TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.91K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
TIKVAH-ETHIOPIA
በአፋር ክልል የተፈፀመው ጥቃት ፦ በአፋር ክልል ዞን 3 ገለአሎ በምትባል ወረዳ፣ ሰርከሞና ቴሌ ቀበሌ በሚባል መንደር የሚገኙ የአርብቶ አደር ማሕበረሰብ ላይ ጥቅምት 16፣ 2013 ዓ.ም ከሌሊቱ 10 ሰዓት በተፈፀመ ጥቃት 8 ሰዎች ተገድለዋል። አቶ አህመድ ካሎታይ (የክልሉ የኮሚኒኬሽን ቢሮ ኃላፊ) ፥ የተፈፀመው "የሽብር ጥቃት ነው፤ ሴቶችና ህፃናት ላይ ያነጣጠረ ነበር" ብለዋል። ይኸው በአካባቢው…
#UPDATE

በሶማሊ ክልል እና አፋር ክልል አዋሳኝ አከባቢ በተፈጠረው ግጭት አስከትሎ የ27 ንፁሃን ዜጎች ህይወት ማለፉን የሶማሊ ክልል ባወጣው መግለጫ አሳውቋል።

ከሟቾቹ መካካል በትላንትናው ዕለት በሲቲ ዞን ገረብ ኢሴ የሞቱት 10 ስዎች ይገኙበታል።

በአካባቢው በተከሰተው ግጭት ምክንያት ህይወታቸውን ላጡ የክልሉ መንግሰት የተሰማዉን ሀዘን ገልጿል።

የክልሉ መንግስት ከፌዴራል መንግሰት ጋር ግንኝነት እያደረገ እንደሚገኝና ለተጎጂዎች አስቸኳይ እርዳታ ለማድረስ እየሰራ መሆኑን አሳውቋል።

የሁለቱም ክልሎች ሰላም ጥያቄ ዉሰጥ በማስገባት የሁለቱ የወንድማማች ህዝቦች ግንኙነት እንዳይፈርስ እየተሰራበት ይገኛል ብሏል።

የዚህ ድርጊት መነሻው፣ የደረሰው የሰው ህይወት መጥፋት እንዲሁም የንብረት ውድመት በዝርዝር በመመርመር መፈትሔ ለማበጀት እየተሰራ እደሆነ ክልሉ አሳውቋል።

ምርመራው እንዳለቀ ለህዝብ ይፋ የሚደረግ ይሆናል ተብሏል።

ምንጭ፦ የሶማሊ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እየተባባሰ የመጣው የኮቪድ-19 ስርጭት ፦

ኮቪድ-19 የኒው ዮርኩን የተባበሩት መንግሥታቱን ድርጅት የሥራ እንቅስቃሴ እያስተጓጎለ ነው። የድርጅቱ ጠቅላላ ጉባዔ ፕሬዚዳንት ቮልካን ቦዚከር በካል የሚካሄዱ ስብሰባዎችን ሰርዘዋል።

ይህ የሆነው በመንግሥታቱ ድርጅት የኒዠር ሚሽን ሰራተኞች የሆኑ አምስት ሰዎች ላይ ኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ተከትሎ ነው።

ዩናይትድ ስቴትስ ዙሪያ ባለፉት ሰባት ቀናት ብቻ አምስት መቶ ሁለት ሽህ ስምንት መቶ ሃያ ስምንት አዲስ የኮሮና ተያዦች ተመዝግቧል።

የኢሊኖይ ክፍለ ግዛት አስተዳዳሪ በተለይ የሀገሪቱ ሦስተኛዋ ትልቅ ከተማ በሆነችው በቺካጎ አዲስ ዙር የቁጥጥርና ገደብ ርምጃዎች አውጥተዋል።

በዚህም መሰረት ከፊታችን ዓርብ ጀምሮ ምግብ ቤቶችና ቡና ቤቶች ደጅ ብቻ እንጂ የቤት ውስጥ አገልግሎት እንዳይሰጡ ተከልክሏል።

የኮሎራዶዋ ዴንቨር ከተማ ዕሁድ ዕለት 327 አዲስ የቫይረሱ ተያዥች መመዝገባቸውን ተከትሎ ቀደም ሲል 50 ከመቶውን ደንበኞቻቸው እንዲያስተናግዱ ተፈቅዶላቸው የነበሩ የምግብ እና መጠጥ ቤቶች ወደ 25 ከመቶ እንዲቀንሱ የከተማዋ ከንቲባ ማዘዛቸውን #ቪኦኤ አስነብቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#በኮሮናቫይረስ_ድጋሚ_የመያዝ_ጉዳይ

(ዶ/ር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሞያ)

ከሰሞኑን በኮሮና ቫይረስ ድጋሚ የመያዝ ጉዳይ እያነጋገረ ነው። ለዚህም በመጠኑ ለማብራራት ያክል በሳይንሳዊው ዓለም ውስጥ 2 አይነት መላምቶች አሉ።

1ኛው፤ በበሽታው ተይዞ በነበረ ግለሰብ ውስጥ እና መልሶ በማገገም ላይ ያለ ነገርግን ቀጣይነት ያለው ወይም እንደገና መነቃቃት የጀመረ ነባር ኢንፌክሽን ጉዳይ ሪፖርት ተደርጎ ሊሆን ይችላል፡፡

2ኛው፤በመጀመሪያው ኢንፌክሽን ሰዐት በተለያዩ የቫይረሶች ክሌድ (clade) የመያዝ መላምት ውስጥ በሽተኛው የመጀመሪያው ናሙና በሚሰበሰብበት ጊዜ አንዱ ክሌድ ብቻ ጎልቶ በመውጣት ሌላኛው ክሌድ ደግሞ ሌላ ጊዜ በተደረገ ምርመራ ሊገኝ መቻል ነው፡፡

ክሌድ ምንድን ነው?

ክሌድ ለሁሉም ሥነ-ፍጥረታት የሚመነጩት ከአንድ የጋራ የዝርያ ግንድ ሲሆኑ የሚሰጥ የቡድን ቃል ነው፡፡

እስካሁን ድረስ ሰባት ዓይነት የኮሮና ቫይረስ ዝርያዎች የሚታወቁ ሲሆን 2 ትልልቅ ክሌዶች አሉ።

የመጀመሪያው እና ትልቁ ክሌድ ውስጥ በተለያዩ አምስት ንዑስ-ዝርያዎች የተከፋፈሉ ሲሆን በሁለተኛው ደግሞ ሁለት ንዑስ-ዝርያዎች አሉ፡፡

የእነዚህ መረጃዎች አንድምታውም በኮሮና-ቫይረስ ድጋሚ የመያዝ እድል እንዳለና ክትባት የማዳበር ሂደቱን ፈታኝ እንደሚያደርገው ነው፡፡

ውጤታማ ክትባት ሆነ የፀረ-ኮሮና መድሃኒቶች ባለመኖሩ የበሽታውን ወረርሽኝ ለማቃለል ሁሉም ሰው ቀደም ሲል በኮቪድ-19 ተይዞ የነበረም ሆነ ያልተያዘ፣ በሌላው አይነት ላለመያዝ ተመሳሳይ ጥንቃቄ ማድረግ አለባቸው ማለት ነው፡፡

ለራሴም ሆነ ለሌላው ምክንያት አልሆንም!

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ትላንት ህይወታቸው ያለፈው የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ሥነ ስርዓት ሀሙስ በቢሾፍቱ እንደሚፈፀም ቤተሰቦቻቸው ተናግረዋል። @tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የክቡር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ የቀብር ስነ-ስርዓት በዛሬው እለት በቢሾፍቱ ከተማ እየተካሔደ ነው፡፡

አርቲስቱ የቀብር ስነ-ስርዓት ቢሾፍቱ ቅዱስ ገብርኤል ቤተክርስቲያን የሚፈፀም ሲሆን በስነ-ስርዓቱ ላይ የኦሮሚያ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ፣ ዘመድ አዝማድና አድናቂዎቻቸው በተገኙበት እየተከናወነ እንደሚገኝ የኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የመውሊድ በዓል እየተከበረ ይገኛል፡፡

በአዲስ አበባ በታላቁ አንዋር መስጊድ የሃማኖቱ ተከታዮች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

የእምነቱ ተከታዮች በዓሉን ከኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ጥንቃቄ በማድረግ እንዲያከብሩ መልእክት ተላልፏል፡፡

PHOTO : Addis Ababa Press Secretary
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በሸበሌ ወንዝ ላይ የተገነባውን የጎዴ የመስኖ ግድብ መጎብኘታቸውን አሳውቀዋል።

በግድቡ አማካኝነት 2,000 ሄክታር የቆላማ አካባቢዎች የግብርና ስራ አካል የሆነው የስንዴ ሰብል መልማቱን ገልፀዋል።

ከስንዴ በተጨማሪ የአትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም የቅባት እህሎች በስፋት ይመረታሉ ብለዋል ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን በእነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ ላይ አስተላልፋው የነበረውን እገዳ ማንሳቷን ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቃለች።

እገዳው ተላልፎባቸው የነበሩት እነ ሊቀ አእላፍ ቀሲስ በላይ በቤተክርስቲያኗ መዋቅር ውስጥ ሆነው ሥራ እንዲሰሩም ውሳኔ ተላልፏል ተብሏል።

እነቀሲስ በላይ በእርቁ ላይ ዛሬ ከሰዓት መግለጫ ይሰጣሉ ተብሎ እንደሚጠበቅ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#GERD

በአሜሪካ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትዉልደ ኢትዮጵያዉያን ፕሬዘዳንት ዶናልድ ትራንፕ በህዳሴዉ ግድብ ላይ የሰጡትን ያልተገባ አስተያያት አስመልክቶ ሰላማዊ ሰልፍ ሊወጡ መሆኑን ከሰልፉ አስተባባሪዎች መካከል የሆኑት አቶ ሁመር ለኦሮሚያ ብሮድካስቲንግ ኔትዎርክ (OBN) ተናግረዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ቲክቫህ ኢትዮጵያ ድረገፁን ይፋ ሊያደርግ ነው።

በየጊዜው የቲክቫህ አባላት ቁጥር መጨመር እንደ ከዚህ ቀደሙ ከአባላቶች ጋር በምቹ ሁኔታ ለመገናኘት አስቸጋሪ አድርጎታል።

አዲሱ ድረገፅ የቲክቫህ አባላት ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ በየአካባቢያቸው ያለውን ጉዳይ በራሳቸው የሚያሳውቁበት ነው።

በተጨማሪ በየወረዳው ያሉ የችግሮች ፣ የመብት ጥሰቶች ፣ በየተቋማቱ ያሉ የመልካም አስተዳደር ችግሮች አባላቶች ይፋ ያደርጉበታል።

ድረገፁ በአንድ አቅጣጫ ብቻ የሚዘወር አይደለም። አባላት ያዩትን ፣ የሰሙትን ፣ የደረሰባቸውን ፣ የፀጥታ ስጋትም ከሆነ ማንነታቸውን ይፋ ሳያደርጉ የሚያሳውቁበት ነው።

የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በነፃነት ስላለባቸው ችግር እንዲሁም ስላሉበት ሁኔታ በድረ ጉፁ ይፅፉበታል።

ይህ ድረገፅ አባላት በየወረዳው ፖስት ስለሚያደርጉበት ፣ ያንን መልዕክትም በወረዳው ያሉ ሰዎች ብቻ ስለማያዩት እና ተጨማሪ መረጃ ስለሚሰጡበት ከሶሻል ሚዲያ ዘመቻ ነፃ ነው።

የህዝቡን ችግር ለፖለቲካ ትርፍ ለሚያውሉም መንገዱን ይዘጋዋል።

የአንድ አካባቢ ችግር እዛው ባሉ አባላት ብቻ ይገለፃል፣ ከሌላ ቦታ ሆነው /ከውጭ ሀገር ችግሮችን ለማባባስ ለሚሞክሩ ሰዎች መንገዱን ይዘጋባቸዋል።

በሂደት ለውስን የህዝብ ድምፅ ለሚያስተጋቡ/ቲክቫህ አባላት ተቀባይነት ላላቸው የሀገር ውስጥ እና የውጭ ሚዲያዎች ክፍት ይደረጋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDTAE

ዛሬ በ1.8 ቢሊየን ብር በሶማሌ ክልል የሚገነባውን የገለልሽ-ደገሀምዶ መንገድ ስራ ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አስጀምረዋል።

ይህ አጠቃላይ 166 ኪ.ሜ የሚረዝመው ከጅግጅጋ -ገለልሽ-ደገሀምዶ የሚደርሰው የመንገድ ፕሮጀክት አካል ነው።

ቀሪው ከጅግጅጋ - ገለልሽ የሚደርሰው 56 ኪ.ሜ የመንገድ ስራው በ1 ቢሊየን ብር ተገንብቶ የተጠናቀቀ ሲሆን ዛሬ ተመርቆ ለአገልግሎት ተከፍቷል።

መንገዱ የክልሉ ዋነኛ የልማት ኮሪደር ከመሆን አንጻር ፋይዳው ከፍተኛ መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትሩ ገልፀዋል።

በሌላ በኩል ፦

ጠ/ሚ ዶክተር አብይ በሶማሌ ክልል አውባሬ ወረዳ የበርሃ አንበጣ ያደረሰውን ጉዳት መመልከታቸውን ገልፀዋል።

የአንበጣ መንጋው በ20 ሺህ ሄክታር የበቆሎ ምርት ላይ ጉዳት ማድረሱ ተገልጾላቸዋል።

ከምስራቅ ቤዝ በሚነሱ አውሮፕላኖች ኬሚካል ርጭት መንጋው አሁን በቁጥጥር ስር እየዋለ መሆኑን ዶ/ር አብይ አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DireDawaIndustrialPark

ዛሬ የድሬዳዋ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ጠ/ሚር ዶክተር አብይ አህመድ በተገኙበት ተመርቋል።

ይህ ኢንዱስትሪ ፓርክ በ150 ሚሊዮን ዶላር ወጪ የተገነባ መሆኑ ተገልጿል።

ፓርኩ ለ1,000 ዜጎች የስራ እድል መፍጠሩ የተገለፀ ሲሆን በሙሉ አቅሙ ስራ ሲጀምር 20 ሺህ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል ይፈጥራል ተብሏል።

በድሬዳዋ ኢንዱስትሪ ፓርክ 15 ሼዶች ያሉ ሲሆን በአልባሳት እና ጨርቃጨርቅ ምርት ላይ የተሠማሩ 4 ኩባንያዎች ሥራ መጀመራቸውን ከENA የተገኘው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#DrLiaTadesse

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,773
• በበሽታው የተያዙ - 481
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 867

በአጠቃላይ በሀገራችን 95,301 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,457 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 50,753 ከበሽታው አገግመዋል።

311 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰላማዊ ሰልፍ በዋይት ሀውስ ፦

የአሜሪካው ፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ሰሞኑን የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን በተመለከተ የተናገሩትን ንግግር በመቃወም ኢትዮጵያውያን እና ትውልደ ኢትዮጵያውን ከዋይት ሀውስ ፊት ለፊት ሰላማዊ ሰልፍ አድርገዋል።

የፕሬዜዳንት ዶናልድ ትራምፕ ንግግር የሁለቱን ሀገራት የቆየ ወዳጅነት የሚያሻክር እና ተገቢነት የለውም ፣ ኢፍትሀዊ ነው ሲሉ ለአሜሪካ ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

ከዚህ በተጨማሪም የሰልፉ ተሳታፊዎች የፕሬዜዳቱ ንግግር የኢትዮጵያን ሉአላዊነት የሚዳፈር ፣ የህዝቡን ደህነት እና የህዝቡን ክብር የሚነካ እንዲሁም ጦርነትን የሚቀሰቅስ በመሆኑ እናወግዛለን ብለዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቡሌ ሆራ ሀሰተኛ የብር ኖት ተያዘ !

በምዕራብ ጉጂ የቡሌ ሆራ ከተማ ፖሊስ በሀሰተኛ የብር ኖት ለመገበያየት የሞከረ ተጠርጣሪ በቁጥጥር ስር ማዋሉን ገልጿል።

ተጠርጣሪው በቁጥጥር ስር የዋለው ሰሞኑን በአንድ ሀሰተኛ ባለ 100 የብር ኖት ከሱቅ እቃ ለመግዛት ሲሞክር እጅ ከፍንጅ ተደርሶበት ነው።

ፖሊስ ተጠርጣሪውን በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ ለማድረግ ሲፈትሽ ተጨማሪ 42 ባለመቶ ሀሰተኛ የብር ኖት ይዞ መገኘቱንም አስታውቋል።

ተጠርጣሪው ለፖሊስ በሰጠው ቃል ሀሰተኛ የብር ኖቱን ያመጣው ነጋዴ በመሆኑ ሞያሌ ከተማ እቃ ሽጦ መሆኑን አስረድቷል፡፡

ሆኖም ተጠርጣሪው ተይዞ ተጨማሪ ሀሰተኛ የብር ኖት ተሰራጭቶ እንደሆነና እንዳልሆነ ለማጣራት ፖሊስ ምርመራና ክትትል በማድረግ እንደሚገኝ ገልጿል።

ፖሊስ በዞኑ ቶሬ ከተማ ቀደም ሲል በ36 ሀሰተኛ ባለ 100 የብር ኖት ለመገበያየት የሞከረ ግለሰብ በቁጥጥር ስር ማዋሉም ተመልክቷል። (ENA)

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በትምህርት ሚኒስቴር እና ባህርዳር ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት በባህርዳር ከተማ አለም አቀፍ የመምህራን ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ በተለያዩ ዝግጂት እየተከበረ ነው።

በመድረኩ በተለያየ ተቋማት የሚሰሩ አንጋፋ መምህራን እና ከፈተኛ የፌዴራል እና የክልል አመራሮች ተገኝተዋል።

መድረኩ ዛሬ እና ነገ የሚቆይ ነው በቆይታውም በተለያዩ መምህራንን የሚመለከት ጉዳዩ ለይ ውይይት ይደረጋል ነው የተባለው።

ምንጭ፦ ጋዜጠኛ ነፃነት ጌታቸው
@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia