በወርቅ ቤቶች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!
በወርቅ ቤቶች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው በተለይ ፒያሳ አካባቢ የዘረፋ ወንጀል የሚፈፅሙ በ2 ቡድን የተደራጁ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።
እንደፖሊስ ገለፃ ፥ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ታጥቀው በተሽከርካሪ እየታገዙ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ በፖሊስ አባላት ክትትል ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከዘረፉት በርካታ ወርቅ፣ ለወንጀል ተግባራቸው ከሚገለገሉባቸው ተሽከርካሪ፣ሽጉጥ እና የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
በሌላ በኩል ፦
ፌሮ ብረት ፣ ዱላ ፣ ድንጋይ እና ስለት በመጠቀም ንብረት ለመውሰድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ሲያደርሱ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ በሁለት ቡድን የተደራጁ 8 ተጠርጣሪዎች በከፍተኛ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡
ተጠርጣሪዎቹ በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በለሊቱ ክፍለ ጊዜ አሳቻ ሰዓት እና ቦታ እየመረጡ ወንጀሉን ሲፈፅሙ ነበር፡፡
ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው አምነው የት ? እና እንዴት ? እንደፈፀሙም ለፖሊስ መርተው ማሳየታቸውን የአ/አ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ምሽት ገልጿል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#Attention😷
በኮቪድ-19 የበርካታ ሰዎች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ሕክምና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለኢፕድ አስታወቁ።
በሚሊኒየም የኮቪድ ሕክምና ማዕከል ብቻ በ51 ሳምንት ውስጥ የፅኑ ሕክምና ፈላጊ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን እና አይ.ሲ.ዩ ክፍሎች በመሙላታቸው በመተንፈሻ ማሽን ለመረዳት ጥያቄ ያቀረቡ ታካሚዎችን ለመመለስ መገደዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡
ዶ/ር ውለታው፤ ወደማዕከሉ የሚገቡት በርካታ ታካሚዎች በፀና የታመሙ፣ ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እና የሕክምና ባለሙያዎችን የተለየ ትኩረትና ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ተጓዳኝ ህመም የሌለባቸውና በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ጭምር እየተጠቁ መሆናቸው የበሽታው ስርጭት አስጊ ደረጃ ላይ ለመድረሱ ማሳያ ነው ብለዋል።
አሁን ባለው ሁኔታ ግን በጣም አስፈሪ የሆነ በርካታ የፅኑ ህሙማን ቁጥር እየተመዘገበ መሆኑን ነው ገልፀው ከችግሩ ስፋት አኳያ የሞት ምጣኔ ወደ ሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን አሳውቀዋል፡፡
«ያለምክንያት ዋጋ መክፈል ይብቃ» የሚሉት ዶክተር ውለታው፤ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና ከአንድ ቤት ሁለት ሦስት ሰው የሚሞትበት ሁኔታ መኖሩን ነው የተናገሩት።
አሁን አይ.ሲ.ዩ ክፍሎቹ ውስጥ ያሉ 20 አልጋዎች በማሽን የሚታገዙ፤ 20 ደግሞ ከማሽን ውጪ የሆኑት ሁሉም በመሙላታቸው በመተንፈሻ ማሽን ለመረዳት ጥያቄ ያቀረቡ ታካሚዎችን ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።
እነዚህ ታካሚዎች አገልግሎት አላገኙም ማለት በሕይወት የመቆየት ዕድላቸው አናሳ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተሩ፤ ማሽኖቹም ላለፉት ዘጠኝ ወራት ያለምንም እረፍት በመስራታቸው እየደከሙ መሆናቸው ጉዳዩን የከፋ እያደረገው መሆኑን ነው የገለፁት።
More : telegra.ph/COVID19Ethiopia-02-20
@tikvahethiopia

ኦነግ ከምርጫ 2013 ወጥቷል ?
ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኦነግ አመራሮችን በሚዲያዎች እየተሰራጨው ስላለው "ኦነግ ከምርጫ 2013 ወጥቷል" የሚል መረጃ ውሳኔ የተላለፈበት መሆን አለመሆኑን ? እንዲሁም ኦነግ በምርጫው አይሳተፍም ወይ ? ሲል ጠይቋል።
የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ በቲክቫህ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም በድርጅታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ ስለሚነሱ ቅሬታዎች ደቂቃዎችን ወስደው ማብራሪያ ሰጥተዋል። (ይህ በቀጣይ የምንዳስሰው ይሆናል)
ትላንት በማህበራዊ ሚዲያ ስለተሰራጨው መረጃ አቶ በቴ ኡርጌሳ የሰጡት ምላሽ ተከታዩን ነው ፦
"ሊቀመንበራችን ያሉት በምርጫው የመሳተፋችን ነገር ተገድቦብናል፣ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻልንም፣ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም የጊዜ ገደቡ ደግሞ እያለቀ ነው ያሉት። ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ አንድ ላይ አመራሩ ተወያይቶ ፣ መክሮ ነው መግለጫ የሚሰጥበት፤ ሊቀመንበሩ ለሚዲያዎች የገለፁት አሁን ባለው ሁኔታ ርጫ እንቅስቃሴ ላይ እየተሳተፍን አይደለም የሚል ብቻ ነው።"
አቶ ዳውድ ኢብሳ (የኦነግ ሊቀመንበር) ሰሞኑ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት ቃለ ምልልስ ትኩረት ያደረገውና ሀሳባቸውን የሰጡት ከላይ በተገለፀው መንገድ ነው ሚዲያዎች እየተቃባበሉ ገና ከወዲሁ "ኦነግ ከምርጫ ወጣ" እያሉ መናገራቸው ምክንያቱ ሊገባን አልቻለም ብለዋል አቶ በቴ።
የሆነው ሆኖ በአንድ ሳምንት የሚቀየር ነገር ይኖራል ብለን አንጠብቅም የሚሉት አቶ በቴ ፤ አዝማሚያዎቹ ግን ወደዛው ናቸው አሁን ላይ ግን ኦነግ ምርጫውን ጥሎ ወጥቷል የሚለው ትክክል አይደለም ፤ ውሳኔም አልተላለፈበትም ብለዋል።
የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ መረጃ ሲኖር በይፋ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጾልናል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#EthiopiaElection2013
የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።
ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።

"ጊዜያዊ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም" - የጋሞ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ
የጋሞ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት የተሰጡ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ የያዙ አሽከሪካሪዎች በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሕጋዊ ተቀባይነት እንደሌላቸው ዛሬ ገለፀ።
ጊዜያዊ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በቀላሉ አመሳስሎ ለመስራት የተጋለጠ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ ብቃት ማረጋገጫ መዘጋጀቱም መምሪያው አሳውቋል።
ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ጊዜያዊ የአሽከሪካሪ ብቃት ማረጋገጫ የወሰዱ ግለሰቦች ፎቶግራፍ በሶፍት ኮፒ እና የደም ዓይነት ምርመራ ከሕጋዊ የጤና ተቋም በማምጣት ተመዝግበው ለአዲስ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ 680 ብር እና ለእድሳት 620 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።
ከዚህ በፊት ተመዝግበው ደረጃውን የጠበቀ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ መጥቶላቸው ያልተወሰዱ 6 ሺህ መንጃ ፈቃዶች በመምሪያው ስለሚገኙ አሽከሪካሪዎች አንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።
ምንጭ፦ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሳይ ካሎሴ ፣ ጋሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን

በዶ/ር ትምኒት ገብሩ መባረር የተተቸው ጉግል ሌላ ባለሙያ አባረረ !
