TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#InjibaraUniversity

የመማር ማስተማር ሂደቱን ለማስቀጠልና የዩኒቨርሲቲውን ሰላም ለማስጠበቅ ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች በመጡ ተማሪዎች መካከል ስምምነት ላይ ተደረሰ!
.
.
በተለያዩ የአገራችን ዩኒቨርሲቲዎች የተከሰተውን አለመረጋጋት ተከትሎ በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተፈጥሮ የነበረውን ስጋት ለመቅረፍ ከሰኞ ማለትም ከቀን 08/02/12 ጀምሮ ምክክር ሲካሄድ ቆይቷል፡፡

በምክክሩ ላይ የአካባቢው የሀገር ሽማግሌዎች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ ከክልልና ከዞን የተወከሉ አመራሮች፣ የዩኒቨርሲቲው የአስተዳደር አካላት፣ መምህራንና የተማሪ ተወካዮች እንዲሁም ሁሉም ተማሪዎች ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

በውይይት ሂደቱም በዋናነት በሌሎች ቦታዎች ላይ የሚከሰቱት አላስፈላጊ ግጭቶች በዩኒቨርሲቲው ውስጥ ሊንፀባረቁ እንደማይገባና ተማሪ ጥያቄ ካለው በሰለጠነ መንገድ ማቅረብ እንዳለበት ተገልጿል፡፡

ከሁሉም አካባቢ የመጡ ተማሪዎች ተቻችለውና ተከባብረው ለዩኒቨርሲቲውና ለሀገር ሰላም በጋራ መቆም እንዳለባቸውም ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡ በመጨረሻ የዩኒቨርሲቲው ፕሬዚደንት ፕ/ር ብርሃኑ በላይ እና የሀገር ሽማግሌዎች ለተማሪዎች ምክር ሰጥተው፤ ለተገኘው ሰላምና በጋራ የመቆም መንፈስ አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋና አቅርበዋል፡፡ ከነገ ማለትም ከ12/03/12 ዓ.ም. ጀምሮ መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት የሚቀጥል ሲሆን ሁሉም ተማሪ በክፍል እንዲገኝም ስምምነት ላይ ተደርሷል፡፡

(Injibara University)

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#InjibaraUniversity

"ቆሻሻን እና አላስፈላጊ አመለካከትን እናስወግድ" በሚል መሪ ቃል የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ከዩኒቨርሲቲ አመራሮችና ከጸጥታ አካላት ጋር በመተባበር ጊቢያቸውን አፅድተዋል፡፡

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኮቪድ-19 ምርመራ ተጀመረ!

በእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምርመራ መጀመሩ ተገልጿል። የምርመራ ማዕከሉ በሙሉ አቅሙ ከሰራ በአንድ ቀን 400 ሰዎችን የመመርመር አቅም አለው።

#InjibaraUniversity
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia