#SouthAfrica
ደቡብ አፍሪካ ውስጥ በአንድ ቀን 1,134 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል፤ አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 19,137 ደርሰዋል።
ከዚህ በተጨማሪ የሰላሳ (30) ሰዎች ህይወት አልፏል። አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ሶስት መቶ ስልሳ ዘጠኝ (369) ደርሷል።
በደቡብ አፍሪካ አጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) ተይዘው በተደረገላቸው ህክምና ያገገሙ ሰዎች 8,950 ናቸው።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot

#UPDATE
በኢትዮጵያ ተጨማሪ 1 ሰው በኮሮና ቫይረስ መያዙ ተረጋገጠ!
መደበኛ 24 ሰአት ዕለታዊ መግለጫ ከተሰጠ በኋላ ለ #MoHEthiopia በደረሰው አዲስ መረጃ መሰረት በሃረሪ ክልል በተደረገ 12 የላብራቶሪ ምርመራ አንድ (1) ሰው የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል።
ቫይረሱ የተገኘበት ግለሰብ የ37 ዓመት የሀረር ከተማ ነዋሪ የሆነ ኢትዮጵያዊ ሲሆን የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት #የሌለው ነው።
#DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

#HARAR
በዛሬዉ እለት በሀረሪ ክልል በተደረገው የላብራቶሪ ምርመራ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ ሰው መገኘቱን የክልሉ ርዕሰ መስተዳደር አቶ ኦርዲን በድሪ አሳውቀዋል።
ግለሰቡ ወደ 'ህክምና ማእከል' ተወስዶ ህክምና እያገኘ እንደሆነ አቶ ኦርዲን ገልፀዋል። ከግለሰቡ ጋር #ንክኪ የነበራቸዉ ሰዎችም ወደ #ኳራንቲን እንዲገቡ የማድረግ ስራ እየተሰራ እንደሆነ አሳውቀዋል።
አቶ ኦርዲን መንግስት ወረርሽኙን ለመከላከልና ለመቆጣጠር አስፈላጊውን ሁሉ የሚያደርግ መሆኑን ያረጋገጡ ሲሆን የክልሉ ህዝብ ከመንግሥት ጎን በመቆም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አሳስበዋል።

የኮቪድ-19 ብዙ ቀውሶች መካከል ጥቂቶች የሚናገሩለት ፤ የጤና ባለሙያዎች ስነአእምሮ ጤንነት!
በዚህ ዓለም አቀፍ ወርሽኝ ወቅት ሰዎች ስለ ግል የጤና መከላከያ መሣሪያዎች(PPE) አጣዳፊነት እና ወሳኝ ፍላጎት፣ የመተንፈሻ መሳሪያዎች (ventilators) እና የምርመራ መጠንን መጨመር አስፈላጊነት እየተናገሩ ነው።
በውጭ ተመልካቾች ፊት የጤና ባለሙያዎች ጠንካራና የጥንካሬ ተምሳሌት እንዲሁም በየቀኑ ስራቸው ላይ የሌሎችን የተሟላ ጤና እና ደህነንት ለመጠበቅ የሚበረቱ ናቸው፥ ሲያልፍ ደግሞ "ሀኪም ደግሞ አይታመም" ተብሎ ይነገራል።
ከስሩ ግን እነሱም ለራሳቸውም፣ ለሚወዷቸውም በቫይረሱ ስለመያዝም ሆነ አያርገው እና መሞትም ይጨነቃሉ፣ ይፈራሉማል። ስለዚህም ነው ገና ከጅማሬው ሆነ ለመጪዎቹ ወራት የአእምሮ ጤንነታቸውን ለመጠበቅ መሞከሩ የሁላችንም ግዴታ የሚሆነው።
የጤና ባለሙያዎችን ለመደገፍ ባለሙያዎችም፣ የሚመለከተው አካል የሌሎች ሀገራትን ተሞክሮ በመውሰድ የራሳቸውን አካላዊ ጤንነት ብቻ ሳይሆን ልክ ጦርነት ላይ እንዳለ ወታደር አእምሯዊ ጤንነታቸውን ለመጠበቅ ጣልቃ መግባት አለባቸው።
የጤና ባለሙያዎችን በአካል እንዴት መጠበቅ እንደሚችሉ መናገር ለመጀመር ረዥም ጊዜ ፈጅቶብናል። አሁን ስለአእምሮ ጤንነት እንነጋገር።
ሁለገብ የሆነ ባለብዙ-ተኮር የመከላከያ ዘዴዎች(የጭንቀት መቀነስ፣ ጥንቃቄ የተሞላበት ውሳኔ እና ትምህርታዊ ቁሳቁሶች ማዘጋጀት)፣ በጊዜው እርምጃዎች( ሆትላይን መዘርጋት፣ የችግር ድጋፍ)፣ እና አስፈላጊም ከሆነ ቴራፒዩቲክ ሕክምና መስጠት ወሳኝ ነው።
ስለዚህ ከውደሳ በዘለለ የጤና ባለሙያዎችን ሁለንተና በመጠበቅ ፤ የህዝባችንን ህልውና እንጠብቅ።
(ዶክተር ያቤፅ ከበደ - የጤና ባለሙያ)

ብራዚል መዘናጋት ዋጋ እያስከፈላት ነው!
ብራዚል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት መጀመሪያ ሰሞን ያሳየችው መዘናጋት ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈላት ይገኛል።
ትላንት ምሽት ባወጣችው ሪፖርት የ1,188 ሰዎች ህይወት በአንድ ቀን #አልፏል፤ 17,564 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
በመላው ሀገሪቱ በኮቪድ-19 ምክንያት አጠቃላይ የሞቱ ሰዎች ብዛት ከ20,000 በልጧል ፤ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ብዛት ደግሞ ከ310,000 በላይ ሆኖ ተመዝግቧል።
መዘናጋትና ቸልተኝነት ዋጋ ያስከፍላል!

'እኔም የዕርቅ ሀሳብ አለኝ' ምዝገባ ተጀምሯል!
በተለያዩ የሀገራችን ክፍል ለምትገኙ ሁሉ በአከባቢያችሁ ስላለው ወይም በቅርበት ስለምታቁት ባህላዊ የዕርቅ ሥርዓት ከ5-10 ገጽ ያልበለጠ ገላጭ ጹሑፍ በማዘጋጀት የሚያውቁትን የዕርቅ ሥርዓት ለሌሎች ያስተዋውቁ፣ በዚህ ውድድርም በመሳተፍ የሰላም ሰርተፍኬት ያግኙ፣ የጹሑፍ ዝግጅቶ የተዋጣለት ከሆነ ደግሞ የተዘጋጀሎትን ሽልማት ይውሰዱ።
ምዝገባ የሚከናወንበት ጊዜ ከግንቦት 14 - 21 ብቻ ነው!
ለመመዝገብ ፦
- ለግል ተሳታፊዎች https://forms.gle/6EEurxKwRDRN6oJJ6
- ለቡድን ተሳታፊዎች https://forms.gle/AMJnaNaD1oSCNr3D7
ለበለጠ መረጃ በቴሌግራም https://t.iss.one/Ihaveanideatikvah ላይ በአጭር የጽሑፍ መልዕክት ይጠይቁ፡፡

#SouthSudan
የደቡብ ሱዳን የኢንፎርሜሽን ሚኒስትር ሚካኤል ማኩዪ ከጤና ሚኒስትሯ ውጭ #ሁሉም የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ግብረ ኃይል አባላት በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ለቢቢሲ #አረጋግጠዋል።
በኮቪድ-19 የተያዙት ሁሉም ሚኒስትሮች በለይቶ ማቆያ የሚገኙ ሲሆን በሙሉ ጤንነትም ላይ ይገኛሉ ተብሏል።
ከዚህም በተጨማሪ የባለስልጣናቱ ጠባቂዎች እንዲሁም ሠራተኞች በኮሮና ቫይረስ ተይዘው በለይቶ ማቆያ ውስጥም ይገኛሉ።
በሌላ በኩል የኢንፎርሜሽን ሚኒስትሩ ፕሬዚዳንት ሳልቫ ኪር በኮቪድ-19 ተይዘዋል የሚለውን ሪፖርት #አጣጥለውታል።

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 30 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ በተደረገው 3,645 የላብራቶሪ ምርመራ ሰላሳ (30) ሰዎች የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። በአጠቃላይ በሀገራችን ቫይረሱ በምርመራ የተገኘባቸው ሰዎች ቁጥር 429 ደርሷል፡፡
ቫይረሱ የተገኘባቸው 26 ወንድ እና 4 ሴት ናቸው። በዜግነት ሁሉም ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ15 እስከ 60 ዓመት የእድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
ቫይረሱ የተገኘባቸው 18 ሰዎች ከአዲስ አበባ፣ 3 ሰዎች ከአፋር ክልል፣ 4 ሰዎች ከኦሮሚያ ክልል፣ 3 ሰዎች ከትግራይ ክልል እንዲሁም 2 የደንበር ተሻጋሪ አሽከርካሪዎች ናቸው።
የዕለቱ ታማሚዎች የጉዞ ታሪክና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት ፦
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ ያላቸው - 9
• በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት ያላቸው - 17
• የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ግንኙነት የሌላቸው - 4
ተጨማሪ መረጃ ፦
በትላትናው ዕለት 5 ሰዎች ከአዲስ አበባ ከበሽታው ያገገመ ሲሆን አጠቃላይ በሀገራችን ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች ቁጥር አንድ መቶ ሃያ ስምንት (128) ደርሷል።

ከኦሮሚያ ክልል ጤና ቢሮ የተሰጠ መረጃ፦
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ የተከናወነው የላብራቶሪ ምርመራ 292 ሲሆን ከእነዚህ መካከል ነው አራት (4) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው።
የታማሚዎች ዝርዝር ሁኔታ ፦
ታማሚ 1 - የ32 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 2 - የ60 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የላቸውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 3 - የ29 ዓመት ኢትዮጵያዊ የቡራዩ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #የለውም፤ በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያለው ግንኙነት #በመጣራት ላይ ነው።
ታማሚ 4 - የ19 ዓመት ኢትዮጵያዊ የምስራቅ ሀረርጌ ነዋሪ ፤ የውጭ ሀገር የጉዞ ታሪክ #ያለው።
በኦሮሚያ ክልል ደረጃ የኮሮና ቫይረስ ወቅታዊ ሁኔታ ፦
• አጠቃላይ የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 3,769
• ባለፉት 24 ሰዓት የተከናወነ የላብራቶሪ ምርመራ - 292
• ዛሬ በበሽታው መያዛቸው የተረጋገጠ - 4
• በቫይረሱ ተይዘው በለይቶ ህክምና ውስጥ ያሉ - 14
• በፅኑ ህክምና ላይ ያሉ - 0
• አጠቃላይ ያገገሙ - 10
• በበሽታው ህይወታቸ ያለፈ - 1
• እስካሁን በበሽታው የተያዙ - 25
Via @tikvahethAFAANOROMOO
#TikvahEthiopia
@tikvhhethiopiaBot @tikvahethiopia

#DrHagosGodefay
በትግራይ ክልል በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱ ሰዎች በለይቶ ማቆያ ውስጥ የሚገኙ መሆናቸውን የትግራይ ክልል ጤና ቢሮ ኃላፊ ዶክተር ሓጎስ ጎደፋይ ነግረውናል።
ሁለቱ (2) ከማይካድራና ሰቲት ሁመራ ለይቶ ማቆያ ፣ አንድ (1) ሰው ከመቐለ ላይቶ ማቆያ መሆኑን የቢሮው ኃላፊ አሳውቀውናል።
ዛሬ በኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19) መያዛቸው የተረጋገጠ ሶስቱም (3) ሰዎች ምንም አይነት ምልክት #የለባቸውም።
ዶክተር ሓጎስ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አሁንም በርካታ ስራዎች እየተሰሩ ናቸው ፤ ዜጎችም በመንግስት የሚስጡ መመሪያዎችንና በጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉ ምክሮችን ሳይዘናጉ እንዲተገብሩ መልዕክት አስተላልፈዋል።

በኬንያ ተጨማሪ 52 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸውን ተረጋገጠ!
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,567 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ ሁለት (52) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,161 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገው 2,567 የላብራቶሪ ምርመራ ሃምሳ ሁለት (52) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች 1,161 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጅቡቲ ውስጥ በአንድ ቀን 223 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
ጅቡቲ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 941 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት መቶ ሃያ ሶስት (223) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,270 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል ትላንት ዘጠኝ (9) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,064 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጅቡቲ ውስጥ ባለፉት 24 ሰዓት 941 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት መቶ ሃያ ሶስት (223) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 2,270 ደርሰዋል።
በሌላ በኩል ትላንት ዘጠኝ (9) ሰዎች በተደረገላቸው ህክምና ከበሽታው (ኮቪድ-19) ማገገማቸውን ተከትሎ አጠቃላይ ከበሽታው ያገገሙ ሰዎች 1,064 ደርሰዋል።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሚኒስትሮች ምክር ቤት ዛሬ ባካሄደው 83ኛ መደበኛ ስብሰባ በተለያዩ አጀንዳዎች ላይ ተወያይቶ #ውሳኔ አሳልፏል!
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#HAWASSA
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ትራንስፖርት እና መንገድ ልማት መምሪያ ዛሬ በሰጠው መግለጫ #ሁሉም አሽከርካሪዎች እና ተሳፋሪዎች ከመጪው ሰኞ ግንቦት 17 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ የፊትና የአፍ መሸፈኛ ማስክ የማድረግ ግዴታ እንደሚኖርባቸው አሳውቋል።
ይህን መመሪያ በሚተላለፉ አሽከርካሪዎች ላይ ተገቢውን እርምጃ እንደሚወስድ መምሪያው በጥብቅ አስታውቋል፡፡
መመሪያው በመላው ሀገሪቱ #እየጨመረ የሚገኘውን ፤ እንዲሁም ወደ ከተማው የመግባት አዝማሚያ እያሳየ ያለውን የኮሮና ቫይረስ ስርጭት ለመከላከል ይረዳል ተብሎ የተዘጋጀ ነው ተብሏል።
የባለ 2 እግር ሞተር ሳይክል አሽከርካሪዎችን እንዲሁም የህዝብ ትራንስፖርት አሽከርካሪዎች ረዳቶችና ተሳፋሪዎችን ፤ እንዲሁም የግልና የመንግስት መኪና አሽከርካሪዎችና ተሳፋሪዎችን፤ ባጃጅና የመሳሰሉትን አነስተኛ የትራንስፖት ዘርፎች የሚያካትት ነው።
አሽከርካሪዎች ይህንን አውቀው በቀጣይ ሁለት (2) ቀናት ውስጥ ተገቢውን ዝግጅት በማድረግ ከመጪው ሰኞ ጀምሮ የፊት ማስኮችን አድርገው መንቀሳቀስ እንደሚኖርባቸው ተገልጿል፡፡
#SRTA

በኢትዮጵያ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋገጠ!
በመደበኛ የ24 ሰዓት ዕለታዊ መግለጫ ከተገለፀው የላብራቶሪ ምርመራ በተጨማሪ በአማራ ክልል በተደረገ 41 የላብራቶሪ ምርመራ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል።
ባለፉት 24 ሰዓት በአጠቃላይ ሰላሳ አራት (34) ሰዎች በምርመራ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶባቸዋል። አጠቃላይ በሀገራችን በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠ ሰዎች ቁጥር አራት መቶ ሰላሳ ሶስት (433) ደርሷል።
ቫይረሱ የተገኘባቸው ሰዎች ሁሉም ወንድ ኢትዮጵያውያን ሲሆኑ ከ29 እስከ 97 ዓመት የዕድሜ ክልል ውስጥ የሚገኙ ናቸው።
አንድ ግለሰብ የውጭ ሀገር ጉዞ ታሪክ ሲኖረው ሶስቱ ግለሰቦች የውጭ ጉዞ ታሪክ የሌላቸው እና በበሽታው ከተያዘ ሰው ጋር ያላቸው ግንኙነት በመጣራት ላይ ነው።
ቫይረሱ በምርመራ ከተገኘባቸው ሰዎች ውስጥ ሁለቱ የመኖሪያ ቦታቸው ምዕራብ ጎንደር ሲሆን ሁለቱ የማዕከላዊ ጎንደር እና የጎንደር ከተማ ነዋሪዎች ናቸው።