TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የእንግሊዝ ፖሊስ ድግሶችን እያስቆመ ነው!

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመቆጣጠር የእንግሊዝ ፖሊስ ፈቃድ ያላገኙ ድግሶችንና የሰዎች መሰባሰብን ለማስወገድ የወጣውን አዲስ ደንብ ተግባራዊ ማድረግ ጀምሯል።

በዚህ መሰረት እነዚህን ዝግጅቶች የሚያዘጋጁ ሰዎች እስከ 10 ሺህ ፓወንድ የሚደርስ የገንዘብ ቅጣት ያጠብቃቸዋል።

በተጨማሪም በእነዚህ ዝግጅቶች ላይ ታድመው የተገኙ ሰዎች ከ100 ፓወንድ ጀምሮ ቅጣት እንደሚጣልባቸው ታውቋል።

አስካሁንም ለእነዚህ ዝግጅቶች የሚያገለግሉ ከፍተኛ ገንዘብ የሚያወጡ ቁሳቁሶች በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋላቸውም ተነግሯል።

Via BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 24/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 783 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 53 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል፤

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 4,067 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 119 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 21 ከምዕራብ አርሲ
- 10 ከአሰላ ከተማ
- 10 ከቢሾፍቱ ከተማ
- 9 ከምዕራብ ሸዋ
- 8 ከጅማ ዞን
- 8 ከነቀምቴ ከተማ ይገኙበታል።

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 307 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 82 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 35 ከጉባ ወረዳ
- 15 ከምዥጓ/ከበሎ ጀጋንፎይ/ ወረዳ
- 9 ከማኦና ኮሞ ልዩ ወረዳ
- 9 ከባምቢስ ወረዳ
- 9 ከአሶሳ ወረዳ ይገኙበታል።

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 5,641 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 91 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የአንድ ሰው ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 33 ከሰ/ወሎ ዞን
- 24 ከምስ/ጎጃም ዞን
- 7 ከማዕ/ጎንደር ዞን
- 6 ከደሴ ከተማ
- 5 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 4 ከጎንደር ከተማ ይገኙበታል።

#DireDawa

ድሬዳዋ ከተማ ባለፉት 24 ሰዓት 164 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 17 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል። ሁሉም ከማህበረሰቡ ከተወሰደ ናሙና የተገኙ ናቸው።

#Afar

በአፋር ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 459 የላብራቶሪ ምርምራ የተደረገ ሲሆን 168 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ51 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 21,499 የላብራቶሪ ምርመራ 1,468 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ23 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 266 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 51,122 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 793 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 18,382 ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 24/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #2፦

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 427 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 59 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል።

አጠቃላይ በሀረሪ፦
- 1143 በቫይረሱ የተያዙ
- 20 ሞት
- 360 ያገገሙ

#Sidama

በሲዳማ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 716 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 16 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ፦
- 7 ከሀዋሳ ከተማ
- 6 ዳራ ወረዳ
- 3 ከወንዶ ገነት ወረዳ

አጠቃላይ በሲዳማ፦
- 1,408 በቫይረሱ የተያዙ
- 15 ሞት
- 633 ያገገሙ

#AddisAbaba

በአዲስ አበባ በ 24 ሰዓታት በተደረገው 5,230 የላብራቶሪ ምርመራዎች 692 ሰዎች ቫይረሱ የተገኘባቸው ሲሆን አጠቃላይ በከተማው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 30,392 ደርሷል፡፡

በሌላ በኩል በ24 ሰዓታት ውስጥ የ ሃያ አንድ (21) ሰዎች ሰዎች ህይወት አልፏል (13 ከአስከሬን ምርመራ 8 ከጤና ተቋም)

በቫይረሱ ከተያዙት 692 ሰዎች መካከል፦
- 139 ከቦሌ
- 91 ከኮልፌ ቀራኒዮ
- 81 ከየካ
- 73 ከቂርቆስ
- 67 ንፋስ ስልክ ላፍቶ
- 64 ከአቃቂ ቃሊት
- 63 ከጉለሌ ይገኙበታል።

@tikvahethiopiaBOT
የጋምቤላ ክልል ባለስልጣናትን ለመግደል የሞከሩ ተጠርጣሪዎች ተያዙ!

የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድርና ሌሎች የክልሉ ባለስልጣናት ሊገድሉ ሙከራ አድርገዋል የተባሉ ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ስር መዋላቸውን የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ አስታውቋል።

ተጠርጣሪዎቹ ባለሥልጣናቱን ሊገድሉ የሞከሩት በክልሉ አኙዋ ዞን ጆር ወረዳ ነሐሴ 22/2012 ዓ/ም በስብሰባ ላይ እያሉ መሆኑን የጋምቤላ ክልል ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነር ቱት ኮር ተናግረዋል።

ቱት ኮር እንዳሉት ከጋምቤላ እና ከጆር ወረዳ በአጠቃላይ 26 ተጠርጣሪዎች በቁጥጥር ሥር ውለዋል።

ከግድያው ሙከራ ጀርባ በአሜሪካ የሚኖሩ የክልሉ ተወላጆች እጅ እንዳለበት ምክትል የፖሊስ ኮሚሽነሩ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

PHOTO : ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኳታር አሚር የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን የሚደነግግ አዋጅ አጸደቁ!

የኳታር አሚር ሼክ ተሚም ቢን ሃማድ አልታኒ በዛሬው እለት የሰራተኞችን ዝቅተኛ የደመወዝ መጠንን የሚደነግግ አዋጅ አጸደቁ። ይህ አዋጅም አዋጅ ቁጥር 17/2020 በሚል ተደንግጓል።

በዚህም መሠረት የሰራተኞች ዝቅተኛው ወርሃዊ የደመወዝ መነሻ 1,000 የኳታር ሪያል ይሆናል።

መጠለያ እና ምግብ የማይቀርብ ከሆነ አሰሪው ለመጠለያ 500 የኳታር ሪያል፣ ለምግብ ደግሞ 300 የኳታር ሪያል ጨምሮ የሚከፍል ይሆናል።

ከዚህ በተጨማሪም ሰራተኞች ስራ መቀየር ሲፈልጉ ከስፖንሰራቸው No Objection Letter (NOC) መያዝ አይጠበቅባቸውም።

ህጉ ተግባራዊ መሆን የሚጀምረው አዋጁ በጋዜጣ ታትሞ ከወጣ ከስድስት ወራት በኋላ እንደሚሆን የኳታር አስተዳደር ልማት፣ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

አሚሩ ከዚህ ተጨማሪ ሁለት አዋጆችን ያጸደቁ ሲሆን፣ አዋጆቹም:-

1. የውጭ ዜጎች ወደ ኳታር የሚገቡበት፣ የሚወጡበት እና የሚኖሩበትን ሁኔታ የሚደነግገውን ነባር አዋጅ ቁጥር 21/2015 ያሻሻለ አዋጅ ቁጥር 19/2020 እና

2. በአዋጅ ቁጥር 14/2004 የተደነገገውን የሰራተኛ ህግ የተወሰኑ አንቀጾች ያሻሻለው አዋጅ ቁጥር 18/2020 ናቸው።

More : https://rb.gy/chx0ti

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤምባሲ-ዶሃ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
'ፎሬይን ፖሊሲ' የተሰኘው መፅሄት ትላንት ምሽት እንደዘገበው የአሜሪካው ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማይክ ፖምፔዎ ሀገሪቱ ለኢትዮጵያ የምታደርገውን ድጋፍ በከፊል እንድታቆም ፍቃዳቸውን ሰጥተዋል ብሏል። ይህም የትራምፕ አስተዳደር ኢትዮጵያ ፣ ግብፅ እና ሱዳንን በህዳሴ ግድብ ዙርያ ለማወያየት የጀመረው እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ተቃውሞ ገጥሞት መቆሙን ተከትሎ የመጣ ነው ብሏል። ፖምፔዎ ፍቃዳቸውን ያኖሩበት ይህ…
በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ፍፁም አረጋ "አሜሪካ ለኢትዮጵያ የመደበችው 130 ሚሊዮን የአሜሪካን ዶላር እንዳይሰጥ መወሰኗን ሰምተን ማብራሪያ ጠይቀናል ማብራሪያውን ለማግኘት ዛሬ ሰኞ በቀጠሮ ይዘናል" ሲሉ አሳውቀዋል።

አምባሳደር ፍፁም አረጋ ጉዳዩ በህዝቡ ጥሪት እየተገነባ ካለው ከታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ድርድር ጋር እንደሚያያዝ ሰምተናል ሲሉ ገልፀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
165 ዜጎቻችን ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለሱ ተደረገ!

በሊባኖስ በአሰሪዎች በደልና የመብት ጥሰቶች ፣ የአካልና የስነ-ልቦና ጉዳት የደረሰባቸው እንዲሁም መጠለያና ምግብ ያጡ የነበሩ 165 ዜጎቻችንን ትላንት ማታ ወደ ሀገራችን እንዲመለሱ ተደርጓል።

ይህ የሆነው በሊባኖስ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጄኔራል ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ኮሙኒቲ ማህበር በትብብር በመስራት፤ እንዲሁም ሌሎች ድጋፍ የሚያደርጉ በጎ አድራጎት ድርጅቶችንና ግለሰቦችን በማስተባበር እንደሆነ ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ችሎት!

አቶ ልደቱ አያሌው ላይ ፖሊስ ሲያካሂድ የቆየውን ምርመራ ማጠናቀቁን ገልፆ አቃቤ ህግ ክስ እስከሚመሰርት ድረስ 14 ቀን ተጨማሪ ጊዜ ይሰጠኝ ሲል የጠየቀ ቢሆንም የፖሊስ ጥያቄ የህግ አግባብነት የለውም ሲል የቢሾፍቱ ከተማ ወረዳ ፍርድ ቤት ውድቅ አደረገ።

በዛሬው ችሎት የቢሾፍቱ ወረደ ፍርድ ቤት የፖሊስ የምርመራ መዝገብ መዘጋቱን ገልፆ አቶ ልደቱ አያሌው በሌላ መዝገብ የዋስትና ጥያቄያቸውን እንዲያቀርቡ አዟል።

Via Tarik Adugna (FBC)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከእስራኤል ወደ ተባበሩት አረብ ኤምሬቶች ለመጀመሪያ ጊዜ የንግድ በረራ ሊካሄድ መሆኑን BBC አስነብቧል።

ይካሄዳል የተባለው የንግድ በረራ በሁለቱ መካከል ያለው ግንኙነት ጤናማ እየሆነ ስለመምጣቱ ጠቋሚ ነው ተብሏል።

የእስራኤሉ ኤል አል አየር መንገድ የእስራኤል ልዑካንን እንዲሁም የአሜሪካ ባለሥልጣኖችን ይዞ የሦሰት ሰዓት በረራ ያካሂዳል።

አውሮፕላኑ በሳዑዲ አረቢያ አየር ክልል እንዲበር ይፈቀድለታል ተብሎ ይጠበቃል። ከዚህ ቀደም የእስራኤል አውሮፕላን በአየር ክልሉ ማለፍ አይችልም ነበር።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኦሮሚያ ትምህርት ቢሮ በ2013 የትምህርት ዘመን የገዳ ስረዓትን በስረዓተ ትምህርቱ ውስጥ በማካተት ለማስተማር ዝግጅት ማድረጉን አስታውቋል።

የቢሮው ኃላፊ ዶ/ር ቶላ በሪሶ እንዳሉት ቢሯቸዉ የገዳ ስረዓትን በክልሉ በሚገኙ አንደኛ ደረጃ ትምሕርት ቤቶች (1-8) ከአዲሱ የኢትዮጵያውያን አመት ጀምሮ ያስተምራል።

ቢሮዉ ትምህርቱን በሁሉም ትምሕርት ቤቶች ለመስጠት ቢያቅድም ከትምህርት ቁሳቁስ ዝግጅት እና አቅርቦት አንጻር በአንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመጀመር መወሰኑን ገልጸዋል።

አዲሱ ትውልድ የገዳ ስረዓት መማሩ የሚያጋጥሙትን ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ችግሮችን ለመቅረፍ ያስችለዋል ማለታቸውን የክልሉ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ቢሮን ዋቢ አድርጎ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ዘግቧል።

በሌላ በኩል የገዳ ስርዓት ትምህርት በአዲስ አበባ ከተማ ለመስጠት ዝግጅት መጠናቀቁን የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ሀላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግረዋል።

ሀላፊው እንደተናገሩት የገዳ ሥርዓት ስርዓተ ትምህርቱ ተጠናቆ የመፅሐፍ ዝግጅት ላይ ተደርሷል፡፡

የመፅሐፍ ዝግጀቱም በ2 እና 3 ሳምንታት ያልቃል በአዲሱ የትምህርት ዘመን የገዳ ሥርዓት እንደ አንድ የትምህርት ዓይነት መሰጠት ይጀምራል ብለዋል፡፡

ትምህርቱን የሚሰጠው በአዲስ አበባ የአፋን ኦሮሞ ትምህርት በሚሰጥባቸው 7 ትምህርት ቤቶች ናቸው ሲሉም ለሬድዮ ጣቢያው ተናግረዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአዲስ_አበባ_ከተማ_የመሬት_ወረራ_እና_የጋራ_መኖሪያ_ቤቶች_ኢፍትሃዊ_ዕደላን_አስመልክቶ_የተደረገ_ጥናት.pdf
278.1 KB
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) በአዲስ አበባ መሬት ወረራ እና የጋራ መኖሪያ ቤቶች ኢፍትሃዊ ዕደላ ላያ ያደረገው ጥናት ውጤት ዛሬ ይፋ አድርጓል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሙስጠፋ አዲብ የሊባኖስ ጠ/ሚ ሆነው ተሾሙ!

በጀርመን ሀገር የሊባኖስ አምባሳደር ሆነው በማገልገል ላይ የነበሩት ሙስጠፋ አዲብ የሊባኖስ ጠቅላይ ሚኒስትር ሆነው ተሾመዋል፡፡

አዲብ 128 አባላት ካሉት የሃገሪቱ ፓርላማ የ90ውን ድጋፍ በማግኘት ነው የተሾሙት፡፡

የሊባኖስ ፕሬዝዳንት ሚሼል አውን አዲሱ ተሿሚ መንግስት እንዲያዋቅሩ ስለመጠየቃቸውም ዘ ናሽናልን ዋቢ አድርጎ አል አዓይን /AlAin/ ነው የዘገበው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ነሃሴ 25/2012 ዓ/ም

የኢትዮጵያ የኮቪድ-19 መረጃዎች #1፦

#Somali

በሱማሌ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 599 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮቪድ-19 መያቸው ተረጋግጧል።

#Oromia

በኦሮሚያ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 3,343 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን 127 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። የሁለት ሰዎች ህይወት አልፏል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል ፦
- 28 ከአርሲ ዞን
- 25 ከጉጂ ዞን
- 14 ከቡራዩ ከተማ
- 13 ከቢሾፍቱ ከተማ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በኦሮሚያ፦
- 6,301 በቫይረሱ የተያዙ
- 45 ሞት
- 1,953 ያገገሙ

#BenishangulGumuz

በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ 161 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ የተያዙት ፦
- 21 ከደምቤ (አጋሎ) ወረዳ
- 1 ከሆምሻ ወረዳ

አጠቃላይ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ፦
- 651 በቫይረሱ የተያዙ
- 303 ያገገሙ

#Amhara

በአማራ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 4,894 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 75 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።

በቫይረሱ ከተያዙት መካከል፦
- 15 ከሰ/ሸዋ ዞን
- 12 ከደ/ጎንደር ዞን
- 10 ከሰ/ወሎ ዞን
- 9 ከዋግ ብ/ሰብ ዞን
- 7 ከባህር ዳር ከተማ
- 6 ከደሴ ከተማ ይገኙበታል።

አጠቃላይ በአማራ፦
- 2,412 በቫይረሱ የተያዙ
- 22 ሞት
- 1,261 ያገገሙ

#Harari

በሀረሪ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 440 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ 4 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።

አጠቃላይ በሀረሪ፦
- 1147 በቫይረሱ የተያዙ
- 21 ሞት
- 376 ያገገሙ

@tikvahethiopiaBot