TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#FakeNews የአማራ ክልል ልዩ ኃይል #ሊፈርስ ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ/በተለይም በfacebook/ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeNews ሌተናል ጄነራል #ሃሰን_ኢብራሂም ታሰሩ በሚል በማህበራዊ ሚዲያ እየተሰራጨ የሚገኘው መረጃ #ሀሰት ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#update በማዕድን ዘርፉ የተሰማሩ ድርጅቶች ሥራቸውን በተለያየ ምክንያት አቋርጠው ወጥተዋል እየተባለ ያለው #ሀሰት መሆኑን የማዕድን ሚኒስቴር አስታውቋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
🏷የ12ኛ ክፍል የፈተና #ዉጤት አስመልክቶ በተለያዩ ማህበረዊ ሚዲያዎች የሚለቀቁ መረጃዎች #ሀሰት መሆናቸውን የፈተናዎች ኤጀንሲ አስታወቀ፡፡ ሀገር አቀፍ የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች ኤጀንሲ እንዳስታወቀዉ የ12ኛ ክፍል ዉጤት #በቅርቡ ይለቃቃል የሚለዉ መረጃ መሰረተ ቢስ ነዉ ብሏል። የኤጀንሲዉ የሕዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ረዲ ሺፋ ለኢትዮኤፍኤም እንዳረጋገጡት ኤጀንሲዉ የፈተናዎቹ ዉጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን አልወሰነም ብለዋል፡፡

በተለያዩ የማህበራዊ ሚዲያዎች ዉጤቱ ተለቋል በዚህ ቀን ይለቀቃልና ሌሎች መሰል መረጃዎች ሀሰት እንደሆኑ አቶ ረዲ ተናግረዋል፡፡ ተማሪዎቹም ሆነ ህብረተሰቡ ከተሳሳተ መረጃ እራሱን እንዲጠብቅ ሃላፊዉ ጠይቀዋል፡፡ በቀጣይ ኤጀንሲዉ የ10ኛ እና የ12ኛ ክፍል የፈተና ዉጤት ይፋ የሚሆንበትን ቀን ለመገናኛ ብዙሃን በይፋ ያሳውቃል ብለዋል፡፡

Via #ኢትዮኤፍኤም
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeBot

"የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር ልናንበሸብሽዎት በ ቴሌግራም መጥተናል። ይህ bot ቁጭ ብለው ገንዘብ የሚያፍሱበት ነው። በዚህ ቦት 1 ሰዉ ሲጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።"

#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ስምን እየተጠቀሙ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መልዕክቶችን በርካታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት ተመልክተናል ይህ ፍፁም #ሀሰት ነው። መልዕክቱም የሚሰራጨው በሀሰተኛ ገፅ ነው!!

@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeBot

"የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብር ልናንበሸብሽዎት በ ቴሌግራም መጥተናል። ይህ bot ቁጭ ብለው ገንዘብ የሚያፍሱበት ነው። በዚህ ቦት 1 ሰዉ ሲጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።"

#የኢትዮጵያ_ንግድ_ባንክ ስምን እየተጠቀሙ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መልዕክቶችን በርካታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት ተመልክተናል ይህ ፍፁም #ሀሰት ነው። መልዕክቱም የሚሰራጨው በሀሰተኛ ገፅ ነው!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#FakeBot በኢትዮ ቴሌኮም ስም!

ትላንት በንግድ ባንክ ስም ዛሬ ደግሞ በኢትዮ ቴሌኮም ስም #ሀሰተኛ መልዕክቶች ሲሰራጩ እየተመለከትን ነው።

"Ethio Telecom ካርድ ልናንበሸብሽዎት በ ቴሌግራም መጥተናል። ይህ bot ቁጭ ብለው ገንዘብ የሚያፍሱበት ነው። በዚህ ቦት 1 ሰዉ ሲጋብዙ 1 ብር ያገኛሉ አሁኑኑ ይቀላቀሉን።"

#የኢትዮቴሌኮምን ስምን እየተጠቀሙ የሚሰራጩ የተሳሳቱ መልዕክቶችን በርካታ የቴሌግራም ተጠቃሚዎች ሲቀባበሉት ተመልክተናል ይህ ፍፁም #ሀሰት ነው። መልዕክቱም የሚሰራጨው በሀሰተኛ ገፅ ነው!!

#ሼር #share
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
የዶክተር ደብረፅዮን መገለጫ ፦ ዛሬ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ ሰጥተው ነበር። ዶ/ር ደብረፅዮን እየተደረገ ባለው ጦርነት ኤርትራ ወታደሮች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥረው እየወጉን ነው ብለዋል። ይህን በተጨባጭ ማሳየት እንችላለን ፣ የያዝናቸው የኢሳያስ (ኤርትራ) ወታደሮች አሉ ሲሉ ገልፀዋል። እስካሁን ከ10 ሺ በላይ ወታደሮች ማርከናል ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የኢሳያስ ወታደሮች…
'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ'

ትላንት ምሽት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ' በአየር ተደብድቧል ፤ የትግራይ ክልል ከተሞች በጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።

በፌዴራል መንግስት ስር የሚተዳደረው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ" ተከዜ በቦንብ እንደተመታ የሚነገረው #ሀሰት ነው ብሏል።

ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው ነው ሲልም ገልጿል።

* የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በጉዳዩ ላይ ያወጣው መረጃ ከላይ ተያይዟል !

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
'የሽምግልና የውይይት ጉዳይ'

በፌዴራል መንግስት ስር የሚገኘው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያ በዩጋንዳ የፌዴራሉ ባለስልጣናት "ከህወሓት" ጋር ለሽምግል እና ውይይት ሊቀመጡ እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ #ሀሰት ነው ብሏል።

ይህ መረጃ በተለያዩ ዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙሃን ሳይቀር ሲሰራጭ ነበር።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማጣሪያው ፥ "የፌዴራል መንግስት በትግራይ ክልል የህግ የበላይነትን ለማስከበር በቁርጠኝነት እየሰራ ይገኛል" ሲል ለህዝብ ባሰራጨው አጭር መግለጫ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia