TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ባህርዳር

በባሕር ዳር ከተማ 19 ሽጉጥ እና 1 ክላሽንኮቭ በቁጥጥር ስር ዋለ፡፡ በህገ ወጥ መንገድ ተደብቀው ከተያዙት19 ሽጉጥና 1 ክላሽንኮቭ በተጨማሪ 3 ሺህ 427 መሰል ጥይቶችም ተይዘዋል። ህገ ወጥ የጦር መሳሪያው በቁጥጥር ስር የዋለው በአንድ ግለስብ ውስጥ መሳሪያው እንዳለ በደረሰ ጥቆማ መሆኑም ነው የተገለጸው፡፡ ግለሰቡ በባህር ዳር ጣና ክፍለ ከተማ ተከረይቶ የሚኖር እንደሆነም የአማራ መገናኛ ብዙሃን ድርጅት ዘግቧል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

በኢትጵያ ጉምሩክ ኮሚሽን የባሕር ዳር ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት በህገ ወጦች ሲንቀሳቀስ የነበረ ንብረትን በቁጥጥር ሥር መዋላቸውን አስታውቋል፡፡የተለያዩ አልባሳት እና ህገ ወጥ የአሳ ማስገሪያ መረቦች ናቸው በፖሊስ የተያዙት፡፡ በሁለት አይሱዙ መኪናዎች ተጭነው ከሁመራ ወደ ጎንደር ከተማ ሊገቡ እያለ ትክል ድንጋይ ላይ እንደተያዙ ጽህፈት ቤቱ ለአማራ ብዙኃን መገናኛ ድርጅት ዛሬ በላከው መረጃ አስታውቋል፡፡

የንብረቶቹ ግምታዊ ዋጋ ከ 2 ሚሊዮን 170 ሺህ ብር በላይ እደሚሆንም ነው የተገለጸው፡፡ ንብረቶቹን የያዙት የአማራ ክልል ፖሊስ አባላት ናቸው ብሏል ጽህፈት ቤቱ፡፡ ንብረቶቹም ለጎንደር ጉምሩክ መቅረጫ ጣቢያ ገቢ እንደተደረጉ ነው የተገለጸው፡፡ ከተያዙት ንብረቶች ውስጥ 3 ሺህ 480 ህገ ወጥ የአሳ ማስገሪያ መረብ ይገኝበታል፡፡ ይህም መጠኑ ለማስገሪያነት ከሚያገለግለው መረብ ያነሰ በመሆኑ የአሳ ጫጩቶች ለምግነብነት ከመድረሳቸው እና ከመራባታቸው በፊት እንዲያዙ፣ የአሳ ምርትም እንዲቀንስ ያደርጋል፡፡

Via #AMMA
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#ባህርዳር

የመስቀል በዓል ዘር፣ ቋንቋና ሃይማኖት ሳይለዩን በጋራ ተግባብተን መኖርን የተማርንበት ዕለት በመሆኑ በድምቀትና ታላቅ ኩራት ልናከብረው ይገባል ሲሉ የባህርዳር ሀገር ስብከት ሊቀ ጳጳስና የቅዱስ ሲኖዶስ አባል ብጹዕ አቡነ አብርሃም ገለጹ።

በየዓመቱ መስከረም 17 የሚከበረው የመስቀል በዓልን አስመልክቶ የሚካሄደው የደመራ ስነ-ስርዓት በርካታ ቁጥር ያላቸው ምዕመናንና የውጭ አገራት ቱሪስቶች በተገኙበት በባህርዳርና በሌሎች ከተሞችም በድምቀት ተከብሯል።

አቡነ አብርሃም በበዓሉ ላይ ለምዕመናን ባስተላለፉት መልዕክት ወቅቱ የመስቀሉ ባለቤት የሆኑ ክርስቲያኖች ፈተና የበዛበት በመሆኑ ይህን አስከፊ ጊዜ በትዕግስት ዕንጂ ጥፋትን በጥፋት በመመለስ መሆን እንደማይገባው ተናግረዋል።

ተጨማሪ ያንብቡ👇
https://telegra.ph/ETH-09-27-3

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የዛሬ የህዳር 10/2012 ዓ/ም በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች ውስጥ ከሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባልት እና ከተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች እና ከሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተሰባሰበ መረጃ👇
https://telegra.ph/ETH-11-20-4

(TIKVAH-ETHIOPIA)

#ድሬዳዋ #ሀረማያ #ወልዲያ #መቱ #ASTU
#መደወላቡ #ባህርዳር #ደባርቅ #ደብረታቦር

@tsegabwolde @tikvahethiopia
እግር ኳስ ለሰላም፣ ለፍቅር፣ ለአንድነት፣ ለአብሮነት፣ ለሀገር ግንባታ!

#ባህርዳር_ከነማ
#መቐለ70_እንደርታ

PHOTO : ጋንታ መቐለ 70 እንደርታ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia