TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.6K photos
1.44K videos
206 files
3.97K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#PASSPORT

የኢምግሬሽን፣ ዜግትና ኩነቶች ምዝገባ ኤጀንሲ ዜጎች ለፓስፖርት 45 ቀናት መጠበቅ እንዳለባቸው መግለጹን ካፒታል ጋዜጣ ዛሬ አስነብቧል፡፡ ኤጀንሲው ለፓስፖርት ሕትመት የውጭ ምንዛሬ ዕጥረት አለብኝ ሲል ገልጻል፡፡ አመልካቾች የተፋጠነ ፓስፖርት ለማግኘት ከመንግሥት ተቋማት የድጋፍ ደብዳቤ፣ የጤንነት ሁኔታ ማረጋገጫ፣ የቪዛ ፍቃድ፣ የአስመጭና ላኪነት ማረጋገጫ የመሳሰሉ ሰነዶችን ማቅረብ አለባቸው ብሏል፡፡ ለተፋጠነ አገልግሎት 2 ሺህ 182 ብር ሲጠየቅ፣ ለመደበኛው ደሞ 600 ብር ነው፡፡

Via #CPAITAL/wazema/
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጥንቃቄ! #አዲስ_አበባ ፓስፖርት እስከ 3 ወር እንደሚያቆይ ይታወቃል። ነገር ግን የተለያዩ አጭበርባሪዎች ፓስፖርት ለማውጣት የሚመጡ ሰዎችን ፓስፖርት 3 ወር ስለሚቆይ አፋጣኝ ፓስፖርት አለ ነገር ግን ለዚህ አገልግሎት 6,000 ብር መክፈል አለባችሁ በሚል እያጭበረበሩ እንደሚገኙ ይዚህ ሰለባ የሆኑ የቲክቫህ ቤተሰቦች ተናግረዋል። ይህን የሚፈፅሙ ሰዎች ኢሚግሬሽን ውስጥ የሚሰራ ሰው እንዳላቸው በማስመሰል…
#PASSPORT

የፓስፖርት አሰጣጥ ቀን መርዘም ምክንያት ደላሎች በህገወጥ መንገድ እናስፈፅማለን በማለት ገንዘብ እንደሚወስዱ በመረጃ ደረጃ እንጂ ለኤጀንሲው የቀረበ ጥቆማም ሆነ አቤቱታ አለመኖሩን የኢምግሬሽን የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ አስታወቀ። ኤጀንሲው ሙስና ሰርተዋል የተባሉ ሰራተኞች ላይ እርምጃ መውሰዱንም ጠቅሷል።

የኢምግሬሽን የዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ የህዝብ ግንኙነትና ኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክተር ደሳለኝ ተሬሳ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለፁት፤ ከፓስፖርት መዘግየት ጋር በተያያዘ ለሙስና የተጋለጡ አሰራሮች እንዳሉ ይሰማል። በተለይ በር ላይ ደላሎች በህገወጥ መንገድ እናስፈፅማለን በማለት ገንዘብ ያጭበረብራሉ ይባላል። ነገር ግን በማስረጃ የተደገፈ ለኤጀንሲው የቀረበ ጥቆማም ሆነ አቤቱታ የለም።

እንደ አቶ ደሳለኝ ገለጻ ፤ የፓስፖርት እጥረቱ ለመፍታት አንድ ሚሊዮን ፓስፖርት ታዞ በውጭ ህትመት ላይ ይገኛል። አጠቃላይ ሚያዝያ ወር ላይ ተጠቃሎ ይገባል ተብሎ ይጠበቃል። በክልል ከተሞች ሆሳህና፣ ነቀምት እና አሶሳ ቅርንጫፍ ፅህፈት ቤት በመክፈት ለህብረተሰቡ ፍትሃዊ በሆነ መንገድ ለማዳረስ እቅድ ተይዟል።

https://telegra.ph/passport-01-27

[አዲስ ዘመን ጋዜጣ]
@tikvahethiopiaBot @tikahethiopia
#PASSPORT

ባልተፈቀደ አግባብ የኢትዮጵያን ፓስፖርት በእጃቸው ያስገቡ 29 የውጭ ሀገር ዜጎች ፓስፖርቶችን እንደተሰረዘ የኢምግሬሽን ሃላፊዎች ማስታወቃቸውን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ዘግቧል፡፡

ፓስፖርት በገንዘብ የገዙ 3 የውጭ ሀገር ዜጎች ከሀገር ተባረዋል፤ ሌላኛው ደሞ ሊወጣ ሲል ታስሯል፡፡ ፓስፖርት በሕ ወጥ መንገድ በመስጠት የተጠረጠረ የተቋሙ ሠራተኛ ታስሯል፡፡

[ሸገር ኤፍ ኤም፣ ዋዜማ]
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PASSPORT

በአሁኑ ሰዓት ከ270,000 - 300,000 የሚደርስ ፓስፖርት እንዳለው የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገልጿል፤ በቀጣይ 500 ሺህ ፓስፖርት ለማስገባት ስምምነት መደረሱም ተሰምቷል።

ኤጀንሲው ከዚህ ቀደም በነበረው አሰራር 'አዲስ ፓስፖርት' ለማውጣት ተመዝግበው ከሁለት ወር እስከ ሶስት ወር የሆናቸው 90,000 ተገልጋዮች እየተጠባበቁ ይገኛሉ።

የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ መሰል ችግሮችን ለማስወገድም ከፊታችን መጋቢት 10 ቀን ጀምሮ አዲስ አሰራር ተግባራዊ ያደርጋል ተብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

የINVEA 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር ውለዋል!

በአስቸኳይ ፓስፖርት ለማውጣት የሚጠየቁ መስፈርቶችን ያላሟሉ እና መደበኛውን ፓስፖርት ያለአግባብ ሲሰጡ የነበሩ ሰራተኞች እንደነበሩ በዛሬው ዕለት ተገልጿል።

ያለአግባብ መስፈርቱን ላላሟሉ እና ለውጭ ዜጎች ፓስፖርት የሰጡ 10 ሰራተኞች በቁጥጥር ስር መዋላቸው ተነግሯል። በተደረገው የማጣራት ስራ ሰራተኞቹ ከውጭ ዜጎቹ ከ5 ሺህ ዶላር በላይ መቀበላቸውን ተገልጿል፤ 77 የሚሆኑ ፓስፖርቶች በህገ ወጥ መልኩ ተሰርተው መገኘታቸውንም ተሰምቷል።

ከዚህ ጋር ተያይዞም ፓስፖርቶቹ ጥቅም ላይ እንዳይውሉ ለኢንተርፖል ማሳወቅ እና ሰዎቹን ተጠያቂ የማድረግ ስራ መስራቱ የፌደራል ኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ገልጿል።

#FBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ፓስፖርትን ጨምሮ ሌሎች ሙሉ አገልግሎቶችን መስጠት ሊጀምር መሆኑን የኢሚግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 ገልጿል።

የትምህርት ፣ የጤና ፣ የስራና የሌሎች አስገዳጅ ጉዞዎች ብቻ የፓስፓርት አገልግሎትን በመስጠት ላይ የሚገኘው ተቋሙ በቀጣይ ሙሉ በሙሉ አገልግሎቱን መስጠት የሚያስፈልግበት ሁኔታ በመፈጠሩ በቅርቡ በሙሉ አቅም ወደ ሰራ ለመግባት መታቀዱን አስታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ኢምግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ከመስከረም ወር ጀምሮ ፓስፖርት በኦንላይን መስጠት እንደሚጀምር ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 አስታውቋል።

ኤጀንሲው ከኢትዮጲያ አየር መንገድ አይቲ ክፍል ጋር ውል በመፈፀም ፤ የፓስፖርት ፣ የቪዛ ማራዘም ፣ የትውልድ መታወቂያ እና የመኖሩያ ፍቃድ እድሳት ኦንላይን እንዲከናወን እየተሰራ ነው ብሏል።

ፖስፖርትም ሆነ የኤጀንሲውን ሌሎች አገልግሎት ፈላጊዎች ቀድመው በኦንላይን ሲስተም ቀጠሮ አስይዘው ወደ ኤጀንሲው በቀጠሯቸው በመሄድ አገልግሎት የሚያገኙበት ስርዓትም እየተዘረጋ እንደሆነና አገልግሎቱ ከ1 ወር ከ15 ቀን በኃላ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልጿል።

ኦንላይን አገልግሎትን ማግኘት ለማይችሉ ሰዎች በተቋሙ በሚኖረው መጨናነቅ ሳቢያ ለኮሮና ቫይረስ እንዳይጋለጡ አማራጭ ቅርንጫፍ ቢሮዎችን ለመክፈት ግንባታ መጀመሩን ኤጀንሲው ለሬድዮ ጣቢያው ተናግሯል።

ኤጀንሲው አዲስ አበባ ላይ ሁለት ቅርንጫፎች እንዲሁም በክልል ከተሞች ኦሳዕና ፣ ጋምቤላ ፣ አሶሳ ላይ የቅርንጫፍ ቢሮ ግንባታ ተጀምሯል፤ በሌሎች ክልሎች ላይም ይህ ሂደት ይቀጥላል ብሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

- የመደበኛ ፓስፖርት እድሳት እና አዲስ ጥያቄ ከጥቅምት 2/2013 ጀምሮ በሁሉም የኤጀንሲው (INVEA) የክልል ቅርንጫፍ ቢሮዎች አገልግሎት መስጠት ይጀምራል፤

- በአዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ፤

- በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት በጥቅምት 10/ 2013 ይጀምራል፤

- ለውጭ አገር ዜጎች በOnline ቪዛ የማራዘም እና ግዜያዊ መኖሪያ ፍቃድ የማደስ እና አዲስ የመጠየቅ አገልግሎት ጥቅምት 2/2013 ይጀምራል፤

- የትውልድ ኢትዮጵያዊ መታወቂያ እድሳትና ጥያቄ መደበኛ አገልግሎት ከጥቅምት 2/2013 እንደሚጀምር ተገልጿል፡፡

ምንጭ፡- የኢማግሬሽን ዜግነትና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል።

*አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#PASSPORT ከነገ ጥቅምት 10/2013 ጀምሮ በ Online ላይ ፖስፖርት ለማደስ እና ለአዲስ ፖስፖርት ቀጠሮ ለማስያዝ የማመልከት አገልግሎት ይጀምራል። *አዲስ አበባ ቢሮ ከህዳር 1/2013 ጀምሮ ሁሉም መደበኛ አገልግሎቶች ይጀምራሉ። (INVEA) @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#PASSPORT

የኢሚግሬሽን ፣ ዜግነት እና ወሳኝ ኩነት ኤጀንሲ ባጋጠመው የኔትወርክ ችግር ምክንያት የኦንላይን (online) አገልግሎቱን ዛሬ ጠዋት መጀመር እንዳልተቻለ ለ 'ኢትዮጵያ ቼክ' ገልጿል።

አገልግሎቱ ከሰአት አካባቢ ይሰራል ተብሎ እንደሚጠበቅና ፣ ስራው ሲጠናቀቅ አገልግሎቱ ማግኘት የሚቻልበት ሊንክ ይፋ እንደሚደረግ ኤጀንሲው አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia