TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ መግለጫ :

ኦፌኮ "ለሚጠፋ የዜጎቻችንና አባሎቻችን ሕይወት መንግስት ኃላፊነቱን ይወስዳል" ሲል መግለጫ አወጣ።

ፓርቲው በሀገሪቱ ሕግ መሠረት ተመዝግቦ እና ዓላማውን በሠላማዊ አግባብ ብቻ ታግሎ ለማሳካት እየተንቀሳቀሰ እንደሚገኝ ገልጿል።

የኦሮሞ ፌዴራላዊ ኮንግረስ በመግለጫው ፥ "ፖሊሲያችን ፣ የፖለቲካ ፕሮግራማችን ፣ አቋማችን በሕዝብ ዘንድ ተቀባይነትን በማግኘቱ ምቾት ያልተሰማው ገዥው ፓርቲ (ኢህአዴግ/ብልፅግና) በተለይ ከ2005 ጀምሮ አባሎቻችን ደጋፊዎቻችንን በአሸባሪነት በመፈረጅ ክስ መስርቶ ሲያንገላታ ከቆየ በኋላ የሞቱት ሞተው በሕይወት የተረፉትና በየእስር ቤቶች ፊዳቸውን ሲቆጥሩ የነበሩት ቄሮ/ቃሬ በአጠቃላይ ሕብረተሰባችን በከፈሉት መስዋዕትነት በ2010 ዓም አጋማሽ በኋላ ሊፈቱ ችለዋል" ሲል አስታውሷል።

ፓርቲው አክሎም፥ "ከዚሁ ጊዜ በኋላ ለረጅም ጊዜ ስንመኘው የነበረው ዴሞክራሲ ሰፍኖ አዲስቷ ኢትዮጵያን እንገነባለን ብለን ተስፋ የሰነቅን ቢሆንም፤ከ2011 አጋማሽ በኋላ በአገረሸው የብልፅግና ፓርቲ ጭፍን የማሳደድ፣ የማሰርና የመግደል እርምጃዎች የተነሳ አንዳች ወንጀል ያልፈጸሙ ከከፍተኛ አካል ጀምሮ እስከ ታችኛው እርከን ድረስ የሚገኙ አባሎቻችንና ደጋፊዎቻችን የሌለ የወንጀል ታፔላ ተለጥፎባቸው እስር ቤቶች እንዲታጎሩ በመደረጋቸው፤ ተስፋችን ሟሸሸ፤ የሕዝቦችን መብትና ነፃነት ለማስከበር ሌላ የትግል ምዕራፍ እንዲካሄድም ጠይቋል" ብሏል።

ኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ የታሳሪ አባሎቹና ወገኖቹ ትግል የግላቸው ወይም የፓርቲውን ፍላጎት ለማስጠበቅ እንዳልሆነ ገልጾ ከ15 ቀናት በፊት የጀመሩት የረሃብ አድማ በሕይወታቸው ላይ "ከፍተኛ አደጋ" እንዲያዣንብብ ማደረጉን አሳውቋል።

* ተጨማሪ የመግለጫው ሃሳብ ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ አግልግሎት ላይ የዋጋ ጭማሪ ማድረጉን አስታወቀ !

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በአንዳንድ የአገልግሎት ዋጋዎች ላይ የማሻሻያ ጭማሪ ማድረጉን አስታውቋል።

ባንኩ ጭማሪውን ለማድረግ የተገደደው ባለፉት 5 ዓመታት የባንኩ እድገት በአማካይ 26 በመቶ በመሆኑ ሂደቱ እየቀነሰ በመምጣቱ መሆኑን የባንኩ ፕሬዝደንት አቶ አቤ ሳኖ ዛሬ አስታውቀዋል።

በዚህም የኮርፖሬት ቦንድ የብድር ወለድ 8 በመቶ የነበረው 9 በመቶ ደርሷል።

ለቤቶች ልማት በ9.5 በመቶ የብድር ወለድ ይሰጥ የነበረ ሲሆን የነበረው 10.5 በመቶ ተደርጓል።

ለውጭ ምንዛሪ አገልግሎትም በ90 ቀናት ወይም በአንድ ፔሬድ የነበረው 5.5 በመቶ ሲሆን አሁን ወደ 9.5 በመቶ ከፍ ማለቱ ተገልጿል።

ነገር ግን ለኤሌክትሪክ ኃይል፣ ለመድሀኒት አቅርቦት ፣ ለስኳር ፣ ለማዳበሪያ እንዲሁም ለዘይት የሚያስፈልጉ የውጭ ምንዛሪያዎች በ4.5 በመቶ ዝቅ ተደርጓል።

የተደረጉት የምንዛሪ አገልግሎት ዋጋ ማሻሻያዎች ከዚህ ወር (የካቲት) ጀምሮ እንደሚተገበሩ ባንኩ መግለፁን የኢትዮጵያ ቴሌቪዥን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Ethiopia😷

በኢትዮጵያ ባለፉት 24 ሰዓታት ከተደረገው 7,056 የኮቪድ-19 የላብራቶሪ ምርመራ 686 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋገጠ።

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የ6 ሰዎች ሞት ሲመዘገብ ፤ 242 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

ኮቪድ-19 ወረርሽኝ በኢትዮጵያ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ 145,548 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከነዚህ መካከል ፣2,177 ሰዎች ሞተዋል፤ 127,864 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

አሁን ላይ 260 ሰዎች በፀና ታመው በህክምና ክትትል ላይ ይገኛሉ።

#Purpose #Tikvah
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የመተከል ዞን 12ኛ ክፍል ተፈታኞች ጉዳይ ፦

በመተከል ዞን 8 ትምህርት ቤት ከፀጥታ ጋር በተያያዘ አሁን ድረስ ምዝገባ አልተጠናቀም።

ትምህርት ሚኒስቴር ተማሪዎቹ ተመዝግበው ፈተናውን እንዲወስዱ ለማድረግ የፀጥታውን ሁኔታም የማረጋገጥ ስራ ከክልሉ ጋር አብሮ እየሰራ እንደሚገኝ በትላንት መገለጫው አሳውቋል።

ነገር ግን በአካባቢው ችግሮቹ ካልተፈቱና የፀጥታ ችግር ካለ በመተከል ዞን 8 የፈተና ጣቢያዎች ያሉትን ተማሪዎች ወደ አሶሳ ዩኒቨርሲቲ / ሌላ ከተሞች አጓጉዞ የማስፈተን እቅድም እንዳለ ተገልጿል።

ትምህርት ሚኒስቴር በአካባቢው ያሉት ችግሮች በሚቀጥለው 1 ወይም 2 ሳምንት ተፈተው ተማሪዎች ባሉበት ሁኔታ/ቦታ ሆነው ይፈተናሉ የሚል እምነት እንዳለው አሳውቋል።

በአካባቢው የከፋ ሁኔታ ከተፈጠረ ግን በትራንፖርት ወደ አሶሳ ከተማ / አሶሳ ዩኒቨርሲቲ ተጓጉዘው እንዲፈተኑ ይደረጋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ2013 ዓ/ም ብሄራዊ ፈተና ተፈታኞች ጉዳይ ፦

የ2013 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች በ2013 ዓ/ም መጨረሻ (ሰኔ አካባቢ) ፈተናቸውን እንዲወስዱ ለማድረግ ከወዲሁ ስራዎች እየተሰሩ ነው ተብሏል።

በ2012 ባች በታብሌቶች መዘግየት የቀረው የኦንላይ ፈተና የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ፈተናውን በኦንላይን እንዲወስዱ ለማድረግ እንደሚሰራ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

አጠቃላይ የ2013 ዓ/ም ተፈታኞች ወደ 800,000 ይሆናሉ።

ትምህርት ሚኒስቴር ለ74 ዓመታት ሲሰጥ የነበረውን የፈተና አሰጣጥ ሂደት በመቀየር ከ2012 ባች ጀምሮ በኦንላይ ለማስፈተን ጥረት ቢያደርግም ግዢ የተፈፀመባቸው 500 ሺህ ታብሌቶች በኮቪድ-19 ምክንያት ወደሀገር ባለመግባታቸው ሳይሳካ ቀርቷል፤ በ2013 ባች ግን ተግባራዊ ለማድረግ በሙሉ አቅሙ እንደሚሰራ አሳውቋል።

የኢፌዴሪ ትምህርት ሚኒስቴር በከፍተኛ ጫና የሚገኘውን የትምህርት ዘመን ከግምት ውስጥ አስገብቶ በ2013 ብሄራዊ ፈተና ላይ ችግር እንዳይገጥም ከወዲሁ እየሰራ እንደሚገኝ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ሪፖርቶች ፦

- ባለፉት 24 ሰዓት በመላው ዓለም 12,356 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መሞታቸው ሲረጋገጥ 423,186 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል።

- በአሜሪካ ወረርሽኙ ሲጀምር 1 ብሎ የጀመረው የሟቾች ቁጥር ዛሬ ላይ 492,521 ደርሷል። በየዕለቱ በሺዎች የሚቆጠሩ አሜሪካውያን እንደቅጠል እየረገፉ ነው። ባለፉት 24 ሰዓት 2,908 የUS ዜጎች በበሽታው ሞተዋል።

- በሜክሲኮ በኮቪድ-19 በሽታ የሞቱ አጠቃላይ ሰዎች 171,234 ደርሷል። ከነዚህ መካከል የ1,474 ሰዎች ሞት የተመዘገበው ትላንት ነው።

- ብራዚል ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 1,204 ሰዎች በበሽታው ሞተዋል፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 237,601 ደርሷል።

- በተጨማሪ ሩስያ 507 ፣ UK 758 ፣ ስፔን 530 ፣ ፈረንሳይ 429 ፣ ጀርመን 523 ፣ ጣልያን 316 ዜጎቻቸውን በ24 ሰዓት አጥተዋል።

- በአህጉረ አፍሪካ አጠቃላይ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 3,753,441 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 97,950 ህይወቱ ኣልፏል።

- በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮቪድ-19 በሽታ የተያዙ ሰዎች 108,730,653 ደርሰዋል ከነዚህ መካከል 2,394,127 ሰዎች ሲሞቱ 80,753,857 ሰዎች አገግመዋል።

ክትባትን የተመለከቱ ጉዳዮች ፦

- በአሜሪካ ዋሽንግቶን ግዛት እስከዛሬ አጠቃላይ የተሰጠው የኮቪድ-19 ክትባት 1 ሚሊዮን ደርሷል። የጤና ጉደዮች ባለስልጣናት ትላንት አርብ 1 ሚሊዮን ክትባት መሰጠቱትን ይፋ አድርገዋል።

- ጎረቤት ኬንያ ይህ ወር ሳይጠናቀቀ የአስትራዜንካ ክትባትን እንደምትቀበል እና ለዜጎቿ እንደምትሰጥ ተሰምቷል። ኬንያ የክትባቱ ውጤታማነት ላይ የሚነሱትን ሀሳቦች ችላ በማለት ነው ክትባቱን የምታስገባው።

@tikvahethiopia
የተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ተማሪዎቻቸውን እያስመረቁ ይገኛሉ !

#WollegaUniversity

ወለጋ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 3ሺህ 398 ተማሪዎችን ዛሬ በወለጋ ስታዲየም እያስመረቀ ነው።

የዩኒቨርሲቲው እያስመረቃቸው ካሉት ተማሪዎች የመጀመሪያ ዲግሪ 3013፣ በሁለተኛ ዲግሪ 344፣ በህክምና ዶክትሪት 40 እና የአካዳሚክ ዶክተር በአጠቃላይ 3 ሺህ 398 ናቸው።

#KebridharUniversity

ቀብሪ ደሀር ዩኒቨርሲቲ ለመጀመሪያ ጊዜ በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን 612 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ነው። ለዚሁ ስነስርዓት የክልሉ ፕሬዜዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ እና የፌዴራል እንዲሁም የክልሉ ባለስልጣናት ትላንት ወደቀብሪድሃር መጓዛቸው ይታወቃል።

#JimmaUniversity

ጅማ ዩኒቨርስቲ በ2ተኛ ዙር በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ፣ በሁለተኛና ሶስተኛ ዲግሪ ያሠለጠናቸውን 4ሺህ 338 ተማሪዎችን እያስመረቀ ነው።

ከተመራቂዎቹ መካከል 3,950 በመጀመሪያ ዲግሪ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 1 ሺህ 530 ሴቶች ናቸው። በ2ተኛ ዲግሪ ደግሞ 45 ሴቶች የሚገኙበት 354 ተማሪዎች ተመርቀዋል፡፡ 3 ተማሪዎች በ3ተኛ ዲግሪ እና 4 ተማሪዎች ደግሞ የ 'ሰብ ስፔሻሊቲ' ተመራቂ ይገኙበታል፡፡

#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ በህክምና ስፔሻሊቲ ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የነበሩ 24 ሰልጣኞቹን በመጀመሪያ ዙር አስመርቋል፡፡

#KotebeMetropolitanUniversity

ኮተቤ ሜትሮፖሊታን ዩኒቨርስቲ 2039 ተማሪዎች እያስመረቀ ነው ፤ 1 ሺህ 104 በመጀመሪያ ዲግሪ፣ 222 በ2ኛ ዲግሪና 711 በዲፕሎማ።

ምንጭ፦ ጅማ ዩኒቨርሲቲ ፣ SRTV፣ ወለጋ ዩኒቨርሲቲ ፣ኤፍ ቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AdigratUniversity

የዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ለ8ኛ ጊዜ 2,576 ተማሪዎቹን እያስመረቀ ይገኛል።

ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ በነበረው ጦርነት ውድመት ደርሶበት ስለነበር ተማሪዎቹ ቀሪ ትምህርታቸውን በመቐለ ዩንቨርስቲ እንዲያጠቅቁ ተደርጎ ነው ዛሬ እየተመረቁ የሚገኙት።

በሌላ በኩል በቅርቡ ተማሪዎችን ያስመረቀው መቐለ ዩኒቨርስቲ ቀሪ 608 ተመራቂ ተማሪዎችን በ2ተኛ ዙር እያስመረቀ እንደሚገኝ ከኢዜአ የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በ24 ሰዓት 4 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገንዘብ አባዝተን እንሠጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ የነበሩ 2 የካሜሮናውን ዜግነት ያላቸው ግለሰቦች በቁጥጥር ስር ዋሉ !

በአዲስ አበባ በማታለል ወንጀል ላይ ተሰማርተው የነበሩ ሁለት ካሜሮናውያን የአሜሪካ ዶላርን ጨምሮ የተለያዩ አገራት የገንዘብ ኖቶችን በ24 ሰዓት ውስጥ እያባዛን እንሰጣለን በማለት ሲያጭበረብሩ በቁጥጥር ስር ዋሉ።

በፓስፖርት ስማቸው ናዋ ሳምፕሰን እና ጁዲ አያምባንግ ተብለው የሚጠሩት እነዚህ ካሜሮናዊያን ተጠርጣሪዎች በአዲስ አበባ ቆይታቸው ማርክና ሳምሶን በሚሉ ሃሰተኛ ስሞች እንደሚጠቀሙ የጠቀሰው ኮሚሽኑ የደቡብ አፍሪካ ዜግነት ጭምር እንዳላቸው በመናገር እና ከተለያዩ ኢትዮጵያውያን ዜጎች ጋር ግንኙነት በመፍጠር ሲንቀሳቀሱ እጅ ከፍንጅ ተይዘዋል።

ተጨማሪ : https://telegra.ph/AddisAbabaPolice-02-13

(የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#TheWhiteHouse

ፕሬዘዳንት ባይደን ስልጣን ዘመናቸው ከማብቃቱ በፊት በሽብር የተጠረጠሩ ግለሰቦች የሚታሰሩበትን የ "ጓንታናሞ ባይ" እስር ቤትን የመዝጋት አላማ እንዳላቸው ኋይት ኃውስ ትላንት አስታውቋል፡፡

የቀድሞ ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራምፕ በፈረንጆቹ 2016 በተካሄደው የምርጫ ቅስቀሳ ወቅት የጓንታናሞ ባይ እስርቤትን በስራ ላይ እንደሚቆይና “በመጥፎ ሰዎች” እንደሚሞላ ገልጸው ነበር፡፡

በባራክ ኦባማ ጊዜ እስረኖች እንደሚለቀቁ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፤ ነገር ግን ኦባማ የኮንግረሱን ፍቃድ ስላላገኙ እስረኞቹ መፈታት አልተሳካም፡፡

በውቅቱ የአሁኑ ፕሬዘዳንት ባይደን የኦባማ ምክትል ነበሩ፡፡

በአሜሪካ "ሴፕቴምበር 11" የተከሰተውን ከባድ አቀናብሬያለሁ ብሎ ኃላፊነት የወሰደውን ፓኪስታናዊ ካሊድ ሸህ መሃመድን ጨምሮ ከ”ዋር ኦን ቴረር” ጋር ግኝኑነት ያላቸው ፍረደኖች በወታደራዊው እስርቤት ይገኛሉ፡፡

በእስርቤቱ እስካሁን 40 እስርኞች የሚገኙበት ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 26ቱ "አደገኞች" ናቸው ተብለው የማይለቀቁና የፍርድ ሂደቱም ነገሩ ውስብስብ ስለሆነ የተጓተተባቸው ናቸው፡፡

AlAin News
Reuters
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ሪፖርቶች ፦

- በመቐለ 80 በመቶ የመንግስት መስሪያ ቤቶች ወደ ስራ መመለሳቸው።

- የትግራይ መልሶ ማቋቋም ስምምነት ፊርማ።

- የክልል ትግራይ ገቢዎች ባለስልጣን የግብር መሰብሰብ ስራ ለመጀመር መዘጋጀት።

- የሰላም ሚኒስቴር በትግራይ እየተደረገ ያለው ድጋፍ መቀጠሉን መግለፁ ።

- በትግራይ የተለያዩ ከተሞች የቀጠለው ተቃውሞ እና አድማ።

- በአክሱም ፣ ውቅሮ፣ በሽረ በተቀሰቀሰው ተቃውሞ የሰዎች ህይወት ስለማለፉ።

- በአክሱም ከተማ የ "ኤርትራ ሰራዊት" ተኩስ ከፍቷል ስለመባሉ።

- በመቐለ ከተማ ከቀናት አድማ/ተቃውሞ በኃላ ከትላንት ጀምሮ ሁሉም አይነት መደበኛ እንቅስቃሴ መጀመሩ።

- የትግራይ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን በክልሉ ጉዳይ ዝርዝር መረጃ እና መግለጫ እንደሚሰጥ ማሳወቁ።

- የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ስራ አስፈፃሚ በወቅታዊ ሁኔታ ላይ የሰጡት አስተያየት እና ያስተላለፉት መልዕክት።

(ለቲክቫህ አባላት የቀረበ)

(Tikvah Family - የካቲት 6 ቀን 2013 ዓ/ም)

https://telegra.ph/TikvahFamily-02-13
በዓዲግራት ከተማ የባንክ አገልግሎት ጀመረ።

በትግራይ ክልል የተለያዩ ከተሞች ተቋርጦ የቆየውን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎት መስጠት እንደሚጀምር ተገለፀ።

የዓዲግራት ንግድ ባንክ ቅርጫፍ አገልግሎት መጀመሩን የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ ኢተነሽ ንጉሰ ለክልሉ ቴሌቪዥን ገልፀዋል።

የአክሱም እና ሽረ ቅርጫፎች በቅርብ ቀን ውስጥ ይከፈታሉ ሲሉ ወ/ሮ ኢተነሽ ተናግረዋል።

የዓድዋ ንግድ ባንክ ቅርጫፍ የደረሰበት ጉዳት ከባድ በመሆኑ ከተወሰነ ጊዜ በኃላ አስፈላጊው ዝግጅት ተደርጎ ይከፈታል ብለዋል የቢሮ ኃላፊዋ።

አገልግሎት በጀመሩ ባንኮች አገልግሎቱ ከጀመረበት ቀን አንስቶ በ14 ቀን ውስጥ ነባሩ የብር ኖት ቅያሬ እንደሚደረግ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ2 ሚሊዮን ጄሪካን በላይ የምግብ ዘይት በቁጥጥር ስር ዋለ !

በአዲስ አበባ ከተማ "ጀሞ ሚካኤል" አካባቢ ልዩ ስሙ "አንበሳ ጋራዥ" በሚባለው ቦታ በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸ ከሁለት ሚሊዮን ጄሪካን በላይ ፓልም የምግብ ዘይት ዛሬ በቁጥጥር ስር መዋሉን የኢብኮ ገለፀ።

በሕገ ወጥ መንገድ የተከማቸው ዘይት ሊያዝ የቻለው ፌዴራል ፖሊስ እና የላፍቶ ክፍለ ከተማ አስተዳደር ከኅብረተሰቡ የደረሳቸውን ጥቆማ መነሻ በማድረግ ለ2 ሳምንታት ባደረጉት ክትትል ነው ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በቤኒሻንጉል ጉመዝ ክልል ውስጥ 'የከፋ' የአመራር ችግር የታየባቸው አመራሮች ከኃላፊነት ሲነሱ የከፋ አመራር የለባቸውም የተባሉት ደግሞ ሽግሽግ አደረጉ !

የቤንሻንጉል ጉሙዝ ብልፅግና ፓርቲ ፥ በቅርቡ የተካሄደውን የከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች ኮንፈረንስ ተከትሎ ህብረ-ብሔራዊነትን በጠበቀ መልኩ አዲስ የአመራር ምደባ እና ሽግሽግ መደረጉን አሳወቀ።

በህዝብ በማስተቸት የከፋ ችግር የታባታቸውን አመራሮች በማንሳት በአዲስ እንዲተኩ በማድረግና የከፋ ችግር የሌለባቸውን ደግሞ በማሸጋሸግ የመተከል ዞንና ወረዳዎች መዋቅር መልሶ የማደራጀት ስራ ተሰርቷል ብሏል።

የመተከል ዞን መምሪያ መዋቅር መልሶ ለማደራጀት በተወሰደ እርምጃ የትምህርት መምሪያ ፣ የከተማ ልማት እና የንግድ መምሪያ፣ ግብርና ተፈጥሮ ሀብት መምሪያ፣ ፍትህ መምሪያ እንዲሁም የውሃ እና ማዕድን መምሪያ ኃላፊ ቦታ ላይ የአመራር አዲስ ምደባና ሽግሽግ ስራ ተሰርቷል ተብሏል።

- የወምበራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የቡለን ወረዳ ምክትል ዋና አስተዳዳሪ እና ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

- የድባጢ ወረዳ ብልጽግና ፓርቲ ጽ/ቤት ኃላፊ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የማንዱራ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ቦታ በሌላ አመራር እንዲተካ ተደርጓል።

- የጉባ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ እና ምክትል ዋና አስተዳዳሪ ቦታዎች በሌላ አመራር እንዲተኩ ተደርጓል።

በተመሳሳይ የካቢኔ እና የጽ/ቤት ኃላፊ ቦታዎች ላይ የአመራር አዲስ ምደባ እና የማሸጋሸግ ስራ በመስራት መልሶ የማዋቀር ስራ መስራቱ ተገልጿል።

* ዝርዝር መግለጫው ከላይ ተያይዟል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia