TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
208 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 9‚147 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በተደረገ 7‚407 የላብራቶሪ ምርመራ 344 ሠዎች የኮሮናቫይረስ እንደተገኘባቸው እና የ13 ሠዎች ሕይወት ማለፉን የጤና ሚኒስቴር አስታውቋል፡፡

በቫይረሱ ሕይወታቸውን ካጡት መካከል አራቱ የሕክምና ክትትል ሲያደርጉ የቆዩ ሲሆኑ ቀሪዎቹ ዘጠኙ በአስከሬን ምርመራ የተለዩ መሆናቸው ተጠቅሷል፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሠዎች ቁጥር 9,147 የደረሰ ሲሆን በአጠቃላይ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ቁጥር ደግሞ 163 ደርሷል፡፡

በትላንትናው ዕለት ሰማንያ ስድስት (86) ሰዎች ከበሽታው በማገገማቸው በአጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 4,900 መድረሱ የኢፌዴሪ ጤና ሚኒስቴር በዕለታዊ መግለጫው ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከፍተኛ ጥንቃቄ!

#SHARE #ሼር

በኢትዮጵያ የምትኖሩ የቲክቫህ አባላት ፣ ይህን መልዕክት የኢንተርኔት አገልግሎት አግኝታችሁ ማንበብ የቻላችሁ በሙሉ የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በከፍተኛ ደረጃ በሀገሪቱ እየተሰራጨ በመሆኑ ጥንቃቄ አድርጉ።

ኢትዮጵያ የመመርመር አቅሟን እያሣደገች መጥቱን ተከትሎ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር ከመቼውም ጊዜ በላይ ጨምሯል።

በሀገሪቱ በሁለት ቀናት #ብቻ (ሀምሌ 9/2012 እና ሀምሌ 10/2012) 672 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው በምርመራ ተረጋግጧል።

በኢትዮጵያ የሟቾች ቁጥርም እየጨመረ መጥቷል በትላንት እንዲሁም በዛሬ ሪፖርት መሰረት 15 ሰዎች ከቫይረሱ ጋር በተገናኘ ህይወታቸውን አጥተዋል።

ይህንን መልዕክት በስልካችሁ ያገኛቹ ወገኖቻችን እራሳችሁ እና ቤተሰባችሁን በሙሉ ከዚህ አስፈሪ ወረርሽኝ ሳትዘናጉ እንድትጠብቁ ጥሪ እናቀርባለን ፤ ኢንተርኔት ማግኘት ላልቻሉ ወዳጆቻችሁ በSMSና በመደወል አሳሳቢውን ሁኔታ አሳውቋቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ ጉዮን ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት ሄደዋል" - የጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ ቤተሰብ አባል

አርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ከመገደሉ ከአንድ (1) ሳምንት በፊት በOMN ቃለመጠይቅ ያደረገለት ጋዜጠኛ ጉዮ ዋሪዮ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ውሏል።

ከጋዜጠኛው ቤተሰብ አባላት አንዱ ለBBC እንደተናገሩት ዛሬ እኩለ ቀን ላይ "የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ አባላት ዩኒፎርም የለበሱ" ጉዮን ከመኖሪያ ቤቱ ይዘውት ሄደዋል፤ የጸጥታ አባላቱ ጉዮን ወደየት ይዘውት እንደሚሄዱ ለመናገር ፍቃደኛ አልነበሩም ሲል ገልጿል።

ከፀጥታ አባላቱ መካከል አምስቱ (5) የኦሮሚያ ልዩ ፖሊስ የደንብ ልብስን የለበሱ ሲሆን አንዱ (1) ደግሞ መደበኛ ልብስ መልበሳቸውን የቤተሰቡ አባል ተናግረዋል።

አክለውም ከሃጫሉ ግድያ እና የOMN ቢሮ መዘጋት በኋላ ከመኖሪያ ቤታቸው ወጥተው ራቅ ያለ ስፍራ ተሸሽገው እንደነበር ተናግረው ፖሊሶቹ ያሉበትን ፈልገው እንዳገኟቸው ገልጿል።

እኚሁ የጋዜጠኛ ጉዮ ቤተሰብ አባል ለBBC እንደገለፁት "የጸጥታ ኃይሎቹ በመሳሪያ ስላስፈራሯቸው" ተከትለውት መሄድ አልቻሉም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
የፌደራል ፍርድ ቤቶች ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡ ነው!

የፌደራል ፍርድ ቤቶች ከሐምሌ 13/2012 ዓ/ም እስከ ሐምሌ 30 ቀን 2012 ዓ.ም ድረስ ኮቪድ-19ን እየተከላከሉ ሙሉ አገልግሎት ሊሰጡ መሆኑ ኢቢሲ ዘግቧል።

ከመጪው ሰኞ ሐምሌ 13 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ዳኞች በመደበኛ የስራ ሰዓት ቢሮ ገብተው አንገብጋቢ የሆኑ ጉዳዮችን በመለየት ክስ መስማት ፤ ምርመራቸው በተገባደደ ጉዳዮች ላይ ውሳኔ መስጠት እና የመሳሰሉ ስራዎችን ያከናውናሉ ተብሏል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ14 ሚሊዮን አለፉ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 14,061,849 ደርሰዋል፤ ከነዚህ መካከል 595,029 ህይወታቸው ያለፈ ሲሆን 8,360,841 ሰዎች አገግመዋል።

በዓለም ከፍተኛ ሰዎች በቫይረሱ የተያዘባቸው ሦስት ሀገራት አሜሪካ (ከ 3.7 ሚሊዮን በላይ) ፣ ብራዚል (ከ 2 ሚሊዮን በላይ) ፣ እንዲሁም ህንድ (ከ 1 ሚሊዮን በላይ) ናቸው።

ከዚህ ባለፈ ከፍተኛ የሰዎች ሞት የተመዘገበባቸው 3 ሀገራት አሜሪካ (141,479) ፣ ብራዚል (76,997) እንዲሁም UK (45,223) ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮቪድ-19 ወረርሽኝ በእስራኤል!

በእስራኤል ከዛሬ ጀምሮ እስከ ሳምንቱ መጨረሻ የመገበያ ግዙፍ መደብሮች ፤ ክፍት የገበያ ቦታዎች ፤ የፀጉር ማስተካከያ ቤቶች፤ የመጽሐፍ መደብሮች እና ሙዚየሞች ዝግ እንዲሆኑ መደረጉ ተሰማ።

በሚቀጥለዉ ሳምንት በሃገሪቱ የመዝናኛ የባህር ዳርቻዎች ዝግ ሆነዉ እንደሚቆዩም የፈረንሳይ የዜና አገልግሎትን ጠቅሶ ዶቼ ቨለ ዘግቧል።

በእስራኤል በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የሚያዘዉ ሰዉ ቁጥር በየቀኑ እየጨመረ መሆኑ የሃገሪቱን መንግሥት ስጋት ላይ እንደጣለው ተገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአቶ በቀለ ገርባ ልጆች ከእስር ተፈተዋል!

ከድምፃዊ ሃጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ጋር በተያያዘ በተነሳው ግርግር በቁጥጥር ስር ከዋሉ ሰዎች መካከል የአቶ በቀለ ገርባ ልጅ ቦንቱ በቀለ፣ ወንድሟ እና የእክስቷ ልጅ ትላንት ከእስር መፈታታቸውን ቢቢሲ በሬድዮ ስርጭቱ ዘግቧል።

ቦንቱ በቀለ ዛሬ ከቢቢሲ የሬድዮ ስርጭት ጋር በነበራት ቆይታ ተከታዩን ብላለች ፦

"ያለ ጥፋታችን ነው የታሰርነው ፣ የተንገላተነው። እኔ እና ወንድሞቼ ከአባቴ ጋር ስለነበርን ነው እንጂ ምንም የሰራነው ወንጀል የለም። አባታችን ፖለቲከኛ ነው፣ ለሰብዓዊ መብት የሚታገል፣ ለዴሞክራሲ የሚታገል፣ ለብሄር ብሄረሰቦች እኩልነት የሚታገል ሰላማዊ ታጋይ ነው።

ከዚህ በፊትም እስር ቤት ነበር አሁንም እስር ቤት ነው በእግዚያብሔር ፍቃድ አንድ ቀን ይወጣል ፤ ሰላማዊ ትግልን ይቀጥላል።

እኛም እንደ ቤተሰብ እሱን ከመደገፍ ወደኃላ አንልም። አባቴ የተቃዋሚ አመራር ስለሆነ እኔ ወይም ወንድሞቼ ለእደዚህ አይነት እንግልት በመዳረጋችን በጣም ነው የምናዝነው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች ከ670 ሺህ አለፉ!

በአፍሪካ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 670,741 ደርሰዋል ከነዚህ መካከል 14,492 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 348,236 ሰዎች አገግመዋል።

ከፍተኛ የሰዎች ቁጥር በቫይረሱ የተያዘባቸው ሦስት ሀገራት ደቡብ አፍሪካ (324,221)፣ ግብፅ (85,771) እንዲሁም ናይጄሪያ (34,854) ናቸው።

እንደ #worldometers መረጃ ሀገራችን ኢትዮጵያ በአፍሪካ ደረጃ ባላት የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር አስራ ሁለተኛ (12) ላይ ትገኛለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሀላፊነት የጎደላቸው የአዲስ አበባ መጠጥ ቤቶች!

(በጋዜጠኛ ጥላሁን በየነ)

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) በሽታ በሀገራችን በከፍተኛ ሁኔታ ስርጭቱ ጨመሯል የሟቾችም ቁጥር ከዕለት ወደዕለት ቁጥሩ እያሻቀበ ይገኛል።

በርካቶች በኮቪድ-19ኝን ለመከላከል የሚወስዱት ጥንቃቄ በእጅጉን አናሳ ሲሆን በተለይ ከቅርብ ጊዜ በኾላ በአዲስ አበባ የሚገኙ የመዝናኛ ስፍራዎች ፍፁም ሀላፊነት በጎደለው መልኩ የመጠጥ ሽያጭን እያከናወኑ ይገኛሉ።

ይባስ ተብሎም አንዳንድ ቤቶች በአንድ ጠረጴዛ ላይ በርከት በማለት ይጠጣል ፣ ይበላል ፣ ይደንሳል፣ ተሰክሮም ይጨፍራል።

ይህ ሁሉ ሲሆን የፀጥታ ሀይሎች ምንም አይነት እርምጃ ሲወስዱ አይታይም።

ጭራሽ 20/80 የሚባል የመጠጥ ቤቶች ሀሜት ይወራል 20%ቱ በአከባቢው ለሚገኙ የፀጥታ አስከባሪዎች ጉርሻ መሆኑ ነው።

ስለዚህ በሽታው በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ እየገደለ ስለሆነ ሁላችንም የሀላፊነት ስሜት ካልተሰማን ኮቪድ-19 ከፍተኛ ዋጋ ያስከፍለናል።

ጉዳዩ ይመለከተናል ፣ የህዝብ ደህንነትና ጤና ያሳስበናል የሚሉ አካላት ሁሉ ከወዲሁ ጥብቅ የሆነ ቁጥጥር እና እርምጃ ሊወስዱ ይገባል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሟቾች ቁጥር ከ600 ሺህ አለፈ!

በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ (COVID-19) መያዛቸው ከተረጋገጠው 14,214,771 ሰዎች መካከል 600,0037 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#GERD

የደቡብ አፍሪካው ፕሬዝደንት ሳይሪል ራማፎዛ የኢትዮጵያ ፣ ግብፅና ሱዳን መሪዎችን በመጪው ማክሰኞ በድጋሜ ለማገናኘት ቀጠሮ መያዛቸውን ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት በዛሬው ዕለት ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝና ረሃብ...

የተባበሩት መንግሥት ድርጅት የዓለም የምግብ ፕሮግራም ትላንት ባወጣው ዘገባ በኮሮና ቫይረስ መዛመት ምክንያት በቀጣዮቹ ወራት ቢያንስ ሃያ አምስት (25) ሃገሮች አስከፊ ረሃብ እንደሚያጋጥማቸው ገልጿል።

ድርጅቱ ከሦስት ወራት በፊት ታይቶ የማይታወቅ ዓይነት ረሃብ ሊከሰት ይችላል ሲል ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የፀጥታ ምክር ቤት አሳውቆ እንዳነበር የምግብ ፕሮግራሙ ዋና ሥራ አስኪያጅ ዴቪድ በስሊ ጠቁመዋል።

በሚልዮኖች የሚቆጠሩ በድኅነት የሚኖሩ ቤተሰቦች ለአስከፊ ሁኔታ ተዳርገዋል ብለዋል። የሚከሰቱትን ችግሮች ለመርዳት የዓለም የምግብ ፕሮግራም $4.9 ቢልዮን ዶላር አንደሚያስፈልገው አስገንዝቧል።

እጅግ ተጋላጭ በሆኑት ሃገሮች ረሃብ እንዳይገባ ለመከላከል $500 ሚልዮን ዶላር እንደሚያስፋልገው ድርጅቱ አስታውቋል።

ለረሃብ የተጋለጡት ሃገሮች በአፍሪካ ፣ በእስያ ፣ በካሪባያን ፣ በላቲን አሜሪካና በመካከለኛው ምሥራቅ እንደሚገኙ የዓለም ምግብ ፕሮግራም አስገንዝቧል #VOA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ በአንድ ቀን 688 ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

በጎረቤታችን ኬንያ በ24 ሰዓት በተደረገው 4,522 የላብራቶሪ ምርመራ 688 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው መረጋገጡን የሀገሪቱ ጤና ሚኒስቴር እየሰጠ በሚገኘው መግለጫ ላይ ተገልጿል።

በአጠቃላይ በኬንያ በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 12,750 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል 4,440 ሰዎች አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ጦርነት ባደቀቃት የመን!

የእርስ በእርስ ጦርነት ባደቀቃት የመን ውስጥ ምን ያህል ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ምክንያት እንደሞቱ በትክክል አይታወቅም።

ከሪሊፍ ዌብ ባገኘነው መረጃ እስካሁን 1,520 ሰዎች ላይ ቫይረሱ እንደተገኘ ማረጋገጥ የተቻለ ሲሆን ከነዚህ ውስጥ 430 ሰዎች ሞተዋል።

ሀገሪቱ በጦርነት ምክንያት የጤና ስርዓቷ ክፉኛ ተጎድቷል፣ የጤና ባለሙያዎች ራሳቸውን ከቫይረሱ የሚከላከሉበት ቁሳቁስ ባለመኖሩ ምክንያት ስራቸውን እየለቀቁ ነው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛይራይድ!

'ዛይራይድ' 50አዳዲስ እና ዘመናዊ ታክሲዎችን ለቀድሞ ሰማያዊ በነጭ አሽከርካሪዎች እና ሴቶች ከትላንት በስቲያ ማስረከቡን አሳውቆናል። በሚቀጥለው ዙር 100 ታክሲዎችን በአንድ ወር ግዜ ውስጥ ለማስረከብ እቅድ እንደተያዘ ገልጾልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢንተርኔት መቋረጥና የትራንስፖርት አገልግሎት...

በአ/አ ከተማ ውስጥ ኢንተርኔትን መሰረት ያደረገ የትራንስፖት አገልግሎት የሚሰጡ ሁለት ኩባንያዎች (ራይድ እና ፈረስ) እና በስራቸው የሚንቀሳቀሱ አገልግሎት ሰጪዎች በ15 ቀናት የኢንተርኔት መቋረጥ ከ400 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ማጣታቸውን ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ሬድዮ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 9,503 ደረሱ!

ባለፉት 24 ሰዓታት በተደረገ 6,886 የላብራቶሪ ምርመራ 356 ሠዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፤ እንዲሁም የ4 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

በቫይረሱ የተያዙት ሠዎች 255 ከአዲስ አበባ ከተማ ፣ 48 ከትግራይ ፣ 14 ከኦሮሚያ፣ 11 ከሶማሌ ፣ 11 ከድሬደዋ ከተማ ፣ 5 ከሀረሪ ፣ 5 ከአማራ፣ 4 ከሲዳማ ፣ 2 ከደቡብ እንዲሁም 1 ከአፋር ክልል ናቸው፡፡

በአጠቃላይ በኢትዮጵያ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) የተያዙ ሰዎች 9 ሺህ 503 የደረሱ ሲሆን ከነዚህ መካከል 167 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል ፤ 4,941 ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#SHARE #ሼር

በኢትዮጵያ ውስጥ በፀጥታ እና የደህንነት ችግር ምክንያት ከአዲስ አበባ ከተማ ውጭ (WiFi እና ብሮድባንድ) በሌሎች የኢትዮጵያ ክልል ከተሞች ኢንተርኔት ባለመኖሩ ብዙዎች በሀገሪቱ ስላለው የኮቪድ-19 ወረርሽኝ አሁን ያለበት ሁኔታ እንደቀደመው እየሰሙ አይደለም።

ዜጎች በየዕለቱ የወረርሽኙን ደረጃ መከታተል መቀነስ በእጅጉ መዘናጋትን የሚፈጥርና ይበልጥ ወረርሽኙን የሚያባብሰው ስለሆነ ይህን ፅሁፍ የምታነቡ በሙሉ ለወዳጅ ዘመዶቻችሁ እራሳቸውን ሳይዘናጉ ከወረርሽኙ እንዲጠብቁ መልዕክት አስተላልፉ።

የምትችሉ ከሆነ ደግሞ ዕለታዊ የኮቪድ-19 መረጃዎችንና ሪፖርቶችን እየተከታተላችሁ በ SMS እና በመደወል አሰሟቸው። ሁላችሁም እራሳችሁን ከአስከፊው ወረርሽኝ ጠብቁ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፖሊስ ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን አስታወቀ!

የአዲስ አበባ ከተማን ደህንነትና ጸጥታ ለመጠበቅ በህጋዊ መንገድ ማህበረሰቡን የማደራጀትና የመኝታ አገልግሎት የሚሰጡ ሆቴል ፣ ፔንሲዮንና መሰል ቤቶችን ድንገተኛ ፍተሻ እያደረገ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ፖሊስ ኮሚሽን ማስታወቁን ኢፕድ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአንድ ቀን ከ259 ሺህ በላይ ሰዎች በኮቪድ-19 ተያዙ!

የዓለም ጤና ድርጅት (WHO) ባለፉት 24 ሰዓታት በመላው ዓለም ከ259,000 በላይ ሰዎች በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው አሳወቀ።

ድርጅቱ ወረርሽኙ ከጀመረበት ጊዜ አንስቶ በአንድ ቀን ውስጥ የተመዘገበ ከፍተኛው በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር መሆኑን ነው የገለጸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia