TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#ONLF

የቀብሪደሃር ነዋሪዎች በኦጋዴን ብሄራዊ ነፃ አውጪ ግንባር (ኦብነግ) እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የተፈረመውን የሰላም ስምምነት ሁለተኛ (2) ዓመት አክበረዋል።

በኦብነግ እና በኢትዮጵያ መንግስት መካከል የሰላም ስምምነቱ የተደረገው እንደእኤአ ጥቅምት 21/2018 በአስመራ ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬ እስራኤልና ባህሬን ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነታቸው በይፋ ይጀመራል፡፡

የእስራኤል “የሰላም አውሮፕላን” የእስራኤልን እና የአሜሪካን ልዑካን ጭኖ በባህሬን ማናማ አውሮፕላን ማረፊያ ደርሷል፡፡

የሁለትዮሽ ግንኙነቱ ባህሬን UAE ተከትላ ከእስራኤል ጋር ያላትን ግንኙነት ለማደስ መስማማቷን ተከትሎ የመጣ ነው።

PHOTO : ALAIN
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከነገ ጥቅምት 9 ጀምሮ በአዲስ አበባ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት ይገባሉ ተብሏል። እነዚህ 560 አውቶብሶች ወደ ስምሪት የሚገቡት የከተማውን የትራንስፖርት ችግር ለመቅርፍ ነው። የአ/አ ከተማ አስተዳደር ከግል የትራንስፖርት ማህበራት ጋር ስምምነት በማድረግ ነው አውቶብሶቹ በኪራይ ወደ ስምሪት አንደሚገቡ የተጠቆመው፡፡ በአሁን ሰዓት በመስቀል አደባባይ ከፍተኛ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ…
560ዎቹ አውቶብሶች ለ1 ሳምንት ነፃ የትራንስፖርት አገልግሎት ለሁሉም የአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች ይሰጣሉ !

የአ/አ ምክትል ከንቲባ አዳነች አቤቤ በኪራይ ወደ ስምሪት የሚገቡ 560 አውቶብሶች ስራ አስጀምረዋል፡፡

የከተማ አስተዳደሩ በየወሩ ለብዙኃን ትራንስፖርት አገልግሎት 121 ሚሊዮን ብር ድጎማ እንደሚያደርግ ምክትል ከንቲባዋ አመልክተዋል፡፡

የትራንስፖርት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ከአውቶብስ አቅርቦት በተጨማሪ ዘመናዊ የትራንስፖርት የመሰረተ ልማት ስርዓት እንዲዘረጋ በልዩ ትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል።

በቀጣይ ሁለት ዓመታት በ12 ቢሊዮን ብር ወጪ 3 ሺህ የሚሆኑ አውቶብሶችን በግዢ ለማስገባት በሂደት ላይ ነው ብለዋል።

በኪራይ ወደ ስምሪት የሚገቡት 560 አውቶብሶች ነገ ስራ የሚጀምሩ ሲሆን ለ1 ሳምንት ያህል ለሁሉም የከተማዋ ነዋሪ የነፃ አገልግሎት እንደሚሰጡ ምክትል ከንቲባዋ መግለፃቸውን ከአ/አ ፕሬስ ሴክሬቴሪያት ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
በሰሜን ወሎ ዞን ሀብሩ ወረዳ የ28 ሺህ አባወራዎች ሰብል ሙሉ በሙሉ መውደሙን የወረዳው ግብርና ጽሕፈት ቤት አስታውቋል።

በሀብሩ ወረዳ ውስጥ 39 ቀበሌዎች ሲኖሩ 17 ወረዳዎች ላይ የተከሰተው የበረሃ አንበጣ 9 ሺህ 100 ሄክታር ሰብል ፣ 60 ሺህ ሄክታር ግጦሽ ፣ 53 ሺህ ሄክታር ደን እና 60 ሺህ ቁጥቋጦ መውደሙን ወረዳው ገልጿል።

አንበጣዉ መንጋው ሙሉ በሙሉ ውድመት ባደረሰባቸው 17 ወረዳዎች 141 ሺህ 240 ዜጎች አስቸኳይ የምግብ ድጋፍ ያስፈልጋቸዋል ተብሏል።

Via Addis Maleda Newspaper
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ሀብሩ_ወረዳ

በዛሬው ዕለት የአማራ ክልል የስራ ሃላፊዎች በሀብሩ ወረዳ በአንበጣ መንጋ ሰብላቸው የወደመባቸው የአርሶ አደር ማሳ ጎብኝተዋል።

የዚህ ጉብኝት አላማ በአንበጣ መንጋ የተጎዱ አካባቢዎችን በማየት የጉዳት መጠናቸውን ለሚመለከታቸው አካላት በመግለጽ ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ለማሳወቅ ነው።

በወረዳው የደረሰው ጉዳት በጣም ከፍተኛ በመሆኑ እና አሁንም የአንበጣ መንጋው እየጨመረ ስለሆነ መነሻው ከሆነው አጎራባች ወረዳ አሰሳ መደረግ እንዳለበት የሀብሩ ወረዳ ግብርና ጽ/ ቤት ሃላፊ አቶ ተመቸ ሲሳይ ገልፀዋል።

በአንበጣ መንጋው ሰብላቸው የወደመባቸውን አካባቢዎች የዞን አመራሮችም ጎብኝተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#ATTENTION📣

በኦሮሚያ ክልል ጭሮ እና አካባቢው የበረሃ አንበጣ መንጋ በሰብል ላይ ጉዳት እያደረሰ መሆኑ የጭሮ ቲክቫህ አባላት መልዕክት አድርሰዋል።

Video : CNSRTC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጭር መረጃ ፦

• ኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ ታማሚዎች ብዛት ደቡብ አፍሪካ ፣ ሞሮኮ እና ግብፅን ተከትላ ከአፍሪካ 4ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ከመላው ዓለም ደግሞ 49ኛ ላይ ትገኛለች።

• በዓለም አቀፍ ደረጃ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ከ40 ሚሊዮን በልጠዋል ፤ ከነዚህ መካከል ከ30 ሚሊዮን በላዩ አገግሟል፤ ከ1.1 ሚሊዮን በላይ ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በደራ ወረዳ ነገ ተማሪዎች ትምህርት ይጀምራሉ !

በደራ ወረዳ ውስጥ በባለፈዉ ዓመት 12ኛ እና 8ኛ ክፍል የነበሩ ተማሪዎች ነገ ጥቅምት 9/2013 ዓ/ም ትምህርት ይጀምራሉ።

ቀሪዎቹ ከ1ኛ -11ኛ ክፍል ያሉ ተማሪዎች ደግሞ ጥቅምት 16/2013 ዓ/ም ትምህርት እንደሚጀምሩ ተገልጿል።

በተጠቀሡት ቀናት ተማሪዎች በሚማሩበት ትምህርት ቤት ተገኝተው ትምህርታቸው እንዲከታተሉ የደራ ወረዳ ትምህርት ጽ/ቤት ጥሪ አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
ማስክ በጊዜ ባለመድረሱ ምክንያት በጋሞ ዞን ነገ ትምህርት አይጀምርም ተብሏል።

ጋሞ ዞን ነገ ጥቅምት 9/2013 ዓ.ም ትምህርት ይጀመራል ተብሎ ቢጠበቅም የማስክ አቅርቦት በተባለው ጊዜ ባለመድረሱ ምክንያት ትምህርት እንደማይጀምር ተገልጿል።

የማስክ አቅርቦት ተሟልቶ ጥቅምት 16 የመማር ማስተማሩ ሂደት እንደሚጀምር የዞኑ ትምህርት መምሪያ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#COVID19Ethiopia

የባለፉት 24 ሰዓት የኮቪድ-19 ሪፖርት ፦

• የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ - 7,151
• በቫይረሱ የተያዙ - 703
• ህይወታቸው ያለፈ - 6
• ከበሽታው ያገገሙ - 550

በአጠቃላይ በሀገራችን 89,137 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ ፤ የ1,352 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ 42,649 ከበሽታው አገግመዋል።

281 ሰዎች በፅኑ ታመው የህክምና ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነገ 17,154 ትምህርት ቤቶች ይከፈታሉ።

ከነገ ጀምሮ ትምህርት የሚጀምሩት በሀገሪቱ ገጠራማ አካባቢ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ናቸው።

ከetv ጋር ቆይታ ያደረጉት በትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ቤቶች መሻሻል ዳይሬክተር ጀነራል የሆኑት አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ 17,154 ትምህርት ቤቶች ነገ ትምህርት ለመጀመር የሚያስፈልጋቸውን ግብዓቶችን አሟልተዋል ብለዋል።

አቶ ዮሀንስ ዎጋሶ ፥ ዝግጅቱን በተመለከተም ነገ የሚከፈቱት ትምህርት ቤቶች አካላዊ ርቀት ለመጠበቅ ምቹ መሆናቸውን ገልፀዋል።

ከዚህ በተጨማሪ እስካሁን 10.7 ሚሊዮን ማስክ የተሰራጨ ሲሆን እንዚህ 17,154 ትምህርት ቤቶች ጋር ማስክ መድረሱን አሳውቀዋል።

@tikvahethiopiaBOT @tikvahethiopia
#UPDATE

5ኛው የኢፌዴሪ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት 6ኛ ዓመት የስራ ዘመን 1ኛ ልዩ ስብሰባ መካሄድ ጀምሯል።

ምክር ቤቱ በጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ነው ስብሰባውን እያካሄደ ያለው።

በስብሰባው ላይ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ተገኝተዋል። ከምክር ቤቱ አባላት ለሚነሱ ጥያቄዎች ምላሽና ማብራሪያ እየሰጡ ይገኛሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በመቅደላ ወረዳ በረዶ ቀላቅሎ የጣለ ዝናብ በደረሱ ሰብሎች ላይ ጉዳት አድርሷል !

በመቅደላ ወረዳ "016 ቀበሌ" ደብረዘይት ልዩ ስሙ ጨረፌ በተባለው ቦታ በቀን 7/01/2013 ዓ/ም በረዶ ቀላቅሎ በጣለው ዝናብ በ256 አርሶ አደሮች ይዞታ በሆነው በ148.5 ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ደርሷል፡፡

የተጎዱ ሰብሎች ስንዴ፣ ጤፍ፣ አተር ፣ ገብስ ሌሎችም ሲሆኑ በጉዳቱ 90% ሰብሎች መውደማቸውን ከወረዳው የግብርና ፅ/ቤት የተገኘው መረጃ ያመልክታል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዛሬ ከኤሚሬትስ ቀጥሎ 2ኛው ትልቁ የ UAE አየር መንገድ የሆነው የኤቲሃድ አውሮፕላን ወደ እስራኤል 'ቴል አቪቭ' መብረሩን አል ዓይን /AlAin/ አስነብቧል።

ይህ የእስራኤልና UAE የሰላም ስምምነት ተከትሎ በሁለቱ ሀገራት መካከል የዩኤኢ ንብረት በሆነ አየር መንገድ የተካሔደ የመጀመሪያው የመንገደኞች የበረራ አገልግሎት ነው፡፡

በረራው ኤቲሃድን ወደ እስራኤል መንገደኞችን በማጓጓዝ ከበባህረሰላጤው ሀገራት አየር መንገዶችም የመጀመሪያው ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በኮቪድ-19 ወረርሽኝ ምክንያት የተቋረጠው ትምህርት ለማስቀጠል እንዲሁም ተመራቂ ተማሪዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ የቀራቸውን ትምህርት ተከታትለው እንዲመረቁ ለማድረግ ዩኒቨርሲቲዎች ጥሪ ማድረግ ጀምረዋል።

ዛሬ የወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ የ2012 ዓ.ም ተመራቂ መደበኛ ተማሪዎች #ብቻ የምዝገባ (Registration) ጊዜ አሳውቋል።

በዚህም ተመራቂ ተማሪዎች ብቻ ጥቅምት 23 እና 24/2013 ዓ/ም እንዲመዘገቡ ጥሪ የቀረበ ሲሆን የመጀመሪያ ቀን ትምህርት (Day - One - Class - One) ጥቅምት 25 / 2013 ዓ/ም እንደሚጀምር ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ መምሪያ ሃላፊ ኮማንደር ታሪኩ ለገሰ በአስቸኳይ አቶ ልደቱን እንዲፈቱ ታዘዋል።

ዛሬ በምስራቅ ሸዋ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤት በዋለው ችሎት ነው ትእዛዙ የተላለፈው።

ኮማንደሩ አቶ ልደቱን የማይለቁት ከሆነ ፍርድ ቤቱ እርምጃ እንደሚወስድ አስጠንቅቋል።

የኢዴፓ ፕሬዜዳንት አቶ አዳነ ታደሰ ስለዛሬው የችሎት ውሎ የሰጡትን ዝርዝር መረጃ ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia