#ETH302
ለቦይንግ 737 አውሮፕላን ሰለባዎች ሙት አመት መታሰቢያ ላይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ካህናት ጸሎት አድርገዋል። የአካባቢው ፈረሰኞች ዛሬ ለአመት የዘለቀው ሀዘን የሚያበቃበት ቀን መሆኑን ለማሣወቅ ጥቁር እና ነጭ ሰንደቅ አላማዎችን በመያዘ ተገኝተው ነበር። አባ ገዳዎችም ምስጋና አቅርበዋል።
#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#AddisAbaba
በአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪዎችን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት አንድ ሺ የሚሆኑ የግል ታክሲዎችን ለማስገባት መታቀዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታውቋል። በመንግሥት ሦስት ሺ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ለማስገባት እየተሠራ መሆኑንም ተሰምቷል።

#ItsMyDam
ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴ ግድብ ላይ ያላትን አቋም ለማስረዳት በተለያዩ አገራት ከፍተኛ የልኡካን ቡድን በመላክ ላይ ትገኛለች።
በዚሁ መሰረት በኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ የተመራ ከፍተኛ የልኡካን ቡድን ዛሬ መጋቢት 3 ቀን 2012 ዓም ኬንያ ናይሮቢ በመገኘት ኢትዮጵያ በታላቁ የህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያላትን ግልጽ አቋም ለፕሬዝዳንት ኡሁሩ ኬንያታ አስረድቷል።
ሁለቱ መሪዎች ከህዳሴው ግድብ ጋር በተያያዘ ያደረጉትን ውይይት ተከትሎም የጋራ የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።
በፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ የሚመራው የልኡካን ቡድን በቀጣይም በሌሎቹ የአባይ ተፋሰስ አገራት ተመሳሳይ ጉብኝት በማድረግ ለአባል አገራቱ መሪዎች የኢትዮጵያን አቋም እንደሚያስረዳ ይጠበቃል።

የመርካቶ የአውቶብስ ተርሚናል!
የመርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የተርሚናሉ ግንባታ 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፥ በ2012 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡
የአውቶቡስ ተርሚናሉ የተሳፋሪዎችን ምቾት በመጠበቀ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል፡፡ ተርሚናሉ በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል፤ የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችን አካቷል፡፡