TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
3.99K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የደረሰው የእሳት አደጋ...

ዛሬ ከቀኑ 6 ሰዓት ገደማ በድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ የእሳት አደጋ ደርሶ እንደነበር የድሬዳዋ ዩኒቨርሲቲ ቲክቫህ አባላት አሳውቀዋል።

አደጋው "ትዊንስ ኬ" በተባለ ብሎክ ላይ ባለ የዕቃ ግምጃ ቤት ውስጥ ነበር የደረሰው።

በግቢው ውስጥ ውሃ ባለመኖሩ አደጋውን ለመቆጣጠር አክብዶት እንደነበር በስፍራው የነበሩ የቲክቫህ አባላት ገልፀዋል።

በአደጋው የአንድ ሰው ህይወት ማለፉን ዩኒቨርሲቲው ዛሬ ምሽት አሳውቋል ፤ ሟቹ የአንዲት የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የሆነ የዘጠኝ አመት ልጅ ነው።

በተማሪዎች ህይወት ሆነ ንብረት ላይ የደረሰ ጉዳት የለም። ግምጃ ቤቱ ውስጥ ባሉ ንብረቶች ላይ ግን ጉዳት ደርሷል።

የአደጋው መንስኤ እየተጣራ ይገኛል፤ ፖሊስ የምርመራ ስራ እየሰራ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ውጤቱን እንደሚያሳውቅ ገልጿል።

PHOTO : Tikvah Family DDU ፣ DireDawa University
@tikvahethiopiaBOT @tikvah
ለበጎፈቃደኞች የቀረበ ጥሪ ፦

የ "እኛ ለእኛ በጎፈቃደኞች" ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ጋር በመተባበር ከተለያዩ ሀገሮች የሚመለሱ ዜጎችን የመቀበል ሥራዎችን ላለፉት ሰባት ወራት ሲያስተባብርና ድጋፍ ሲሰጥ ቆይቷል።

በቅርቡም በርካታ ከስደት ተመላሽ ዜጎች ወደ ሀገር ለመመለስ ዝግጅት ላይ ናቸው።

በመሆኑም ከዚህ ቀደም የነበረውን ተግባር ማጠናከርና ዜጎቻችን ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ የተለያዩ እገዛዎችን የሚያስተባብሩ በጎፈቃደኞችን መመልመል ይፈልጋል።

በዚህም መሰረት ጥሩ ተነሳሽነት ያላችሁ ፤ ነዋሪነታችሁ በአዲስ አበባ የሆነ፤ በጎፈቃድ አገልግሎቱ ለመሳተፍ ፍላጎቱና አቅሙ ያላችሁ በሙሉ በፎርሙ የሰፈሩትን መረጃዎች በማንበብና ቅጹን በመሙላት መሳተፍ ትችላላችሁ ተብሏል።

https://forms.gle/5ZyCzPEMshG14WbR9

@tikvahethiopia @tikvagethiopiabot
"...የእኔና የምወክለው መንግስት ትኩረት አሁን ባለው የጦርነቱ ማግስት ሁኔታ ላይ ነው።" - ተሰናባቹ አምባሳደር ማይክ ሬይነር

ተሰናባቹ በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ማይክ ሬይነር ትላንት በአሜሪካ ኤምባሲ ከተመረጡ ሚዲያዎች ጋር ቆይታ አድርገው ነበር።

በቆይታቸውም በትግራይ ክልል የተካሄደውን ጦርነት ጨምሮ ልዩ ልዩ ጉዳዮች ተነስተዋል።

ተሰናባቹ አምባሳደር ሀገራቸው በትግራይ ክልል ጦርነት የተሳተፉትን ሁለት ወገኖች ለያይታ እንደምትመለከት ተናግረዋል።

ማይክ ሬይነር ፥ "በጦርነቱ የተሳተፉትን ሁለት ወገኖች በእኩል ደረጃ እንደማንመለከት ከመጀመሪያውም ግልፅ አድርገናል። አንደኛው የሀገሩን የግዛት አንድነት እና የህዝቦቹን ደህንነት የመጠበቅ ግዴታ ያለበት የፌዴራል መንግስት ሌላኛው ደግሞ ህገወጥ በሆነ የትጥቅ አመፅ የተሳተፈ ነበር" ብለዋል።

ይህም ሆኖ ግን ጦርነት ምንጊዜም ጥሩ ውጤት እንደሌለው ነው የገለፁት።

"የጦርነት ማግስት ሁሌም የጠራ ሆኖ አያውቅም፤ ሁል ጊዜ የተመሰቃቀለ ማግስት ነው የሚኖረው እንዳለመታደል ሆኖ አሁን ያለነው እዚያ ደረጃ ላይ ነው፤ እንደአሜሪካም ትኩረታችን ያ ነው። በተለይ የሰዎች መብት እና ደህንነት መከበሩን ማረጋገጥ ፣ ሰብዓዊ ፍላጎቶቻቸው መሟላቱን ማረጋገጥ፣ አሁን ከሆነው በላይ ችግሩ አከባቢያዊ እንዳይሆን፣ ያ በሆነበት አካባቢ ችግሩ እንዲያበቃ ማድረግ ነው።" ሲሉ ገልፀዋል።

አሜሪካ ከጦርነቱ በኃላ በትግራይ ክልል እየታዩ ያሉ ችግሮች እንደሚያሳስባት ተሰናባቹ አምባሳደር አሳውቀዋል።

"ማንኛውም መንግስት በትጥቅ ከተደገፈ አመፅ እራሱን የመከላከል መብት እና ግዴታ አለበት በዚህ ነጥብ ላይ ግልፅ መሆን ፈልጋለሁ ፥ የእኔና የምወክለው መንግስት ትኩረት አሁን ባለው የጦርነቱ ማግስት ሁኔታ ላይ ነው። በሚያሳዝን ሁኔታ እየተራዘመ የመጣው የሰብዓዊ ድጋፍ ፍላጎት፣ ግድያዎች፣ የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች፣ ፆታዊ ጥቃቶች፣ በየቦታው የሚፈፀሙ የተለያዩ ነገሮችን በተመለከተ እዚያ በሚንቀሳቀሱ አካላት ላይ ተጠያቂነት አለመኖር ነው።"

በተለይም ደግሞ የሰብዓዊ ድጋፍ እንቅስቃሴው ሊፋጠን እንደሚገባ ነው አምባሳደር ሬይነር ያሳሰቡት።

አምባሳደሩ ፥ "ከ3 ወራት በኃላም ሰብዓዊ ድጋፍ እጅግ ተጋላጭ ወደሆኑ አካባቢዎች በበቂ ሁኔታ ሲደርስ እያየን አይደለም። የኢትዮጵያም ሆኑ ዓለም አቀፍ የሰብዓዊ እርዳታ ድርጅቶች በስቃይ ላይ ላሉ በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ሰዎች ሰብዓዊ ድጋፍ ማድረግ እንዲችሉ በአስቸኳይ ሙሉ እድል ሊሰጣቸው ይገባል።" ሲሉ ተናግረዋል።

አምባሳደሩ በትላንትናው ማብራሪያቸው በትግራይ ውስጥ ይገኛሉ ስላሏቸው የኤርትራ ወታደሮችም ጠቅሰው አልፈዋል።

ማይክ ሬይነር ፥ "በትግራይ ክልል ያሉ የኤርትራ ወታደሮች እንቅስቃሴ እያሳሰበን ቀጥሏል። ይህ በፍጥነት እንዲያበቃ ጥሪ ማድረጋችንን እንቀጥላለን" ብለዋል።

አክለውም፥ "ግድያዎችን፣ የፆታ ጥቃቶችን፣ እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶችን በየመለከቱ ተጨባጭነት ባላቸው ሪፖርቶች ላይ በትግራይ እንደዚሁም መተከልን በመሳሰሉ ሌሎች ቦታዎች ገለልተኛ ማጣራት እንዲደረግ እንጠይቃለን" ብለዋል።

አሜሪካን ጨምሮ የተለያዩ ዓለም አቀፍ አካላት የኤርትራ ወታደሮች በትግራይ ክልል ስለመገኘታቸው በተደጋጋሚ ቢገልፁም የኢትዮጵያ መንግስት ግን ሲያስተባብል ነው የቆየው።

Via ጋዜጠኛ እስክንድር ፍሬው ፣ ከአሜሪካ ድምፅ ሬዲዮ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በየሳምንቱ 1,000 ዜጎች ወደ ሀገር ሊመለሱ ነው።

የኢትዮጵያ መንግስት ከሳዑዲ መንግስት ጋር ባደረገው ስምምነት መሰረት በየሳምንቱ 1000 ተመላሾች ወደ አገር እንደሚገቡ በጅዳ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጽ/ቤት አስታውቋል።

በመንግስት በኩል በሚሰጡ አቅጣጫዎች መሰረት የተመላሾች ቁጥርም ይጨምራልም ሲል ገልጿል።

ወደ ሳዑዲአረቢያ ህጋዊ ባልሆኑ መንገዶች ሲገቡ ተይዘው በሳዑዲ የተለያዩ ቦታዎች በሚገኙ የስደተኞች ማቆያ ጣብያ ውስጥ የሚገኙና ላለፉት ወራት ከኮሮና ወረርሽኝ ጋር ተያይዞ ወደ አገር መመለስ ያልቻሉ የነበሩ ዜጎችን በስፋት ወደ አገር የመመለስ ስራ መጀመሩንም አስታውሷል።

ጅዳ ሹሜሲ የህገወጥ ስደተኞች ማቆያ ውስጥ የነበሩ የመጀመርያዎቹ 296 ኢትዮጵያውያን ወንድ ስደተኞች ዛሬ ማክሰኞ ወደ ሀገራቸው እንደሚመለሱም ይጠበቃል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጆሴፍ ማጉፊሊ በታንዛኒያ የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ከእስር ለመልቀቅ ወሰኑ። የታንዛኒያው ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ በሀራቸው የታሰሩ ኢትዮጵያውያን ክእስር ለመልቀቅ ከፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ጋር መስማማታቸውን ገለፁ። ፕሬዜዳንት ሳህለወርቅ ለይፋዊ የስራ ጉብኝት በታንዛኒያ ይገኛሉ። ፕሬዚዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ፕሬዚዳንት ጆሴፍ ማጉፊሊ የሁለትዮሽ ውይይት ካደረጉ በኋላ በጋራ መግለጫ ሰጥተዋል። ፕሬዚዳንቱ…
ታንዛንያ ለ1 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ስደተኞች ምሕረት አድርጋለች።

ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ በትላንትናው ዕለት በታንዛንያ የአንድ ቀን ይፋዊ የሥራ ጉብኝት ባደረጉበት ወቅት ታንዛንያ 1 ሺህ 700 ኢትዮጵያውያን ሕገ ወጥ ስደተኞችን ወደ አገራቸው እንደምትመልስ ገልጻለች።

የታንዛንያ ፕሬዝዳነት ማጉፉሊ፤ ፕሬዝዳንት ሳህለወርቅን ባስተናገዱበት በትናንትናው ዕለት፤ "በሁለቱ አገራት መካከል ካለው ወዳጅነት የተነሳ [ኢትዮጵያውያን እስረኞች] በነጻ ወደ አገራቸው እንዲሄዱ መፍቀዳችንን ነግሬያቸዋለሁ" ብለዋል።

በታንዛንያ እስር ቤቶች ውስጥ ለሰባት ዓመት ያህል የቆዩ እንደሚገኙበትም ተናግረዋል።

ማጉፉሊ አክለውም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግዙፍ አየር መንገድ መሆኑን በመጥቀስ፤ 260 ሰው የመጫን አቅም ያለው ድሪም ላይነር አውሮፕላን በሁለት በረራ ከአንድ ኤር ባስ ጋር ተጨምሮ እስረኞቹን በአንድ ጊዜ ወደ አገራቸው መመለስ እንደሚቻል ገልፀዋል።

"ዛሬ እንኳን የታሰረ እስረኛ ቢኖር ሁሉንም ለመውሰድ እስከመጣችሁ ድረስ እንዲለቀቅ እፈቅዳለሁ፤ ይህ ደግሞ በሁለቱ አገራት መካከል ያለው መልካም ግንኙነት ማሳያ ነው" ብለዋል።

በታህሳስ ወር በዳሬ ሰላም የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ በታንዛኒያ 4 ግዛቶች ውስጥ በሚገኙ ማረሚያ ቤቶች ባደረገው ጉብኝት ቁጥራቸው 1100 የሆኑ ኢትዮጵያውያን ታስረው ማግኘቱን ገልጾ ነበር።

ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ በታንዛንያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ከ3100 በላይ ዜጎችን ከእስር አስፈትቶ ወደ አገር ቤት መመለሱንም ገልጿል። ~ BBC

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#Attention

ተጓዳኝ ሕመም የሌለባቸውና በዕድሜ ወጣት የሆኑ ሰዎች በኮቪድ-19 ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን በሚሊኒየም የኮቪድ19 ሕክምና ማዕከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው ጫኔ አስታወቁ።

ቫይረሱ በራሱ ተጨማሪ ተጓዳኝ የጤና ችግሮችን እንደሚያስከትል አሳስበዋል።

ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ውለታው ፤ "የኮቪድ 19 ቫይረስ ተጓዳኝ ህመም ያለባቸውንና በዕድሜ የገፉትን ብቻ ነው የሚያጠቃው የሚለው የተሳሳተ ግንዛቤ አሁንም በስፋት ይስተዋላል። እስከ ቅርብ ጊዜ ድረስ የታየው ግን የተጠቁት ተጓዳኝ ህመም የሌለባቸው በ30ዎቹ የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ጭምር ናቸው" ብለዋል።

ምንም ዓይነት ተጓዳኝ ህመም የሌለባቸውና በዕድሜ ወጣት የሆኑ ሰዎች በቫይረሱ ሕይወታቸው እያለፈ መሆኑን የጠቆሙት ዶክተሩ፣ ምናልባት በዕድሜ የገፉና ተጓዳኝ ህመም ያለባቸው ላይ የበለጠ ቢከፋም እየሞቱ ያሉት ግን በሁሉም የዕድሜ ክልል ውስጥ ያሉ ዜጎች መሆናቸውን ገልፀዋል።

አሁን ላይ ባለው ሁኔታ የጽኑ ህሙማን ታካሚዎችና በኮቪድ-19 ሕይወታቸው የሚያልፍ ወገኖች ቁጥር ጨምሯል። የማሽን ድጋፍና ኦክስጅን የሚያስፈልጋቸው ታካሚዎች ቁጥር ከዕለት ወደ ዕለት እያደገ መምጣቱን አስታውቀዋል።

እንደዶ/ር ውለታው ገለፃ፤ ከወራት በፊት 60 % የሚሆኑ ታካሚዎች ቶሎ አገግመው የሚወጡ ታካሚዎች ነበሩ፤አሁን ላይ ግን ከ50 በመቶ በላይ ያለው ታካሚ በፀና ታሞ የሚመጣ ነው። ይህም የሚያሳየው መዘናጋት መኖሩንና ከውጭ ተጎድተው መቆየታቸውን ነው።

ጥንቃቄ በጎደለ ቁጥር የቫይረሱ ዝውውር እየሰፋ እንደሚሄድ ያመለከቱት ዶክተሩ ከሰዎች ጋር ሳይገናኙ በቤት ውስጥ የቆዩ እናቶችና አባቶች መዘናጋት በመኖሩ ምክንያት በቫይረሱ የመጠቃት ዕድላቸው እየጨመረ መጥቷል። ይህም የሞት ቁጥር እንዲጨምር ማድረጉን አመልክተዋል።~ #EPA

@tikvahethiopia
ለሰርግ ማድመቂያ የተተኮሰው ጥይት የ2 ሰው ህይወት አጠፋ።

በጎንደር ዙሪያ ወረዳ ለሠርግ ማድመቂያ በሚል በተተኮሰ ጥይት የወንድ ሙሽራው ሁለት አጃቢዎች ህይወታቸው ማለፉን ፖሊስ አስታወቀ፡፡

የወረዳው ፖሊስ ጽህፈት ቤት ፥ አጃቢዎቹ ህይወታቸው ያለፈው በወረዳው ጭህራ ማንጠርኖ በተባለ የገጠር ቀበሌ ውስጥ መሆኑ አሳውቋል።

ጥር 16/2013 አመሻሽ የተከሰተው አደጋ ሙሽራው ከወንድ አጃቢዎቹ ጋር በመሆን ሴት ሙሽራዋን ከቤተሰቦቹዋ ቤትና ከመንደሩዋ ይዟት በመውጣት ላይ እያለ መሆኑን ነው ፖሊስ የገለፀው።

ለሠርጉ ማድመቂያ ተብሎ በአንድ ግለሰብ በተተኮሰው ጥይት 2ቱ የሙሽራው አጃቢዎች ክፉኛ ቆስለው ወደ ህክምና በመወሰድ ላይ እያሉ ነው ህይወታቻው ያለፈው።

ፖሊስ የሙሽራውን አጃቢዎች አሟሟት በህክምና በማረጋገጥ አስከሬናቸውን ለቤተሰቦቻቸው ማስረከቡንና የቀብር ሥነ-ሥርዓታቸውም ትናንት መፈጸሙን ገልጿል።

በሠርጉ እለት ድርጊቱን የፈጸመው ግለሰብ ለጊዜው ከአካባቢው ሸሽቶ ማምለጡን ያመለከተው ፖሊስ ግለሰቡን ለመያዝ የተጠናከረ ፍለጋ እያካሄደ እንደሚገኝ ለኢዜአ አሳውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"...ሱዳን ቀድማ ወደነበረችበት ቦታ ሳትመለስ በድንበሩ ጉዳይ ድርድር አይኖርም" - አምባሳደር ዲና ሙፍቲ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ አምባሳደር ዲና ሙፍቲ በሳምንታዊ መግለጫቸው የኢትዮ-ሱዳን ድንበር ውዝግብ እልባት ማግኘት የሚችለው በሰላማዊ የውይይት መድረክ ብቻ ነው የሚለው የኢትዮጵያ አቋም ዛሬም የፀና ነው ብለዋል።

አምባደር ዲና ፥ በጉዳዩ ላይ እናደራድራችሁ ለሚሉ አገራትና ወገኖች ክብር አለን ያሉ ሲሆን፤ ከየትኛውም ድርድር በፊት ግን መቅደም ያለበት ቅድመ ሁኔታ እንዳለ ገልፀዋል።

ይኸውም ሱዳን መጀመሪያ ወደነበረችበት ቦታ መመለስና የያዘችውን መሬት መልቀቅ አለባት የሚል እንደሆነ ነው ያሰመሩበት።

ምንጭ፦ አሐዱ ቴሌቪዥን
@tikavhethiopiaBOT @tikvahethiopia
#AddisTV_Live

የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ በህገወጥ የመሬት ወረራ ፣ ባለቤት አልባ ህንፃዎች እና የጋራ መኖሪያ ቤት እና የቀበሌ ቤቶች ዙሪያ የማጥራት ስራ ውጤት ለመገናኛ ብዙሃን ማብራሪያ በመስጠት ላይ ይገኛሉ።

ምክትል ከንቲባዋ እየሰጡ የሚገኙትን ማብራሪያ በ "አዲስ ቴሌቪዥን ጣቢያ" በቀጥታ መከታትል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ወ/ሮ አዳነች አቤቤ እየሰጡት ከሚገኘው ማብራሪያ ፦

- በአጠቃላይ በአዲስ አበባ ከተማ 13,389,955 ካሬ ወይም 1,338 ሄክታር መሬት በህገወጦች ተይዟል። በከተማዋ ካሉ 121 ወረዳዎች በ88ቱ ወይም በ73 % በሚሆኑት ላይ ወረራ ተፈፅሟል።

- በአጠቃላይ ባለቤት አልባ በሚል የተለዩ ህንፃዎች በድምሩ 322 ሲሆኑ የቦታ ስፋታቸው 229,556 ካሬ ነው። ከነዚህ ውስጥ ግንባታቸው የተጠናቀቁት 58 ሲሆኑ 125፣ 409 ካሬ ላይ ተገንብተውና ተከራይተው ያሉ ነገር ግን ባለቤት ነኝ የሚል አካል መረጃውን እንዲያቀርብ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም ማቅረብ ባለመቻላቸው ባለቤት አልባ ሆነው ተገኝተዋል።

- ግንባታቸው ያልተጠናቀቀ እንዲሁም ባለቤታቸው ያልታወቁ ህንፃዎች ብዛት በድምሩ 264 ሲሆኑ ስፋታቸው ደግሞ 104,147 ካሬ ላይ ያረፉ ቤቶች እና ህንፃዎች ናቸው። እነዚህ ቤቶች በተለይ በየካና በላፍቶ ክ/ከተሞች ላይ በአንድ አካባቢ መሬት በመውረር ግንባታ የተገነባባቸው ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኮንደሚኒየም ቤቶችን በተመለከተ ፦

- በህገወጥ መንገድ የተያዙ የጋራ መኖርያ ቤቶች በጠቅላላው 21,695 ሲሆኑ 15, 891 የጋራ መኖሪያ ቤቶች መረጃ ያልቀረበባቸው ናቸው።

- 4530 ባዶ የሆኑ ፣ 850 ዝግ የሆኑ ፣ እና 424 በህገወጥ መልኩ በግለሰቦች ተይዘው ይገኛሉ።

- በዕጣ ሳይሆን በተለያዪ አግባቦች ወደ ተጠቃሚው ግለሰቦች የተላለፉ ደግሞ 51,064 ቤቶች ተገኝተዋል፡፡

- በቤቶች ኮርፖሬሽን ተመዝግቦ የሚገኘው ባለዕጣዎች ስም ዝርዝር እና በመስክ በተገኘው የተጠቃሚዎች የስም ዝርዝር መሀከል ልዩነት ያላቸው ቤቶች 132,678 እንደሆኑና 18,423 ቤቶች ደግሞ የቤት ባለቤት ስም የሌላቸው ናቸው። በእነዚህ ቤቶች የሚኖሩ ግለሰቦች መረጃቸውን እንዲያቀርቡ በተደጋጋሚ ቢጠየቁም መረጃ ማቅረብ ያልቻሉ ወይም ያልፈለጉ በመሆናቸው ቤቶቹ በህገወጥ መንገድ የተያዙ መሆናቸውም ታውቋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#UPDATE

ያልተገነቡ የጋራ መኖሪያ ቤቶች እና የጋራ መጠቀሚያ ህንፃዎች በተመለከተ ፦

28 ብሎክ ማለትም ከ782 እስከ 842 የሚሆኑ ቤቶች እና የጋራ መጠቀሚያ ህንፃዎች (ኮሚናል ) ደግሞ 83 ሳይገነቡ መቅረታቸውን ተገልጿል።

በፌደራል እና በአዲስ አበባ ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶች በተሰራው የኦዲት ውጤት መሰረት በአጠቃላይ ላልተገነቡ ህንፃዎች የቦርድም ሆነ የስራ አመራር የውሳኔ ቃለ ጉባኤ አልተገኘም።

ምክትል ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች ፥ ምንም እንኳን መረጃ ባይገኝም ለግንባታው ክፍያ አልተከፈለም ብሎ መደምደም እንደሚያስቸግር በኦዲት ጥናቱ ማመልከቱን ገልፀዋል፡፡

Via ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ስር የሚተዳደሩ 150 ሺህ 737 የቀበሌ መኖሪያ እና ንግድ ቤቶች አሉ፡፡

ዛሬ ይፋ በሆነው ጥናት ተደራሽ መሆን የተቻለው 138 ሺህ 652 የመኖሪያ እና የንግድ ቤቶችን እንደሆነ ተገልጿል።

በከተማዋ 10 ሺህ 565 የቀበሌ ቤቶች በቁልፍ ግዥ፣ ሰብሮ በመግባት ፣ እና በሌሎች ህጉ ከሚፈቅደው ውጪ በህገ-ወጥ መንገድ እንደተያዙ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ገልፀዋል።

በጥናቱ ተደራሽ ከተደረጉ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች ውስጥ፡-

1ኛ. 7,723 ቤቶች ውል በሌላቸው (ህገወጥ) በሆኑ ሰዎች ተይዘዋል፡፡

2ኛ. 2,207 የቀበሌ ቤቶች ወደግል የዞሩ፣

3ኛ. 265 በሶስተኛ ወገን የተያዙ፣

4ኛ. 164 ኮንደምንየም በደረሳቸው/የራሳቸው ቤት ባለቸው ሰዎች የተያዙ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች መኖራቸው ታውቋል።

5ኛ. 137 ለመኖሪያነት የሚያገለግሉ የቀበሌ ቤቶች በሽያጭ ወደ ግል የተላለፉ፤

6ኛ. 1 ሺህ 243 ታሽገው/ተዘግተው የተቀመጡ፣

7ኛ. 5 ሺህ 43 የፈረሱ፤

8ኛ. 180 አድራሻቸው የማይታዎቁ/የጠፉ የቀበሌ መኖሪያ ቤቶች እንዳሉ ተረጋግጧል፡፡

የቀበሌ ንግድ ቤቶችን በተመለከተ፦

በአጠቃላይ የንግድ ቤቶች ብዛታቸው 25,096 ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ በህገወጥ መንገድ የተያዙ የቀበሌ የንግድ ቤቶች ብዛት 4,076 ናቸው።

1ኛ. 1 ሺህ 70 የንግድ ቤቶች ውል የሌላቸው ነጋዴዎች እየተጠቀሙባቸው መሆኑ ተለይቷል

2ኛ. 2 ሺህ 451 የቀበሌ የንግድ ቤቶች ከአንድ በላይ የንግድ ቤት በያዙ 1,086 ነጋዴዎች እንደተያዙ ተለይቷል

3ኛ. 376 የቀበሌ ንግድ ቤቶች ደግሞ በተከራይ ተከራይ በሶስተኛ ወገን መያዛቸው ተለይቷል፣

4ኛ. 179 የታሸጉ የንግድ ቤቶች እንዳሉ ተለይቷል፡፡

Via ADDIS ABABA PRESS SECRETARY
@tikvahethiopia
#NEBE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ባወጣው የጊዜ ሰሌዳ መሰረት የፓርቲዎች የምርጫ ምልክት መረጣ እየተከናወነ ይገኛል።

እስከአሁን ድረስ 45 ያህል ፓርቲዎች ምልክቶቻቸውን ማስገባታቸውን ታውቋል።

የሚከተሉት ፓርቲዎች የመረጧቸው ምልክቶች በተለያዩ ምክንያቶች ቀይረው እንዲያቀርቡ ጥሪ እንደተደረገላቸው ቦርዱ አሳውቋል ፦

1ኛ. የአማራ ዴሞክራሲያዊ ሃይል ንቅናቄ - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

2ኛ. የጋሞ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ- የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

3ኛ. የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) - የመረጠው ምልክት ከዚህ በፊት በነበረው ምርጫ ሌላ ፓርቲ ሲጠቀምበት የነበረ በመሆኑ እና ፓርቲው የቀድሞ ምልክቱን ለመጠቀም በመጠየቁ

4ኛ. የምእራብ ሶማሌ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ - ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በሆኑ

5ኛ. የአርጎባ ብሔረሰብ ዴሞክራሲያቂ ንቅናቄ- ከሌላ ፓርቲ ምልክት ጋር ምልክቱ የተቀራረበ በመሆኑ

6ኛ. የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) - ህጋዊ ሃላፊነት በተሰጠው አካል ምልክታቸውን እንዲመርጡ የተጠየቁ (በዚህም መሰረት የድርጅቱ ሊቀመንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ የምርጫ ምልክት አስገብተዋል።)

የምርጫ ምልክት ያላስገቡ፣ እንዲቀይሩ የተገለፀላቸው ወይም መቀየር የሚፈልጉ እስከ ጥር 23 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንዲያጠናቁ ቦርዱ አሳስቧል።

የጸደቁ ምልክቶችን እና የፓርቲዎች ዝርዝር ሂደቱ ሲጠናቀቅ ይፋ የሚያደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ዛሬ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia