TIKVAH-ETHIOPIA
ችሎት ! የሰሜን ዕዝን የሬዲዮ መገናኛ በመጥለፍ የተጠረጠሩ ሰባት የጄኔራል መኮንኖች ዛሬ ፍርድ ቤት መቅረባቸው ተገልጿል። ጄኔራል መኮንኖቹ ሕገ-መንግሥታዊ ሥርዓቱን በመናድ እና በሀገር ክህደት ወንጀል የተጠረጠሩ መሆናቸው ተገልጿል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE
ፍርድ ቤት የቀረቡት በ ሜ/ጄ ገብረመድህን ፍቃዱ መዝገብ የሚጠሩ 7 ተጠርጣሪዎች ናቸው።
የቀረቡት ፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ አንደኛ ወንጀል ችሎት ነው።
የወንጀል ምርመራ ቢሮ ፦
ተጠርጣሪዎች ጥቅምት 24 ቀን 2013 ዓ/ም መቐለ ከተማ ለሚገኘው 'የሕወሓት ቡድን አመራሮች' መረጃ በመስጠት እንዲሁም ተልዕኮ በመቀበል የሬዲዮ መገናኛውን በመጥለፍ ሠራዊቱ እርስ በእርሱ እንዳይገናኝ በማድረግ ሀገር የማፍረስ ወንጀል ሠርተዋል በሚል ጠርጥሯቸዋል።
ድርጊቱን በመፈፀማቸው በርካታ የመከላከያ ሠራዊት አባላት ለህልፈትና ለአካል ጉዳት ተዳርገዋል ፤ ከባድ የሆነ የንብረት ውድመት ደርሷል ብሏል።
በእነዚህ እና በሌሎች ተያያዥ ወንጀሎች ፖሊስ የ14 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ጠይቋል።
ተጠርጣሪዎቹ ፦
የተጠቀሰውን ወንጀል አልፈፀምንም ሲሉ ተከራክረዋል።
ፍርድ ቤት ፦
ግራ ቀኙን የመረመረው ፍርድ ቤት የወንጀሉን ውስብስብነት እና ክብደት በሀገር ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት የሚያደርስ መሆኑን ከግምት በማስገባት ፖሊስ የጠየቀውን የ14 ቀናት ተጨማሪ ጊዜ ፈቅዷል።
የምርመራ ውጤቱን ለመጠባበቅም ለህዳር 17 ቀን 2013 ዓ.ም ተለዋጭ ቀጠሮ ሰጥቷል። (ኢቲቪ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#DrTedrosAdhanom
ዓለም የኮቪድ-19 መከላከያ ክትባት ወደማግኘት እየተቃረበ ቢሆንም የኮቪድ-19 መከላከያዎችን ማላላት የለበትም ሲሉ የዓለም ጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድሃኖም አሳሰቡ።
ዶ/ር ቴድሮስ ፥ "የኮሮናቫይረስ (ኮቪድ-19) አሁንም የዛሬ 8 ወር እንደነበረው አስጊ ወረርሽኝ መሆኑን እንደቀጠለ ነው" ብለዋል።
በፓሪስ እየተካሄደ በሚገኝ የሰላም ጉባዔ ላይ "በኮቪድ-19 ታክቶን ይሆናል ነገር ግን እርሱ ገና አልሰለቸንም" ብለዋል ዶ/ር ቴድሮስ አድሃኖም።
የአውሮፓ አገራት እየታገሉ ነው ነገር ግን ስርጭቱን ለማቆም የተወሰዱት እርምጃዎች እንዲሁም ቫይረሱ ምንም ለውጥ አላሳየም" ሲሉ ተናገረዋል።
ከሰሞኑን የተለያዩ ሀገራት ተመራማሪዎች "ውጤታማ" የሆነ ክትባት ማግኘታቸውን እየገለፁ ነው።
ዶ/ር ቴድሮስ ገና ደህንነቱ እና ውጤታማነቱ መፈተሽ ባለበት ክትባት ላይ መተማመን አደገኛ መሆኑን ገልፀዋል።
"ክትባት በፍጥነት ያስፈልጋል ፣ ነገር ግን እጃችንን አጣጥፈን ቁጭ አንልም" ብለዋል። (BBC)
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia

#COVID19Ethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,478
• በበሽታው የተያዙ - 521
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 771
አጠቃላይ 101,248 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,554 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,268 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
313 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,478
• በበሽታው የተያዙ - 521
• ህይወታቸው ያለፈ - 9
• ከበሽታው ያገገሙ - 771
አጠቃላይ 101,248 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,554 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,268 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
313 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የዶክተር ደብረፅዮን መገለጫ ፦
ዛሬ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ ሰጥተው ነበር።
ዶ/ር ደብረፅዮን እየተደረገ ባለው ጦርነት ኤርትራ ወታደሮች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥረው እየወጉን ነው ብለዋል።
ይህን በተጨባጭ ማሳየት እንችላለን ፣ የያዝናቸው የኢሳያስ (ኤርትራ) ወታደሮች አሉ ሲሉ ገልፀዋል።
እስካሁን ከ10 ሺ በላይ ወታደሮች ማርከናል ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የኢሳያስ ወታደሮች አሉበት ብለዋል።
ዶክተር ደብረፅዮን ፥ ለኢሳያስ ተሰጥቶ "በሻብያ ወታደሮች" ቁጥጥር ስር የነበሩ/የትግራይ ቦታዎችን ማስመለስ ችለናል ሲሉም ተደምጠዋል።
ከዚህ በተጨማሪም "የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ ፓዎር" የአየር ድብደባ ተፈፅሞበታል ፤ የትግራይ ከተሞችም ጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርገዋል ሲሉ ከሰዋል።
ዶ/ር ደብረፅዮን፥ " አሁንም በተለያዩ አቅጣጫዎች የጦርነት ዝግጅቶች አሉ ። ውጊያው ገና ነው ፤ ገና ጅምር ነው " ሲሉ ተናገረዋል።
* ሙሉ መግለጫ (27 MB) ከላይ ተያይዟል (WiFi ተጠቀሙ)

* Federal Police Commission
የፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን "በሀገር መክዳት ወንጀል" ፈፅመዋል ያላቸውን የህወሓት አባላት ላይ የፍርድ ቤት ማዘዣ ትዕዛዛ እንደወጣባቸው ባሰራጨው መግለጫ አሳውቋል።
* መላው ህዝቡ ፥ የሀገር መከላከያ ሰራዊቱ ፣ ፖሊስ አባላት ፣ የደህንነት ተቋማት ተፈላጊዎቹን አድኖ ለህግ ለማቅረብ እያደረጉ ያለውን ጥረት ባለበት ሆኖ ጥረት እንዲያደርግ ጥሪ አቅርቧል።
ህዳር 3/2013 ዓ/ም

#BREAKING
በትግራይ ብሄራዊ ክልል የሚቋቋመውን ጊዜያዊ አስተዳደር አስመልክቶ የሚኒስትሮች ም/ቤት ደንብ ማጽደቁ ይታወቃል።
በጸደቀው ደንብ መሠረት ዶ/ር ሙሉ ነጋ በክልሉ የተቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰይመዋል።
ዋና ሥራ አስፈጻሚው የጊዜያዊ አስተዳደሩ አካል ይሆናሉ።
የክልሉን መንግሥት አስፈጻሚ አካላትን የሚመሩ ኃላፊዎችን በክልሉ ከሚንቀሳቀሱ የተለያዩ ሕጋዊ የፖለቲካ ፓርቲዎች በመመልመል ይሾማሉ።

#DrMuluNega
በትግራይ ክልል የተቋቋመው "ጊዜያዊ አስተዳደር" ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሆነው ተሰየሙት ዶ/ር ሙሉ ነጋ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር (MoSHE) ዴኤታ በመሆን ሲያገለግሉ ነበር።

#HadiyaZone
የሀድያ ዞን ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ማቲዮስ ሎንቦሶን በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሀድያ ዞን ምክር ቤት ትላንት ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ አቶ ማቲዮስ ሎንቦሶን በምክትል አስተዳዳሪ ማዕረግ የዞኑ ዋና አስተዳዳሪ አድርጎ ሾሟል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መንግስት ከህወሓት ጋር ድርድር አያደርግም" - አቶ ዛዲግ ኣብርሃ
ኣቶ ዛዲግ ኣብርሃ "የህወሃት የጥፋት ቡድን" በእርቅ ስም እድሜውን ለማራዘም ቢፈልግም መንግስት ግን አይቀበለውም አሉ አቶ ዛዲግ አብርሃ።
ቡድኑ የፈፀመው "ደባ" ከባድ በመሆኑ በእርቅ ስም እድሜ ለማራዘምና ሽብርተኝነቱን ለማስፋፋት መፈለጉ ተቀባይነት የለውም ብለዋል።
መንግስት ከጥፋት ኃይል ጋር ድርድር አያደርግም ሲሉ ገልፀዋል።
አቶ ዛዲግ ይህን ያሉት በዛሬው ዕለት ለሀገሪቱ ምሁራን በወቅታዊ ጉዳይ ዙሪያ ገለጻ ባደረጉበት ወቅት ነው።
ህወሓት መንግስት ሆኖ ሀገር መከላከያን እና ደህንነቱ ላይ የነበረውን የበላይነት ሲያጣ በማኩረፍ መቐለ ላይ መመሸግን መርጧል ሲሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ባለፈ የጥፋት ሃይል በመሆን በመከላከያ ላይ ጥቃት ማድረሱ የሃገርን ህልውና አደጋ ላይ የጣለ ድርጊት ነው ብለዋል።
አቶ ዛዲግ አብርሃ፥ "ህወሓት የሰባ እና ሰማንያ ዓመት ሽማግሌዎችን በዋናነት ይዞ ነው እንጂ አዲስ ትውልድ ቢተካ ኖሮ ይህን ያክል ከዴሞክራሲ ጋር ተቃርኖ አይኖረውም ነበር" ሲሉ ተደምጠዋል።
የመከለከያ ሰራዊቱ እየወሰደ ያለው የህግ ማስከበር እርምጃ "የሀገርን ህልውና የማዳን ዘመቻ" በመሆኑ ሁሉም አካል ድጋፉን ሊሰጥ ይገባል ብለዋል። (EPA)

የዶክተር ደብረፅዮን መገለጫ ፦ ዛሬ ዶክተር ደብረፅዮን ገብረሚካኤል መግለጫ ሰጥተው ነበር። ዶ/ር ደብረፅዮን እየተደረገ ባለው ጦርነት ኤርትራ ወታደሮች ከፌዴራል የፀጥታ ኃይል ጋር ግንባር ፈጥረው እየወጉን ነው ብለዋል። ይህን በተጨባጭ ማሳየት እንችላለን ፣ የያዝናቸው የኢሳያስ (ኤርትራ) ወታደሮች አሉ ሲሉ ገልፀዋል። እስካሁን ከ10 ሺ በላይ ወታደሮች ማርከናል ከነዚህ ውስጥ ደግሞ የኢሳያስ ወታደሮች…
'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ'
ትላንት ምሽት ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል 'የተከዜ ሃይድሮ ኤሌክትሪክ ማመንጫ' በአየር ተደብድቧል ፤ የትግራይ ክልል ከተሞች በጨለማ ውስጥ እንዲቆዩ ተደርጓል ሲሉ መናገራቸው ይታወሳል።
በፌዴራል መንግስት ስር የሚተዳደረው "የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ" ተከዜ በቦንብ እንደተመታ የሚነገረው #ሀሰት ነው ብሏል።
ባለሁለት ክበብ ቅስት ያለው እና በውሀ የተሞላ ግድብ በቦንብ ቢመታ ሊያስከትል የሚችለው መጥለቅለቅ እና ጥፋት ማንም ሊገምተው የሚችለው ነው ሲልም ገልጿል።
* የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ መረጃ ማጣሪያ በጉዳዩ ላይ ያወጣው መረጃ ከላይ ተያይዟል !

This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የጠቅላይ ሚኒስትሩ የትግርኛ መልዕክት ፦
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ፥ የትግራይ ክልል ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላት ከቀናት ያልበለጠ ዕድሜ ለሌለው ቡድን ሲሉ ህይወታቸው እንዳያጡ ጥሪ አቀረቡ።
የትግራይ ልዩ ሃይል እና የፀጥታ አካላቱ እጃቸውን ለመከላከያ ሰራዊት በመስጠት በሚቀጥሉት 2 እና 3 ቀናት ራሳቸውን እንዲያድኑ ጥሪ አቅርበዋል።
የትግራይ ህዝብም ልጆቹን እየቀበረ ለሚገኘው 'ሃይል' ሲል መስዋዕት ከመክፈል እንዲቆጠብና ፈጥኖ እንዲታደጋቸውም ጠይቀዋል።
* የጠቅላይ ሚኒስትሩ ሙሉ መልዕክት ከላይ ባለው ቪድዮ ተያይዟል !

#DrLiaTadesse
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,532
• በበሽታው የተያዙ - 509
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 303
አጠቃላይ 101,757 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,558 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,571 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት :
• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 5,532
• በበሽታው የተያዙ - 509
• ህይወታቸው ያለፈ - 4
• ከበሽታው ያገገሙ - 303
አጠቃላይ 101,757 ሰዎች በበሽታው መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,558 ሰዎች ህይወታቸውን አጥተዋል ፤ 63,571 ሰዎች ደግሞ ከበሽታው አገግመዋል።
316 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባህር ዳር ምን ተፈጠረ ?
ዛሬ ምሽት ከ5:00 በኃላ በባህር ዳር ከተማ ውስጥ ፍንዳታ እና የተኩስ ልውውጥ ነበር።
መኮድ አካባቢ 2 የቦንብ ፍንዳታዎች ነበሩ። ከፍንዳታዎቹ በኃላ የተኩስ ልውውጥ ነበር።
የፀጥታ ኃይሎች ወደ ስፍራው ደርሰው ተቆጣጥረውታል።
አንድ ስማቸው በይፋ ያልተገለፀ የአማራ ክልል የፀጥታ ዘርፍ ከፍተኛ ኃላፊ ለኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን፥ "ብዙም ችግር የለም፤ ወዲያው ተቆጣጥረነዋል፣ አካባቢው ተረጋግቷል ፤ ስለጉዳዩ ምርመራ እየተደረገ ነው" ብለዋል።

የአማራ ክልል ኮሚኒኬሽን ቢሮ መገለጫ ፦
"የተከበራችሁ የክልላችን ህዝቦች አሁን ምሽት ላይ በባህር ዳር ከተማ በተለምዶ መኮድ በሚባለው አካባቢ የተፈጠረ ፍንዳታ የነበረ ቢሆንም ፍንዳታው በጸጥታ ኃይሉ በትንሽ ደቂቃዎች ውስጥ በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በከተማችን የተለየ የመብራተ መቆራረጥ አልተፈጠረም፡፡ ከተማችን በሰላማዊ ሁኔታ ውስጥ ትገኛለች፡፡
ፍንዳታው ከጁንታው ቡድን የአጥፍቶ ጠፊነት የሽብር ተግባር ጋር ስለመገናኘት አለመገናኘቱ መረጃዎቹ በሚመለከተው አካል በመጣራት ላይ ነው።
ጉዳዩ ተጣርቶ እንዳለቀ እናሳውቃለን፡፡"

ጎንደር ፦
የአማራ ክልል መንግስት በጎንደር አዘዞ አካባቢ ከ5:00 በኃላ ልክ የባህር ዳሩን አይነት ፍንዳታ መፈፀሙን አሳውቋል።
በአሁን ሰዓት ሁሉም ነገር ሰላም እንደሆነ ገልጿል።
የክልሉ መንግስት ሁሉም ህብረተሰብ ተረጋግቶ አካባቢውን እና እራሱን እንዲጠብቅ በጥብቅ አሳስቧል።