TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
16 የኮቪድ-19 ታማሚዎች እየተፈለጉ ነው!

በሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል አስራ ስድስት (16) ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል፡፡

የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አውላቸዉ ታደሰ ለአብመድ እንደተናገሩት በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡

አስተባባሪ እንዳሉት ከ79 ተመርማሪዎች 36 አሽርካሪዎች ሲሆኑ ከእነዚህ መካከል 16 የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡

በቫይረሱ ከተያዙ ግለሰቦች መካከል አንደኛው በሞጃና ወደራ ወረዳ በአስከሬን ምርመራ የተገኘ ነው።

ከሳምንት በፊት በእንሳሮ ወረዳ በቫይረሱ ተይዞ ሕይወቱ ካለፈ ሰው የቀብር ሥነ ሥርዓቱ ላይ የተገኙና ከግለሰቡ ጋር የቀጥታ ንክኪ ከነበራቸዉ 45 ሰዎች መካል አራቱ በቫይረሱ መያዛቸው መረጋገጡንም መምሪያው አስታውቋል፡፡

አንድ ግለሰብ ደግሞ ከጣርማበር ወረዳ ደብረሲና ከተማ ቫይረሱ ተገኝቶበታል፤ ግለሰቡ #በአስተናጋጅነት ሥራ ላይ የተሰማራ እንደሆነም አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡

እንሳሮ ወረዳ ላይ የተገኘባቸዉ አራት ግለሰቦች ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ሕክምና መስጫ እንዲገቡ እየተደረገ መሆኑም ታውቋል፡፡

ኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸዉ ሃያ ሁለት (22) ሰዎች መካከል 16ቱ አሽከርካሪዎች 'የት እንዳሉ እንደማይታወቅና' እየተፈለጉ እንደሚገኙ አስተባባሪው ተናግረዋል፡፡ ከግለሰቦቹ ጋር የቀጥታ ንክኪ ያላቸዉ የኅብረተሰብ ክፍሎችን የማግኘቱ ሥራ እንደተጀመረም ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ የአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ከአ/አ ወደ ወላይታ ዞን የገባው የኮቪድ-19 ታማሚ! ባለፉት 24 ሰዓት ዉስጥ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ በሽታ (COVID-19) ላቦራቶሪ ምርመራ ተደርጎ የኮሮና ቫይረስ በሽታ እንዳለበት የተረጋገጠበት አንድ ዕድሜው 20 የሆነ ግለሰብ ትክክለኛ ባለሆነ መንገድ ተደብቆ ህብረተሰቡን ለአደጋ ሊያጋልጥ በሚችል መልኩ ቤተሰቦቹ ወደሚገኙበት ወላይታ ዞን ገብቷል። ግለሰቡ ወደ ወላይታ ዞን ከገባ በኋላ በህብረተሰቡ…
#ATTENTION

በትላትናው ዕለት የደቡብ ክልል ጤና ቢሮ አንድ ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ዞን ስለገባ የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ታማሚ መግለጫ መስጠቱ ይታወቃል።

ዛሬ ከዞኑ ጤና መምሪያ በወጣው መረጃ መሰረት ግለሰቡ ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ ዞን በህዝብ ትራንስፖርት (አይሩፍ/አባዱላ መኪና) ቅዳሜ ሰኔ 6/2012 ዓ/ም እንደገባ ተገልጿል።

በዕለቱ በእነዚህ መኪና ከአዲስ አበባ ወደ ወላይታ የገቡ ግለሰቦች እና አሽከርካሪዎች ለራሳቸውና ለቤተሰባቸው ብሎም ለህብረተሰቡ ሲሉ በአቅራቢያ ወዳሉ ጤና ተቋማት/ዞን ጤና መምሪያ ሪፖርት እንዲያደርጉ #ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።

በዕለቱ ተጠርጣሪውን ጭኖ የመጣውን መኪናና አብረውት የመጡ ሰዎችን ለማግኘት የዞን እና የከተማ ፀጥታ አካለት እየሠሩ እንደሆነ የተገለፀ ሲሆን ህብረተሰቡ አስፈላጊዉን ትብብር እንዲያደርግ የዞኑ ጤና መምሪያ ጥሪ አቀርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያና ጎረቤት ሀገራት ያገገሙ ሰዎች 8,409 ደረሱ!

በኢትዮጵያ ፣ ኬንያ ፣ ሱማሊያ፣ ጅቡቲ፣ ሱዳን ፣ ደቡብ ሱዳን እና ኤርትራ በአጠቃላይ 23,400 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል።

ከኤርትራ ውጭ በስድስቱ (6) ሀገራት የ781 ሰዎች ህይወት አልፏል ፤ በአጠቃላይ 8,409 ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው አገግመዋል።

በኢትዮጵያና በጎረቤት ሀገራት ያለውን የኮቪድ-19 ወቅታዊ መረጃ ከ CARD ጋር በመተባበር ባዘጋጀነው ምስል ከላይ መመልከት ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
እኔም የእርቅ ሀሳብ አለኝ!

'እኔም የእርቅ ሀሳብ አለኝ' 1,167 የቲክቫህ አባላት በግል ለመወዳደር የተመዘገቡ ሲሆን 96ቱ በቡድን የተመዘገቡ ናቸው።

ከምዝገባ በኃላ ከ900 የሚበልጡ ተወዳዳሪዎች 15 ቀን በተሰጣቸው የዝግጅት ጊዜያት ውስጥ የሚሰጡ መመሪያዎችን ሲከታተሉና ያልገባቸውን ሲጠይቁ ቆይተዋል።

አሁን ላይ የዝግጅት ጊዜው አብቅቶ እስካሁን ድረስ ሦስት መቶ (300) የሚጠጉ ተሳታፊዎች ከትግራይ ፣ ከአማራ ፣ ከኦሮሚያ ፣ ከደቡብ ፣ ከሐረሪ ፣ ከአዲስ አበባ ፣ ከድሬዳዋ፣ ከቤኒሻንጉል ጉሙዝ፣ ከአፋር የመወዳደሪያ ፅሁፋቸውን አስገብተዋል፡፡

በቀጣይ ተሳታፊዎቹ የላኩት ዶክመንት በአግባቡ ተሰብስቦ ከተቀናጀ በኃላ ሥራዎቹን እንዲገመግሙ ለተመረጡ ዳኞች ይቀርባል፡፡

ቀጣዩን ሂደት እናሳውቃለን!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ህይወት እያለፈ ነው!

(ዶክተር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሙያ)

ከሬድዮ አንድ ዜና ሰማሁ፤ 'አንድ የሀገራችን ከተማ ላይ፥መንገድ ላይ ተዘርግቶ ከሚሸጡ ሸቀቶች መሀል 5 የሚሆኑ የፊት ጭምብሎች እያነሳ በመለካት ላይ የነበረ ግለሰብ ከሻጩ ጋር በዋጋ ባለመስማማት ሊሄድ ሲል የፀጥታ አስከባሪ የሆነ አንተ አንስተህ የለካኸውን ማን እንዲገዛ ነው በማለት አምስቱንም አስገዝቶታል።'

በመዲናችን ጭምር መንገዶች ላይ ፌስታል ተዘርግቶ እና በየትራፊክ መብራቶች ላይ በፊት የተለያዩ ሸቀጦች ይሸጡ የነበሩ ግለሰቦች አሁን የአፍ እና አፍንጫ ጭምብሎች እየሸጡ ነው። ይህ ፈፅሞ መሆን የለበትም!

ይህ ዜና በጣም አስፈሪ ሆነብኝ፤ ምን ያህል ሰው ለክቷቸው ይሆን? እንደኚህ አይነት የምናደርጋቸው ቀላል በማይባሉ መዘናጋቶች ከ3 ሺህ 500 በላይ አድርሶናል፣ብዙዎች እያለፉ እንደሚገኙም ልብ ልንል ይገባል፡፡

በአንፃሩ ህዝብን የሚያገለግሉ የጤና ባለሙያዎችም በቂ ባልሆነ የግል መጠበቂያ መሳሪያዎች(PPE) ማነስ በቫይረሱ እየተያዙ፣ በየማቆያውም ተገቢ አያያዝ እና ክትትል እያጡ እንደሆነ፣ አልፎም ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል።

