TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ስዊዲን ለመተከል ተፈናቃዮች 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት ሰብአዊ ድጋፍ ማድረጓ ተገለጸ !

የስዊዲን መንግስት ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል መተከል ዞን ተፈናቅለው በአማራ ክልል አዊ ዞን ቻግኒ ከተማ ለሚገኙ ዜጎች 6 ሚሊዮን ዶላር የሚገመት የሰብአዊ ድጋፍ ማድረጉን በኢትዮጵያ የስዊዲን ኤምባሲ አስታወቀ።

በኢትዮጵያ የስዊዲን አምባሳደር ሃንስ ሄነሪክ ሉንድኩዊስት የተመራ ልዑክ በቻግኒ ከተማ የሚገኙ የመተከል ዞን ተፈናቃዮችን ጎብኝቷል።

ልዑኩ በነበረው ቆይታ ከአማራ ክልል ርእሰ መስትዳደር አቶ አገኘው ተሻገርና ከክልሉ ከፍተኛ የስራ ሃላፊዎች ጋር መወያየቱን ተገልጿል።

በተጨማሪ በድጋፍ ስራ ላይ ከተሰማሩ ባለሙያዎች እንዲሁም ድጋፍ ከተደረገላቸው ጋር ውይይት መካሄዱ ተጠቁሟል።

Via ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ እና ደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ስምምነት...

በኢትዮጵያ እና በደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹሞች መካከል የሁለትዮሽ የጋራ ስምምነት ፊርማ መደረጉን የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት ገለፀ።

የፊርማ ስነ-ስርዓቱ የተደረገው 11ኛው የ2ቱ ሀገሮች የጋራ የኢታማዦር ሹሞች ስብሰባ በዛሬው ዕለት በመኮንኖች ክበብ በተጠናቀቀበት ወቅት ነው።

በደቡብ ሱዳን ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ጀ/ል ጆንሰን ጁማ ኡኮት የተመራው የደቡብ ሱዳን የመከላከያ ከፍተኛ ጀነራል መኮንኖች ልዑክ ፣ ትላንት ከኢፌዴሪ አቻው ጋር ተገናኝቶ በሁለቱ ሀገሮች የጋራ ወታደራዊ ጉዳዮች ላይ መክሯል።

ዛሬ ደግሞ በመከሩባቸው ጉዳዮች ላይ ከስምምነት ደርሰው የፊርማ ስነ ስርዓት አከናውነዋል።

ስምምነቱ ምን ያካትታል ?

- በሁለቱ ሀገራት የወታደራዊ ደህንነቶች መረጃ ልውውጥ ፣
- ድንበር ላይ የሚደረጉ ህገ-ወጥ የሰዎች ዝውውር መግታት
- የጦር መሳሪያ ዝውውር በጋራ መግታት ፣
- ወታደራዊ ዲፕሎማሲን ለማጠናከር እንዲሁም በተለያዩ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች ፣ በትምህርት እና ስልጠናዎች በመደጋገፍ በጋራ መስራት ይገኙበታል ፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

ኢትዮጵያ ውስጥ ኮቪድ-19 የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በእጅጉ እያሻቀበ ነው።

ባለፉት 24 ሰዓታት 6,901 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 837 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

በዚሁ በ24 ሰዓታት የ10 ሰዎች ሞት ሪፖርት ተደርጓል ፤ ትላንት 167 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 151,016 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,259 ሰዎች ሞተዋል ፤ 130,566 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 327 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እጅግ አደገኛ ናቸው የተባሉ የዘረፋ እንዲሁም የግድያ ወንጀል የፈፀሙ ተጠርጣሪዎች ተያዙ !

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን በተለያዩ አካባቢዎች በቡድን በመደራጀት የዘረፋ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ 53 ተጠርጣሪዎችን በቁጥጥር ስር ማዋሉን አስታወቀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ እጅግ አደገኛ እና ደጋጋሚ ወንጀል ፈፃሚዎች መሆናቸውን ከጣት አሻራ ሪከርዳቸው ማረጋገጥ እንደተቻለ ተገልጿል።

ከተጠርጣሪዎች መካከል ለ55 ፣ ለ30 እና ለ10 ጊዜ የወንጀል የጣት አሻራ ሪከርድ የተመዘገበባቸው መገኘታቸውን ታውቋል።

በ4 ቡድን የተደራጁ 36 ተጠርጣሪዎች በከተማችን የተለያዩ አካባቢዎች ባንክ ቤትን ጨምሮ በተለያዩ መኖሪያ ቤቶች ላይ ጥናት በማድረግ እና በተሽከርካሪ በመንቀሳቀስ የዘረፋ ወንጀል ሲፈፅሙ ቆይተዋል፡፡

እነዚህ የወንጀል ቡድኖች የሚጠቀሙባቸው 4 ሽጉጦች ፣ የካዝና መሰርሰሪያ እና ለወንጀል ተግባራቸው የሚገለገሉባቸው ሌሎች ቁሳቁሶች እና ተሽከርካሪዎች ከተጠርጣሪዎቹ ጋር ሙሉ በሙሉ ሊያዙ መቻላቸውን እና 14 የምርመራ መዝገብ እንደተደራጀባቸው ፖሊስ ገልጿል

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወርቅ ቤቶች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው ዘረፋ ሲፈፅሙ የነበሩ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር ዋሉ!

በወርቅ ቤቶች ላይ ብቻ ትኩረት አድርገው በተለይ ፒያሳ አካባቢ የዘረፋ ወንጀል የሚፈፅሙ በ2 ቡድን የተደራጁ 9 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የአዲስ አበባ ፖሊስ ገለፀ።

እንደፖሊስ ገለፃ ፥ ተጠርጣሪዎች ወንጀል ለመፈፀም የፖሊስ የደንብ ልብስ ለብሰው እና የጦር መሳሪያ ታጥቀው በተሽከርካሪ እየታገዙ የሚንቀሳቀሱ ሲሆኑ በፖሊስ አባላት ክትትል ሁሉም ተጠርጣሪዎች ከዘረፉት በርካታ ወርቅ፣ ለወንጀል ተግባራቸው ከሚገለገሉባቸው ተሽከርካሪ፣ሽጉጥ እና የፀጥታ አካላት የደንብ ልብስ ጋር በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

በሌላ በኩል ፦

ፌሮ ብረት ፣ ዱላ ፣ ድንጋይ እና ስለት በመጠቀም ንብረት ለመውሰድ በሰው አካል ላይ ጉዳት ሲያደርሱ እና የግድያ ወንጀል ሲፈፅሙ የነበሩ በሁለት ቡድን የተደራጁ 8 ተጠርጣሪዎች በከፍተኛ ክትትል በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በተለይ በየካ ክፍለ ከተማ ፈረንሳይ ለጋሲዮን ተብሎ በሚጠራው አካባቢ በለሊቱ ክፍለ ጊዜ አሳቻ ሰዓት እና ቦታ እየመረጡ ወንጀሉን ሲፈፅሙ ነበር፡፡

ወንጀሉን ስለመፈፀማቸው አምነው የት ? እና እንዴት ? እንደፈፀሙም ለፖሊስ መርተው ማሳየታቸውን የአ/አ ከተማ ፖሊስ ኮሚሽን ዛሬ ምሽት ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention😷

በኮቪድ-19 የበርካታ ሰዎች ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን በሚሊኒየም የኮቪድ 19 ሕክምና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ውለታው ጫኔ ለኢፕድ አስታወቁ።

በሚሊኒየም የኮቪድ ሕክምና ማዕከል ብቻ በ51 ሳምንት ውስጥ የፅኑ ሕክምና ፈላጊ ቁጥር በእጥፍ መጨመሩን እና አይ.ሲ.ዩ ክፍሎች በመሙላታቸው በመተንፈሻ ማሽን ለመረዳት ጥያቄ ያቀረቡ ታካሚዎችን ለመመለስ መገደዳቸውንም ጠቁመዋል፡፡

ዶ/ር ውለታው፤ ወደማዕከሉ የሚገቡት በርካታ ታካሚዎች በፀና የታመሙ፣ ዕድሜያቸው ከፍ ያለ እና የሕክምና ባለሙያዎችን የተለየ ትኩረትና ድጋፍ የሚሹ ሰዎች ናቸው፡፡ ሆኖም ተጓዳኝ ህመም የሌለባቸውና በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ጭምር እየተጠቁ መሆናቸው የበሽታው ስርጭት አስጊ ደረጃ ላይ ለመድረሱ ማሳያ ነው ብለዋል።

አሁን ባለው ሁኔታ ግን በጣም አስፈሪ የሆነ በርካታ የፅኑ ህሙማን ቁጥር እየተመዘገበ መሆኑን ነው ገልፀው ከችግሩ ስፋት አኳያ የሞት ምጣኔ ወደ ሰባት በመቶ ከፍ ማለቱን አሳውቀዋል፡፡

«ያለምክንያት ዋጋ መክፈል ይብቃ» የሚሉት ዶክተር ውለታው፤ ችግሩ ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተባባሰ እና ከአንድ ቤት ሁለት ሦስት ሰው የሚሞትበት ሁኔታ መኖሩን ነው የተናገሩት።

አሁን አይ.ሲ.ዩ ክፍሎቹ ውስጥ ያሉ 20 አልጋዎች በማሽን የሚታገዙ፤ 20 ደግሞ ከማሽን ውጪ የሆኑት ሁሉም በመሙላታቸው በመተንፈሻ ማሽን ለመረዳት ጥያቄ ያቀረቡ ታካሚዎችን ለመመለስ መገደዳቸውን ገልጸዋል።

እነዚህ ታካሚዎች አገልግሎት አላገኙም ማለት በሕይወት የመቆየት ዕድላቸው አናሳ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተሩ፤ ማሽኖቹም ላለፉት ዘጠኝ ወራት ያለምንም እረፍት በመስራታቸው እየደከሙ መሆናቸው ጉዳዩን የከፋ እያደረገው መሆኑን ነው የገለፁት።

More : telegra.ph/COVID19Ethiopia-02-20

@tikvahethiopia
ኦነግ ከምርጫ 2013 ወጥቷል ?

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የኦነግ አመራሮችን በሚዲያዎች እየተሰራጨው ስላለው "ኦነግ ከምርጫ 2013 ወጥቷል" የሚል መረጃ ውሳኔ የተላለፈበት መሆን አለመሆኑን ? እንዲሁም ኦነግ በምርጫው አይሳተፍም ወይ ? ሲል ጠይቋል።

የኦነግ ህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ በቴ ኡርጌሳ በቲክቫህ አባላት ለተነሱ ጥያቄዎች እንዲሁም በድርጅታቸው ከምርጫው ጋር በተያያዘ ስለሚነሱ ቅሬታዎች ደቂቃዎችን ወስደው ማብራሪያ ሰጥተዋል። (ይህ በቀጣይ የምንዳስሰው ይሆናል)

ትላንት በማህበራዊ ሚዲያ ስለተሰራጨው መረጃ አቶ በቴ ኡርጌሳ የሰጡት ምላሽ ተከታዩን ነው ፦

"ሊቀመንበራችን ያሉት በምርጫው የመሳተፋችን ነገር ተገድቦብናል፣ እንቅስቃሴ ማድረግ አልቻልንም፣ እጩ ማስመዝገብ አልቻልንም የጊዜ ገደቡ ደግሞ እያለቀ ነው ያሉት። ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ አንድ ላይ አመራሩ ተወያይቶ ፣ መክሮ ነው መግለጫ የሚሰጥበት፤ ሊቀመንበሩ ለሚዲያዎች የገለፁት አሁን ባለው ሁኔታ ርጫ እንቅስቃሴ ላይ እየተሳተፍን አይደለም የሚል ብቻ ነው።"

አቶ ዳውድ ኢብሳ (የኦነግ ሊቀመንበር) ሰሞኑ ለውጭ ሀገር ሚዲያዎች የሰጡት ቃለ ምልልስ ትኩረት ያደረገውና ሀሳባቸውን የሰጡት ከላይ በተገለፀው መንገድ ነው ሚዲያዎች እየተቃባበሉ ገና ከወዲሁ "ኦነግ ከምርጫ ወጣ" እያሉ መናገራቸው ምክንያቱ ሊገባን አልቻለም ብለዋል አቶ በቴ።

የሆነው ሆኖ በአንድ ሳምንት የሚቀየር ነገር ይኖራል ብለን አንጠብቅም የሚሉት አቶ በቴ ፤ አዝማሚያዎቹ ግን ወደዛው ናቸው አሁን ላይ ግን ኦነግ ምርጫውን ጥሎ ወጥቷል የሚለው ትክክል አይደለም ፤ ውሳኔም አልተላለፈበትም ብለዋል።

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር ከዚህ ጉዳይ ጋር በተያያዘ አስፈላጊ መረጃ ሲኖር በይፋ ለህዝብ እንደሚያሳውቅ ገልጾልናል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#EthiopiaElection2013

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ነገ እሁድ በአዲስ አበባ ፣ በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ደሴ እና ደብረ ብርሃን ከተሞች የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብር እንደሚያካሂድ አስታውቋል።

ፓርቲው በአዲስ አበባ አብሮ ለመስራት ከተስማማቸው ፓርቲዎች ጋር (ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ፣ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት፣ የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ) በጋራ የምርጫ ቅስቀሳ ማስጀመሪያ መርኃ ግብሩን ለሚመለከተው የመንግስት አካል በደብዳቤ ማሳወቁንም ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ጊዜያዊ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ ሕጋዊ ተቀባይነት የለውም" - የጋሞ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ

የጋሞ ዞን ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ በጊዜያዊነት የተሰጡ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ የያዙ አሽከሪካሪዎች በትራንስፖርት እንቅስቃሴ ሕጋዊ ተቀባይነት እንደሌላቸው ዛሬ ገለፀ።

ጊዜያዊ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ ፈቃድ በቀላሉ አመሳስሎ ለመስራት የተጋለጠ በመሆኑ ደረጃውን የጠበቀ ብቃት ማረጋገጫ መዘጋጀቱም መምሪያው አሳውቋል።

ከ2000 ዓ.ም ጀምሮ ጊዜያዊ የአሽከሪካሪ ብቃት ማረጋገጫ የወሰዱ ግለሰቦች ፎቶግራፍ በሶፍት ኮፒ እና የደም ዓይነት ምርመራ ከሕጋዊ የጤና ተቋም በማምጣት ተመዝግበው ለአዲስ የአሽከርካሪ ብቃት ማረጋገጫ 680 ብር እና ለእድሳት 620 ብር በመክፈል መውሰድ ይችላሉ ተብሏል።

ከዚህ በፊት ተመዝግበው ደረጃውን የጠበቀ የአሽከርካሪዎች ብቃት ማረጋገጫ መጥቶላቸው ያልተወሰዱ 6 ሺህ መንጃ ፈቃዶች በመምሪያው ስለሚገኙ አሽከሪካሪዎች አንዲወስዱ ጥሪ ቀርቧል።

ምንጭ፦ የመምሪያው ምክትል ኃላፊ እና የትራንስፖርት ዘርፍ ኃላፊ አቶ መሳይ ካሎሴ ፣ ጋሞ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia