሪያ የእሳት አደጋ ደረሰ።

በአዲስ አበባ ከተማ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ አውቶቢስተራ አካባቢ በተለምዶ "ትንሹ መናኸርያ" ተብሎ በሚጠራው የአውቶቡስ መናኸሪያ ላይ የእሳት አደጋ መድረሱ ተገለጸ።

ዛሬ ከሰዓት በኋላ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ የአጭር ርቀት መስመሮችን የትራንስፖርት አገልገሎት በሚሰጠው በተለምዶ ስሙ ትንሹ መናኸሪያ ላይ የእሳት አደጋ ደርሷል።

የተከሰተውን የእሳት አደጋ ለመቆጣጠር የእሳትና ድንገተኛ አደጋ ሰራተኞች ርብርብ እያደረጉ እንደሚገኝ ኢዜአ ዘግቧል።

Video : Abdu (Tikvah Family A.A)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ዘ ዊኬንድ ለትግራይ ድጋፍ የሚሆን 1 ሚሊዮን ዶላር አበረከተ።

አቤል ተስፋዬ (ዘ ዊኬንድ) ትውልደ ኢትዮጵያዊው ድምፃዊ በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል የሰብዓዊ ደጋፍ ለማቅረብ የሚውል የ1 ሚሊየን ዶላር ድጋፍ ማደረጉን WFP USA አሳውቋል።

More : https://t.co/9vS6PfQQFj

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Attention😷

ባለፉት 24 ሰዓት 27 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።

በተመሳሳይ ከተደረገው 6,962 የላብራቶሪ ምርመራ 1,878 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

ትላንት 742 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

በአጠቃላይ 215,189 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,963 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 161,968 ሰዎች አገግመዋል።

በአሁን ሰዓት 742 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።

#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#NewsAlert

በሙርሌ ጎሳ አባላት ታግተው ከተወሰዱት ዜጎቻችን መካከል 5ቱ ወደ ሀገራቸው ተመለሱ፡፡

ከጋምቤላ ክልል በደቡብ ሱዳን ሙርሌ ታጣቂዎች ታፍነው ተወስደው ከነበሩ ህፃናትና ሴቶች መካከል አምስቱ ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ አስታውቀዋል።

አቶ ኡሞድ እንዳሉት፥ ከ2008 እስከ 2012 ዓ.ም ድረስ 275 ህፃናት በሙርሌ ጎሳ ታጣቂዎች እንደተወሰዱ ጠቁመው በወቅቱም የሀገር መከላከያ ሰራዊት ባደረገው ኦፕሬሽን 208 ህፃናት ማስመለስ እንደተቻለ አስታውሰዋል።

በ2012 ዓ.ም ደግሞ ከደቡብ ሱዳን ጋር በተደረገው መልካም ግንኙነት 13 ህፃናት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን ጠቅሰዋል።

በአሁኑ ሰዓት 3 ህፃናትና 2 ሴቶች በድምሩ 5 ዜጎቻችን መመለሳቸውን በመግለጽ ቀሪ ያልተመለሱትን ህፃናት ለማስመለስ ከደቡብ ሱዳን መንግስት ጋር እየተሰራ እንደሚገኝ መግለፃቸውን የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬቴሪያት አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ከመጋቢት 27 ቀን 2013 ዓ.መ ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የተሰጡ ሹመቶች :

- መሐመድ ኢድሪስ መሐመድ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር

- ዮናታን ተስፋዬ ረጋሳ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

- ግዛው ተስፋዬ የኢትዮጲያ ብሮድካስት ባለስልጣን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

#PMOEthiopia

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT