TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59K photos
1.5K videos
211 files
4.08K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#Ethiopia

ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር 130,772 ደረሰ።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 6,111 የላብራቶሪ ምርመራ 446 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ተረጋግጧል።

በ24 ሰዓት ውስጥ የ6 ሰዎች ሞት መመዝገቡን ተከትሎ አጠቃላይ በበሽታው የሞቱ ሰዎች 2,029 ደርሷል።

ትናንት 617 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 116,045 ደርሷል።

@tikvahethiopia
"ዘይት ምክንያቱ ሳይታወቅ ከነበረበት 330 ብር ወደ 450 ብር ከፍ ብሏል፥ የዘይት ጫማሪው ከማከፋፈያ በመሆኑ አስደንጋጭ ነው" - የችርቻሮ ሱቅ ባለቤት (አዲስ አበባ 4 ኪሎ አካባቢ)
ከ100 ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ ያሳየው የዘይት ዋጋ !

የዘይት ዋጋ ቀደም ሲል ከነበረበት ዋጋ ከ100 ብር በላይ የዋጋ ጭማሪ ማሳየቱን አዲስ ዘመን ጋዜጣ ቸርቻሪ ባለሱቆችን ጠቅሶ አስነብቧል።

4 ኪሎ አካባቢ የችርቻሮ ሱቅ ባለቤት የሆኑት አቶ ኑረዲን ጸሃ ለጋዜጣው የተናገሩት ፦

"ዘይት ምክንያቱን ሳናውቀው ከነበረበት 330 ብር ወደ 450 ብር ከፍ ብሏል። የዘይት ጭማሪው ከማከፋፈያው በመሆኑ አስደንጋጭ ነው።

አምስት ሊትር ዘይትን የምናመጣው ከ390 ብር እስከ 420 ብር ሲሆን የአውራጅና የታክሲ ክፍያን ከፍለን 500 ብር ካልሸጥን በስተቀር ትርፍ አይኖረውም።

አሁን የተስተዋለው የዘይቱ ዋጋ ከበርካታ ዜጎች የኑሮ ደረጃ ጋር የሚመጣጠን አይደለም።

ሸማቹ በተከሰተው ነገር ተደናግሮ የመግዛት ፍላጎት የለውም። እኛም እንደ ነጋዴ ሸጠን ገንዘባችንን ማንቀሳቀስ አልችልንም።"

የችርቻሮ ሱቅ ባለቤት አቶ ሁነኛው በየነ ፦

"የዘይት ውድነት በአልን ተከትሎ የመጣና በዓል ሲያልፍ እንደሚስተካከል ተስፋ አድርገን ነበር።

የጅምላ አከፋፋይ በ5 ሊትር ዘይት ላይ ከ90 እስከ 120 ብር ድረስ ጭማሪ አድርገዋል።

ከ4 መቶ ብር በላይ መጥቶ ሱቅ እስኪደርስ ድረስ የተለያዩ ወጪዎች ተጨምረውበት ስንት መሸጥ እንዳለበት ግራ ተጋብተናል።

ቀደም ሲል እንደነበረው አሁን ከዋጋው መወደድ ጋር ተያይዞ ገዥም የለም ብለዋል።

ጭማሪው ምንን አስመልክቶ እንደሆነ መረዳት አልቻልንም።"

የትኛው የህብረተሰብ ክፍል ነው በዚህ ዋጋ ገዝቶ ሊጠቀም የሚችለው ? መንግስት ችግሩን ለይቶ መፍትሔ ካላበጀለት በስተቀር ዘይት የጥቂት ሰዎች ምግብ ብቻ እየሆነ ሊመጣ ይችላል"

የመንግስት ምላሽ ፦

በንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር የቢዝነስ እቃዎች የዋጋ ጥናት ፣ ግምገማና ቁጥጥር ዳይሬክተር አቶ ካሳሁን ሙላት፣ የዘይት ዋጋ ላይ አላግባብ የዋጋ ጭማሪ ተደርጓል ብለዋል።

ዘይት ላይ ወደ 5 በመቶ ቀረጥ የተጣለበት ቢሆንም ቀረጥ ተከፍሎበት የሚገባው ዘይት ገና በመሆኑ አሁን የሚስተዋለው ጭማሪ ተቀባይነት የሌለውና ህገ ወጥ መሆኑን ገልፀዋል።

ጉምሩክ ዘይት እየተቀረጠ እንዲገባ ማለቱን ተከትሎ ነጋዴዎች አላግባብ ሀብት ለማካበት በማሰብ ብቻ ምርቱ ወደ ሀገር ሳይገባ ከቀረጥ ነፃ የገባ ምርት ላይ ጭማሪ አድርገዋል።

ከ5 ወር በፊት 3 መቶ ብር ድረስ ይሸጥ የነበረው የ5 ሊትር ዘይት ተጨማሪ ምርት ባለመግባቱ የተነሳ እስከ 330 ብር ደርሶ ነበር።

በአሁኑ ወቅት ደግሞ 4 መቶ ብር መድረሱን አስታውቀዋል።

አሁን እየተሸጠ ያለው የዘይት ምርት ቀደም ሲል ከታክስ ነጻ የገባ በመሆኑ መሸጥ የነበረበት ቀደም ሲል በነበረበት ዋጋ ነው።

ይህን ህገ ወጥ ጭማሪ ለማስተካከል ከክልሎች እና ከከተማ አስተዳደሮች ጋር ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ እየተነጋገረ ነው ብለዋል።

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AssosaUniversity

ዛሬ የአሶሳ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ትምህርታቸውን የተከታተሉ ከ2 ሺህ 1 መቶ በላይ ተማሪዎችን ለሰባተኛ ጊዜ አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል በመደበኛው መርሃ-ግብር ውስጥ 1,636 ተማሪዎች ፣ በቅዳሜ እና እሁድ 401 ተማሪዎች፣ 145 ተማሪዎች ደግሞ የድህረ-ምረቃ ምሩቃን መሆናቸው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot
"...ወደ ጥምቀተ ባህሩ ማስክ ሳያደርጉ መግባት አይቻልም" - የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ

የጎንደር ከተማ ጤና መምሪያ የጥምቀት በዓል ሲከበር በተለይ ወደ ጥምቀተ ባህሩ ሲገባ ማስክ ማድረግ ግድ እንደሚል መልዕክት አስተላልፏል።

የመምሪያው ኃላፊ አቶ ገቢያው አሻግሬ ፥ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከእለት ወደ እለት ቁጥሩ እየጨመረ እና ቫይረሱ ፀባዩን እየቀየረ በመምጣቱ ህብረተሰቡ ከምንጊዜውም በላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለበት ብለዋል።

ዘንድሮ በሚከበረው የጥምቀት በዓል ላይ በተለይ ወደ ጥምቀተ ባህሩ ቅጥር ግቢ ለሚገቡ ከኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር 400,000 /አራት መቶ ሺ/ የአፍ እና አፍንጫ መሸፈኛ (ማስክ) መዘጋጀቱን ገልጻዋል።

ኃላፊው ማስክ ያላደረገ ወደ ጥምቀተ ባህሩ መግባት እንደማይቻል አሳስበዋል፡፡

Via Gondar City Communication
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጥምቀት በዓል ዝግጅት !

#Hawassa

በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር የጥምቀት በዓል ካለምንም የጸጥታ ችግር እንዲከበር የሚመለከታቸው አካላትን ያሳተፈ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ እየሰራ ነው።

ግብረ ሀይሉ የጸጥታ ሃይሎች ፣ የመንግስት የሥራ ሃላፊዎች ፣ የአገር ሽማግሌዎች እንዲሁም የእምነት አባቶችን ያካተተ ነው።

በዓሉ በድምቀት እንዲከበር ከተማዋን የማጽዳትና የማስዋብ ሥራ በወጣቶች እየተካሄደ መሆኑንም ተገልጿል።

የከተማው ሰላምና ፀጥታ መምሪያ ፥ "በየክ/ከተማ ከሚገኙ የወጣት አደረጃጀቶች በአሉ በሰላም እንዲከበር ከጸጥታ ሀይሉ ጋር እየሰሩ ነው” ብሏል።

በሐዋሳ ከተማ እንግዶች ካለምንም የፀጥታ ስጋት ከተማዋን ጎብኝተው እንዲወጡ የተቀናጀ የጸጥታ የማስከበር ስራ እየተሰራ መሆኑን አሳውቋል።

#WolaitaSodo

የሶዶ ከተማ ሰላምና ፀጥታ ጽ/ቤት የጥምቀት በዓል በሰላም እንዲከበር ቅድመ ዝግጅት መጠናቀቁን አሳውቋል።

ከከተራ ጀምሮ በዓሉ እስኪጠናቀቅ መከናወን በሚገባቸው ተግባራት ዙሪያ የፀጥታ አካላት ጋር በመወያየት በየአካባቢው ምደባ መደረጉ ተገልጿል።

#DireDawa

የድሬዳዋ ፖሊስ ኮሚሽን ከህብረተሰቡና ከሀይማኖት አባቶች ጋር ተወያይቶ በዓሉ ያለምንም የጸጥታ እና ደህንነት ችግር በድምቀት እንዲከበር ለማድረግ ዝግጅት እንዳጠናቀቀ አሳውቋል።

የጸጥታ ማስከበር ስራው በድሬደዋ ፖሊስና በፌደራል ፖሊስ ቅንጅት የሚከናወን ነው ተብሏል።

በጸጥታ ማስከበር ስራው በየቀበሌው እና በየአካባቢው የተደራጁ ወጣቶችም ተሳታፊ ይሆናሉ ተብሏል። ~ ENA

PHOTO : FILE
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፕሮፌሰሩ 3.2 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ መኪና ተሸለሙ።

ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ በሀገሪቱ በተለያየ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእዉቅና እና 3.2 ሚሊየን ብር የሚያወጣ 2020 ሃይኦንዳይ መኪና ሽልማት ተበረከተላቸው።

ፕሮፌሰሩ ሽልማቱ የተበረከተላቸው በዉጭ ሀገራት የሚኖሩ የሀድያ ዞን ተወላጅ ዲያስፖራዎች በሀገሪቱ በተለያየ ዘርፍ ላበረከቱት አስተዋጽኦ የእዉቅና እና ሽልማት ፕሮግራም በሆሳዕና ከተማ ባካሄዱበት ወቅት መሆኑ ከዞኑ ኮሚኒኬሽን ሰምተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ዩዌሪ ሙሴቬኒ ምርጫውን እንዳሸነፉ ተገለፀ። ለ35 ዓመታት ያህል ኡጋንዳን የመሩት ዩዌሪ ሙሴቬኒ የኡጋንዳን ፕሬዜዳንታዊ ምርጫ እንዳሸነፉ የሀገሪቱ የምርጫ ኮሚሽን ዛሬ አሳወቀ። ሙሴቬኒ 5.85 ሚሊዮን ድምፅ ወይም በ58.64 በመቶ እንዳሸነፉ ነው ኮሚሽኑ የገለፀው። ተፎካካሪያቸው የነበሩት ቦቢ ዋይን 3.48 ሚሊዮን ድምፅ (34.83 %) አግኝተዋል። @tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
"ለራሴ እና ለባለቤቴ ህይወት ፈርቻለሁ" - ቦቢ ዋይን

ሮበርት ካያጉላንይ የምርጫውን ውጤት እንደማይቀበለው ተናግሯል ፤ ምርጫው በከፍተኛ ማጭበርበር የተሞላ ነው በማለት ክስ አቅርቧል።

በኡጋንዳ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዩኤሪ ሙሴቪኒ ማሸነፋቸው ትላንት መገለፁ ይታወቃል።

ፕሬዚዳንት ዩዌሪ ሙሴቪኒ ምርጫውን ማሸነፋቸውን ተከትሎ የ38 ዓመቱ ቦቢ ዋይን ለህይወቱ እንደሚፈራ ገልጿል።

ቦቢ ዋይን ከቢቢሲ ጋር በስልክ ጋር ባደረገው ቆይታ "ለራሴ እና ለባለቤቴ ህይወት ፈርቻለሁ" ብሏል።

መኖሪያ ቤቱ በፀጥታ ኃይሎች መከበቡንና ከቤቱም መውጣት እንደተከለከለ ገልጿል።

"ማንም ሰው ወደ ቤት እንዲገባ ሆነ እንዲወጣ ከልክለዋል። ከዚህ በተጨማሪ የአገር ውስጥ ሆነ ዓለም አቀፍ ጋዜጠኞች ወደ ቤቴ እንዳይገቡ እንዲሁ ታግደዋል" በማለት ያለውን ሁኔታ አስረድቷል። ~ ቢቢሲ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
#Ethiopia

በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 131,195 ደርሷል።

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 4,788 የላብራቶሪ ምርመራ 423 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ታውቋል።

በ24 ሰዓት ውስጥ አንድ ሰው በበሽታው ምክንያት የሞተ ሲሆን ይህም አጠቃላይ የሟቾችን ቁጥር 2,030 አድርሶታል ፤ ትላንት 102 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 116,147 ደርሰዋል።

በአሁን ሰዓት 225 ሰዎች በፀና ታመው ህክምና እየተከታተሉ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ከኢትዮጵያ ጋር ጦርነት ውስጥ የመግባት ፍላጎት የለንም" - ሌ/ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን

የሱዳን ሉዓላዊ ምክር ቤት ሊቀመንበር ፣ ሌ/ጄኔራል አብዱል ፈታህ አል ቡርሃን ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር በፍፁም ወደ ጦርነት የመግባት ፍላጎት የላትም ብለዋል።

ይህን ያሉት ትላንት ምሽት በኻርቱም ለሱዳን ጦር ድጋፍ (ከነጋዴዎች እና ስራ ፈጣሪዎች ጋር) በተዘጋጀ ፕሮግራም ላይ ነው።

አል ቡርሃን ፥ ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ብቻ ሳይሆን ከየትኛውም ጎረቤቷ ጋር ወደጦርነት የመግባት ፍላጎት እንደሌላት ገልፀዋል።

ቡርሃን ፥ በኢትዮ-ሱዳን ድንበር አካባቢ ባለው ውዝግብ በሌላ የውጭ ኃይል (በ3ተኛ ወገን) እየተመሩ ነው የሚባለው ጉዳይም ትክክል አይደለም ብለዋል።

ሱዳን ጦሯን ያሰፈረችው "በራሷ ድንበር" ነው ሲሉም ተደምጠዋል።

ከትላንት በስቲያ የኢትዮጵያ የጦር ኃይሎች ጠ/ኢታማዦር ሹም ጄነራል ብርሃኑ ጁላ ፥ "በሱዳን እና በኢትዮጵያ መካከል ያለው ድንበር 150 ዓመት ሳይካለል ቢቆይም ሁለቱም የነበሩበት ቦታ ይታወቃል ፤ ነገር ግን የሱዳን ኃይል ከነበረበት አልፎ ገብቷል" ብለው ተናግረው ነበር።

ጄኔራሉ ፥ እርምጃው የሱዳን መንግስት እና ህዝብ ተነጋግረው እና አምነውበት የተወሰደ አለመሆኑን ገልፀው ድንበር አካባቢ እየተጠጋ የሚቀሰቅሰው እና የሚፎክረው ኃይል ጥቂት 'ተላላኪ ግሩፕ'/የ3ተኛ ወገን አጀንዳን የያዘ ነው ሲሉ መጥራታቸው ይታወሳል።

ጄነራል ብርሃኑ፥ ለኢትዮ-ሱዳን ድንበር ጉዳይ ጦርነት መፍትሄ እንዳማይሆን ፤ ችግሩ በመነጋገር፣ በመደራደር እና ሰጥቶ በመቀበል መፈታት እንዳለበት መናገራቸው ይታወሳል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
ከፌዴራል ፖሊስ የተሰጠ ማሳሰቢያ ፦

ከሚመለከተው ህጋዊ አካል ፈቃድ ያልተሰጣቸው ግለሰቦች እና ተቋማት ከጥምቀት በዓል ጋር ተያይዞ ድሮን ማብረር እንደማይችሉ የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን አስታውቋል።

ከተገቢው አካል ፈቃድ የሌላቸው ግለሰቦች ሆኑ ተቋማት ድሮኖችን እንዳያበሩ ወይም እንዳይንቀሳቀሱ ጥብቅ ቁጥጥር ይደረጋል ተብሏል።

ድሮኖችን ለተለያዩ አገልግሎቶች ለማዋልም ህጋዊ ስልጣን ካለው አካል ፈቃድ ማውጣት እንደሚቻል ኮሚሽኑ ገልጿል።

@tikvahethiopia
ባለፉት 2 ቀናት በሱዳን ዳርፉር 83 ሰዎች ተገደሉ !

በሱዳን ምዕራብ ዳርፉር ግዛት በሁለት ጎሳዎች መካከል በተነሳ ግጭት በትንሹ 83 ሰዎች ተገድለዋል።

የሱዳን ዜና አገልግሎት (ሱና) የሐኪሞች ማኅበርን ጠቅሶ እንደጻፈው ግጭቱ በዳርፉር ግዛት ዋና ከተማ ኢል ገነይና ቅዳሜ ዕለት ነው የተከሰተው።

የግጭቱ መነሻ አንድ ሰው በጩቤ ተወግቶ መገደሉ ነው ተብሏል።

አሁን ግጭቱን ተከትሎ በዳርፉር ሰዓት እላፊ የታወጀ ሲሆን ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሒ ሐምዶክ አንድ ከፍተኛ የልዑካን ቡድን ግጭቱን እንዲመረምር ወደዚያው ልከዋል።

በፈረንጆች በ2003 ዓ/ም የጀመረው የዳርፉር ግጭት በሚሊዯን የሚቆጠሩ ሕዝቦችን ከቤት ንብረታቸው አፈናቅሏል።

ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰላም አስከባሪ ኃይል ገብቶ የማረጋጋት ሥራ ሰርቷል። የሰላም ንግግሮችም ቀጥለዋል። ሆኖም አሁንም ውጥረቱ እንዳለ ነው።

የቅዳሜ ግጭት የተቀሰቀሰው የተባበሩት መንግሥታት ድርጅትና የአፍሪካ ኀብረት የሰላም ማስከበሩን ተግባር ለ13 ዓመታት ካስጠበቁ በኋላ ለሱዳን አስረክበው መውጣታቸውን ተከትሎ ነው። ~ ቢቢሲ

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBOT
4,615 ተተኳሽ የክላሽ ጥይት ተያዘ።

ትላንት ከመቐለ ከተማ ወደ ባህር ዳር ከተማ ሲጓጓዝ ከነበረ አይሱዙ FSR መካከለኛ የጭነት ተሽከርካሪ በወልደያ መቆጣጠሪያ ጣቢያ በጉምሩክ ሰራተኞች አማካኝነት በተካሄደ ፍተሻ ብዛቱ 4,615 የሆኑ ተተኳሽ የክላሽ ጥይቶች መያዛቸውን ኤፍ ቢ ሲ ዘግቧል።

ህገ ወጥ የጦር መሳሪያዎቹን በመደበቅ ለማሳለፍ የሞከሩ አሽከርካሪውን ጨምሮ 4 ተጠርጣሪዎች  በቁጥጥር ስር ውለው ተጨማሪ ማጣራት እየተደረገባቸው ይገኛል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBOT
ሀዋሳ ከተማ የሚዘጉ መንገዶች ይፋ ሆኑ።

ከጥር 10 ቀን 2013 ዓ/ም ጀምሮ ለተከታታይ ሶስት ቀናት የሚከበረውን የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ በሀዋሳ ከተማ ለትራፊክ እንቅስቃሴ ዝግ የሚሆኑ መንገዶች ይፋ ተደርጓል።

በዓሉ በሚከበርበት ወቅት ህዝበ ክርስትያኑም ሆነ የከተማው ነዋሪ እንዲሁም አሽከርካሪዎች ለትራፊክ ፍሰቱ ተገቢውን ድጋፍ በመጠቆም በበዓሉ ዋዜማ ከየቤተክርስትያናቱ ታቦታቱ ሲወጡም ሆነ ሲገቡ በትራፊክ ፖሊስ ሞተረኛ እየታጀቡ ቅድምያ የሚሰጥ ይሆናል።

በዋናነት የሚዘጉ መንገዶች ፦

- ከሱሙዳ /ቅዱስ ገብረኤል ቤተ-ክርስትያን እስከ ማዘጋጃ አደባባይ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ

- ከግሎባል ጋራዥ እስከ ማዘጋጃ አደባባይ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ

- ከአዲሱ ዳህላክ እስከ ማዘጋጃ አደባባይ/ በዓሉ ሚከበርበት ድረስ መንገዱ የሚዘጋ ይሆናል።

ለጥቆማና አስተያየት ለበለጠ መረጃ ሀዋሣ ከተማ ፖሊስ መምሪያ የ24 ሰዓት መረጃ ሰልክ ቁጥር 0462201046 ላይ መደወል ይቻላል።

(በሲዳማ ክልላዊ መንግሥት፣ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ፓሊስ መምሪያ)

@tikvahethiopia