TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.7K photos
1.49K videos
211 files
4.06K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ዛሬ ጥዋት የONLF ሊቀመንበር አብድራህማን ማሃዲ ፣ የሱማሌ ክልል ፕሬዘዳንት ሙስጠፌ ሙሃመድ ፣ የሱማሌ ብልፅግና ፓርቲ (PP) እና የONLF ከፍተኛ አመራሮች ውይይት አድርገዋል ፤ በውይይታቸው የሱማሌ ክልልን ሰላም ፣ መረጋጋት እና መልካም አስተዳደር #ለማጠናከር መስማማታቸው ተሰምቷል - #ONLF

@tikvahethiopiaOfficial
2 ልጆቿን በኮቪድ-19 ያጣችው እናት!

ፍሎሪዳ ውስጥ ነዋሪ የሆነችው ' ሞንቴ ሂክስ ' የምትባል እናት በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የሁለት (2) ልጆቿን ህይወት አጥታለች።

የመጀመሪያው የ20 ዓመት ልጇ ሲሆን እሱ ህይወቱ ካለፈ ከ11 ቀን በኃላ ደግሞ የ22 ዓመት ሴት ልጇን በዚህ አስከፊ በሽታ ተነጥቃለች።

እስካሁን ድረስ እጅግ መሪር በሆነ ሀዘን ውስጥ የምትገኘው ሞንቴ ሂክስ ከ NBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ ' ሰዎች እራሳቸውን እንዲጠብቁ ፣ ወረርሽኙን እንደቀልድ እንዳያዩት ' መክራለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ችሎት!

የኦሮሞ ፌደራሊስት ኮንግረስ [ኦፌኮ] አመራር አቶ ደጀኔ ጣፋ እና አቶ ኮርሳ ደቻሳ በኮሮና በሽታ ተይዘው በሆስፒታል ህክምና ላይ በመሆናቸው ፤ ዛሬ በነበራቸው የፍርድ ቤት ቀጠሮ ላይ ሳይገኙ መቅረታቸውን ጠበቆቻቸው ገለጹ።

ፖሊስ አቶ ደጀኔን ጨምሮ በተመሳሳይ መዝገብ የተካቱቱ ሶስት ተጠርጣሪዎችን ፤ የድምጻዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያን ተከትሎ በአዲስ አበባ ፣ ቡራዮ እና በተለያዩ የኦሮሚያ አካባቢዎች በተቀሰቀሰው ሁከት ፤ 'ተሳትፎ አላቸው' በሚል እንደጠረጠራቸው ለፍርድ ቤት አስታውቋል።

የሶስቱን ተጠርጣሪዎች የጊዜ ቀጠሮ ጉዳይ እየተመለከተ የሚገኘው የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት፤ የ8 ቀናት ተጨማሪ የምርመራ ጊዜ ለፖሊስ መፍቀዱን ጠበቃቸው ተናግረዋል። ከተጠርጣሪዎቹ መካከል በዛሬው ችሎት የቀረቡት አቶ ሚሻ አደም ብቻ ናቸው።

ምንጭ፦ ኢትዮጵያ ኢንሳይደር (Ethiopia Insider)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ችሎት!

የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ ፓርቲ (ኢዜማ) የብሔራዊ ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ አባል እና የሙያ ማኅበራት ተጠሪ ሂሩት ክፍሌ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20 ቀን 2012 ዓ·ም ፍርድ ቤት ቀርበው ነበር።

ፖሊስ ተጨማሪ ምርመራዎች ለማድረግ 14 ቀን ጊዜ ቀጠሮ የጠየቀ ሲሆን፤ የሂሩት ክፍሌ ጠበቃ ፖሊስ ከዚህ ቀደም ምርመራ እንዲያደርግ በተሰጠው 10 ቀን በቂ ምርመራ ሳያደርግ ተጨማሪ ጊዜ መጠየቁ አግባብ ባለመሆኑ ፍርድ ቤቱ የጊዜ ቀጠሮ መዝገቡን ዘግቶ የደንበኛቸውን የዋስትና መብት እንዲያስከብር ጠይቀው ነበር።

ፍርድ ቤቱ ክርክሩን አዳምጦ መዝገቡን ለመመርመር ተጨማሪ ጊዜ ወስዶ ካየ በኋላ ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ እንዲያቀርብ ተጨማሪ 8 ቀን ፈቅዷል።

በሌላ መረጃ የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ (OMN) ባልደረባ የነበሩት አቶ ሸምሰዲን ጣሃ ዛሬ ሰኞ ሐምሌ 20/2012 የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ ችሎት ቀርበው እንደነበር ጠበቃቸው ተናግረዋል። ፖሊስ ተጨማሪ 8 የምርመራ ቀናት ተፈቅዶለታል።

ምንጭ፦ Ethiopia Insider/ኢዜማ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#Qatar

በኳታር ከነገ ጀምሮ 80 ከመቶ የሚሆኑ የመንግስትም ሆኑ የግል ተቋማት ሰራተኞች ወደ ስራ ገበታቸው ይመለሳሉ። ስብሰባዎች መደረግ የሚችሉት ግን ቢበዛ በአስር (10) ሰዎች ብቻ እንደሆነ ተገልጿል።

የኳታር መንግስት ጥሏቸው የቆዩ እገዳዎችን ቀስ በቀስ ለማንሳት ባስቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሶስተኛ ደረጃ (Third Phase) ማሻሻያዎች ከነገ ጀምሮ ተግባራዊ መሆን ይጀምራሉ።

በኳታር የምትኖሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ አባላት ከነገ ጀምሮ የተደረጉ ማሻሻያዎችንና መደረግ ያለባቸውን ጥንቃቄዎች ከላይ ባለው ምስል (በዶሃ - የኢትዮጵያ ኤምባሲ የተዘጋጀ) መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ14 ሺህ አለፉ!

ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 7,009 የላብራቶሪ ምርመራ 579 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሲረጋገጥ የ5 ሰዎች ህይወት አልፏል። በተጨማሪ በትላንትናው ዕለት 170 ሰዎች አገግመዋል።

በአጠቃላይ በሀገራችን በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 14,547 የደረሱ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 228 ደርሷል ፤ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 6,386 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የትግራይ ክልል ምርጫ!

የትግራይ ምርጫ ኮሚሽን ጽህፈት ቤት በመጪው ነሐሴ ወር መጨረሻ ላይ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ ላይ ለመሳተፍ ለሚፈልጉ ፓርቲዎች ጥሪ አቅርቧል።

በዚህም መሰረት ኮሚሽኑ ነሐሴ መጨረሻ ላይ በሚካሄደው ምርጫ ላይ ለመወዳደር የሚፈልጉ በሙሉ ቀርበው እንዲመዘገቡ ይፋዊ ጥሪ አቅርቧል።

በምርጫው ላይ ለመሳተፍ የሚፈልጉ የፖለቲካ ድርጅቶችና የግል ተወዳዳሪዎች ከማክሰኞ (ሐምሌ 21/2012) እስከ ሐሙስ (ሐምሌ 23/2012) ባሉት 3 ቀናት ሊመዘገቡ እንደሚችሉ የኮሚሽኑ ኮሚሽነር መምህር ሙሉወርቅ ኪዳነ ማርያም #ለBBC ገልጸዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
አቶ ዳውድ ኢብሳ ከኃላፊነታቸው ተነስተዋል ?

የኦሮሞ ነጻነት ግንባር (ኦነግ) ያለ ግንባሩ ሊቀመንበር ያካሄደው ስብሰባ ዛሬ መጠናቀቁን አስታውቋል።

ስብሰባው ከሳምንት በፊት በድርጅቱ ማዕከላዊ ኮሚቴ የአባላቱ መታሰር እና የግንባሩ የወደ ፊት ስራዎች ላይ ለመምከር የተጠራ መሆኑን የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ተናግረዋል።

አቶ ቀጀላ የኦነግ ሊ/መንበር አቶ ዳውድ ኢብሳ ከ10 ቀናት አንስቶ በመንግስት የፀጥታ አካላት ሲጠበቁ ስለነበር አስቀድሞም እንደማይሳተፉ የተገመተ በመሆኑ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን ገልጸዋል።

ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ 'ከእውነት የራቀ' ሲሉ አስተባብለዋል።

አቶ ቀጄላ አሁን የአመራር ለውጥ ለማድረግ ፓርቲው ምንም እቅድ እንደሌለውም ገልጸዋል።

አቶ ዳውድ ያሉበትን ሁኔታ ማየት አልቻልንም ያሉት የግንባሩ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ስልካቸውም ከባለፈው አርብ ጀምሮ መዘጋቱን ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ አረጋግጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ችሎት!

የፌደራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በአቶ በቀለ ገርባ ላይ ተጨማሪ ስምንት (8) ቀናት የምርመራ ጊዜ ፈቅዷል። ዛሬ ስለነበረው አጠቃላይ የችሎት ውሎ በዚህ ማስፈንጠሪያ ማግኘት ትችላላሁ : https://telegra.ph/BekeleGerba-07-27

በሌላ መረጃ ደግሞ አቶ በቀለ ገርባ ለሶስት ቀናት የረሃብ አድማ አድረገው እንደነበር ተሰምቷል። ለዚህም ምክንያቱ በሚጠይቋቸው ሰዎች ላይ የተጣለው ገደብ እንደሆነ ነው የታወቀው።

አቶ በቀለ ገርባን መጠየቅ የሚችሉት 3 ሰዎች ብቻ ሲሆኑ ፣ እነሱም ባለቤታቸውና ሁለት ልጆቻቸው ብቻ እንዲሆን በመደረጉ "ከልጆቼ መርጬ እንዲጠይቁኝ አላደርግም፤ ልጆቼ እኔን ማግኘት አለባቸው፤ እኔም ልጆቼን ማግኘት አለብኝ" ማለታቸውን ባለቤታቸውን ወ/ሮ ሃና ረጋሳ ለBBC ተናግረዋል።

በተጨማሪ መረጃ የአቶ በቀለ ገርባን ጨምሮ የመላው ቤተሰቡ የባንክ አካውንት መታገዱን ባለቤታቸው ወ/ሮ ሃና ገልፀዋል።

አካውንቱ ለምን እንደተዘጋ እንደማያውቁ የተናገሩት ወ/ሮ ሃና 'አቶ በቀለ የመንግሥት ሠራተኛ ነው ፤ ነጋዴም አይደለም። በአካውንታችን ላይ የተለየ ገንዘብ የለም ፤ እኔም ብሆን ሠራተኛ አይደለሁም' በማለት ለእለት መተዳዳሪያ ያስቀመጧትን ገንዘብ ሊያወጡ በሄዱበት የእርሳቸው እና የባለቤታቸው አካውንት መታገዱ እንደተነገራቸው ለBBC አስረድተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሰራዋ መኪና!

ዛሬ የኢፌዴሪ ጠ/ሚ ዶክተር ዐቢይ አህመድ 'በኤሌክትሪክ ኃይል' የምትሠራ መኪና በማራቶን ሞተርስ ሙሉ በሙሉ #በኢትዮጵያ የተገጣጠመች በስጦታነት እንደተበረከተላቸው ይታወቃል።

ይህች በኤሌክትሪክ ኃይል የምትሰራው መኪና በአንድ ጊዜ ሙሉ ቻርጅ 300 ኪሎ ሜትር (ከአዲስ አበባ - ሀዋሳ) ድረስ መጓዝ እንደምትችል ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር አብይ ሲናገሩ ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በደቡብ ክልል!

ባለፉት 24 ሰዓት የተመዘገበውን 11 ኬዝ ጨምሮ በደ/ብ/ብ/ህ/ክ/ መንግስት በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች 101 ደርሰዋል።

ባለፉት 24 ሰዓት ከተመዘገቡት ኬዞች ከወላይታ ዞን 6 እና ስልጤ ዞን 5 ሰዎች መሆናቸውን ከክልሉ ጤና ቢሮ ያገኘነው መረጃ ይጠቁማል።

ውድ የTIKVAH-ETHIOPIA አባላት በሌሎችም የሀገራችን ክልሎች ያለውን የወረርሽኙን ሁኔታ በተመሳሳይ አሰባስበን የምናስቀምጥላችሁ ይሆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
#OLF

ትላንት የኦነግ የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ቀጄላ መርዳሳ እሁድ የተደረገው ስብሰባ አቶ ዳውድ ሊገኙ የማይችሉበት ሁኔታ ስለተፈጠረ ስብሰባው በምክትል ሊቀመንበሩ መካሄዱን መናገራቸው አይዘነጋም።

ስብሰባው የተካሄደው ሊቀመንበሩን ከኃላፊነታቸው ለማንሳት ነው በሚል በማህበራዊ ሚዲያ የተሰራጨውን መረጃ 'ከእውነት የራቀ' ሲሉ ማስተባበላቸውም ይታወቃል።

በተመሳሳይ አቶ አራርሶ ቢቂላ እሁድ በኦነግ ጽሕፈት ቤት የተካሄደው ስብሰባ የሊቀ መንበሩ አቶ ዳውድ ኢብሳ እውቅና የነበረው መሆኑን በመናገር አሁንም የድርጅቱ ሊቀ መንበር አቶ ዳውድ መሆናቸውን ገልጸዋል።

አቶ አራርሶ የስብሰባው ዋና አጀንዳ የነበረው “ሕዝቡ ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ ይገኛል? ድርጅታችንስ ምን ድረጃ ላይ ነው? በተለይ ደግሞ ወደ አገር ከገባን በኋላ ምን አገኝን፣ ምን አጣን? የሚለውን ነበር ሲሉ ተናግረዋል።

በተቃራኒው የኦሮሞ ነጻነት ግንባር ቢሮ ኃላፊ የሆኑት ዶክተር ገዳ ኦልጅራ እሁድ በአቶ አራርሶ ቢቂላ የተመራው ሰብሰባ የድርጅቱ እውቅና የለውም፤ በግንባሩ ሊቀ መንበርም የማይታወቅ መሆኑን ተናግረዋል።

አቶ አራርሶ ቢቂላ ፤ ከአቶ ዳውድ ስብሰባ ለማካሄድ ፍቃድ እንደተሰጣቸው ተናግረው ስብሰባ ሲጠሩ ፤ ዶ/ር ገዳ ወደ አቶ ዳውድ እንደደወሉና ፤ አቶ ዳውድ ስለ ስብሰባው መረጃ እንዳልደረሳቸው እንደገለጹላቸው ተናግረዋል።

ያለ ድርጅቱ ሊቀ መንበር እውቅና ስብሰባ ማካሄድ ተገቢ አይደለም ብለው ለስብሰባ የሄዱ ሰዎችን እንደከለከሉ ገልጸው ፤ ' ሲከለከሉም የታጠቁ የመንግሥት አካላትን ይዘው መጥተው ፣ በጉልበት ገብተው ነው ስብሰባቸውን ያካሄዱት። ስብሰባው ሕጋዊ አልነበረም' ብለዋል ዶ/ር ገዳ https://telegra.ph/OLF-07-28 (BBC,DW)

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
ከኮቪድ-19 ያገገሙ ሰዎች ከ10 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) መያዛቸው ከተረጋገጠ 16,659,395 ሰዎች መካከል 10,253,211 ሰዎች ከበሽታው ማገገማቸው ታውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
'One Voice for Our Dam'

ዓለም አቀፍ ድምፅ ለግድባችን!

#ለግድባችን ያለንን ድጋፍ እሁድ ሐምሌ 26 / 2012 ከቀኑ 10:00 ሰዓት ሁላችንም በአንድ ላይ ባማረና በደመቀ ሁኔታ በያለንበት ሆነን በዓለም አቀፍ ደረጃ ድምፃችንን እናሰማለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዓረና በትግራይ በሚደረገው ምርጫ አልሳተፍም አለ!

ዓረና ትግራይ ለዴሞክራሲና ሉዓላዊነት (ዓረና) ሓምለ 17 ባወጣው መግለጫ ነፃ ፣ ፍትሓዊና ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ ምርጫ አልሳተፍም ሲል አስታውቋል።

ፓርቲዊው በዚህ ምርጫ ላለመሳተፍ የወሰንኩበት አንዱ ምክንያት ህወሓት ሕገ-መንግስቱን በግላጭ የሚፃረር የምርጫ አካሄድ በመምረጡ ነው ብሏል።

በተጨማሪ ህወሓት አካሂደዋለሁ በሚለው ሕገ-ወጥ ምርጫ ከተቋቋመ 12 ዓመታትን ያስቆጠረውና በትግራይ ፖለቲካ ተፅዕኖ ያለውን ዓረናን አግልሎ ራሱ የመረጣቸው ፓርቲዎች አቅፎ ለመሄድ በመወሰኑ ነው ሲል ገልጿል።

ዓረና ባወጣው መግለጫው የመፍትሄ ሃሳቦች ናቸው ያለውን ያቀረበ ሲሆን ከመፍትሄዎቹ የመጀመሪያው ነጥብ ህወሃት እየሄደበት ያለው የምርጫ እንቅስቃሴ ኢ-ሕገ መንግስታዊና ኢ-ሕጋዊ በመሆኑ ይህን ውሳኔውን በማጤን ሊቀለብሰው እንደሚገባና በዚህ ምትክም ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በመሆን እና በተናጠል ከፌዴራሉ መንግስት ጋር የምር ድርድር እንዲያካሂድ የሚጠይቅ ነው።

ፓርቲው 'ነፃ ፣ ፍትሓዊ እና ሕገ-መንግስታዊ ባልሆነ ምርጫ አልሳተፍም' በሚል ያወጣውን መግለጫ ሙሉ ሃሳብ በ : https://telegra.ph/TigrayElection-07-25 ገብታችሁ ማንበብ ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በትግራይ ክልል ምርጫ እንሳተፋለን ያሉ ፓርቲዎች!

በትግራይ ክልላዊ ምርጫ ላይ እንደሚሳተፉ እስካሁን ድረስ ካሳወቁ የፖለቲካ ድርጅቶች መካከል የክልሉ ገዢ ፓርቲ ህወሓት ፣ ሳልሳይ ወያኔ ትግራይ ፣ ባይቶና ትግራይና ውድብ ናፅነት ትግራይ ይገኙበታል።

ከዚህ በተቃራኒ ዓረና ትግራይ እና የትግራይ ዲሞክራሲያዊ ፓርቲ በክልሉ ሊካሄድ በታቀደው ምርጫ የተለያዩ ጥያቄዎችን በማንሳት በሂደቱ ላለመሳተፍ መወሰናቸውን ከቢቢሲ ያገኘነው መረጃ ያሳያል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ክትባት!

' ሞደርና ' የተባለው የባዮቴክኖሎጂ ኩባንያ አንድ አዲስ የኮሮናቫይረስ ክትባት መድሃኒት በ30,000 ጎልማሶች ላይ ሙከራ መጀመሩን አስታውቋል።

ከብሄራዊ የአለርጂ እና የተላላፊ በሽታዎች ተቋም ጋር በመተባበር ሙከራው ትላንት የተጀመረው በሳቫና ጆርጂያ መሆኑን ኩባንያው አስታውቋል። ሳቫና በሀገቱ ዙሪያ ካሉት፣ በርካታ የሙከራ ቦታዎች፣ አንዱ ነው ተብሏል።

ክትባቱ እንዲሞከርባቸው ከቀረቡት ስዎች ግማሾቹ እውነተኛው ክትባት እንደሚሰጣቸው የተቀሩት ግን የውሸት ክትባት እንደሚከተቡ አሶሼተድ ፕሬስ የዜና አገልግሎት ዘግቧል።

ሞደርና እስካሁን ባለው ጊዜ ባደረጋቸው የክትባቱ መድሃኒት ሙከራዎች ጠንካራ የመከላከል ምላሽ ማሳየቱን በያዝነው ወር ቀደም ሲል አስታውቋል።

ድካምን ፣ ራስ ምታት ፣ የብርድ-ብርድ የማለት እንዲሁም የሰውነት መቀጥቀጥን የመሳሰሉት ቀለል ያሉ የጎንዮሽ ስሜቶች ማስከተሉ #ከቪኦኤ የተገኘው መረጃ ይገልፃል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ 'ከፋና ትግርኛ' ጋር በነበራቸው ቆይታ የተናገሩት ፦

የፌደራል መንግስት የትግራይ ክልልን መንግስትን ወይም የትግራይ ክልል ህዝብን ሊያጠቃ ይችላል ብሎ ማሰብ በራሱ እብደት ነው።

እኔ ይህ ምን ማለት እንደሆነ አይገባኝም ፤ ካሰቡት አካላት ይልቅ ይሄንን እንደ ቁምነገር አንስተው የሚያወሩት ናቸው እኔም የሚያስገርሙኝ።

ከትግራይ ክልል ብቻ ሳይሆን ከኤርትራ ፣ ከሱዳንም ሆነ ከሱማሊያ ጋር ምንም አይነት ግጭት አንፈልግም። በሰላም ልማትን ማምጣት ብቻ ነው የምንፈልገው እያልን የፌደራል መንግስት የትግራይን ህዝብ ሊያጠቃነው ማለት ምን ማለት ነው ?

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaOfficial
የህወሓት እና ፌደራል መንግስት አለመግባባት!

ዶ/ር አብይ አህመድ 'ከፋና ትግርኛ' ጋር በነበራቸው ቆይታ በፌደራል መንግስት እና በትግራይ ክልል መካከል ስላለው አለመግባባት/የአቋም ልዩነት ተከታዩን ብለዋል ፦

በእኔ በኩል ያለው አለመግባባት መፈታት አለበት ብዬ ነው የማምነው፤ መፈታትም አለበት። ከዚህ በኃላ ችግሩን ፈተን በተሻለ የልማትና የዴሞክራሲ መንገድ መቀጠል አለብን ብዬ ነው የማምነው።

በቶሎ መግባባት ላይ እንዲደረስ የትግራይ ህዝብ በአመራር ቦታ ላይ ላሉ እንደነ ዶ/ር ደብረፅዮን የመሰሉ ልማትና ሰላም ፈላጊ የሆኑ አመራሮችን መደገፍ አለበት።

እነዶክተር ደብረፅዮን ከመጀመሪያው ጀምሮ ቢሆን ከፌደራል መንግስት ጋር ቁጭ ብለው በእኛም ሆነ በነሱ በኩል ባሉ ችግሮች ዙሪያ ለመወያየት ዝግጁ ናቸው ፤ ለዚህ የትግራይ ህዝብም ድጋፍ ሊያደርግ ይገባል ብዬ አምናለሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia