#CHINA
በቻይና ያሉ ተማሪዎችና ነዋሪ ኢትዮጵያውያን ለኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መከላከያ የሚውል 452 ሺህ 589 ዩዋን ድጋፍ መደረጉን በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ አስታውቋል።
በቻይና የሚገኙ የኢትዮጵያ ተማሪዎችና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉ የቤጅንግ ነዋሪ በድምሩ 101 ሺህ 189 ዩዋን ገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል።
በሌላ በኩል በቤጂንግ የኢትዮጵያ ኤምባሲ ሰራተኞች 9 ሺህ 500 ዩዋን ፣ ከተለያዩ የኢፌዴሪ ቆንስላ ጽህፈት ቤቶች አባላት ማለትም ከጓንዦ 3 ሺህ ዩዋን ፣ ከሻንሃይ 5 ሺህ 200 ዩዋን ፣ ከክችንችን 211 ሺህ ዩዋን ሲሰበሰብ በጓንዦ ከተማ ዳያስፖራ አባላት ደግሞ 120 ሺህ ዩዋን ድጋፍ ተገኝቷል።
ከዚህም ውስጥ 351 ሺህ 400 ዩዋን በቀጥታ ቫይረሱን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በኢትዮጵያ ለተቋቋመው ብሔራዊ ሀብት አሰባሳቢ ግብረ ኃይል መላኩን ኤምባሲው ገልጿል።
ቀሪው ከተማሪዎች እና አቶ አስቻለው በላይ ከተባሉት የቤጂነግ ነዋሪ ኢትዮጵያዊ የተገኘው 101 ሺህ 189 ዩዋን ደግሞ የህክምና መሳሪያዎችን ገዝቶ ለመላክ ምርቶችን በማፈላለግ ላይ መሆኑን ኤምሳቢው አስታውቋል።
ምንጭ፦ ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#CHINA
በቻይና ነዋሪነታቸውን ያደረጉ በመቶዎች የሚቆጠሩ አፍሪካውያን የንግድ ማህበረሰብ አባላትና ተማሪዎች ከቻይናዋ ግዛት ከሚገኙ ሆቴሎችና የጋራ መኖሪያ ቤቶቸ እንዲወጡ ተደረጉ።
የአካባቢው የጤና ባለሙያዎች የኮሮናቫይረስ ምርመራ ለማድረግ ነው ቢሉም፣ ከመኖሪያቸው የተባረሩት አፍሪካውያን በበኩላቸው የዘር መድልዎ ተፈፅሞብናል ብለዋል።
"ቫይረሱ አለባችሁ እያሉ ይወነጅሉናል" በማለት በጉዋንግዙ ተማሪ የሆነው ናይጄሪያዊው ቶቤና ቪክተር ተናግሯል።
"የቤት ኪራይ ከፍለናል፤ ኪራዩን ከተቀበሉ በኋላ ከቤት አባረሩን። ከትናንት ጀምሮ ውጭ ነው ያለነው" ብሏል።
ከሰሞኑ አፍሪካውያን በሚኖሩባቸው መንደሮች የኮሮና ቫይረስ እየተዛመተ ነው መባሉን ተከትሎ እነዚህ ሰፈሮች እንዲዘጉ ትእዛዝ ተላልፏል ቢባልም የቻይና ባለስልጣናት አስተባብለዋል።
📹Demola Olarewaju
ምንጭ፦ BBC

ቻይና የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መነሻን የሚመረምሩ ዓለም አቀፍ አጥኚዎችን አሁን ወደ ሀገርዋ እንደማትጋብዝ አስታውቃለች።
በጄኔቫ የቻይና አምባሳደር እንዳሉት ቻይና አጥኚዎቹን የምትጋብዘው ቻይና በኮሮና ቫይረስ ላይ ድል ከተቀዳጀች በኋላ ነው ብለዋል።
አምባሳደር ቼን ሹ ሀገራቸው አሁን ቅድሚያ የምትሰጠው ወረርሽኙን ማሸነፍ እና የቫይረሱን ጉዳይ ፖለቲካዊ ለማድረግ የሚሰነዘሩ ትርጉም የሌላቸው ውንጀላዎችን መቋቋም ላይ መሆኑን አስረድተዋል።
የዓለም የጤና ድርጅት በበኩሉ የቫይረሱን ምንጭ ለማጣራት በሚካሄደው ምርመራ ላይ ለመሳተፍ የቻይናን #ግብዣ እየተጠበቀ መሆኑን አስታውቋል።
ቻይና ግብዣውን መቼ ልታቀርብ እንደምትችል የተጠየቁት ሊቼን ሹ በአሁኑ ወቅት ቅድሚያ ሊሰጣቸው በሚችሉ ጉዳዮች ላይ እንደሚያተኩሩ ተናግረው ፤ ይህን ለማድረግ ደግሞ ትክክለኛውን ድባብ እንፈልጋለን ብለዋል - #DW

#China #SouthKorea #Russia
- ባለፉት 24 ሰዓት በቻይና አስራ አራት (14) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ ፤ ሁለቱ ከውጭ የገቡ እንደሆኑ ተገልጿል። በቻይና በአንድ ቀን ከ10 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ ከ9 ቀናት በኃላ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
- በደቡብ ኮሪያ በ24 ሰዓት 34 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። በደቡብ ኮሪያ ከአንድ ወር በኃላ በአንድ ቀን ከ30 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ሲያዙ ለመጀመሪያ ጊዜ ነው።
- ሩሲያ ውስጥ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዙ ሰዎች ቁጥር በፍጥነት እየጨመረ ነው ፤ ባለፉት 24 ሰዓት ብቻ 11,012 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል። በተጨማሪ 88 ሰዎች ሞተዋል።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot