TIKVAH-ETHIOPIA via @like
"በወደቀ አገር ውስጥ የተከበረ ጀነራል መኖር አይችልም የወደቀ አገር የሚያከብረው ጀነራል የለውም። ጠንካራ አገር ያለው አስር አለቃ ይሻላል ከወደቀ አገር ጀነራል።"
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ ለሀገር መከላከያ ሀላፊዎች የተናገሩት!
@tsegabwolde @tikvahethiopia

ሰሞነኛ ጉዳዮችን በወፍ በረር!
ከሀገር ውስጥ
🗞ከሰሞኑ ከእስር የተፈቱት የግንቦት ሰባት መሪ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ወደ እንግሊዝ በማምራት ከቤተሰቦቻቸው ጋር ተቀላቀሉ።
🗞በቤተመንግስት ዙሪያ ጥበቃ የሚያደርጉ እንዲሁም ጠ/ሚኒስትሩን የሚያጅቡ ሰዎች እየተቀየሩ ሲሆን ከ 20 አመታት በላይ የቤተመንግስት ዋና ሃላፊ በመሆን ሲያገለግሉ የቆዩት ገብረትንሳኤ ገብረሚካኤል ከስልጣናቸው ተወግደው በምትካቸው የሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ የነበሩት ወርቅነሽ ብሩ ሲተኩ ገብረትንሳይ ከስልጣን እንደተነሱ በእርሳቸው ስር የነበሩ ጠባቂዎችና አጃቢዎችም እንዲቀየሩ ተደረገ።
🗞በአዲ ረመጥ ከተማ ፌስቡክ ላይ ጽፋችሁዋል የተባሉ ወጣቶች ታሰሩ።
🗞ባሳለፍነው ሳምንት መገባደጃ በምዕራብ አርሲ ዞን የጣለው ከባድ ዝናብ ባስከተለው የመሬት መንሸራተት አደጋ 22 ሰዎች ሲሞቱ ሰባት ሰዎች ቆሰሉ፡፡ በአደጋው 45 የቤት እንስሳት ያለቁ ሲሆን በንብረት ላይ 2.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ጉዳት መድረሱ ታወቀ፡፡
🗞የግንቦት ሰባት ሊቀርመንበር ዶ/ር ብርሃኑ ነጋና የኦሮሞ ሚዲያ ኔትወርክ ሥራ አስኪያጅ አቶ ጃዋር መሀመድ እንደዚሁም ደግሞ ኢሳት እና ኦኤምኤን ቴሌቪዥንን ጨምሮ የ 137 አካላት ክስ ተቋረጠ፡፡
🗞በሰሜን ሸዋ ዞን አንጎለላ እና ጠራ ወረዳ ሰርቲ ቀበሌ በደረሰ የትራፊክ አደጋ የ18 ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡
🗞ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ዘንድሮ በዳላስ ከተማ በሚካሄደው 35ኛው የባህል እና ስፖርት ፌስቲቫል ላይ መገኘት አይችሉም ሲል የኢትዮጵያዊያን የስፖርት ፌዴሬሽን በሰሜን አሜሪካ ወሰነ፡፡
🗞የጋምቤላ ክልል ፕሬዚዳንት ዶ/ር ጋትሎክ ቱት ውጭ አገር ሄደው እንዲታከሙ የክልሉ ካቢኔ 1 ሚሊዮን ብር ከክልሉ መጠባበቂያ በጀት ወጪ እንዲሆን ወሰነ።
🗞በርካታ የሃና ማርያም ተፈናቃዮች ወደ ቤተ መንግስት በመሄድ ተቃውሞ ቢያሰሙም መልስ የሚሰጣቸው አካል አለማግኘታቸውን ተከትሎ ወደ አሜሪካ ኤምባሲ ሲያመሩ በፌደራል ፖሊሶች መንገድ ላይ እንዲታገዱ መደረጉ ተነገረ።
🗞ሁለት ኢትዮጵያውያን ዶክተሮች "ጎ ፈንድሚ" በተባለው የገቢ ማሰባሰቢያ ድረ-ገፅ በኩል ለጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል የሕፃናት የሕክምና ክፍል የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችን ለመግዛት ጥረት እያደረጉ መሆኑ ተገለፀ።
🗞መንግሥት በፖለቲካ ምክንያት የታሠሩ ዜጎችን መፍታት ያለበት በአንድ ጊዜና በአጠቃላይ ምህረት እንጂ ተራ በተራ አይደለም ሲሉ ዶክተር መረራ ጉዲና ተናገሩ።
🗞የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ መፈታት የዘገየው ማረሚያ ቤቱ “ሰነድ አልደረሰኝም” በማለቱ እንደነበር ተገለፀ፡፡
🗞በቅርቡ በምህረት የተፈቱት የልብ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት ዶክተር ፍቅሩ ማሩ የእሳቸው ሕክምና ክትትል ያስፈልጋቸው የነበሩ ከ 20 የሚልቁ ሕሙማን በእስር ማረሚያ ቤት በቆዩባቸው ዓመታት ውስጥ መሞታቸውን ገልፀው ከመታሰራቸው በፊት የልብ ባትሪ የገጠሙላቸውን እነዚህኑ ሕሙማን በፖሊስ እየተጠበቁም ቢሆን ለማከም ቢጠይቁም ውድቅ እንደተደረገባቸው ተናገሩ።
🗞"መታሠሬ በሕይወቴ ልጽፈው የማልችለውን መጽሐፍ እንድጽፍ ረድቶኛል። የሕዝቡ መልካም እና ደማቅ አቀባበልም አኩርቶኛል።" ሲሉ ከእስር ቤት የተፈቱት የአርበኞች ግንቦት ሰባት ዋና ፀሐፊ አቶ አንዳርጋቸው ፅጌ ገልፀዋል።
ከውጭ
🗞ኡጋንዳ የዋትስአፕ ተጠቃሚዎችን ቀረጥ ልታስከፍል ነው፡፡
🗞በአልጄሪያ መርከብ ሙሉ ኮኬይን የተሰኘው አደንዛዥ ዕፅ ተያዘ።
🗞በደቡብ አፍሪካ ዝቅተኛው የሠራተኞች ወርሃዊ ክፍያ 7ሺ ብር እንዲሆን የሀገሪቱ ፓርላማ ረቂቅ ህገ ደንብ አፀደቀ፡፡
🗞ፓፓዋ ኒው ጊኒ ሐሰተኛ የፌስ ቡክ ገጾችን ለመለየት እና ማህበራዊ ገፁ በሀገሪቱ ላይ ያለውን ተፅእኖ ለመለየት በሚል ፌስ ቡክን ለአንድ ወር ልታግድ ነው።
🗞በፈረንሳይ የአጫሾች ቁጥር በ 1 ሚሊዮን መቀነሱ ይፋ ተደረገ።
🗞የ22 አመቱ ማሊያዊው ፍልሰተኛ ማማዱ ጋሳማ አንድ የአራት ዓመት ሕፃን ልጅ ከአራተኛ ፎቅ ላይ ሊወድቅ ሲል በድንገት በመድረስ ከሞት በመታደጉ በሀገሪቱ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን የፈረንሳይ ዜግነት ተሰጠው፡፡
🗞የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በጋዛ ሰርጥ እስላማዊ ጂሃድ የተባለው አማፂ ቡድን ይዞታዎችን ዒላማ ያደረገ ጥቃት አካሄዱ።
🗞የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ከሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ጋር ሊያደርጉት ስለታቀደው ጉባዔ የሚወያዩት ከፍተኛ የሰሜን ኮሪያ ባለሥልጣን ኒውዮርክ የደረሱ ሲሆን ከፕሬዚዳንት ትራምፕ ጋርም ተገናኝተዋል።
ስፖርት
🗞የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ ዚነዲን ዚዳን ከስፔኑ ክለብ ጋር ተለያየ።
🗞የቀድሞው የቼልሲ አማካኝ ፍራንክ ላምፓርድ የደርቢ ካውንቲ አዲስ አሰልጣኝ ተደርጎ ተሾመ።
🗞የቀድሞው የሁል ሲቲና ዋትፎርድ አለቃ ማርኮ ሲልቫ የኤቨርተን አሰልጣኝ ሆኑ።
****************
አንኳር ዘገባዎቹ የተጠናቀሩት ከቢቢሲ አማርኛ፣ ከቪቮኤ አማርኛ፣ ከዶቼዌሌ አማርኛ እና ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥን ኢሳት እና ዘጋርዲያን ጋዜጣ ነው፡፡
# EthioNews
# Wekly News Brief
# VOA Amharic
# DWAmharic
# ESAT

የዩኒቨርሲቲ ተማሪው ለፍርድ ቀረበ! በጋሞ ጎፋ ዞን ጨንቻ ሁለተኛ ደረጃና መሰናዶ ትምህርት ቤት የ10ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ለጓደኛው ሲፈተን የተገኘው የዩኒቨርሲቲ ተማሪ ለፍርድ ቀረበ፡፡
ግለሰቡ በአርባምንጭ ዩኒቨርስቲ የሶስተኛ ዓመት የሲቪል ምህንድስና ተማሪ መሆኑ እንደተረጋገጠም የዞኑ የብሔራዊ ፈተናዎች ኮማንድ ፖስት ማስታወቁን ኢዜአ ዘግቧል፡፡
ተጠርጣሪው ሀሰተኛ የመፈተኛ መታወቂያ ይዞ በመግባት ለጓኛው የሂሳብ ፈተና ሲፈተን እንደተደረሰበትም ነው የተገለጸው፡፡
የራሱን ፈተና ለሌላ ሰው አሳልፎ በመስጠት የተጠረጠረው የትምህርት ቤቱ ተማሪም አብሮ ተይዟል።
ሁለቱም ተማሪዎች ዛሬ ጠዋት ለፍርድ ቀርበው ውሳኔያቸውን እየተጠባበቁ እንደሚገኙ ተገልጿል፡፡
ምንጭ፦ ኢዜአ

ሰበር ዜና! የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰኗል። ምክር ቤቱ ዛሬ መደነኛ ስብሰባውን አድርጓል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አዋጁ እንዲነሳ ተወሰነ! ዛሬ መደበኛ ስብሰባውን ያደረገው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወሰነ።
ምክር ቤቱ በስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ገምግሟል።
አሁን ላይም በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ መወሰኑን የጠቅላይ ሚኒስትር ልዩ ፅህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፍፁም አረጋ አስታውቀዋል።
የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ የሚጠይቅ ረቂቅ የውሳኔ ሀሳብ እንዲፀድቅ ወደ ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ልኳል።
ረቂቅ የውሳኔ ሀሳቡ በምክር ቤቱ ሲፀድቅ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ይነሳል ተብሎ ይጠበቃል።
የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የካቲት 23 2010 ዓ.ም ባካሄደው አስቸኳይ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የካቲት 9 ቀን 2010 ዓመተ ምህረት ለስድስት ወራት
ያወጀውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማፅደቁ ይታወሳል።
ምክር ቤቱ በኢፌዴሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 93 ንዑስ አንቀጽ 1 (ሀ) መሰረት በታወጀው የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ላይ ከተወያየ በኋላ በምክር ቤቱ ያፀደቀው።
በህገ መንግስቱና በህገ መንግስታዊ ስርዓቱ ላይ የተጋረጠውን ይህን አደጋ በመደበኛው የህግ ማስከበር ስርዓት ለመከላከልና ለመቆጣጠር ከማይቻልበት ደረጃ ላይ መድረሱንና ህገ መንግስታዊ ስርአቱን ለመጠበቅ የሚያስችል የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ማውጣት በማስፈለጉ ነበር የታወጀው።
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው ስብሰባው የሀገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ከገመገመ በኋላ አሁን ላይ በሀገሪቱ ስርዓት ሰፍኖ ሰላምና መረጋጋት በመመለሱ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ እንዲነሳ ወስኗል።
ምንጭ፦ ፋና

⬆️የዋልድባ አባቶች ወደ ገዳም ተመልሰዋል! በመጀመሪያ በማዕከላዊ በመቀጠል በቂሊንጦ እስር ላይ የነበሩት እና በቅርቡ ከእስር የተፈቱት ሁለቱ የዋልድባ አባቶች ወደገዳማቸው መመለሳቸው ተነግሯል። መነኮሳቱ የ14 ሰዓታት የበረሃ የእግር ጉዞ በማድረግ ዋልድባ ከገዳማቸው መድረሳቸው ነው የተነገረው።
አባቶቹ ዋልድባ ሲደርሱ ማኅበረ መነኮሳቱ ከየ በአታቸው በመውጣት ተቀብለዋቸዋል። እነሱም በአበው እግር ስር ተደፍተው በግምባራቸው በመውደቅ ጸሎት ቡራኬ ተቀብለዋል። በአታቸውን የዘጉና በአርምሞ የሚኖሩ አባቶች ጭምር መነኮሳቱን ከበአታቸው እንደተቀበሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
ምንጭ፦ ዘመድኩን በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አባቶቹ ዋልድባ ሲደርሱ ማኅበረ መነኮሳቱ ከየ በአታቸው በመውጣት ተቀብለዋቸዋል። እነሱም በአበው እግር ስር ተደፍተው በግምባራቸው በመውደቅ ጸሎት ቡራኬ ተቀብለዋል። በአታቸውን የዘጉና በአርምሞ የሚኖሩ አባቶች ጭምር መነኮሳቱን ከበአታቸው እንደተቀበሏቸው ለማወቅ ተችሏል።
ምንጭ፦ ዘመድኩን በቀለ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
ሀዘን! የደ/ብርሀን ዩኒቨርሲቲ በያዝነው ሳምንት በነበረው አሰቃቂ የመኪና አደጋ 3 ተማሪዎቹን አጥቷል።
በአጠቃላይ በአደጋው ህይወታቸው ላለፉ ወገኖች ነብስ ይማር እያልን ለቤተሰብ እና ወዳጆች መፅናናትን እንመኛለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
በአጠቃላይ በአደጋው ህይወታቸው ላለፉ ወገኖች ነብስ ይማር እያልን ለቤተሰብ እና ወዳጆች መፅናናትን እንመኛለን!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ውሸት ነው! የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተሰርቆ ወጥቷል በዚህም ፈተናው ተራዝሟል በማለት የሚናፈሰው ወሬ ከእውነት የራቀ ነው። ተማሪዎች በተረጋጋ መንፈስ ሰኞ ፈተናችሁን እንድትፈተኑ ቻናላችን መልዕክቱን ያስተላልፋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
አቶ ሌንጮ በደኖ የሚባል ቦታ ረግጬ አላውቀውም አሉ። ከቢቢሲ ጋር ያደረጉትን ቃለ መጠይቅ ከአፍታ በኋላ ለጥፋላችኋለሁ።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
BBC: ''በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም'' አቶ ሌንጮ ለታ
በኢትዮጵያ ፖለቲካ ውስጥ ለአስርት ዓመታት የቆዩትና የኦሮሞ ነፃ አውጭ ግንባር መስራች የሆኑት ሌንጮ ለታ የኦሮሞ ጥያቄዎችን ወደፊት በማስቀደም ፈር ቀዳጅ እንደሆኑ ይነገርላቸዋል።
ኢህአዴግ አዲስ አበባን ሲቆጣጠርም በሽግግር መንግሥት ምስረታው ተሳታፊ ነበሩ። ለረጅም ዓመታት በስደት የቆዩት አቶ ሌንጮ ከሦስት ዓመት በፊትም የኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር የተሰኘ ፖርቲንም አቋቁመዋል።
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድ ወደ ስልጣን ከመምጣታቸው ጋር ተያይዞ አገር ቤት ባለው ፓለቲካ ውስጥ ለመሳተፍ ተመልሰዋል። በመጪው ፖለቲካዊ ተሳትፏቸውና ከኦነግ ጋር ተያይዞ በሚቀርብባቸው አወዛጋቢ ጉዳዮች ላይ ከቢቢሲ ጋር ቆይታ አድርገዋል።
*⃣ከኢትዮጵያ መንግሥት ጋር እያደረጋችሁት ያለው ድርድር በምን መንገድ እየሄደ ነው?
▪️አቶ ሌንጮ፡ ድርድር ልለው አልችልም። ውይይት ነው እያካሄድን ያለነው። አሁን እየተፈጠረ ያለው ለውጥ ደካማና ጠንካራ ጎኑን እንዲሁም እኛ ልናበረክተው የምንችለው አስተዋፅኦ ምን ሊሆን ይችላል? በሚለው እየተወያየን ነው። ውይይቱ ጅማሮ ላይ ነው ሰፊ ጉዳዮችም አልተነሱም። እኛ ለብዙ ዓመታት ከዚህ አገር ተገልለን ባዕድ አገር ከመኖራችን አንፃር፤ እንዲሁም በስደት በነበርንበት ወቅት ኢትዮጵያ ውስጥ ብዙ ለውጥ በመከሰቱ ይህንን ለመረዳት እየሞከርን ነው። ያንን ሳንረዳ የሚረባ አስተዋፅኦ ልናበረክት አንችልም።
*⃣ከመንግሥት ጋር እያደረጋችሁት ያለው ውይይት በጥሩ መንገድ ከሄደ ምን ለማድረግ ታስባላችሁ?
▪️አቶ ሌንጮ፡ እንደ ኦሮሞ ዴሞክራሲያዊ ግንባር በኢትዮጵያ ውስጥ ባለው ፖለቲካ ውስጥ መሳተፍ እንፈልጋለን። በአሰራሩ መሰረት መመዝገብ እንዲሁም ቢሮ መክፈት እንፈልጋለን። በእነዚህም ጉዳዮች ላይ ውይይት አካሂደናል። የተፈጠረው ሁኔታ አበረታች ነው። ለመሰማራት ዝግጁ ነን።
*⃣ለአስርት ዓመታት በኢትዮጵያ ፖለቲካ ከመሳተፍዎ አንፃር የእርስዎ አስተዋፅኦ ምንድን ነው?
▪️አቶ ሌንጮ፡ይሄን ያህል አይደለም። ትልቁ አስተዋፅኦ የምለው የኦሮሞ ነፃነት ግንባርን በማቋቋም ተሳትፌያለሁ። ደርጅቱም የኦሮሞን ሁኔታ በመለወጥ ከፍተኛ አስተዋፅኦ አለው። በኋላ ሁኔታዎች እንደፈለግነው አልሆኑም እንጂ አዲስ ምዕራፍ ከፍቶ ነበር። ወደሚቀጥለው ምዕራፍ ለመሸጋገር ምን ያስፈልጋል በሚለው ላይ እናተኩራለን። ስላለፈው የኢትዮጵያ ታሪክ ብዙ እንነታረካለን፤ ጥቅሙ የረባ አይደለም።
*⃣ወደኋላ ዞር ብለው ሲመለከቱ ባደረጉት ነገር የሚፀፅትዎት ነገር አለ?
▪️አቶ ሌንጮ፡ ከአፄ ኃይለሥላሴ ወደ ደርግ ሥርዓተ- መንግሥት በነበረው ሽግግር ወጣቶች ነበርን። እኔም ሆንኩ እኩዮቼ የፈፀምናቸው ስህተቶች ነበሩ። ከደርግ ወደ ኢህአዴግም ስንሸጋገር ብልህነትንና ጥበብን የተካነ እርምጃዎች መውሰድ ሲኖርብን ያው በስሜታዊነት ተነድነተን ያደረግናቸው ነገሮች አሉ። ይህ ሁሉ የሚያሳየው ኢትዮጵያ በፖለቲካ ዕውቀት ደሀ መሆኗን ነው። እኔ ተማሪ በነበርኩበት ወቅትም ሆነ በደርግ ወቅት ፖለቲካ ወንጀል ነበር። ፖለቲካ ህጋዊ የሆነው ባለፉት 27 ዓመታት ነው። ይህም ቢሆን ዲሞክራሲያዊ የሆነ የፖለቲካ ባህል እንድናዳብር ይሄን ያህል የረዳ አይመስለኝም። ይሄ እንዳይደገም ዴሞክራሲያዊ የፖለቲካ ባህል መገንባት ላይ መሰማራት አለብን። ብቻችንን የምንሰራው ሳይሆን ሌሎች ድርጅቶችንም ጨምሮ ህብረተሰቡን ያሳተፈ ሊሆን ይገባል። አምባገነንነት ፈፅሞ እንዳይከሰት መረባረብ ያስፈልጋል።
*⃣ኦነግ በደኖ ላይ ከተከሰተው ግድያ ጋር ተያይዞ ስሙ ይነሳል። ጭፍጨፋውን ፈፅሟል እያሉ የሚያነሱት አካላት አሉ። የእርስዎ ምላሽ ምንድን ነው?
▪️አቶ ሌንጮ፡ በኢትዮጵያ ታሪክ ከሚያሳዝነው አንደኛው ጉዳይ ለፖለቲካ ፍጆታ የሚነሳ ነገርና የፍትህ ጥያቄን ለመመለስ ተጠንቶ የሚቀርብ ሁኔታ የለም። ፕሮፓጋንዳ ነው? ወይስ የፍትህ ጥያቄ የሚለውን መለየት አይቻልም። በመጀመሪያ ነገር እኔ በደኖ የሚባል ቦታን ረግጨው አላውቅም። ቦታው ላይ የነበረውንም ሰራዊት አላዘዝኩም። ሁለተኛ ገለልተኛ በሆነ አካል የተጠና ጥናት የለም። እንደዚህ አይነት ጉዳዮችን ዝም ብለን ከማራገብ ጥናት ተደርጎ እልባት ቢደረግላቸው ይሻላል። በእንዲህ አይነት ጉዳይ ከመወነጃጀል እንዳይደገም ማተኮሩ ነው የሚበጀው።
*⃣ተጠንቶ ጭፍጨፋው ከኦነግ ጋር የሚገናኝ ቢሆን ይቅርታ ለመጠየቅ ዝግጁ ነዎት?
▪️አቶ ሌንጮ፡ በእኛ ላይ በትክክለኛ መንገድ ተጠንቶ ማስረጃ ከቀረበ ያን ጊዜ ከኦነግ መሪዎች አንዱ ስለነበርኩ ማንኛውንም ህጋዊ ውሳኔ እቀበላለሁ።
*⃣በባለፉት ሦስት ዓመታት እንዲሁም የባለፉትን ሁለት ወራት ውስጥ ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን ሁኔታ እንዴት ገመገሙት?
▪️አቶ ሌንጮ፡ በእድሜዬ ይህ ሦስተኛው እድል ነው። ከአፄ ኃይለሥላሴ ወደ ደርግ የነበረው የሽግግር ሁኔታ ዴሞክራሲያዊ መልክ አልነበረውም። ለተፈጠረው ዴሞክራሲያዊ ጅምር መጨናገፍ ብዙ ኃይሎች ያበረከቱት አስተዋፅኦ አለ። ከደርግ ወደ ኢህአዴግ ሽግግር ሲደረግ ለመጀመሪያ ጊዜ በፅሁፍ ቃልኪዳን ገብተን ነበር። በተለያዩ ምክንያቶች እንደፈለግነው ሳይሆን ቀረ። እውነተኛ ዴሞክራሲም እውን ሳይሆነ ተጨናገፈ። በዚህ ወቅት ስህተት መፈፀም የለብንም። ይህ የመጨረሻ ሊሆን ይችላል። ሁሉም የሚመለከታቸው ኃይሎች እንዲሁም ህብረተሰቡን ጨምሮ ተረባርበን ዴሞክራሲን እውን ልናደርግ ይገባል።
*⃣ባለፉት ዓመታት ብሔርተኝነት በከፍተኛ ሁኔታ የተስፋፋበት ሁኔታ ተፈጥሯል። ይህም በተለያዩ አካባቢዎች ላሉት መፈናቀሎች አስተዋፅኦ እንዳደረገ አስተያየታቸውን የሚሰጡ እንዳሉ ሁሉ ጥሩ ነው የሚሉ አሉ። ይህንን የብሔርተኝነት ጉዳይ እንዴት ያዩታል?
▪️አቶ ሌንጮ፡ ብሔርተኝነት ማንም ግለሰብ ከመሬት ተነስቶ ሊፈጥረው የሚችለው ነገር አይደለም። ብሔርተኝነት የሚነሳው በምክንያት ነው። ብሔርተኝነትን ከመቃወም በፊት ምክንያቱ ምንድን ነው የሚለው ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል። በግሌ ብሔርተኝነትን በፍራቻ መነፅር የሚያዩ ሰዎች ችግራቸው ይገባኛል፤ ነገር ግን የነሱን ያህል አልሰጋም። መረዳት ያለብን ኦሮሞም ሆነ፣ አፋርም፣ ጉራጌም ሆነ የተለያየ ብሔር ያለው ግለሰብ ሆኖ ኢትዮጵያዊ መሆን ከተቻለ፤ ኢትዮጵያዊነት ደግሞ የብሔርን ማንነት በሚያንፀባርቅ መልኩ ከተዋቀረ ሁሉም ሰው ኢትዮጵያን ሲያያት ራሱን ለማየት ከቻለ ኢትዮጵያ ኃያል ሀገር ትሆናለች። ብሔርተኝነት እንደማንኛውም ፖለቲካዊ አቋም አደጋ ሊኖረው ይችላል፤ ሊጠቅምም ይችላል።
©BBC
@tseagabwolde @tikvahethiopia

የዚህን ሳምንት የግዕዝ ትምህርት ወደ @TIKVAHETHEDU ገብታችሁ መከታተል ትችላላችሁ።
በወጣት ዮርዳኖስ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ!
@tseagbwolde @tikvahethiopia
በወጣት ዮርዳኖስ ተዘጋጅቶ የሚቀርብ!
@tseagbwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
STOP EVICTION NOW! ማንኛውም ኢትዮጵያዊ ዜጋ ሁሉም የሀገራችን ክፍል የሱ ነው። ዜጎችን ማፈናቀል ሊቆም ይገባል።
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ኢትዮጵያዊነት ይለምልም!
@tsegabwolde @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA via @like
አነጋጋሪው ፎቶ!⬆️በፎቶዉ ላይ የምትመለከቷቸዉ ዶ/ር አብይ አህመድ አይደሉም! በመልክ እና በስም የሚመስሏቸው ሊቀ ትጉኃን ዐቢይ ሥልጣን እንጂ። ሊቀ ትጉኃን ዐቢይ በአሜሪካ በሲያትል ደብረ አሚን አቡነ ተ/ሃይማኖት ቤት ክርስቲያን አገልጋይ አባት ናቸው።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ፕሬዘዳንቱ ዶርም ድረስ! ትናንት የቱርኩ ፕሬዝዳንት ኤርዶጋን ለህዝባቸው ምን ያክል ቅርብና ታዛዥ መሆናቸው የሚሳይ ተግባር በመፈፀማቸው የአለምን መገናኛ ብዙሃን እያነጋገረ ይገኛል።
በትናንትናው ዕለት አንድ የዩንቨርስቲ ተማሪ በትዊተር አካውንቱ እሱ ወደ ሚማርበት ዩኒቨርሲቲ ዶርም መጥተው
ፕሬዝዳንቱ አብረውት እንድያፈጥሩ ይጠይቃቸዋል።
የቱርኩ ፕሬዜዳንት ጠይብ ኤርዶጋንም የተማሪውን መልዕክት አይተው በቅፅበት ያለምንም ማቅማማት ተማሪው ወደ ሚገኘበት የተማሪዎች መኝታ ዶርም ሱሁር ላይ እመጣለሁ ነገር ግን ሻይ ካዘጋጀህ ይሉታል።
ተማሪውም እሺ ብሎ ተማሪዎቹን በማስተባበር ዝግጅት አድርገው ጠበቋቸው እሳቸውም በቦታው ድረስ በመገኘት ከተማሪዎቹ ጋ አብርው በመመገብ ንግግር
አደርገውላቸው ዓለምን አስገርመዋል።
ምንጭ፦ የፕሬዘዳንት ኤርዶጋን ገፅ

ነብስ ይማር! የደብረ ብርሀን ዩኒቨርሲቲ ተማሪዋ ቃል ይህች ነበረች። የሊዛ ትምህርት ቤት ተማሪዎች ይህ ፎቶ ልከዋል። ሀዘናቸውንም ገልፀዋል።
@tsegabwolde @tikvahethiopia
@tsegabwolde @tikvahethiopia
ቃልዬ እንደወጣች ቀረች! "በህይወቴ እጅግ ብዙ ጊዜ አሳዛኝ አስደሳች ጊዜን አሳልፌያለው።
ግን እንደዚ በጣም ያስከፋኝ ያሳዘነኝ አስከፊ አሰቃቂ ሞት ገጥሞኝ አያውቅም።
ቃሌ ትባላለች አዲስ አበባ ከምሰራበት ቦታ ብዙም አይርቅም ቤታቸው።
የደብረብርሃን ዩንቨርሲቲ ተማሪ ናት። ስትወጣ ስትገባ አያታለው።
በጣም ጨዋ ተግባቢ ደግና ሩህሩህ ናት።
ባወኳት ጥቂት ጊዜ ያወኩት ህልም ያላት ና ቤተሰቦቿን ሁሌ መርዳት የምትወድ፤ ደረስኩላቹ የምትል፤ የልጅ አዋቂ የሆነች፤ የ18 አመት ወጣት እንደወጣች ቀረች፡፡
ድንገት ባላት የሁለት ቀን እረፍት ቤተሰቦቿን ለማየት መጥታ ስትመለስ አይዞሽ ደርሼልሻለው፤ ያለቻት እናቷ ብትሸኛትም ህይወት እንዳሰበችው ሳይሆን ኢትዮጵያ ውስጥ ቤተሰብ እየበተነ ያለው የመኪና አደጋ፤ (ከፃድቃኔ ይመጣ የነበረ ታታ ጋር የተጋጨው ሀይሩፍ) ቃልየን ጨምሮ የያዛቸውን ጨምሮ ነጠቀን። ያሳዝናል። ህይወት እንዲ ናት።
ከልቤ አዘንኩ።
ስንቱ የቤተሰብ አልኝታ በቸልተኛ ሹፌር እንደወጣ ሲቀር ማየት ያሳዝናል።
ፈጣሪ ነብስሽን በገነት ያኑረው። ለቤተሰብሽ መጽናናትን ተመኘው። ጋዜጠኛ ጌጡ ተመስገን"