ደከመኝ፣ ሰለቸኝ ሳይሉ እያገለገሉ ያሉ ብሎም መስዋዕት እየሆኑ ያሉትን እነኚህን ጀግኖች የሚመለከተው ባለድርሻ አካል ሙሉ በሙሉ ማገዝ አለበት። ባለሙያዎችም እራሳቸውን ለመጠበቅ ለኮቪድ-19 የወጡ መመሪያዎችን በከፍተኛ ስርዓተ-ምሪት መተግበር አለባቸው።

በክልል ከተሞችም ጭምር የተቀዛቀዘው ግንዛቤ የማስጨበጥ እና የጥንቃቄ ስራ ካልጠነከረ የመዲናችን ሁኔታ የነሱም እጣፈንታ ስለሚሆን በፅናት መታገል ይኖርባቸዋል።

የከፋ ዋጋ ላለመክፈል ሁሉም የየራሱን ሀላፊነት ይወጣ፤ እንዲሁም የሚወዷቸውን ላጡ መፅናናትን እንመኛለን!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ጥራት ጉዳይ...

የአፍና የአፍንጫ መሸፍኛ ጭንብሎች ጥራት መረጋገጥ እንዳለበት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አሳስቧል።

የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርዱ ይህን ያሳሰበው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን አስመልክቶ በቅርቡ የኢትዮጵያን ምግብና መድኃኒት ባለስልጣን መስሪያ ቤትን የስራ እንቅስቃሴ በአካል በተመለከተበት ወቅት ነው።

በምልከታውም ወቅት ከውጭ የሚገቡና በአገር ውስጥ የሚመረቱ የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭንብሎች ጥራትን፣ በአገሪቱ የመድሃኒት አቅርቦትና ስርጭት ተደራሽነትን እና የኮሮና በሽታን አስመልክቶ የሚፈጸም የኮንትሮባንድ ንግድን የተመለከቱ ጥያቄዎች በመርማሪ ቦርዱ አባላት ተነስተው ምላሽ ተሰጥቶባቸዋል https://telegra.ph/E-06-16

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኒው ዚላንድ!

በሽታውን በቁጥጥር ሥር ማዋሏን በተናገረችው ኒው ዚላንድ ሁለት (2) ሰዎች ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸዋል። ሁለቱም ከዩኬ ወደ ኒው ዚላንድ የገቡ መሆናቸውም ተገልጿል።

በ30ዎቹ እና በ40ዎቹ እድሜ ክልል የሚገኙት ሴቶች ወደ ኒው ዚላንድ እንዲገቡ የተፈቀደው በሞት አፋፍ ላይ የነበረ ወላጃቸውን ለማየት ጥያቄ ስላቀረቡ ነው ተብሏል።

ግለሰቦቹ ሰኔ 7/2020 ኒው ዚላንድ እንደገቡ ወደ ለይቶ ማቆያ ተወስደዋል። የአገሪቱ የጤና ሚንስትር ዋና ኃላፊ ዶ/ር አሽሊ ብሉሚፊልድ እንዳሉት፤ አንደኛዋ ሰው መጠነኛ ምልክት ታሳይ ነበር https://telegra.ph/BBC-06-16-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኤርትራ በኮቪድ-19 የተያዙ ሰዎች 109 ደረሱ!

በኣዲባራ ለይቶ ማቆያ ውስጥ ከሚገኙ ከውጭ ተመላሾች መካከል 13 ሰዎች /ከሱዳን የተመለሱ/ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው መረጋገጡን የኤርትራ ጤና ሚኒስቴር ትላንት አሳውቋል።

በአጠቃላይ በሀገሪቱበኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 109 የደረሰ ሲሆን ከነዚህ መካከል ሰላሳ ዘጠኝ (39) ሰዎች ከበሽታው አገግመዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
16 የኮቪድ-19 ታማሚዎች እየተፈለጉ ነው! በሰሜን ሸዋ ዞን የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው 22 ሰዎች መካከል አስራ ስድስት (16) ሰዎች እየተፈለጉ መሆኑን መምሪያው አስታውቋል፡፡ የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ የኅብረተሰብ ጤና አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ኬዝ ቲም አስተባባሪ አቶ አውላቸዉ ታደሰ ለአብመድ እንደተናገሩት በ79 ሰዎች ላይ ምርመራ ተደርጎ 22 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል፡፡ አስተባባሪ…
#UPDATE

የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለባቸው ተረጋግጦ ሲፈለጉ ከነበሩት አሽከርካሪዎች መካከል 15 መገኘታቸውን የሰሜን ሸዋ ዞን ጤና መምሪያ አስታውቋል፡፡

ኮቪድ-19 ተገኝቶባቸው ወደ ለይቶ ማከሚያ ያልገቡትን አሽከርካሪዎች እና ንክኪ ያላቸውን ሰዎች የማፈላለጉ ሥራ መቀጠሉን ጤና መምሪያው አስታውቋል፡፡

ከተገኙት 15 አሽከርካሪዎች ውስጥ አስራ ሁለቱ (12) ወደ ደብረ ብርሃን ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እና ሦስቱ ደግሞ አዲስ አበባ ወደ ሚገኝ ለይቶ ማከሚያ ማዕከል እንዲገቡ ተደርገዋል፡፡

አንድ (1) የኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) እንዳለበት የተረጋገጠ አሽከርካሪ ተንቀሳቃሽ ስልኩ ጥሪ ባለመቀበሉ እስካሁን እንዳልተገኘ እና ፍለጋው መቀጠሉንም ጤና መምሪያው አስታውቋል - #AMMA

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ የፀሃይ ግርዶሽ ይከሰታል! በኢትዮጵያ በመጪው ሰኔ ወር አጋማሽ ቀለበታዊ የፀሃይ ግርዶሽ እንደሚከሰት የኢትዮጵያ ስፔስ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት አስታውቋል። ግርዶሹ ከምዕራብ እስከ ሰሜን ምስራቅ ኢትዮጵያ የሚታይ ሲሆን ክስተቱም ወለጋ፣ ከፊል ጎጃምና ጎንደር፣ በወሎ በተለይ ላሊበላ አካባቢ ቀኑ #የሚጨልም ይሆናል ተብሏል። በተቀረው የአገሪቱ ክፍል ደግሞ በዕለቱ…
የፀሐይ ግርዶሽ እና ጥንቃቄ!

የፀሐይ ግርዶሽን በዓይን በቀጥታ መመልከት ቋሚ ጉዳት በዓይን ላይ ያደርሳል። ግርዶሹን ለመመልከት ፦

1. ደረጃውን የጠበቀ የግርዶሽ መነፅር መጠቀም

2. ፒን ሆል ካሜራ ወይም በአነስተኛ ቀዳዳ ወደ ድፍን ካርቶን የሚገባውን ብርሃን የሚስለውን ስእል ጀርባ ለፀሐይ በማዞር መመልከት

3. ጨለማ ክፍል ውስጥ በቀዳዳ የሚገባውን የፀሐይ ብርሃን መሬት ወይም ግድግዳ ላይ የሚሰራውን ስእል መመልከት

4. በዛፎች ቅጠል አልፎ መሬት ላይ የሚያርፈውን የፀሐይ ስእል መመልከት

5. ለቴሌስኮፕም ሆነ ባይነኩላር የፀሐይ ብርሃን መጣኝ ደረጃውን የጠበቀ ፊልተር ግጥሞ መመልከት

6. ግርዶሹን የሚያሳዩ የቀጥታ ስርጭቶችን መመልከት

የፀሐይ መነፅር ፣ ፍሎፒ ዲስክ ፣ የፎቶ ፊልም ፣የራጅ ፊልም እና የመሳሰሉት ቁሶች መጠቀም በዓይን ላይ ጉዳት ያደርሳል - #ESSS

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከኮቪድ-19 ያገገሙ 87 ሰዎች ከሚሊኒየም ማገገሚያ ማዕከል ወጡ!

'በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሊኒየም ሜዲካል ኮሌጅ' ስር በሚገኘው የሚሌኒየም ማገገሚያ ማዕከል ውስጥ ከኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ያገገሙ 87 ሰዎች ከማዕከሉ መውጣታቸውን ኢዜአ ዘግቧል።

የማዕከሉ ክሊኒካል ዳይሬክተር የሆኑት ዶክተር ውለታው ጫኔ እንደገለጹት ፤ በአሁኑ ወቅት በማዕከሉ ውስጥ 656 ኮሮና ቫይረስ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛሉ።

ከነዚህ ውስጥ 157 ሰዎች የመጀመሪያ የላቦራቶሪ ምርመራ ውጤታቸው ከኮሮና ቫይረስ ማገገማቸውን (ኔጋቲቭ) ያሳየ መሆኑን ገልጸው ፤ 87 ሰዎች ዛሬ ከማዕከሉ እንዲወጡ መደረጉን አመልክተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።" - ዶክተር ሊያ ታደሰ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 109 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል!

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 5,102 የላብራቶሪ ምርመራ 109 ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል፡፡ በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 3,630 ደርሷል።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 60 ወንድ እና 49 ሴት ሲሆኑ የዕድሜ ክልላቸው ከ1 እስከ 78 ዓመት ውስጥ ይገኛል። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ናቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 81 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 9 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 4 ሰዎች ከሱማሌ ክልል፣ 4 ሰዎች ከደቡብ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአማራ ክልል፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል እና 2 ሰዎች ከሐረሪ ክልል ናቸው።

ከጠቅላላው የላብራቶሪ ምርመራ ውስጥ 20 (5 ከጤና ተቋም እና 15 ከማህበረሰብ በተወሰደ ናሙና) ናሙናዎች በአስክሬን ላይ የተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን የ45 ዓመት ኢትዮጵያዊ የአዲስ አበባ ነዋሪ ሴት ከማህበረሰቡ በተወሰደ ናሙና የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባታል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ የተገኘባቸውና ህይወታቸው የለፈ ሰዎች ቁጥር ስልሳ አንድ (61) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ በአንድ ቀን 118 ሰዎች አገገሙ!

በትላንትናው ዕለት አንድ መቶ አስራ ስምንት (118) ሰዎች (115 ከአዲስ አበባ ፣ 3 ከትግራይ ክልል) ያገገሙ ሲሆን በአጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው (ኮቪድ-19) ያገገሙ ሰዎች ቁጥር ሰባት መቶ ሰላሳ ስምንት (738) ደርሷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SOMALI

ባለፉት 24 ሰዓት በሱማሌ ክልል 101 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 4 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው 3 ሰዎች የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸውና በጅግጅጋ ዩኒቨርሲቲ ለይቶ ማቆያ የሚገኙ ናቸው። 1 ሰው ከደገሃቡር የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር የታወቀ ግንኙነት የሌለው ነው።

#SNNPRS

በደቡብ ክልል ባለፉት 24 ሰዓት 434 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል 4 ሰዎች ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ የሌላቸው ሲሆኑ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ንክኪ አላቸው።

ቫይረሱ የተገኘባቸው የ25 ዓመት (ወ) ይርጋለም ወረዳ ነዋሪ፣የ15 ዓመት (ወ) በንሳ ወረዳ ነዋሪ፣የ25 ዓመት (ወ) በንሳ ወረዳ ነዋሪ የመጨረሻው የ25 ዓመት (ወ) ሀዋሳ ከተማ ነዋሪ ናቸው።

#AFAR

በአፋር ክልል በኮቪድ-19 መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር 52 ደርሷል።ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተካሄደው የላብራቶሪ ምርመራ 68 ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

#TIGRAY

ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተደረገው 393 የላብራቶሪ ምርመራ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 3 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።

ሁሉም የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው ናቸው። በአጠቃላይ በትግራይ ክልል በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 156 የደረሱ ሲሆን 15 ሰዎች አገግመዋል።

#HARARI

ባለፉት 24 ሰዓት በሐረሪ ክልል 92 የላብራቶሪ ምርመራ የተደረገ ሲሆን ከነዚህ መካከል ነው 2 ሰዎዥ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው። ሁለቱም በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ የ35 ዓመት ወንድ (የጂኔላ ወረዳ)ና የ27 ዓመት ወንድ(የአወዳይ ከተማ) ነዋሪዎች ናቸው።

#tikvah