ችሎት!
አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ አቃቤ ህግ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል የጠየቀ ቢሆንም የፖሊስ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም ሲል የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።
በዛሬው ችሎት የቢሾፍቱ ወረደ ፍርድ ቤት የፖሊስ የምርመራ መዝገብ መዘጋቱን ገልፆ አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ አዟል።
Via Tarik Adugna (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

ከእስራኤል ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ መሆኑን BBC አስነብቧል።
ይካሄዳል የተባለው የንግድ በረራ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል።
አውሮፕላኑ በሳዑዲ አረቢያ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ይካሄዳል የተባለው የንግድ በረራ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል።
የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል።
አውሮፕላኑ በሳዑዲ አረቢያ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የገዳ ስረዓትን በስረዓተ ትምህርቱ ውስጥ በማካተት ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።
የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ እንዳሉት ቢሯቸዉ የገዳ ስረዓትን በክልሉ በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች (1-8) ከአዲሱ የኢትዮጵያውያን አመት ጀምሮ ያስተምራል።
ቢሮዉ ትምህርቱን በሁሉም ትምሕርት ቤቶች ለመስጠት ቢያቅድም ከትምህርት ቁሳቁስ ዝግጅት እና አቅርቦት አንጻር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር መወሰኑን ገልጸዋል።
አዲሱ ትውልድ የገዳ ስረዓት መማሩ የሚያጋጥሙትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችለዋል ማለታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮን ዋቢ አድርጎ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።
በሌላ በኩል የገዳ ስርዓት ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።
ሀላፊው እንደተናገሩት የገዳ ሥርዓት ስርዓተ ትምህርቱ ተጠናቆ የመፅሐፍ ዝግጅት ላይ ተደርሷል፡፡
የመፅሐፍ ዝግጀቱም በ2 እና 3 ሳምንታት ያልቃል በአዲሱ የትምህርት ዘመን የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መሰጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡
ትምህርቱን የሚሰጠው በአዲስ አበባ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሚሰጥባቸው 7 ትምህርት ቤቶች ናቸው ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

በአዲስ_አበባ_ከተማ_የመሬት_ወረራ_እና_የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኢፍትሃዊ_ዕደላን_አስመልክቶ_የተደረገ_ጥናት.pdf
278.1 KB
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ላያ ያደረገው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሙስጠፋ አዲብ የሊባኖስ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ!
በጀርመን ሀገር የሊባኖስ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት ሙስጠፋ አዲብ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡
አዲብ 128 አባላት ካሉት የሃገሪቱ ፓርላማ የ90ውን ድጋፍ በማግኘት ነው የተሾሙት፡፡
የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ሚሼል አውን አዲሱ ተሿሚ መንግስት እንዲያዋቅሩ ስለመጠየቃቸውም ዘ ናሽናልን ዋቢ አድርጎ አል አዓይን /AlAin/ ነው የዘገበው፡፡

ነሃሴ 25/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 599 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,343 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 127 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 28 ከአርሲ ዞን
- 25 ከጉጂ ዞን
- 14 ከቡራዩ ከተማ
- 13 ከቢሾፍቱ ከተማ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በኦሮሚያ፦
- 6,301 በቫይረሱ የተያዙ
- 45 ሞት
- 1,953 ያገገሙ
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 161 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- 21 ከደምቤ (አጋሎ) ወረዳ
- 1 ከሆምሻ ወረዳ
አጠቃላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፦
- 651 በቫይረሱ የተያዙ
- 303 ያገገሙ
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,894 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 75 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 15 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 12 ከደ/ጎንደር ዞን
- 10 ከሰ/ወሎ ዞን
- 9 ከዋግ ብ/ሰብ ዞን
- 7 ከባህር ዳር ከተማ
- 6 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።
አጠቃላይ በአማራ፦
- 2,412 በቫይረሱ የተያዙ
- 22 ሞት
- 1,261 ያገገሙ
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 440 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።
አጠቃላይ በሀረሪ፦
- 1147 በቫይረሱ የተያዙ
- 21 ሞት
- 376 ያገገሙ
@tikvahethiopiaBot

በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 ህይወታቸው ያለፈ ሰዎች ቁጥር ከ800 አለፈ!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,364 የላብራቶሪ ምርመራ 1,009 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 612 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 52,131 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 809 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,994 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 19,364 የላብራቶሪ ምርመራ 1,009 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ16 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 612 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 52,131 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 809 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,994 ደርሷል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 25/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦
#SNNPRS
በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 2,337 የላብራቶሪ ምርመራ 53 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት ፦
- ከጋሞ 17 (12 ከአርባምንጭ ከተማ እና 5 ከአርባምንጭ ዙሪያ) ፣
- ከደቡብ ኦሞ 17 (10 ከማሌ ፣ 3 ከደቡብ አሪ ፣ 3 ከሰሜን አሪ እና 1 ከባካ ዳውላ)፣
- ከቤንች ሸኮ 6 (5 ከሚዛን አማን እና 1 ሰሜን ቤንች)፣
- ከጉራጌ 3 (1 ከእነሞርና ኢነር ፣ 1 ጉመር እና 1 ም/አክሊል)
- ከሃዲያ 3 (3ቱም ከሾኔ) ፣
- ከወላይታ 3 (1 ከአረካ፣ 1 ከኪንዶ ኮይሻ እና 1 ከቦሎሶ ሶሬ)፣
- ከካፋ 1 (ጨታ)፣
- ከጎፋ 1 (ገዜ ጎፋ)፣
- ከሃላባ 1 እና 1 ከባስኬቶ ዞኖች እና ልዩ ወረዳዎች ናቸው፡፡
አጠቃላይ በደቡብ ፦
- 1,339 በቫይረሱ የተያዙ
- 9 ሞት
- 538 ያገገሙ
#Sidama
በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 468 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ የተያዙት፦
- 13 ከሀዋሳ ከተማ
- 10 ከሀዌላ ወረዳ
- 3 ከወንዶ ገነት ወረዳ
- 2 ከማልጋ
- 2 ከሸበዲኖ ወረዳ
አጠቃላይ በሲዳማ፦
- 1,438 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 695 ያገገሙ
#DireDawa
ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 464 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 42 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።
አጠቃላይ በድሬዳዋ ፦
- 1,017 በቫይረሱ የተያዙ
- 20 ሞት
- 770 ያገገሙ
@tikvahethiopiaBOT

በትግራይ ክልል ለሚካሄደው ክልላዊ ምርጫ ከ2.7 ሚሊዮን በላይ ሰዎች መመዝገባቸው BBC አስነብቧል።
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተካሄደው የትግራይ መራጮች ምዝገባ 2,740,888 ሰዎች መመዝገባቸውን የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜ እና እሑድ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የምርጫ ቅስቀሳው ደግሞ አርብ ይጠናቀቃል ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ካለፈው ሳምንት ጀምሮ በተካሄደው የትግራይ መራጮች ምዝገባ 2,740,888 ሰዎች መመዝገባቸውን የትግራይ ክልል የምርጫ ኮሚሽነር አቶ ሙሉወርቅ ኪዳነማርያም ገልጸዋል።
ባለፈው ሳምንት መመዝገብ ያልቻሉ ሰዎች ቅዳሜ እና እሑድ እንዲመዘገቡ የተደረገ ሲሆን፤ አሁን የመራጮች ምዝገባ መጠናቀቁን ኮሚሽነሩ ተናግረዋል።
የምርጫ ቅስቀሳው ደግሞ አርብ ይጠናቀቃል ተብሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ "አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗን ሰምተን ማብራሪያ ጠይቀናል ማብራሪያውን ለማግኘት ዛሬ ሰኞ በቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ አሳውቀዋል። አምባሳደር ፍፁም አረጋ ጉዳዩ በህዝቡ ጥሪት እየተገነባ ካለው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር እንደሚያያዝ ሰምተናል ሲሉ ገልፀዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
“አሜሪካ ለኢትዮጵያ ልትሰጥ የመደበችውን ገንዘብ (130 ሚሊዮን ዶላር) ያገደችው በጊዜያዊነት ነው”- አምባሳደር ፍጹም አረጋ (በይፋዊ የፌስቡክ ገፃቸው)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
“የወሲብ ጥቃት ከፈፀሙብኝ ሥድስት ሰዎች አምስቱ ሲያዙ አንዱ አምልጧል። የወሲብ ጥቃት ፈፃሚዎቹ ላይ ምንም ዓይነት ፍርድ አልተሰጠም” - በባህር ዳር ከተማ በሥድስት ወጣቶች የተደፈረችው የ17 ዓመቷ ታዳጊ
በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ በ2 ወር ብቻ ከ54 በላይ ታዳጊዎች የወሲብ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ጠቁሟል።
ምንጭ፦ ቪኦኤ (አስቴር ምስጋናው)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአማራ ክልል የኮሮና ቫይረስ ከተከሰተ ወዲህ በ2 ወር ብቻ ከ54 በላይ ታዳጊዎች የወሲብ ጥቃት እንደተፈፀመባቸው የክልሉ ሴቶች ጉዳይ ቢሮ ጠቁሟል።
ምንጭ፦ ቪኦኤ (አስቴር ምስጋናው)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...በህገ ወጥ መንገድ የተሰጠ ምንም አይነት ቤት የለም" - ኢ/ር ታከለ ኡማ (የቀድሞ የአ/አ ከተማ ምክትል ከንቲባ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!
የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ ምክትል ዋና ጸሀፊ የሆኑት አቶ ደጀኔ ጣፋ በሕገ መንግስት እና በሕገ መንግስታዊ ስርዓት ላይ በሚደረግ ወንጀል መከሰሳቸውን ኢትዮጵያ ኢንሳይደር ዘግቧል። አቶ ደጀኔ ክስ የቀረበባቸው ዛሬ ማክሰኞ ነሐሴ 26 ባስቻለው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ ወንጀል ችሎት ነው።
በሌላ መረጃ አቃቤ ህግ በእነ አቶ ጃዋር መዝገብ በሁሉም ተጠርጣሪዎች ላይ የሚመሰክሩ ቀሪ የቅድመ ምርመራ ምስክሮችን አቅርቦ ጭብጥ ማስመዝገቡን ፋና ዘግቧል።
በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ተረኛ ችሎት ተጠርጣሪዎቹ የቀረቡ ሲሆን፥ ከዚህ በፊት ፍርድ ቤቱ በ3ኛ፣ 13ኛ እና 14ኛ ተጠርጣሪዎች በድጋሜ የኮቪድ-19 ምርመራ እንዲደረግላቸው ያቀረቡትን አቤቱታ ተከትሎ የአ/አ እስረኞች አስተዳደር ተወካይ በባለፈው ቀርቦ አለማብራራቱን ተከትሎ ታስሮ እንዲቀርብ በሰጠው ትእዛዝ መሰረት ቀርቧል።
MORE : https://telegra.ph/FBC-09-01

ወ/ሮ አለምፀሐይ ጳውሎስ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ሆነው መሾማቸውን ከጤና ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።
በወይዘሮ አለምፀሐይ ሹመት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር ሊያ "ባለፉት በርካታ አመታት በጤናውና በማህበራዊ ዘርፉ ባካበቱት ከፍተኛ የአመራር ልምድ በቀጣይ የጤናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማሻሻል በጋራ እንደምንሰራና ለውጥ እንደምናመጣ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ" ብለዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በወይዘሮ አለምፀሐይ ሹመት የእንኳን ደስ አለዎት መልዕክት ያስተላለፉት ዶክተር ሊያ "ባለፉት በርካታ አመታት በጤናውና በማህበራዊ ዘርፉ ባካበቱት ከፍተኛ የአመራር ልምድ በቀጣይ የጤናውን ዘርፍ ይበልጥ ለማሻሻል በጋራ እንደምንሰራና ለውጥ እንደምናመጣ ባለሙሉ ተስፋ ነኝ" ብለዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ከእስር ተፈታ!
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ከእስር መፈታቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ማረጋገጥ ችሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (OMN) ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ከእስር መፈታቱን ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከቤተሰቦቹ ማረጋገጥ ችሏል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 26/2012 ዓ/ም
የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦
#Somali
በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 511 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 10 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።
#Oromia
በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 2,685 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 146 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 30 ከምስራቅ ሀረርጌ
- 20 ከፊንፊኔ ዙሪያ ልዩ ዞን
- 12 ከሞጆ
- 10 ከቢሾፍቱ
- 9 ከአዳማ
- 8 ከጅማ ዞን
- 8 ከጉጂ ዞን ይገኙበታል።
#BenishangulGumuz
በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 323 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።
#Amhara
በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,115 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 47 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል (ከደ/ብርሃን)
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 16 ከጎንደር ከተማ
- 9 ከደ/ወሎ ዞን
- 8 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 5 ከምዕ/ጎንደር ዞን ይገኙበታል።
#Harari
በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 540 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 40 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።
በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 13 ከሸንኮር ወረዳ
- 9 ከአባዲር ወረዳ
- 8 ከሶፊ ወረዳ ይገኙበታል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1,173 ሰዎች በኮቪድ-19 ሲያዙ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል!
ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 18,160 የላብራቶሪ ምርመራ 1,173 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ19 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 493 ሰዎች አገግመዋል።
በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 53,304 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 828 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 19,487 ደርሷል።