TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.96K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
'ከብርሃኔ አደሬ ሞል' በተላከልን መልዕክት ድርጅቱ በቦሌ ክፍለ ከተማ ባለው ህንፃ ለሱቅ እና ለቢሮ አገልግሎት ለተከራዩ 162 ተከራዮች የሶስት ወር የቤት ኪራይ 50 % ቅናሽ መድረጉ ተገልጾልናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኬንያ 9 ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፣ 1 ሰው ሞቷል!

ባለፉት 24 ሰዓት 800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቃላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥርም 225 ደርሷል። ዛሬ በቫይረሱ መያዛቸው ከተረጋገጡት 9 ሰዎች መካከል አምስቱ (5) ከናይሮቢ አራቱ (4) ከሞንባሳ ናቸው።

ከዚህ በተጨማሪ ተጨማሪ አንድ ሰው በቫይረሱ በመሞቱ የማቾች ቁጥር 10 ደርሷል። እንዲሁም አስራ ሁለት (12) ሰዎች ከቫይረሱ ማገገማቸው በመረጋገጡ አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 53 መድረሱን የኬንያ ጤና ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው መግለጫ አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮቪድ-19 ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለውም!

በመዘናጋት ከፍተኛ ዋጋ እንዳንከፈል በድጋሚ አደራ ለማለት እንወዳለን። በአሁን ሰዓት ለኮሮና ቫይረስ በሽታ [ኮቪድ-19] ምንም የተረጋገጠ ክትባትም ሆነ መድሃኒት የለውም።

በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች የምትሰሟቸው መረጃዎች በስራ ላይ ያሉ እጅግ በጣም ጊዜ የሚፈልጉ ናቸው። አሁን ያለው ብቸኛው መድሃኒት የጤና ባለሞያዎችን ምክር ማዳመጥ ነው።

ከሰሞኑን በአሜሪካ የጤና ተቋም CDC በኃላፊነት የሚሰሩት ዶክተር ኤርሚያስ በላይ ይህን ማለታቸው አይዘነጋም ፦ "...ለዚህኛው ቫይረስ [ለኮቪድ-19] ክትባት እንደሚገኝለት ተስፋ አደርጋለሁ። ግን ይሄን ክትባት ለማግኘት ብዙ ጊዜ ይወስዳል። ከ8-12 #ወራት ሊወስድ ይችላል።"

በተለያዩ ባልተጨበጡ መረጃዎች ፣ እንዲሁም በሂደት ላይ ባሉ የምርምር ስራዎች ዙሪያ የሚወጡ መረጃዎችን በመስማት የስፔን እና ጣልያን አሁን ደግሞ የአሜሪካ ዜጎች እየከፈለቱ ያለውን ዋጋ እንዳንከፍል አደራ።

እራሳችንን እንጠብቅ፤ የምንባለውን እናድምጥ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ወጣት ኢዘዲን ካሚል በኮሮና ቫይረስ ለተያዘ ሰው መተንፈሻ የሚሆን “ቬንትሌተር” ሰርቷል፡፡ አል አይን የአማርኛው አገልግሎት ክፍል ወጣቱን አነጋግሮታል ከላይ ባለው ቪድዮ ይመልከቱ።

📹5 MB
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ቡሌ ሆራ!

በዛሬው ዕለት በቡሌ ሆራ ከተማ እና አካባቢው ለማህበረሰቡ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን መከላከል ላይ ያተኮረ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራ ሲሰራ ውሏል።

የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራውን የሰሩት የቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ የጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ መምህራን ፣ የዩኒቨርስቲው አመራርና ሠራተኞች ፣ የም/ጉጂ ዞን አስተዳደር፣ የም/ጉጂ ዞን ጤና መምሪያ ከቡሌ ሆራ ሆስፒታል የጤና ባለሙያዎች ጋር በመተባበር ነው።

በቅስቀሳው ላይ የጉጂ አባ ጋዳ እና የኦሮሞ አባ ጋዳዎች ምክር ቤት ሰብሳቢ አባ ጋዳ ጅሎ ማንዶ እና የም/ጉጂ ዞን አስተዳደር አቶ አበራ ቡኖ ተገኝተዉ መልዕክት አስተላልፈዋል።

ምንጭ፦ ቡሌ ሆራ ዩኒቨርሲቲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች፦

- የኢትዮጵያ የፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት "በዚህ አስገዳጅ ምክንያት (በኮቪድ-19 ወረርሽኝ) የፖለቲካ ፓርቲዎች ለነሀሴ 23 ቀን 2012 ዓ.ም ተቆርጦለት የነበረውን የኢትዮጵያ ጠቅላላ ምርጫ የጊዜ ሰሌዳ በተረጋጋ መንፈስ የምርጫ ህጎችንና የአለም አቀፍ መስፈርት ባሟለላ መልኩ ማካሄድ እስኪቻል ድረስ መራዘም እንደሚኖርበት ተስማምተናል" ብሏል፡፡

- በትግራይ ክልል የሚገኙ የአቢሲንያ ባንክ፣ ሞሓ የለስላሳ መጠጦች እንዱስትሪ አ/ማ፣ ሆርን አፍሪካ ኮንስትራክሽን እና ንግድ አ/ማ እና የዓለም የምግብ ፕሮግራም ሰራተኞች በክልሉ የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ተግባር የሚውል ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ድጋፍ አድርገዋል፡፡

- በጋምቤላ ክልል የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ተጥሎ የነበረው የትራንስፖርት አገልግሎት እገዳ ማሻሻያ እንደተደረገበት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ ገልፀዋል MORE @TIKVAHETHMAGAZINE

- የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ተከትሎ የጤና ባለሙያዎችን፣ የሀይማኖት አባቶችን፣ አርቲስቶችንና በጎ ፈቃደኛ ወጣቶችን በማስተባበር የከተማው ነዋሪ እራሱን ከኮሮና ቫይረስ እንዲከላከል የግንዛቤ ማስጨበጫ ስራዎችን አከናውኗል፡፡

- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ ሥርጭት ምክንያት አብዛኛዉን የመንገደኞች በረራ ማቋረጡን ተከትሎ 60 በመቶ ለሚሆኑት ሰራተኞቹ የዓመት ፈቃድ መስጠቱን አስታውቋል።

ምንጭ፦ etv፣ WALATA፣ ኢዜአ፣ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬተሪያት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሀዲያ ዞን የትራንስፖርት እገዳው ይቀጥላል!

የሀዲያ ዞን ትራንስፖርትና መንገድ ልማት መምሪያ ኃላፊ አቶ ኤራጎ ሱጌቦ ከተናገሩት፦

- ከ07/08/2012 ዓ.ም ጀምሮ የትራንስፖርት አገልግሎት ይጀምራል የተባለ ቢሆንም የቫይረሱ ስርጭት እየተስፋፋ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ በሀዲያ ዞን ከሚገኙ የትራንስፖርት ማህበራት እና ከአንዳንድ ተሸከርካሪ ባለንብረቶች ጋር በተደረገው ውይይት የትራንስፖርት አገልግሎት ላልተወሰነ ጊዜ እንዲራዘም ከስምምነት ላይ ተደርሷል።

- በመናኻሪያ አካባቢ የሙቀት መለኪያን ጨምሮ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ባለመመቻቸታቸው እንዲሁም የሆሳዕና መናኻሪያ ጠባብ ከመሆኑ ጋር ተያይዞ የሰው ቁጥር ሊበዛ ስለሚችል የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠር አደጋች በመሆኑ ነው ውሳኔው የተላለፈው።

ምንጭ፦ የሀዲያ ህዝብ ግንኙነት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ፦

- በጣልያን ባለፉት 24 ሰዓት 578 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል፤ 2,667 ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል። በሟቾች እንዲሁም አዲስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር መቀነስ አሳይቷል።

- በሩሲያ በቫይረሱ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ ነው። ባልፉት 24 ሰዓት 3,388 በቫይረሱ ተይዘዋል። አጠቅላይ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 24,490 ደርሷል።

- በአሜሪካ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች ቁጥር 50,000 ደርሰዋል።

- በዩናይትድ ኪንግድደም ባለፉት 24 ሰዓት 761 ሰዎች ሞተዋል። 4,605 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

- በስፔን የሟቾች ቁጥር 18,579 ደርሷል። ባልፉት 24 ሰዓት 523 ሰዎች ሞተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ምክንያት በማድረግ የመማር ማስተማር ሒደቱ ቢቋረጥም፣ ልጆች ላልተማሩበት እንዲከፍሉ መደረጋቸውን ተከትሎ መንግሥት አዲስ ውሳኔ ሊያስተላልፍ እንደሆነ ተገልጻል።

የንግድ ውድድር እና ሸማቾች ጥበቃ ባለሥልጣን አቤቱታ ምርመራ ዳይሬክተር አቶ ጌትነት አሸናፊን ጠቅሶ አዲስ ማለዳ እንደዘገበው ወላጆች ልጆቻቸው ላልተማሩባቸው ጊዜያት ክፍያ እንዳይከፍሉ የሚያስችል ወሳኔ ሊተላለፍ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ለአስተማሪዎች የሚከፈለውን ክፍያን በተመለከተም መንግሥት ለአገልግሎቱ የተወሰነ ያህል ድጎማ ማድረግ እና የአስተማሪዎችን ክፍያ መሸፈን ሊታሰብበት ያስፈልጋልም ሲሉ ዳይሬክተሩ መግለጻቸው በዘገባው ተካቷል፡፡

https://addismaleda.com/archives/11059

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#WorldHealthOrganization ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ለኮሮናቫይረስ የሰጠው ምላሽ ቀርፋፋ ነው፤ በአካሄዱም ቻይናን ማዕከል አድርጓል ላሉት የዓለም ጤና ድርጅት አገራቸው የምታበረክተውን የገንዘብ መዋጮ እዲቋረጥ አዘዋል። ይህም ማለት አሜሪካ ለድርጅቱ በየዓመቱ ለድርጅቱ ትሰጥ የነበረው ገንዘብ እንዲቆም የሚያደርግ ነው ተብሏል። የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ የትራምፕን…
#DrTedrosAdhanom

የዓለም የጤና ድርጅት ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ቴድሮስ አድኃኖም አሜሪካ ለድርጅታቸው የምታደርገውን ድጋፍ አቋርጣለሁ ማለቷ እንዳሳዘናቸው ተናገሩ።

በውሳኔው ቅር ተሰኝተናል ያሉት ኃላፊው፤ "ለህብረተሰብ ጤና፣ ለሳይንስ እና ለሁሉም የዓለም ሕዝብ ያለ አድልዎ እና ፍርሃት ማገልገላችን ይቀጥላል" ብለዋል።

ዶክተር ቴድሮስ አሜሪካ የምትሰጠውን ፈንድ ማቋረጧ በድርጅታቸው ላይ የሚያስከትለውን ጉዳት እንደሚያጤኑት እና ሥራዎች ሳይቋረጡ መከናወናቸውን እንደሚያረጋግጡ መናገራቸውን ቢቢሲ ዘግቧል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ፣ ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዩኒክ ስታር ኮሌጅ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት በሚደረገው ጥረት ሀገራዊ ኃላፊነቱን መወጣቱን ገልጾልናል።

ኮሌጁ 400,000 ብር በገንዘብ እንዲሁም ወረርሽኙን ለመግታት የሚያገለግሉ የተለያዩ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

ከዚህ በተጨማሪ ኮሌጁ በሲዳማ ዞን በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር፣ ጩኮ፣ በንሳ፣ አርቤጎና የሚገኙትን ካምፓሶች ለኳራንቲን እንዲሆኑ ለመንግስት አስረክቧል።

የኮሌጁ ተማሪዎች የተቋረጠውን የመማር ማስተማር ስርዓት በያሉበት ሆነው እንዲቀጥሉ ለማድረግም የኦንላይን የትምህርት ስርዓት መዘርጋቱን አሳውቋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#FightCOVID19

'ፋልከን አካዳሚ' በላከልን መልዕክት በአዲስ አበባ ከተማ በንፋስ ስልክ ወረዳ 09 የሚገኘውን B+G+5 የትምህርት ቤት ሕንፃ የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት የሚደረገውን ጥረት ለማገዝ በማቆያነት እንዲያገለግል ለክፍለ ከተማው አስተዳደር በማስረከብ ማህበራዊ ግዴታውን መወጣቱን አሳውቆናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮ ቴሌኮም የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመከላከል እያደረገ ካለው ጥረት በተጨማሪ ዛሬ የ100,000,000 ብር ድጋፍ አድርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በፈረንሳይ ተጨማሪ 1,438 ሰዎች ሞቱ!

ባለፉት 24 ሰዓት በፈረንሳይ 1,438 ሰዎች መሞታቸው ሪፖርት ተደርጓል። አጠቅላይ የሟቾች ቁጥር 17,167 ደርሷል። በሌላ በኩል በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 147,863 የደረሰ ሲሆን ከእነዚህ ውስጥ 4,560 ሰዎች በአንድ ቀን በቫይረሱ የተያዙ ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SOMALIA #RWANDA #SUDAN

- በሩዋንዳ ባለፉት 24 ሰዓት 923 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ተጨማሪ ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል። አጠቅላይ በሀገሪቱ በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች 136 ደርሰዋል። በሌላ በኩል 5 ተጨማሪ ሰዎች አገግመዋል። አጠቃላይ ከቫይረሱ ያገገሙ ሰዎች 54 ደርሰዋል።

- ዛሬ በሱማሊያ 3 ሰዎች በመሞታቸው አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 5 ደርሷል። በቫይረሱ የተያዙ አጠቃላይ ሰዎች ቁጥርም 60 ደርሷል፤ ከእነዚህም ውስጥ የ20 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው ባለፉት 24 ሰዓት በተደረገ የላብራቶሪ ምርመራ ነው።

- በሱዳን ዛሬ አዲስ ኬዝ አልተመዘገበም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)

የኮሮና ቫይረስ በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ እና የስራ እድል ፈጠራ መስክ ላይ የሚያደርሰው ጉዳት ለሶስት ወራት ቢቀጥል 1.4 ሚልዮን ስራዎች ስጋት ውስጥ ሊወድቁ እንደሚችሉ የስራ እድል ፈጠራ ኮሚሽን ገለፀ።

ከኮሚሽኑ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው ቫይረሱ በስራ መስክ ላይ የጋረጠው ችግር ለስድስት ወራት ቢቀጥል ደግሞ 2.1 ሚልዮን ስራዎች ስጋት ውስጥ ይገባሉ።

"ከዚህ በተጨማሪ በውሎ ገብ ስራ የሚተዳደሩ 1.9 ሚልዮን ሰዎች በሶስት ወራት ውስጥ 8 ቢልዮን ብር ገደማ ገቢ ያጣሉ ስለዚህ የሴፍቲ ኔት ድጋፍ ይሻሉ" ብሏል ኮሚሽኑ።

መግለጫው ጉዳዩን ሲያብራራ "ወረርሽኙ በጤና ዘርፍ ላይ ከፍተኛ ተፅእኖ እንደፈጠረው ሁሉ ይህ ጫና መልኩን ወደ ስራ እና ማህበራዊ ቀውስነት ሲለውጥ በቀላሉ ሊጎዱ የሚችሉ ቢዝነሶችና ቀጥተኛ ጉዳት የሚያጋጥማቸው ቤተሰቦችን ገቢ በመቀነስ ከፍተኛ የኢኮኖሚ መናጋትን ሊያስከትል ይችላል" ይላል።

ይህ ትንተና አካላዊ ርቀት በማህበረሰቡ በመካከለኛ ደረጃ ቢጠበቅ የሚለውን ከግምት ውስጥ በማስገባት COVID-19 በኢትዮጵያ ኢኮኖሚ ላይ ሊያሳድር የሚችለውን ተጽዕኖ የሚያሳይ ነው የተባለ ሲሆን በስራ ዕድሎች ላይ ያንዣበበው ስጋት ሊያስከትል በሚችለው የገቢ መቃወስ ላይ ብቻ የሚያተኩር ነው።

በዚህ ሪፖርት ውስጥ የቀረቡ የፖሊሲ አማራጭ ሃሳቦች ያሉ ሲሆን በአሁኑ ወቅት በመንግስት አካላት ውይይት እየተደረገባቸው ያሉና ውሳኔ የሚሰጥባቸው ናቸውም ብሏል ኮሚሽኑ።

(ጋዜጠኛ ኤልያስ መሰረት)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ባለፉት 24 ሰዓት ውስጥ ፦

• በሩዋንዳ 923 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሁለት (2) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኬንያ 800 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ዘጠኝ (9) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በጅቡቲ 580 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሰባ ሁለት (72) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

• በኢትዮጵያ 431 የላብራቶሪ ምርመራ ተደርጎ ሶስት (3) ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia