የተሰረቁ የመኪና መለዋወጫዎችእና 4 ተጠርጣሪዎች ተያዙ።
የአዲስ አበባ ፖኪስ በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ለልማት ተብለው በተዘጋጁ የመንግስት ቦታዎች ላይ ፖሊስ በምሽቱ ክፍለ ጊዜ ባደረገው የአሰሳ ስራ በርካታ የተሰረቁ የመኪና መለዋወጫ እቃዎችን ከ4 ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።
የምርመራ ስራም እየተሰራ መሆኑን አሳውቋል።
ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት በአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ክልል ልዩ ቦታ አሜሪካን ግቢ እየተባለ ከሚጠራው አካባቢ ነው።
መንግስት ለልማት ብሎ ባዘጋጀቸው ቦታዎች ላይ ግለሰቦቹ በህገ- ወጥ መንገድ የሸራ ቤት ወጥረው ለተለያዩ ህገ-ወጥ ተግባርና ለወንጀል መሸሸጊያነት በማዋል ከተለያዩ ቦታዎች የሰረቋቸውን የመኪና እቃ መለዋወጫዎችን በዚሁ የሸራ ቤት ውስጥ አከማችተው በደላላ አማካኝነት በተለምዶ ሱማሌ ተራ እየተባለ ወደሚጠራው አካባቢ በመውሰድ ለሌሎች ግለሰቦች ሲሸጡ እንደነበረ የምርመራ ውጤቱ አመላክቷል።
ከተያዙት የመኪና እቃ መለዋወጫዎች መካከል ፦
- 183 ስፖኪዮ፣
- 122 የመኪና የፍሬን ጉሚኒ፣
- 21 ፍሬቻ ባለመስታወት ፣
- 3 የመኪና ቴፕ፣
- 36 የመኪና ቸርኬ ጌጣጌጥ በኤግዚቢትነት መያዛቸውን ፖሊስ አሳውቋል።
ንብረት የጠፋባቸው ግለሰቦች በወቅቱ ወደ አቅራቢያቸው ፖሊስ ጣቢያ ሄደው ስለማመልከታቸውና የጠፋባቸውን የእቃ አይነት ማስረጃዎችን ይዘው በመቅረብ ንብረታቸውን መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
መረጃው የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ መርካቶ አካባቢ ፖሊስ ነው።
@tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! እነ አቶ ስብሃት ነጋ ጉዳያችን በትግራይ ክልል ፍርድ ቤት ይታይልን ሲሉ አቤቱታ አቀረቡ፡፡ ይህን አቤቱታ ያቀረቡት ዛሬ በፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድቤት አራዳ ምድብ ችሎት ነው። የጠቅላይ አቃቤ ህግ ቡድን በበኩላቸው የፌዴራል መንግስትን ስልጣን ለመጣል በሚል የሽብር አዋጁን በመተላለፍ በመላው ሀገሪቱ የተፈጸመ ወንጀል መሆኑን በመጥቀስ ተጠርጣሪዎቹ መቀሌ ሆነው በሰጡት ትዕዛዝ ባህርዳር…
6 ተጠርጣሪዎች ወደቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዘዘ።
ሻምበል ጻዲቅ ኪሮስ፣ ዋና ሳጅን ብርሃኑ ፍጹም፣ ዋና ሳጅን አሰፋ መአዛ፣ ዋና ሳጅን ሞገስ ደሳለኝ፣ ሃይሌ አብርሃ እና ፈይሳ ተካ የተባሉ ተጠርጣሪዎች ወደ ቂሊንጦ ማረሚያ ቤት እንዲወርዱ ታዟል።
ግለሰቦቹ ከ 'ህወሓት' ጋር በመቀናጀት የተለያዩ ተልዕኮዎችን በመፈጸም ላይ እንዳሉ ተይዘዋል ተብለው የተጠረጠሩ የትግራይ ልዩ ሃይል እና ሚሊሻዎች ናቸው።
በሌላ በኩል እነአቶ ስብሃት ነጋ በትግራይ ፍርድ ቤት ጉዳያችን ይታይልን ሲሉ ያቀረቡት ጥያቄ ፍርድ ቤት ውድቅ አድርጎታል።
ከዚህ በፊት በነበረው ቀጥሮ ተጠርጣሪዎቹ ጉዳያችን በፌደራል ፍርድ ቤት ሳይሆን በትግራይ ክልል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ነው መታየት ያለበት ሲሉ አቤቱታ አቅርበው ነበር፡፡
አቤቱታውን የተመለከተው ፍርድቤት ጉዳያቸው መታየት ያለበት አካባቢ ወሰን ሳይደረግበት ወንጀሉ ሲፈፀምም ከክልሉ ውጪ ባህር ዳርና ጎንደር በሮኬት የተመታ እና በሃገር መከላከያ ሰራዊት ላይ ጥቃት የደረሰ በመሆኑ እንዲሁም የፌደራል መንግስትን ስልጣን በሃይል ለመቆጣጠር የተፈፀመ በመሆኑ የአካባቢ ዳኝነት ስልጣን ያለው የፌደራል ፍርድ ቤቶች ነው ሲል ጥያቄቸውን ውድቅ አድርጓል።
የዛሬ ችሎት ውሎ ዝርዝር : telegra.ph/UPDATE-04-02 ~ ኤፍቢሲ

#እጅግ_ከፍተኛ_ጥንቃቄ😷
ባለፉት 24 ሰዓት 25 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 9,017 የላብራቶሪ ምርመራ 2,353 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 493 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 211,314 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,915 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 159,929 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 829 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።
#Purpose
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT

የትግራይ አብዛኛዎቹ ከተማዎች በጨለማ ተውጠዋል።
ከትላንት ሀሙስ ከሰዓት ጀምሮ በትግራይ መቐለን ጨምሮ በበርካታ ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል ተቋርጧል።
የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል የኮሚኒኬሽን ዳይሬክተር አቶ ሞገስ መኮንን በአብዛኞቹ የትግራይ ክልል ከተሞች የኤሌክትሪክ ኃይል መቋረጡን ገልፀው ፥ "ኤሌክትሪክ የተቋረጠው ከመሆኒ 40 ኪ.ሜ ላይ ወደ መቐለ ባለ መስመር ላይ ሊሆን እንደሚችል ነው የተቋሙ ባለሞያዎች የለዩት" ብለዋል።
ትክክለኛው ቦታ ባይታወቅም የባለሞያዎቹ ግምት ወደዛ መስመር ነው ሲሉ አስረድተዋል።
የኤሌክትሪክ መቋረጡን ምክንያት በተመለከተም አቶ ሞገስ ፥ ቦታው ተለይቶ ያጋጠመውን ችግር መለየት እስኪቻል ድረስ ምክንያቱ ይሄ ነው ብሎ መግለፅ እንደማይቻል ተናግረዋል።
ኤሌክትሪክ በተቋረጠባቸው ከተሞች ኤሌክትሪክ ሚመለሰው ችግሩ ተለይቶ አስቸኳይ የጥገና ስራ እንደተጠናቀቀ ነው ሊመጣ የሚችለው ፥ ትክክለኛው ቦታውን የመለየት ስራ ተጀምሯል ብለዋል።
መቼ ነው የኤሌክትሪክ አገልግሎት ለሚመለሰው ለሚለው ጥያቄም ችግሩ ስላልተለየ ለመገመት እንደማይቻል ገልፀዋል።
በትግራይ ውስጥ ግጭት ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በተለያየ ጊዜ እና በተለያየ ምክንያት ኤሌክትሪክ እየተቋረጠ የክልሉ ነዋሪዎች ረጅም ጊዜያትን በጨለማ ውስጥ ለማሳለፍ ሲገደዱ እንደነበር አይዘነጋም።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Share
"የኮቪድ-19 ክትባትን ለማግኘት ምንም ዓይነት የኮቪድ 19 ቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ማድረግ አያስፈልግም" - ጤና ሚኒስቴር
የጤና ሚኒስቴር ዛሬ ምሽት ባሰራጨው መልዕክት የኮቪድ-19 ክትባት መርሃ ግብር በታቀደው መሰረት በመላው ኢትዮጵያ መሰጠት መቀጠሉን ገልጿል።
እስካሁን ባለው ቁጥራቸው በርካታ የሆኑ የጤና ባለሙያዎች ተከትበዋል።
እድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ የሆኑ የማህበረሰብ ክፍሎች እና ከ55-64 ዓመት ሆነው የሚታወቅ ተጓዳኝ የጤና ችግር ያለባቸው የህብረተሰብ ክፍሎች ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የኮቪድ 19 ክትባትን ማግኘት ይጀምራሉ፡፡
ጤና ሚኒስቴር ክትባቱን ለመውሰድ የኮቪድ- 19 የቅድመ ላብራቶሪ ምርመራ ያስፈልጋል እና ሌሎች ክትባቱን በተመለከተ የሚነገሩት ነገሮች ማህበረሰቡ ትክክል እንዳልሆኑ በመገንዘብ የክትባቱን እንዲወስድ ፥ ከአላስፈላጊ ወጪ አልፎም ከሚፈጠረው ትርምስ እንዲሁም አካላዊ ንክኪ እንዲቆጠብ ብሏል።

"ለእናቶች ደም እንለግስ" - የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒተል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ 'ለእናቶች ደም እንለግስ' በሚል ከፊታችን መጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የደም ልገሳ መርሃግብር ማዘጋጀቱን አሳውቆናል።
የደም ልገሳው መጋቢት 30 ፣ ሚያዚያ 1 እና ሚያዚያ 2 ሲሆን 5ኛ በር አካባቢ ነው የሚደረገው።
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የአ/አ ቲክቫህ አባላት በተባሉት ቀናት እና ቦታ በመገኘት ለእናቶች ደግም እንድትለግሱ መልዕክት አስተላልፎላችኃል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ 'ለእናቶች ደም እንለግስ' በሚል ከፊታችን መጋቢት 30 እስከ ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ዓ/ም ድረስ የደም ልገሳ መርሃግብር ማዘጋጀቱን አሳውቆናል።
የደም ልገሳው መጋቢት 30 ፣ ሚያዚያ 1 እና ሚያዚያ 2 ሲሆን 5ኛ በር አካባቢ ነው የሚደረገው።
ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ህክምና ኮሌጅ የአ/አ ቲክቫህ አባላት በተባሉት ቀናት እና ቦታ በመገኘት ለእናቶች ደግም እንድትለግሱ መልዕክት አስተላልፎላችኃል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#ማስታወሻ ከዛሬ ጀምሮ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ በማኅበር ተደራጅተው ቤት ለመስራት አቅም እና ፍላጎት ያላቸው በአማራጭ ጋራ መኖሪያ ቤት ግንባታ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ምዝገባ ይጀምራል። የወጣውን መስፈርት የምታሟሉ መመዝገብ ትችላላችሁ። aahdab.gov.et በሚለው የቢሮው አድራሻ በኦንላይን ነው መመዝገብ የሚቻለው። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...በ4 ቀናት 3000 ነዋሪዎች ተመዝግበዋል" - የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ
የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት ቢሮ በቅርቡ በ20/80 እና በ40/60 ፕሮግራም ሙሉ ክፍያ ከፍለው ቤት ለማግኘት እየተጠባበቁ ላሉና 70 በመቶ መክፈል የሚችሉ ነዋሪዎች በማህበር ተደራጅተው መኖሪያ ቤት መገንባት እንዲችሉ አማራጭ አቅርቦ ነበር።
ቢሮው ፥ ለግንባታው የሚሆን መሬት በ5 ክፍለ ከተሞች እነዚህም በአዲስ ከተማ፣ በንፋስ ስልክ ላፍቶ፣ በአቃቂ ቃሊቲ፣ በኮልፌ ቀራንዮና በቦሌ ክፍለ ከተሞች መዘጋጀቱን አሳውቋል።
የመጀመሪያ ዙር ከ100 እስከ 130 ማህበራት ለማደራጀትና 10 ሺ የሚደርሱ ቤት ፈላጊ አባወራዎችን ተጠቃሚ ለማድረግ እየተሠራ ነው የተባለ ሲሆን ምዝገባው በተጀመረ ባሉት አራት ቀናት ውስጥ ብቻ ከ3,000 በላይ ሰዎች ተመዝግበዋል ተብሏል።
የቤት ግንባታው የሚከናወነው በ2 አይነት መንገድ ነው ፦ አንደኛው እስከ 9 ፎቆች፣ ሁለተኛው ደግሞ 13 ፎቆች መሆኑ ተገልጿል፤ የግንባታ ሥራው በ18 ወራት ይጠናቀቃል ተብሎ የሚጠበቅ ሲሆን ማህበራቱ በፈለጉት ኮንትራክተር ማስገንባት እንደሚችሉ የአዲስ አበባ ከተማ ቤቶች ልማት ቢሮ መግለፁን ኢፕድ በድረገፁ አስነብቧል።

በጅሌ ጥሙጋ የሰዓት እላፊ ገደብ ታወጀ።
የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ቤት፥ የአካባቢውን ሰላም የበለጠ ለማረጋገጥ እንዲቻል በወረዳ ደረጃ ኮማንድ ፖስት መቋቋሙን አሳውቋል።
ኮማንድ ፖስቱ የሰው እና የባጃጅ እንቅስቃሴ የምሽት የሰአት አለፊ ገደብ አስቀምጧል።
በዚህም መሰረት ባጃጅ እስከ ምሽቱ 2 ሰአት ሲሆን ሰዎች ደግሞ እስከ ምሽቱ 3 ሰአት ብቻ መንቀሳቀስ የሚችኑ መሆኑን ኮማንድ ፖስቱ አስታውቋል።
ከተጠቀሰው ሰአት ውጭ የሚንቀሳቀስ ሰውም ሆነ ባጃጅ ካለ የህግ እርምጃ እደሚወሰድበት የጅሌ ጥሙጋ ወረዳ ፖሊስ ፅ/ ቤት አሳስቧል።

የጢስ ዓባይ ባህር ዳር የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ስርቆት ተፈፀመበት ! ከጢስ ዓባይ የውሃ ኃይል ማመንጫ ወደ ባህር ዳር የተዘረጋው ባለ 132 ኮሎ ቮልት የከፍተኛ ኃይል ተሸካሚ መስመር ምሰሶ ላይ ስርቆት መፈፀሙን የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ገለፀ። ከሰኞ ምሽት ጀምሮ በተፈፀሙ ስርቆቶች 8 ምሰሶዎች ወድቀዋል፡፡ ይሁንና በአካባቢው ኃይል እንዳልተቋረጠ ማረጋገጥ ተችሏል፡፡ ምሰሶዎቹ በመውደቃቸው…
ዘራፊዎቹ ተያዙ።
ከጢስ ዓባይ - ባህር ዳር በተዘረጋው የባለ 132 ኮሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ መስመር ምሰሶዎች ላይ ስርቆት የፈፀሙ ሁለት ተጠርጣሪዎች ከሰረቁት ንብረት ጋር እጅ ከፍንጅ መያዛቸው ተሰምቷል።
ህብረተሰቡ ለፀጥታ ኃይሎች በሰጠው ጥቆማ ምሰሶውን በመቆራረጥ በማዳበሪያ ጠቅልለው ከመሸጣቸው በፊት በአማራ ክልል የፀጥታ ኃይሎች የተያዙ ሲሆን ከወንጀሉ ጋር የተገናኙ ሌሎች ተጠርጣሪዎችን ለመያዝ ምርመራ ቀጥሏል ተብሏል።
በጢስ ዓባይ - ባህር ዳር ባለ 132 ኮሎ ቮልት የኃይል ማስተላለፊያ ምሰሶዎች ላይ የተፈፀመው ስርቆት የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይልን ከ16 ሚሊዮን ብር በላይ ለሆነ ኪሳራ ዳርጎታል።
ከዘረፉት ንብረት ጋር እጅ ከፍንጅ የተያዙት ግለሰቦች ምን አይነት ቅጣት ይጠብቃቸው ይሆን ? የኢነርጂ አዋጁ ምን ይላል : telegra.ph/Ethiopian-Electric-Power-04-03

በመራጭነት ለመመዝገብ ምን ያስፈልጋል? መምረጥ የማይችሉ ዜጎች አሉ ?
ለመራጭነት ለመመዝገብ ፦
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት
- እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ
- 6 ወራት ነዋሪነት
- ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ ወይም ነዋሪነት የሚያውቁ ምስክሮች
በመራጭነት መመዝገብ የማይችሉ ፦
- በአዕምሮ ሕመም ሳቢያ የመወሰን አቅም ውስንነት ያለባቸው
- የእስር ፍርደኞች
- የመምረጥ መብታቸው በሕግ የተገደበባቸው
#CARD
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለመራጭነት ለመመዝገብ ፦
- ኢትዮጵያዊ ዜግነት
- እድሜያቸው ከ18 ዓመት በላይ
- 6 ወራት ነዋሪነት
- ነዋሪነት ማረጋገጫ መታወቂያ ወይም ሌላ ሰነድ ወይም ነዋሪነት የሚያውቁ ምስክሮች
በመራጭነት መመዝገብ የማይችሉ ፦
- በአዕምሮ ሕመም ሳቢያ የመወሰን አቅም ውስንነት ያለባቸው
- የእስር ፍርደኞች
- የመምረጥ መብታቸው በሕግ የተገደበባቸው
#CARD
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በአንድ የምርጫ ጣቢያ ላይ የዘረፋ ሙከራ ተደርጓል" - ወ/ሪት ሶሊያና
የምርጫ ቦርድ ኮሚኒኬሽን አማካሪ ወ/ሪት ሶሊያና ሽመልስ ፥ ከሰሞኑን አዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ወረዳ ስምንት ምርጫ ጣቢያ ላይ የዘረፋ ሙከራ መደረጉን ተናግረዋል።
ወ/ሪት ሶሊያና እንደተናገሩት ፥ የምርጫ ጣቢያው ቢሮው ተከፍቶ "ብሉ ቦክስ" / እቃዎች ታሽገው የተቀመጡበት ሳጥን ተወስዶ 100 ሜትር ርቀት ላይ ተገኝቷል።
በሙከራው ምንም የተወሰደ ንብረት የሌለ ሲሆን ሳጥኑ እንደታሸገ ነው የተገኘው። እቃው ተመልሶ ምርጫ ጣቢያው ስራውን ቀጥሏል።
በዚህ ጉዳይ ምርጫ ቦርድ ከከተማው አስተዳደር እና ከፖሊስ ጋር የተነጋገረ ሲሆን እንዲህ ያለ ነገር ዳግም እንዳይፈጠር ምርጫ ጣቢያ አካባቢ ጥበቃ እንዲጠናከር አሳስቧል።
በአዲስ አበባ ከተማ የካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ኃላፊ ኮማንደር ደመና ተስፋዬ ፥ ከሰሞኑን አንድ ምርጫ ጣቢያ በሩ ተከፍቶ ንብረት መወሰዱን እና የተወሰደውን ንብረት ሁሉንም ማግኘች መቻሉን እና ወደምርጫ ጣቢያው ምንም ቁሳቁስ ሳይጎድል እንዲመለስ ማድረግ መቻሉን አሳውቀዋል።
በምርጫ ጣቢያው ላይ ይተፈፀመው ተራ ዘረፋ ? ወይስ ሌላ ተልዕኮ ያለው ? በሚል የተጠየቁት የመምሪያው ኃላፊ ፥ "ዘረፋ ነው አይደለም፤ ሌላ ነገር ሆኖ ምርመራ ጀምረን እውነት የሚመስሉ ነገሮችን አግኝተናል" ብለዋል። ይህን ሊሉ የቻሉት ምርመራው በሂደት ላይ ስለሆነ እርግጠኛ መሆን ስላልተቻለ መሆኑን ገልፀዋል።
አሁን ላይ በሁሉም የምርጫ ጣቢያዎች የጥበቃው ሁኔታ መጠናከሩን አሳውቀዋል።
መረጃውን ያገኘነው ከሸገር ኤፍ ኤም ሬድዮ ጣቢያ ነው።

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
"... በሁለት ተርባይኖች በአመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት ስራ እንዲጀመር እየተሰራ ነው" - ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ
የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ሚኒስትሩ ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ በቀለ የታላቁ የህዳሴ ግድብ ምስረታ 10ኛ ዓመት አስመልክተው ባስተላለፉት መልዕክት የግድቡ ሁለት ተርባይኖች በዓመቱ መጨረሻ ኤሌክትሪክ ሀይል ማመንጨት እንዲጀምሩ እየተሰራ መሆኑን አሳውቀዋል።
ዶ/ር ኢ/ር ስለሺ፥ ግድቡ 79 በመቶ ያህል መድረሱን ገልፀው ፥ በዚህ ዓመት የውሃ ማስተላለፊያ ፥ ወደ ታችኛው ተፋሰሶች የሚያስተላፍ የውሃ ማስወጫ ስራዎች በስፋት የሚሰራበት ነው ብለዋል።
በተጨማሪ ይህ ዓመት 11ዱን ተርባይኖች ማንሳት የሚችሉ የብረት ስራዎች እየተሰሩ ያሉበት መሆኑንና የግድቡን ቁመት ለማሳደግ የኮንክሪት ስራ እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

"የሀገር መከላከያ ሰራዊትና የፌዴራሉ ሰራዊት በ8 ግንባሮች ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረጉ ፤ መስዋእትነት እየከፈሉ ነው" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ በሩቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን አይችሉም ብለው የሚያስቡ ኃይሎች ሽፍቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያን ለመከፋፈል እየሰሩ ነው ሲሉ ተደምጠዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ይህንን ያሉት ዛሬ በእንጦጦ ኦብዘርቫቶሪ ምርምር ማእከል ደመናን ወደ ዝናብ የመቀየር ቴክኖሎጂን የማስተዋወቅ መርሃ ግብር ላይ ባደረጉት ንግግር ነው።
ጠ/ሚሩ ፥ "በሩቅ ያሉ ኢትዮጵያውያን አትችሉም ስለዝናብ ስለ ግድብ አታስቡ እናተ በበሬ እያረሳችሁ የጎደላችሁን ስንዴ እኛ እየረዳናችሁ መኖር ብቻ ነው የተፈቀደላችሁ የሚሉ ኃይሎች ከውስጥ ከተገዙ ሽፍቶች ማንነታቸውን የማያውቁ ሽፍቶችን በመጠቀም ኢትዮጵያውያንን እርስ እርስ ለማባላት እና ለማከፋፈል ቀን ከሌት እየሰሩ ይገኛሉ" ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ በንግግራቸው 'ሽፍቶችን' እየተጠቀሙ ነው ያሉትን እና ኢትዮጵያውያን አይችሉም የሚሉት ኃይሎች እነማን እንደሆኑ ስም ጠቅሰው አልተናገሩም።
ነገር ግን ተላላኪ የተባሉትን ኃይሎች እና አሸባሪዎችን ጠራርጎ ማጥፋት ከተቻለ ዋናው የላከውን ኃይል መጋፈጥ እና ፍላጎቱን መገንዘብ የሚቻልበት ጊዜ ሩቅ አይደለም ብለዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ፥ ባደረጉት ንግግር የሀገር መከላከያ እና የፌዴራል ሰራዊት በ8 ግንባሮች ፀረ አርሶ አደረ፣ ፀረ ንፁሃን ዜጎች የሆኑ በሰሜን በምዕራብ ተሰልፈው ኢትዮጵያን ሊያባሉ ከተነሱ ኃይሎች ጋር ከፍተኛ ፍልሚያ እያደረጉ እና መስዋዕትነት እየከፈሉ ይገኛሉ ሲሉ ተደምጠዋል።
More : telegra.ph/PM-Dr-Abiy-Ahmed-04-03

ፔካ ሐቪስቶ ወደ አዲስ አበባ ይመጣሉ።
By : www.ethiopiainsider.com
የአውሮፓ ህብረት ልዩ መልዕክተኛ የሆኑት የፊንላንዱ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ፔካ ሐቪስቶ “በኢትዮጵያ ነባራዊ ሁኔታ በተለይ የትግራይ ክልል ቀውስ እና በቀጠናው ባለው አንድምታ ላይ ለመወያየት” በድጋሚ ወደ አ/አ እንደሚያቀኑ የአውሮፓ ህብረት አስታውቋል
ሚኒስትሩ ከሁለተኛው ዙር የኢትዮጵያ ጉብኝታቸው በኋላ ፤ የተመለከቷቸውን ጉዳዮች የያዘ ሪፖርት በሚቀጥለው ወር ለሚካሔደው የአውሮፓ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሮች ስብሰባ ያቀርባሉ ተብሏል።
የአውሮፓ ህብረት የውጭ ግንኙነት ቢሮ ዛሬ ቅዳሜ ባወጣው መግለጫ ፤ ሐቪስቶ “ከኢትዮጵያ ባለሥልጣናት ተገናኝተው የአውሮፓ ህብረት በትግራይ ባለው ሰብዓዊ ሁኔታ አሁንም ያለውን ስጋት” ያስረዳሉ።
በዚሁ ጉዟቸው “ሁሉም ወገኖች ከግጭት እንዲታቀቡ፣ ዓለም አቀፍ ሰብዓዊ እና የስደተኞች መብቶች ጥበቃ ህግጋት እንዲያከብሩ እንዲሁም ተፈጽመዋል በተባሉ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ገለልተኛ ምርመራ እንዲከናወን እንዲፈቅዱ ” ጥሪ እንደሚያቀርቡ በመግለጫው ተመልክቷል።
ሐቪስቶ በኢትዮጵያ ቆይታቸው የሚያነሱት ሌላው ጉዳይ የኤርትራ ወታደሮች ከትግራይ ክልል መውጣት የተመለከተ እንደሆነ መግለጫው ላይ ጠቅሷል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#Attention😷
በኢትዮጵያ የኮቪድ-19 ሟቾች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።
ባለፉት 24 ሰዓት 21 ሰዎች በኮቪድ-19 መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል።
በተመሳሳይ ከተደረገው 8,392 የላብራቶሪ ምርመራ 1,997 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ትላንት 1,297 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።
በአጠቃላይ 213,311 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ሲረጋገጥ ከእነዚህ መካከል 2,936 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል፤ 161,226 ሰዎች አገግመዋል።
በአሁን ሰዓት 818 ሰዎች በፅኑ ታመዋል።