ጉግል ከወራት በፊት የሰው ሠራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የሥነ ምግባር ክፍል ባለሙያ የሆነችው ዶክተር ትምኒት ገብሩን በማባረሩ ሲተች ነበር።
አሁን ደግሞ ማርጋሬት ሚቼል የተባለች ሌላ ባለሙያ ማባረሩን ቢቢሲ/BBC ዘግቧል።
ማርጋሬት የሰው ሠራሽ ክህሎት ክፍሉ፣ የሥነ ምግባር ቅርንጫፍ መስራች ናት።
ጉግል ማርጋሬት የተባረረችው የጉግልን መርህ በመጣስ ፣ ከድርጅቱ ሰነድ ስላወጣች ነው ብሏል። (BBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጉግል ከወራት በፊት የሰው ሠራሽ ክህሎት (አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ) የሥነ ምግባር ክፍል ባለሙያ የሆነችው ዶክተር ትምኒት ገብሩን በማባረሩ ሲተች ነበር።
አሁን ደግሞ ማርጋሬት ሚቼል የተባለች ሌላ ባለሙያ ማባረሩን ቢቢሲ/BBC ዘግቧል።
ማርጋሬት የሰው ሠራሽ ክህሎት ክፍሉ፣ የሥነ ምግባር ቅርንጫፍ መስራች ናት።
ጉግል ማርጋሬት የተባረረችው የጉግልን መርህ በመጣስ ፣ ከድርጅቱ ሰነድ ስላወጣች ነው ብሏል። (BBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
"4 የታጠቁ ሰዎች መኪናችንን ዘረፉን" - የቲክቫህ አባላት መነሻውን ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ያደረገ የታርጋ ቁጥር 22984 "ሀይሮፍ መኪና" በ4 መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች እንደተዘረፈባቸው የመኪናው ባለቤቶች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ጠቁመዋል። አራቱ ሰዎች መኪናውን ኮንትራት ይዘው ይጓዙ የነበረ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል ሹፌሩ እና ረዳቱን በመደብደብ መኪናውን ሰርቀው ጠፍተዋል። መኪናው…
በ4 የታጠቁ ሰዎች ተዘርፎ የነበረው መኪና በጸጥታ ሃይል ክትትል ባህርዳር ተገኝቷል!
ከጥቂት ቀናት በፊት መነሻውን ከከሚሴ ወደ አዲስ አበባ ያደረገ የታርጋ ቁጥር 22984 "ሀይሮፍ መኪና" በ4 መሳሪያ የታጠቁ ሰዎች እንደተዘረፈባቸው የመኪናው ባለቤቶች የሆኑ የቲክቫህ አባላት ጠቁመው እንደነበረ ይታወሳል።
አራቱ ሰዎች መኪናውን ኮንትራት ይዘው ይጓዙ የነበረ ሲሆን ወደ አዲስ አበባ ሊገባ ሲል አሌልቱ ሲደርሱ ለሽንት ቁምልን ካሉ ቡሃላ ሹፌሩን እና ረዳቱን በመደብደብ መኪናውን ሰርቀው ጠፍተው ነበር።
መኪናው የተዘረፈባቸው የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ጉዳዩን ለፖሊስ ባሳወቁት መሰረት የከሚሴ ከተማ የህዝብ ሰላም እና ደህንነት እንዲሁም የዞኑ የጸጥታ አካላት ባደረጉት ክትትል መኪናው በባህርዳር ከተማ መገኘቱን እና ባለቤቶቹ እጅ መግባቱን የከሚሴ ከተማ የህዝብ ሰላም እና ደህንነት እን ም/ከንቲባ አቶ ጀማል ኢብራሂም ገልጸዋል።

በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 5 ሺህ 626 ኩንታል ስኳርና ጨው በቁጥጥር ስር ዋለ!
በደቡብ ወሎ ዞን ቃሉ ወረዳ በህገ ወጥ መንገድ ተከማችቶ የተገኘ 5 ሺህ 626 ኩንታል ስኳርና አዮዲን የሌለው ጨው በቁጥጥር ስር መዋሉን የወረዳው ንግድና ገበያ ልማት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ሰይድ ይማም እንደገለጹት ስኳር እና ጨዉ የተገኘው ትናንት ከህብረተሰቡ በደረሰ ጥቆማ ነው።
በጥቆማው መሰረት ከፖሊስ ጋር በመቀናጀት ባደረጉት ክትትል 4 ሺህ 26 ኩንታል ስኳር እና አንድ ሺህ 600 ኩንታል አዮዲን የሌለው ጨው በህገ ወጥ መንገድ በተለያዩ መጋዘኖች ተከማችቶ ማግኘታቸውን አስታውቀዋል።
በጉዳዩ የተጠረጠሩ ግለሰቦችን በቁጥጥር ስር ለማዋል የጸጥታ ኃይሉ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡
አካባቢው ገጠር በመሆኑ የጸጥታ ኃይል ሊያየው አይችልም በሚል የተከማቸ መሆኑን ጠቁመው ፤ ህብረተሰቡ ላደረገው ትብብር ምስጋና አቅርበዋል። (ENA)

የምርጫው ዘመቻው እየተሟሟቀ ነው ...
ዛሬ ኢዜማ የምርጫ ዘመቻ ማስጀመሪያ ስነ ስርዓት በኢዲስ አበባ ከተማ አከናውኗል።
የፓርቲው መሪ የሆኑት ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ፓርቲያቸው “ብርሃን” እንጂ “አምፖል ይዞ” ወደ ምርጫው አልመጣም ሲሉ ተናገረዋል።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ ፤ ገዢው ፓርቲ በምርጫ ምልክትነት የመረጠውን ቁስ ያነጻጸሩበት አገላለጽ በደጋፊዎቻቸው ዘንድ የ“ይደገም” አድናቆት አስገኝቶላቸው ነበር።
ፕሮፌሰር ብርሃኑ በመርሃ ግብሩ ላይ ባሰሙት ንግግር፥ ገዢው ፓርቲ ከመጪው ምርጫ ጋር በተገናኘ “ግልጽ አቋሙን ሊያሳውቅባቸው ይገባል” ያሏቸውን ነጥቦች አንስተዋል።
“ብልጽግና ፓርቲ የህወሓት እና የኢህአዴግ ወራሽ ሳይሆን ከሁለቱ የተለየ ፓርቲ መሆኑን በተግባር እንዲያሳየን እንሻለን” ብለዋል በንግግራቸው።
የኢዜማው መሪ፤ መጪው ምርጫ ከዚህ ቀደም ከተካሄዱት አምስት ጠቅላላ ምርጫዎች የተለየ መሆኑን በንግግራቸው ጠቅሰዋል።
“ኢህአዴግ ይባል የነበረው ድርጅት ስልጣን ከያዘ ወዲህ ምርጫ መሰል ነገሮች ሁሉ ተቆጥረው ስድስተኛ ይባል እንጂ፤ የእኛ ተስፋ ይህ ምርጫ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ዲሞክራሲያዊ ምርጫ ነው” ሲሉ ለአሁኑ ምርጫ ያላቸውን ከፍተኛ ግምት ተናግረዋል። “ታሪክ በእኛ ላይ የጣለው ሃላፊነት ይህ ምርጫ ከዚህ በፊት እንደነበሩት የይስሙላ ወይም የሙከራ ሳይሆን፤ በእርግጥም የመጀመሪያ ዴሞክራሲያዊ ምርጫ ማድረግ ነው” ሲሉም አክለዋል።
ይህ ፁሁፍ የተዘጋጀው በኢትዮጵያ ኢንሳይደር ነው።

የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሉ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሉ ም/ርዕሰ -መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ!
ከየካቲት 29/2013 ዓ.ም ጀምሮ የሚሰጠው የ12ተኛ ክፍል ፈተና በክልሉ በሠላማዊ መንገድ እንዲጠናቀቅ ለማድረግ ከወዲሁ ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን የክልሉ ምክትል ርዕሰ-መስተዳድር አቶ ጌታሁን አብዲሳ ገለጹ፡፡
ፈተናው በሠላማዊ እና በተረጋጋ መንገድ ተሰጥቶ እንዲጠናቀቅ ለማስቻል የተቋቋመው ክልል አቀፍ የፈተና ኮማንድ ፖስት ዛሬ በጉዳዩ ዙሪያ ውይይት አካሂዷል፡፡
የሚመለከታቸውን የክልል ተቋማት አመራሮችን፣ የጸጥታ አመራሮችን፣ የሀገር መከላከያ ሠራዊት እንዲሁም የፌዴራል ፖሊስ አመራሮችን አካቶ የተዋቀረው የፈተና ኮማንድ ፖስቱ፣ ከፈተና ወረቀት ሥርጭት ጀምሮ ፈተናው እስኪጠናቀቅ ድረስ ሠላማዊ ሂደት እንዲኖረው የሚያስችሉ ሥራዎችን እንደሚያከናውንም ተገልጿል፡፡
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልላዊ መንግስት በ21 የመፈተኛ ጣቢያዎች 3 ሺ 114 ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተናውን እንደሚወስዱም በውይይቱ ወቅት መገለፁን የክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ አሳውቋል።
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia