TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
206 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ከአክሱም...

"ሰላም ባንተ ላይ ይሁን ፀጋአብ ወልዴ እኔ የአክሱም ነዋሪ ነኝ አክሱም ላይ መስጂድ እንደሌለ የምታውቅ ይመስለኛል። እኛ የአክሱም ሙስሊሞች ለዚህች ሀገር አባቶቻችን ተጋድለዋል ነገር ግን እስካሁን ዴሞክራሲያዊ መብታችን ሊከበር አልቻለም። ስለዚህ ነገር ብትፅፍ መልካም ይመሰለኛል። እኛ የአክሱን ሙስሊሞች ፍትህ እንፈልጋለን! ሬድ ከአክሱም።"

@tsegabwolde @tikvahethiopia
የአዳማ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች በግቢው ውስጥ ላሉት ዘርፈ ብዙ ችግሮች የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር መፍትሄ እንዲሰጥ ጠይቀዋል። የውይይት መድረክም እንዲመቻች ይፈልጋሉ።

"...ተማሪው ተስፋ እየቆረጠ ለሱሰኝነት እየተዳረገ ነው።"
@tsegabwolde @tikvahethiopia
የእርዳታ ጥሪ ለወንድም አቤነዘር ተሾመ!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ጎንደር! አቶ መላኩ ፈንታ የ2 ሚሊዮን ብር መኪና ተበረከተለት። አቶ መላኩ ገንደር ሲገባ የጎንደር ከተማ ከንቲባን ጨምሮ የተለያዩ የመንግስት ሹማምንት ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! በጃዋር መሀመድ የሚመራው OMN በአዲስ አበባ ቅርጫፍ ቢሮ ለመክፈት በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከመንግስት ጋር ለመነጋገር ወደ አዲስ አበባ ምክትል ዳይሬክተሩን እንደላከ ተሰማ።

የኦሮሚያ ሚዲያ ኔትወርክ የማኔጅመንት አባልና የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር የሆኑት ሞሐመድ አብዶሽ በመንገድ ላይ ነን ብለዋል፡፡

ላለፉት አራት አመታት መቀመጫውን አሜሪካ ሴንት ፖል ሚኔሶታ ላርፐንተር ጎዳና ላይ በማድረግ በሳተላይት የቴሌቪዥ ስርጭቱን እያከሄደ የሚገኘውና በጃዋር መሃመድ የሚመራው Oromia Media Network ኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ (ኦኤምኤን) በኢትዮጵያ ውስጥ ቅርንጫፍ መክፈት በሚቻልበት መንገድ ለመነጋገር ልዑካኑን ወደ አዲስ አበባ ልኳል።

የቴሌቪዥን ተቋሙ የማኔጅመንት አባልና የኦፕሬሽን ምክትል ዳይሬክተር በሆኑት አቶ ሞሃመድ አብዶሽ መሪነትና ሌላ አንድ የአመራር አባልን የያዘው ቡድን ዛሬ ምሽት ወይም ነገ ማለዳ ላይ አዲስ አበባ ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ኦኤምኤን የተለያዩ የሃገራችንን በተለይ የኦሮሚያን ወቅታዊ ጉዳዪች በኦሮምኛ፣ በአማርኛ፣ በአረብኛ፣ በሲዳምኛ፣ በእንግሊዝኛና በተለያዩ ቋንቋዎች ስርጭቱን የሚያስተላልፍ ሲሆን፤ በኔዘርላንድ፣ በለንደንና በካይሮ ተባባሪ ስቱዲዮዎችም አሉት።

የአሁኑ የቴሌቪዥን ተቋሙ አመራሮች ውሳኔ ባሳለፍነው ሳምንት የኢትዮጵያ ጠቅላይ አቃቤ ሕግ በዶ/ር መረራ ጉዲና የክስ መዝገብ ጋር በተያያዘ ክስ ተመስርቶባቸው ከነበሩት የኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን (ኢሳት)፣ ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦኤምኤን ስራ አስኪያጅ የሆነው ጃዋር መሃመድ ጋር በኦኤምኤን ላይም አብሮ ቀርቦ የነበረው ክስ መቋረጡን ተከትሎ ነው።

ምንጭ፦ አዲስ ስታንዳርድ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና! ዛሬ በሰመራ በተካሄደው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ምርጫ የኦሮሚያ ክልል ተወካይ የነበሩት አቶ ኢሳያስ ጅራ አብላጫ ድምፅ በማግኘት ፕሬዘዳንት ሆነው ተመርጠዋል።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ማስታወሻ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!

ከቤት ሳትወጡ...

* የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሟላ የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ መልበስ እንዳትረሱ።

* የትምህርት ቤቱን መታወቂያ መያዝ እንዳትረሱ።

* የመፈተኛ ካርዱን(Ad.ID) መያዛችሁን እንዳትረሱ።

* ለፈተናው የሚሆን ቁሳቁስ እንደ እርሳስ እና ላጲስ መያዛችሁን እንዳትረሱ።

* የሞባይል ስልካችሁንና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎቻችሁ ቤታችሁ ማስቀመጥ እንዳትረሱ።

የፈተና ጣቢያ ስትደርሱ...

* ለህግ አስከባሪዎች ታዘዙ።

* ለምትጠየቁት ጥያቄ ሳትበሳጩ በጨዋነት ምላሽ ስጡ።

በፈተና ክፍል ውስጥ...

* ከፈተናው ሰዓት ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።

* ለፈተኞች እና ተቆጣጣሪዎች ታዘዙ።

* ፈታኞች ካስቀመጧቹ ቦታ በፍፁም እንዳትነሱ እንዳትቀያየሩ።

* ፈተናውን ጀምሩ እንስክትባሉ በትዕግስት ጠብቁ።

* ፈተና መስራት ስትጀምሩ የሚቀላችሁን አስቀድሙ።

* የፈተና መልስ መስጫ ወረቀታችሁን በፍፁም በእስክርቢቶ እንዳትነኩ። መልስ መስጠት ያለባችሁ በእርሳስ መሆኑን አትዘንጉ።

* በፈተናው ዙሪያ ችግር ቢኖር ለፈተኞች አሳውቁ።

* በተመደበው ጊዜ ፈተናችሁን ለመጨረስ ሞክሩ።

* በፍፁም ፈተና ለመቀያየር እዳትሞክሩ።

* ከፈተናው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወረቀቶች ይዛችሁ እንዳትገኙ።

> ለናተ ያለው የትም ስለማይሄድ ሳትጨነቁ ተፈተኑ።

ለፈታኞች...

* ፈተኞች ተማሪዎችን በማክበር ህግ እንዳይጣስ ስሩ። ተማሪዎችን በማስፈራራት መጪው ጊዜ ጨለማ እንዲመስላቸው ልታደርጉ እና ልታስፈራሩ አይገባም።

ልዩ...

* የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሌሎችም ለተፈታኝ ተማሪዎች ለመፈተን እንዳትሞክሩ በህግ ያስጠያቃችኋል።

ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ እንዲሁም በደል ደርሶባቹ ከሆነ በዚህ ቻናል እናስተላልፋለን።

@tsegabwopde @tikvahethiopia
‹‹ኢትዮጵያን አልሠረኳትም፡፡ የሠረቁትን ለመጠየቅ ህጎችን እያወጣሁ እያለ ነው የታሰርኩት፡፡ እንዲህ እንደምሆንም አውቅ ነበር፡፡ በማረሚያ ቤት የቆየሁባቸው ዓመታት ለተሻለ ስራ እንዳስብ አድርገውኛል፡፡ በቀጣይ ለተሻለ ስራ እና ፍትህ እንዲሰፍን እሠራለሁ ››

አቶ መላኩ ፈንታ ጎንደር ከተማ ሲገቡ የተናገሩት፡፡
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሠመራ! ምርጫው ድጋሚ እየተካሄደ ነው። አቶ ኢሳያስ ያገኙት ድምፅ በህጉ መሰረት በቂ አይደለም በሚል የቀረበውን ተቃውሞ ተከትሎ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን ፕሬዘዳንት ምርጫ በድጋሚ እየተካሄደ መሆኑን ተሰምቷል።

አቶ ኢሳያስ Vs አቶ ተካ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሰበር ዜና ከሰመራ! የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል እግር ኳስ ፌደሬሽኖች እና በስራቸው የሚገኙ ክለቦች እንዲሁ አቶ ኢሳያስ ጀራ የስብሰባ አዳራሹን ለቀው ወጡ።

አቶ ተስፋይ እና አቶ ጁነዲን ከድጋሚ ምርጫው ራሳቸውን አግልለዋል።

ምንጭ፦ ሶከር ኢትዮጵያ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ተመልሰዋል! አዳራሹን ለቀው የወጡት የኦሮሚያ እና የደቡብ ክልል የእግር ኳስ ፌደሬሽኖች በመቶ አለቃ ፈቀደ ማሞ አግባቢነት በደጋሚ ወደ አዳራሹ ተመልሰዋል።

©SoccerEthiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from Yenesport (Fiker abi)
አቶ እሳያስ ጂራ የኢ.ት እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ምርጫ አሸናፊ ሆነዋል በ60% አብላጫ ድምፅ።
©Soccer Ethiopia
@Yenesport @Yenesport
ፕሬዘዳንቱ ታመዋል! ከተሾሙ ጥቂት ዓመታት ያስቆጠሩት የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ጋትሉዋክ ቱት የጤና ችግር እንደገጠማቸው ምንጮች ገለጹ፡፡

የሪፖርተር ምንጮች ፕሬዚዳንቱ ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ የጤና ዕክል እንደገጠማቸው፣ በተደጋጋሚ በአገር ውስጥ ሕክምና ሲከታተሉ መቆየታቸውን ያስረዳሉ፡፡

የገጠማቸውን የጤና እክል ከመናገር የተቆጠቡት የሪፖርተር ምንጮች፣ ፕሬዚዳንቱ በጦር ኃይሎች ሆስፒታል ሕክምናቸውን ሲከታተሉ ቢቆዩም በጤናቸው ላይ ለውጥ ሊታይ አልቻለም፡፡

ሆስፒታሉ ውጭ አገር ሄደው የተሻለ ሕክምና እንዲያገኙ በመወሰን ሪፊር የጻፈላቸው መሆኑን ገልጸዋል፡፡

ይሁን እንጂ ፕሬዚዳንቱ ውጭ አገር በመሄድ ሕክምና ለማግኘት አቅም ስለሌላቸው፣ ከዚህ በፊት የመንግሥት የሥራ ኃላፊዎች ሕክምና ወጪ በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኩል ተፈጽሞ የሚወራረድበት አሠራር በመቋረጡ፣ የክልሉ መንግሥት የሕክምና ወጪያቸው እንዴት እንደሚሸፈን ለመወሰን የካቢኔ ስብሰባ ሰኞ ግንቦት 20 ቀን 2010 ዓ.ም. ማካሄዱን ለማወቅ ተችሏል፡፡

የክልሉ ካቢኔ በጉዳዩ ላይ በጥልቀት ከተወያየ በኋላ ከክልሉ የመጠባበቂያ በጀት አንድ ሚሊዮን ብር ወጪ ተደርጎ፣ ለፕሬዚዳንቱ ሕክምና ድጋፍ እንዲውል መወሰኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡

አቶ ጋትሉዋክ በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) በጋምቤላ ክልል ተገኝተው ከኅብረተሰቡ ጋር ተወያይተው ከተመለሱ በኋላ፣ በቀናት ልዩነት የጤና ችግር አጋጥሟቸው ሆስፒታል ገብተዋል፡፡

ሕክምናውን በአገር ውስጥ ማከናወን ባለመቻሉም ወደ ውጭ ሄደው እንዲታከሙ መሰናዶዎች እየተደረጉ እንደሆነ ታውቋል፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በነገው እለት በመላው ሀገሪቱ የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና የምትወስዱ ውድ የኢትዮጵያ ልጆች መልካሙ ሁሉ እንዲገጥማችሁ እንመኛለን!

መልካም ፈተና!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
Forwarded from TIKVAH-ETHIOPIA (Tsegab Wolde)
ማስታወሻ ለ12ኛ ክፍል ተፈታኞች!

ከቤት ሳትወጡ...

* የግል እና የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች የተሟላ የትምህርት ቤቱን የደንብ ልብስ መልበስ እንዳትረሱ።

* የትምህርት ቤቱን መታወቂያ መያዝ እንዳትረሱ።

* የመፈተኛ ካርዱን(Ad.ID) መያዛችሁን እንዳትረሱ።

* ለፈተናው የሚሆን ቁሳቁስ እንደ እርሳስ እና ላጲስ መያዛችሁን እንዳትረሱ።

* የሞባይል ስልካችሁንና ሌሎች የኤሌክትሮኒክስ እቃዎቻችሁ ቤታችሁ ማስቀመጥ እንዳትረሱ።

የፈተና ጣቢያ ስትደርሱ...

* ለህግ አስከባሪዎች ታዘዙ።

* ለምትጠየቁት ጥያቄ ሳትበሳጩ በጨዋነት ምላሽ ስጡ።

በፈተና ክፍል ውስጥ...

* ከፈተናው ሰዓት ቀደም ብላችሁ ለመገኘት ሞክሩ።

* ለፈተኞች እና ተቆጣጣሪዎች ታዘዙ።

* ፈታኞች ካስቀመጧቹ ቦታ በፍፁም እንዳትነሱ እንዳትቀያየሩ።

* ፈተናውን ጀምሩ እንስክትባሉ በትዕግስት ጠብቁ።

* ፈተና መስራት ስትጀምሩ የሚቀላችሁን አስቀድሙ።

* የፈተና መልስ መስጫ ወረቀታችሁን በፍፁም በእስክርቢቶ እንዳትነኩ። መልስ መስጠት ያለባችሁ በእርሳስ መሆኑን አትዘንጉ።

* በፈተናው ዙሪያ ችግር ቢኖር ለፈተኞች አሳውቁ።

* በተመደበው ጊዜ ፈተናችሁን ለመጨረስ ሞክሩ።

* በፍፁም ፈተና ለመቀያየር እዳትሞክሩ።

* ከፈተናው ጋር ተያያዥነት ያላቸውን ወረቀቶች ይዛችሁ እንዳትገኙ።

> ለናተ ያለው የትም ስለማይሄድ ሳትጨነቁ ተፈተኑ።

ለፈታኞች...

* ፈተኞች ተማሪዎችን በማክበር ህግ እንዳይጣስ ስሩ። ተማሪዎችን በማስፈራራት መጪው ጊዜ ጨለማ እንዲመስላቸው ልታደርጉ እና ልታስፈራሩ አይገባም።

ልዩ...

* የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች እና ሌሎችም ለተፈታኝ ተማሪዎች ለመፈተን እንዳትሞክሩ በህግ ያስጠያቃችኋል።

ማንኛውም አይነት አስተያየት እና ጥቆማ እንዲሁም በደል ደርሶባቹ ከሆነ በዚህ ቻናል እናስተላልፋለን።

@tsegabwopde @tikvahethiopia
የአላህ ቁጣ ነው! “ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህ ላይ የደረሰው ጉዳት ፆም በማቋረጡ ከአላህ የመጣ ቅጣት እንጂ በሰርጅዮ ራሞስ ምክንያት አይደለም” ኡስታዝ ሙባራክ አል ባታሊ

ሙባራክ አል ባታሊ የታወቁ ኩዌታዊ የእስልምና መምህር ናቸው።

ባለፈው ቅዳሜ በዩክሬይኗ መዲና ኪየቭ በስፔኑ ሪያል ማድሪድና በእንግሊዙ ሊቨርፑል ክለቦች መካከል በተካሄደው የ2018 የአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የፍፃሜ ጨዋታ ጉዳት የደረሰበት ሞሃመድ ሳላህ በመጀመሪያው 45 ደቂቃ ጨዋታውን አቋርጦ ለመውጣት መገደዱ ይታወቃል።

ጉዳቱ የሊቨርፑል ደጋፊዎችን ብቻ ሳይሆን በተለይ ከቀናት በኋላ በሩሲያ በሚጀመረው የአለም ዋንጫ ላይደርስ ይችላል በሚል ስጋት ግብፃውያንን አስከፍቷቸዋል።

ጉዳት ያደረሰበት የማድሪዱ ተከላካይና ካፕቴይን ሰርጂዮ ራሞስንም ፊፋና የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር ቅጣት እንዲያስተላልፉበት በሚል በኦንላይን የተከፈው ዘመቻ ከ500 ሺህ በላይ ድምፅ መሰብሰብ የቻለ መሆኑን አለም እየተመለከተው ነው።

ዛሬ ለየት ያለ ጉዳይ ይዞ ወደ ትዊተር የመጣው የኡስታዝ ሙባራክ ኣል ባታሊ መልዕክት ግን አነጋጋሪ ሆኖ ተገኝቷል።

ኡስታዝ እንደሚሉት ሳላህ ታላቁ የረመዳን ፆምን ኳስ ለመጫወት ብሎ ማቋረጡ ስህተት ነው ባይ ናቸው።

እርግጥ ነው ፆምን በጉዞና በህመም ምክንያቶች ማቋረጥ የሚቻል ቢሆንም ቅሪላ ለመግፋት ተብሎ መብላትና መጠጣት ትክክል አይደለም ይላሉ።

ለዚህም ሳላህ ፆሙን እንዲያቋርጥ የመከሩትን ይኮንናሉ።

ሳላህም የእስልምናን ህግ ተላልፎ የፍፃሜው ጨዋታ ዕለት ፆም አፍርሶ ወደ ሜዳ በመግባቱ አላህ ርምጃ ወስዶበት በጉዳት ከሜዳ ሊወጣ ችሏል ብለዋል።

“ግብፃዊው ሞሃመድ ሳላህ ላይ የደረሰው ጉዳት ፆም በማቋረጡ ከአላህ የመጣ ቅጣት እንጂ ከሰርጅዮ ራሞስ አይደለም ሼህ ሙባራክ አል ባታሊሳላህ ከፍፃሜው ጨዋታ ሁለት ቀናት ቀደን ብሎ በጊዜያዊነት ፆሙን እንደሚያቋርጥ መናገራቸው ይታወሳል “ሙስሊም በምክንያትና በጥረት የሚመራ አይምሰላሁ ህይወት ለፈቀዳት በፈጣሪ እጅ ናት። ምናልባት ይሄ ጉዳትም ለበጎ ሊሆን ይችላል” ብለዋል

ኡስታዝ ለሳላህ ያላቸውንም አድናቆት ገልፀዋል።

ሳላህ የምዕራቡ አለም አምባሳደራችን ነው የቡድን ጏዶቹ አልኮል በሚጠጡበት ወቅት አብሯቸው ባለመሆን እንዲሁም ጎል ካስቆጠረ በኋላም ለፈጣሪው ሰላት በመስገድ ምስጋና ማቅረቡን እንደሚወዱለት፤ አሁንም የደረሰበትን ጉዳትና የፈፀመውን ቀኖናዊ ስህተት በመረዳት ለንስሃ የፈጣሪው በር ማንኳኳት አለበት ብለዋል።

ሞሃመድ ሳላህ ባሁኑ ጊዜ በስፔን ህክምናውን በመከታተል ላይ ያለ ሲሆን ለ አለም ዋንጫም መድረስ እንደሚችል የህክምና ባለሙያዎች እየተናገሩ ነው።

ታላቁ የግብፅ ሙፍቲ ሻውኪ ኣላም በአለም ዋንጫ ግብፅን ወክለው የሚጫወቱ የብሄራዊ ቡዱኑ አባላት ጨዋታ ያላቸው ቀን እንዳይፆሙና ከረመዳን ፍች በኋላ በመፆም እንዲያካክሱ ፈቃድ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ጴጥሮስ አሸናፊ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ሀሰተኛ መልሶች! በተለያዩ ከተሞች የሚገኙ የቲክቫክህ ኢትዮጵያ አባላት የነገው ፈተና ተሰርቆ እንደወጣ እና የፈተናው መልሶች እ ንደደረሳቸው እየነገሩን ነው። ይህ 10000000000% ውሸት እና እየተ ሰራጩ ያሉትም ሀሰተኛ መልሶች መሆኑን አውቃችሁ በተረጋጋ መንፈስ ፈታናችሁን እንድትፈተኑ መልዕክታችንን እናስተላልፋለን።

*ተማሪዎችን ለማወናበድ እና በአግባቡ ፈተናቸውን እንዳይፈተኑ ለማድረግ እየተንቀሳቀሳቹ ያላቹ ካላችሁ ከዚህ አስነዋሪ ድርጊታችሁ ልትቆጠቡ ይገባል እንላለን።

@tsegabwolde @tikvahethiopia
ዘመኑ የፎቶ ሾፕ ነው⬆️ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) የአንዳርጋቸው ፅጌን ፎቶ ይዞ መደረክ ላይ አልወጣም። ይህ የተቀነባበረ ፎቶ ነው።

@tsegabwolde @tikvahethiopia