TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.2K photos
1.5K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አጫጭር ሀገር አቀፍ መረጃዎች፦

- የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከፍተኛ አመራሮች የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ሥራ እንዲውል የአንድ ወር ደመወዛቸውን ለግሰዋል።

- ሼህ ሁሴን አሊ አላሙዲ የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝን ለመግታት የ120 ሚሊዮን ብር ድጋፍ አድርገዋል። በተጨማሪ የሚድሮክ ቴክኖሎጂ ግሩፕ ማኔጅመንት፣ አመራር እና ሠራተኞች ከ10 ሚልዮን ብር በላይ ለተመሳሳይ አላማ አበርክተዋል።

- የሀዋሳ ኢንዱስትሪያል ፓርክ 14, 000 ሰራተኞቹን በጊዚያዊነት ከስራ አሰናብቷል። ሰራተኞቹ ከስራ የተሰናበቱት በአሜሪካና በአውሮፓ ገበያዎች የምርቶቹ ዋነኛ ተቀባይ የነበሩት ድርጅቶች በኮሮና ምክንያት የገበያ ፍላጎታቸው እየተቀዛቀዘ በመምጣቱ ነው።

- መከላከያ ሰራዊት ነገ በአዲስ አበባ የቫይረሱን ስርጭትን ለመግታት የሚያግዙ መልዕክቶችን የያዙ በራሪ ወረቀቶችን በሄሊኮፕተር ይበትናል፡፡ በተጨማሪም የተለያዩ አካባቢዎች በመንቀሳቀስ በማርሽ ባንድ የታጀበ የማንቂያ ቅስቀሳ ያደርጋል፡፡

- አልማ የኮሮና ወረርሽኝን ለመከላከል ከ15 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቋል።

#DW #etv #EliasMeseret #fbc #ena
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከ7,600 በላይ ታራሚዎች እንዲፈቱ ተወስኗል!

የአማራ ክልል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ መሥሪያ ቤት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመከላከል በሚል ከ7,600 በላይ ታራሚዎችን በይቅርታ እንዲፈቱ ወስኗል።

ከእስር በይቅርታ እንዲፈቱ የተወሰነላቸው፦

- የሚያጠቡ እናቶች፣
- የአመክሮ ጊዜያቸው አንድ ዓመት የቀራቸው፣
- ቀላል ወንጀል ፈፅመው ጊዜያቸው አንድ ዐመት የቀራቸው፣
- የሌላ አገር እስረኛ ዜጎች ናቸው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#RUSSIA

ሩሲያ በአንድ ቀን ብቻ 9,623 ሰዎች በኮቪድ-19 መያዛቸው ተረጋገጠ። አብዛኞቹ በዋና ከተማዋ #ሞስኮ የሚኖሩ ናቸው። ይህ ቁጥር ወረርሽኙ ሩሲያ ከደረሰ በኋላ ከተመዘገቡት ሁሉ ከፍተኛው ነው።

በሌላ በኩል ባለፉት 24 ሰዓታት 57 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል። በመላ አገሪቱ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ የሞቱ ሰዎች ቁጥር ወደ 1,222 ማሻቀቡን ወረርሽኙን ለመቆጣጠር የተቋቋመው ኮሚቴ አስታውቋል።

የሞስኮ ከተማ ከንቲባ የሆኑት ሰርጌይ ሶብያኒን የከተማው ነዋሪዎች ራሳቸውን በመኖሪያ ቤታቸው ለይተው እንዲያቆዩ ተማፅነዋል።

በኮሮና ቫይረስ በጽኑ የታመሙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መሆኑን የተናገሩት ከንቲባው እጅግ የከፋ ደረጃ አለመድረሱን ገልጸዋል። ሁኔታው ከከፋ በሞስኮ ከተማ ለመንቀሳቀስ የሚሰጥ ፈቃድ ሊቀነስ እንደሚችልም ከንቲባው ገልጸዋል።

በሞስኮ ከተማ ነዋሪዎች ከመንግሥት ልዩ ፈቃድ ካላገኙ በቀር ከቤታቸው መውጣት የሚችሉት ዕቃ ለመሸመት፣ ውሾቻቸውን ለማንሸራሸር እና ቆሻሻ ለመጣል ብቻ ነው።

#DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopi