ለጋምቤላ ክልል የመንግስት ሰራተኞች በሙሉ ፦
በጋምቤላ ክልል የሙቀቱ መጠን እየጨመረ በመምጣቱ የመንግስት የሥራ ሠዓት ለውጥ ተደርጓል።
የሙቀቱ መጠን እየጨመር በመምጣቱና ለስራ አመቺ ባለመሆኑ ከየካቲት 3 ቀን 2013 ዓ.ም ጀምሮ ለ3 ወራት የሚቆይ ጊዜያዊ የመንግስት ሥራ ስዓት ለውጥ ተደርጓል።
በለውጡ መሰረት ቀደም ሲል በመደበኛው የሥራ ስዓት ከጠዋቱ 1 ሠዓት እስከ 6 ሠዓት ተኩል የነበረው ከ1 ሠዓት እስከ 5 ሠዓት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል።
እንዲሁም ከሠዓት በኋላ ከ9 ሠዓት እስከ 11 ሠዓት ተኩል የነበረው ከ10 ሰዓት እስከ 12 ሠዓት ተኩል እንዲሆን ተወስኗል።
የስራ ሠዓት ለውጡ ወይናደጋ የሆነውን የማጃንግ ዞን እንደማይጨምር የተገለፀ ሲሆን የመንግስት ሠራተኞች በተጠቀሰው ጊዜ ወደ ቢሮ በመግባት የተለመደውን ሥራቸውን እንዲያከናኑ ጥሪ ቀርቧል።
* በብሔራዊ ሜትሮዎሎጂ ኤጀንሲ የጋምቤላ ክልል አገልግሎት ማዕከል መረጃ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት የክልሉ የቀኑ ከፍተኛ የሙቀት መጠን 40 ነጥብ 4 ዲግሪ ሴልሽየስ፣ የሌሊቱ ደግሞ 16 ነጥብ 6 ዲግሪ ሴልሽየስ ነው።
የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር ጽህፈት ቤት
(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

"ሼር አድርገን እንሳፈር" ከሚሉ ዘራፊዎች ይጠንቀቁ !
(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ የቀረበ)
በአዲስ አበባ ከተማ ዕለት ተዕለት የረቀቁ ወንጀሎች ይፈጸማሉ ሰሞኑን ተፈጸመ የተባለ አንድ ወንጀልን ለጥንቃቄ ይረዳቹ ዘንድ ላካፍላቹ።
ማለዳ ጠዋት በስራ መግቢያ እና መውጫ የሚገጥመን የትራንስፖርት ችግር አለ።
ትራንስፖርት በምንጠብቅበት ስፍራ አከባቢም የተለያዩ አጨበርባሪ ሌቦች ፈንጠር ፈንጠር ብለው ይቆማሉ። (ሌቦቹ የጾታ ልዩነት የላቸውም)እርሶም በትራንስፖርት ጥበቃ ላይ እያሉ አንዱ(አንዷ)ወደ እርሶ ጠጋ በማለት "ለምን ሼር አድርገን በኮንትራት አንሄድም"በማለት ሀሳብ ይቀርባል። እርሶም በሀሳቡ እንደተስማሙ የሌቦቹ ተባባሪዎች ወደ እርሶ ጠጋ በማላት በሀሳቡ ይስማማሉ።
በቀጣይም በስልክ እና በአፕልኬሽን የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ወደ ሚገኙት ካንፓኒዎች አንዱ ጋር እንዲደወል በመነጋገር ብዙም ሳይቆይ ተደወለለት የተባለው መኪና እርሶ ከቆሙበት ስፍራ ይደርሳል።
የፊት መቀመጫውን ከሌቦቹ አንዱ ቀድሞ በመያዝ እርሶ እና ቀሪ ሌቦቹ ግን ከጀርባ ካላው ወንበር ላይ እርሶን ከመሀል በማድረግ ጉዞ ይጀመራል። ነገር ግን እዚህ ላይ ማወቅ ያለቦትን አንድ ጉዳይ እናሳውቆት ቀደም ሲል ስልክ በመደወል መኪና እንደሚያዝ በማስመሰል የደወለው ግለሰብ የሌቦቹ ተባባሪ ሲሆን ስልክም የደወለው የትራንስፖርት አገልግሎት እየሰጡ ወዳሉት ካንፓኒዎች አይደለም።
በቀጣይም የተሳፈሩበት መኪና ሹፌሩም ተሳፋሪውም ዘራፊ ሊሆኑ ስለሚችሉ ፍጹም ከማያውቋቸው ሰዎች ጋር በኮንትራት ባይሳፈሩ ይመረጣል። በተለይ ከ12ሰዓት በኾላ ስለዚህ ከእንዲህ ዓይነቶቹ ሌቦች እንዲጠነቁ ይህንን ጥቆማ ወደ እናንተ አደረስን።

* የ12ኛ ክፍል ተፈታኞች የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ህብረተሰቡ ኃላፊነቱን እንዲወጣ ተጠየቀ !
ከየካቲት 29 እስከ መጋቢት 2 በወረቀት በሚሰጠው የ12ኛ ክፍል ፈተና ተፈታኝ ተማሪዎች በቂ የስነልቦና ዝግጅት እንዲኖራቸው በሚደረገው ጥረት ወላጆች እና ማህበረሰቡ ሃላፊነታቸውን ሊወጡ እንደሚገባ የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ ጥሪ አቀረበ፡፡
በጋምቤላ ክልል ሀገር አቀፍ ብሄራዊ ፈተናውን በመደበኛ፣ በግል እና በማታ 3653 ያህል ተማሪዎች ይወስዳሉ።
ለፈተናው 17 የፈተና ጣቢያዎች ዝግጁ መሆናቸውን ተገልጿል።
ፈተናውን ለመስጠት ልዩ ልዩ የፈተና ቁሳቁሶች ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን የፈተና ሂደቱን ሊያስተባብሩ የሚችሉ አካላትን የመምረጥ ስራ እንደሚከናወን ክልል አሳውቋል።
የዘገየው የ8ኛ ክፍል ውጤት ጉዳይ ፦
የጋምቤላ ክልል አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት በሚቀጥሉት ሁለት (2) ሳምንታት ለተማሪዎች ይፋ እንደሚደረግም የክልሉ ትምህርት ቢሮ አመልክቷል፡፡
ቢሮው ለስምንተኛ ክፍል ፈተና ውጤት መዘግየት እርማቱን ለማከናወን ባለሙያዎችን በበቂ ሁኔታ አለማግኘት በምክንያትነት አስቀምጧል።
ከአሁን በፊት ክልላዊ ፈተናው በክረምት ሰዓት ይታረም ስለነበር በወቅቱ ደግሞ በርካታ መምህራንን ማሳተፍ ይቻል እንደነበር የተገለፀ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በ60 መምህራን ብቻ እንዲታረም መደረጉ እንዲዘገይ አድርጎታል ተብሏል።
በቀጣዮቹ 2 ሳምንታት የ8ኛ ክፍል የተማሪዎች ውጤት ይፋ እየተሰራ እንደሚገኝ ቢሮው ያሳወቀ ሲሆን ተማሪና የተማሪ ቤተሰቦች ውጤቱን በትዕግስት እንዲጠባበቁ ጥሪ ቀርቧል።
የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት
የጋምቤላ ክልል ትምህርት ቢሮ
አቶ ሙሴ ጋጂት (የክልል ትምህርት ቢሮ ኃላፊ)

ወደ ደ/ሱዳን ለሚዘምቱ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አባላት የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት ተሰጠ !
ወደ ደቡብ ሱዳን "ጁባ" የሚያቀኑ የ15ኛ ሞተራይዝድ ሠላም አስከባሪ ሻላቃ አባላት ተልዕኳቸውን በብቃት እንዲወጡ የሚያስችል የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርት እንደተሰጣቸው ተገልጿል።
በግንዛቤ የማስጨበጫ ትምህርቱ ላይ የመከላከያ ኢንዶክትሪኔሽን ዋና ዳይሬክተር ሜ/ጄ መሀመድ ተሰማ ፥ ሀገርን ወክለው ወደ ጁባ የሚሄዱ የሠራዊት አባላት የምንም ዓይነት ልዩነት ሳይኖር ለቆሙለት አላማ በፅናት መሠለፍ እንዳለባቸው አስገንዝበል።
ወደ ደ/ሱዳን ጁባ ለሰላም ማስከበር የሚዘምቱ የመከላከያ ሠራዊት አባላት በሄዱበት ሁሉ ስኬታማ ሥራ በመሥራት የሀገራቸውን ሥም ለማስጠራት መዘጋጀታቸውን እንደተናገሩ የኢፌዴሪ መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።

ቢቢሲ በቻይና ታገደ !
ቻይናን በተመለከተ የሚሰራቸው ዘገባዎች አድሎአዊ እና ሀሰተኛ ናቸው በሚል ነው ቢቢሲ የታገደው፡፡
የቻይናው የብሮድካስቲንግ ተቆጣጣሪ ‘ቢቢሲ ወርልድ ኒውስ’ን በሀገሪቱ ከባድ የይዘት ጥሰት ፈጽሟል በሚል ከአየር ላይ ማውረዱን ይፋ አድርጓል፡፡
ቻይናን በተመለከተ ቢቢሲ የሚሰራቸው ዘገባዎች የዜና ዘገባ እውነተኛ እና ከአድሎ የነጻ መሆን አለበት ከሚሉት መስፈርቶች ጋር የሚቃረን መሆኑ የተገለጸ ሲሆን እና የቻይናን ብሄራዊ ጥቅሞች እና የህዝቡን አብሮነት የሚጻረር እንደሆነም የሀገሪቱ ብሮድካስቲንግ ተቆጣጣሪ አስታውቋል፡፡
“ቻናሉ በቻይና እንደ ባህር ማዶ ቻናል ለማሰራጨት የሚያስፈልጉትን መስፈርቶች ማሟላት ባለመቻሉ ፣ ቢቢሲ ወርልድ ኒውስ በቻይና ግዛት ውስጥ አገልግሎቱን እንዲቀጥል አይፈቀደለትም፡፡
ብሔራዊ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን አስተዳደር ለአዲሱ ዓመት የቢቢሲን የስርጭት ጥያቄ አይቀበልም” ብሏል ተቆጣጣሪ መስሪያ ቤቱ በመግለጫው፡፡
የሆንግ ኮንግ ሬዲዮ እና ቴሌቪዥን ከአርብ ጀምሮ የ’ቢቢሲ ወርልድ ሰርቪስ’ን እና የቢቢሲ ሳምንታዊ ዜናን እንደማያሰራጭ ባወጣው መግለጫ አስታውቋል፡፡
የቢቢሲ ቃል አቀባይ ለCNN ፥ “የቻይና ባለሥልጣናት ይህንን እርምጃ ለመውሰድ በመወሰናቸው ቅር ብሎናል ፤ ቢቢሲ በዓለም ላይ እምነት የሚጣልበት ዓለም አቀፍ የዜና አውታር ሲሆን የዓለም ዘገባዎችን በፍትሃዊነት ፣ በገለልተኝነት የሚያቀርብ ነው” ብለዋል፡፡
የቻይናው ዓለም አቀፍ የቴሌቪዥን ኔትዎርክ "CGTN" ም በብሪታኒያ እንዳይሰራጭ ከሳምንት በፊት ታግዷል፡፡ ቻይና እና ብሪታንያ ከሆንግ ኮንግ ጉዳይ ጋር በተያያዘ ከፍተኛ የሆነ አለመግባባት መፍጠራቸው ይታወቃል፡፡
ምንጭ፦ አል ዓይን ኒውስ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#Woldia "...የታሪፍ ማሻሻያ ይደረግለን" - የባጃጅ አሽከርካሪዎች ከሰሞኑን በተደረገ ቤንዚንና ናፍጣ ዋጋ ጭማሪ ዙሪያ ከወልዲያ ከተማ ባጃጅ አሽከርካሪዎች ጋር ዛሬ ውይይት መደረጉን ወልዲያ ኮሚኒኬሽን አሳውቋል። በውይይቱ ከቤንዚን እና ናፍጣ የዋጋ ጭማሪ በተጨማሪም የተሽከርካሪዎች የመለዋወጫ እቃ መጨመሩ በነበረው ታሪፍ ለመስራት አላስቻለንም ያሉ አሽከርካሪዎቹ የታሪፍ ማሻሻያ እንዲደረግላቸው…
በወልድያ ከተማ የትራንስፖርት አገልግሎት ታሪፍ ተሻሻለ፡፡
የወልዲያ ከተማ የትራንስፖርት ዋና ሥራ ክፍል ከቤኒዚን የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የባጃጅ ታሪፍን መሻሻሉን በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
የተሻሻለው ታሪፍ ከላይ ተያይዟል።
ከታሪፍ ውጭ ለሚደረግ ህገ-ወጥ ምዝበራ ተገልጋዮች መብታቸውን ለማስከበር ከተሟላ መረጃ ጋር ጥቆማ በስልክ በአካላም መስጠት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል ፤ ለስልክ ጥቆማ : 033-331-04-32 መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የወልዲያ ከተማ የትራንስፖርት ዋና ሥራ ክፍል ከቤኒዚን የዋጋ ጭማሪ ጋር ተያይዞ የባጃጅ ታሪፍን መሻሻሉን በዛሬው ዕለት አስታውቋል፡፡
የተሻሻለው ታሪፍ ከላይ ተያይዟል።
ከታሪፍ ውጭ ለሚደረግ ህገ-ወጥ ምዝበራ ተገልጋዮች መብታቸውን ለማስከበር ከተሟላ መረጃ ጋር ጥቆማ በስልክ በአካላም መስጠት የሚችሉ መሆኑን ተገልጿል ፤ ለስልክ ጥቆማ : 033-331-04-32 መጠቀም ይቻላል ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር ከጅግጅጋ ወደ ቀብሪደሃር ከተማ አቀኑ !
የሶማሊ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፌ ሙሁመድ ኡመር የተመራው የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ከጅግጅጋ ከተማ ወደ ቀብሪደሃር ከተማ አቅንተዋል።
ፕሬዝዳንት ሙስጠፌ በነገው ዕለት ለመጀመሪያ ጊዜ ተማሪዎችን የሚያስመሪቀው የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ የተማሪዎች የምረቃ ሥነ ስርዓት ላይ እንደሚሳተፉ ይጠበቃል።
የቀብሪደሃር ዩኒቨርስቲ ሶስተኛው ትውልድ ከሚባሉት ዩኒቨርስቲዎች ውስጥ አንዱ ሲሆን በሶማሊ ክልልም ከጅግጅጋ ዩኒቨርስቲ ቀጥሎ ሁለተኛው ዩኒቨርስቲ ነው። (SRTV)

በአለታ ወንዶ ትላንት በደረሰ እሳት አደጋ እስካሁን መጠኑ ያልታወቀ ንብረት ወድሟል !
ትላንት ከቀኑ 9:00 በአለታ ወንዶ ከተማ መሳለሚያ ቀበሌ ልዩ ስሙ መለቦ ተብሎ በሚጠራ አከባቢ ድንገት በተፈጠረ እሳት ለግዜዉ ግምቱ ያልታወቀ ንብረት እና የሱቆች ቃጠሎ ዉድመት ደርሷል።
ቃጠሎዉ ከባድ ከመሆኑ አንፃር የከተማዉ ህዝብ በነቂስ ወጥቶ በቁጥጥር ስር ባያዉለው ኖሮ በከተማዉ ለይ ከፍተኛ ጉዳት ሊደርስ ይችል ነበር።
የአለታ ወንዶ ከተማ አስተዳደር አደጋዉን ለመቆጣጠር ዋጋ ለከፈለው ለአለታ ወንዶ ህዝብ በይፋ አክብሮቱን እና ምስጋናውን አቅርቧል።

አሜሪካና UN የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት ዳግም አረጋገጡ !
የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር የሆኑት አንቶኒ ብሊንከን ከተባበሩት መንግስታት (UN) ዋና ፀሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ ጋር በትላንትናው ዕለት በስልክ ባደረጉት የትውውቅ ቆይታ በተለያዩ ዓለም አቀፍ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡
የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በድረገጹ እንዳስታወቀው ፣ ሁለቱ ግለሰቦች ከተወያዩባቸው ጉዳዮች መካከል በኢትዮጵያ ትግራይ ክልል ያለው ወቅታዊ ጉዳይ ይገኝበታል፡፡
ኢትዮጵያን በተመለከተው ውይይታቸው ፣ ሁለቱም በትግራይ ክልል ለተፈጠረው ቀውስ ምላሽ ለመስጠት የኢትዮጵያን ጥረት ለመደገፍ ያላቸውን ቁርጠኝነት በድጋሚ አረጋግጠዋል፡፡
[U.S. Department of State , AlIN News]