TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.9K photos
1.44K videos
207 files
4K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
በኦሮሚያ ክልል 45 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ ተጠርጥረው ወደ ለይቶ ማቆያ ገብተዋል። ከነዚህ ውስጥ 22 ሰዎች በተደረገላቸው ምርመራ ከኮሮና ቫይረስ ነፃ መሆናቸው ተረጋግጧል። የተቀሩት ደግሞ ውጤታቸው እየተጠባበቁ ነው ተብሏል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኦሮሚያ ክልል አምስት መቶ ሺህ (500,000) የአፍ መሸፈኛ (ማስክ) እና 48,000 ሊትር ሳኒታይዘር እንዳዘጋጀ ገልጿል። በቅርቡ ለነዋሪዎች እንደሚያሰራጭ አሳውቋል።

በኦሮሚያ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በአራት አካባቢዎች የለይቶ ማቆያዎች ተዘጋጅተዋል። ለህክምና የሚያስፈልጉ ቁሳቁሶችም ተሟልተዋል ተብሏል።

በክልል የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ምልክት የታየበትን ሰው ጥቆማ ለመስጠት የ24 ሰዓት አገልግሎት የሚሰጥ ነፃ የስልክ መስመር 6955 ይፋ ተደርጓል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#TurkishAirlines

የቱርክ አየር መንገድ በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ወረርሽኝ ምክንያት ኢትዮጵያን ጨምሮ ከ5 አገሮች በስተቀር ዓለም አቀፍ በረራዎችን እ.ኤ.አ ከመጋቢት 27 ቀን 2020 ጀምሮ እንደሚያቆም አስታውቋል። አየር መንገዱ ወደ ሆንግ ኮንግ፣ ሞስኮ፣ አዲስ አበባ፣ ኒው ዮርክና ዋሽንግተን የሚያደርገው በረራ እንደማይቋረጥ የአየር መንገዱ ዋና ሥራ አስፈጻሚ የሆኑት ቢላል ኢክሲ ማስታወቃቸውን ሮይተርስ ዘግቧል።

#Reuters #etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኢትዮጵያ ድንበሮቿን ለሰዎች ዝውውር ዝግ አደረገች!

የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በአገሪቱ የሚገኙ ሁሉም ድንበሮች ለሰዎች ዝውውር ዝግ መደረጋቸውን ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ አስታውቀዋል።

ወረርሽኙን ለመከላከልም መንግስት አምስት ቢሊዮን ብር መበጀቱንም ነው ጠቅላይ ሚኒስትሩ ያስታወቁት።

በአውሮፕላን ከውጭ በሚገቡ መንገደኞች ላይ ለ14 ቀናት ተለይው እንዲያቆዩ የሚያስገድደው ውሳኔም ከዛሬ ጀምሮ በመተግበር ላይ ነው።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ ከደህንነት ዘርፍ ኃላፊዎች ጋር ውይይት አድርገዋል። ከውይይቱ በኋላ የሚከተሉት ዐበይት እርምጃዎች የሚተገበሩ መሆኑን ይፋ አድርገዋል፦

- ከዛሬ መጋቢት 14 ቀን አንስቶ፣ የደህንነት ዘርፉ በቁጥር የበዛ ሰው የሚሳተፍባቸውን ስብሰባዎችን የሚያስቆምና ማህበራዊ ርቀትን መጠበቅ የሚያስተገብር ይሆናል፡፡

- የፖለቲካ ፓርቲዎችን ጨምሮ የመንግስት ተቋማት ማህበራዊ ርቀትን ተፈጻሚ ማድረግና ስብሰባ ሲያካሄዱ ቫይረሱን የመከላከል ቅድመ ጥንቃቄዎችን ተፈጻሚ ማድረግ አለባቸው፡፡

- የመንግስት ተቋማት የተቀጣሪዎቻቸውን ሁኔታ በማጣራት እንደየሁኔታው አንዳንዶች በቤታቸውን ሆነው የሚሰሩበትን ሁኔታ ማመቻቸት፤

- የሕዝብ መጓጓዠ አገልግሎት ሰጪዎች አጨናንቆ ተሳፋሪዎችን መጫን የማይችሉ ሲሆን፣ ይህን ማድረጋቸው በትራፊክ ፖሊስና በበጎ ፈቃደኞች አማካኝነት ቁጥጥር የሚደረግበት ይሆናል፡፡

- ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊትና ፖሊስ ውስጣዊ ቅደመ ዝግጅት በማድረግ በአገር ደረጃ የቫይረሱ ስርጭት የመከላከል ስራን ለማስፈጸም ማዘጋጀት፣

- በተጠቃሚው ማህበረሰብ ላይ ሕገ ወጥ የዋጋ ጭማሪ የሚያደርጉ ተቋማት ላይ የሚወሰዱ እርምጃዎች የሚቀጥሉ ይሆናል፡፡

- መገናኛ ብዙሃን በትኩረት በየደረጃው ግንዛቤን የማሳደግ ሚናን መጫወት ይጠበቅባቸዋል፡፡

- ብሔራዊ የመከላከያ ሰራዊት በድንበር አከባቢ የሚደረጉ እንቅስቃሴዎችን በሙሉ ይገታሉ፡፡ ይህ እርምጃ ወደ አገሪቱ የሚገቡ ሸቀጦችና አስፈላጊ መገልገያዎችን አይጨምርም፡፡

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በአፍሪካ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ የተከሰተባቸው አገራት አርባ ሶስት (43) መድረሳቸውን እና በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 1 ሺህ 396 መድረሱን የዓለም ጤና ድርጅት አስታውቋል። በቫይረሱ ከተያዙት ውስጥ በአሁኑ ሰዓት 122 ሰዎች ማገገማቸውን ድርጅቱ ጠቁሟል።

ናይጄሪያ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት የመጀመሪያውን ሞት ማስመዝገቧን ደግሞ ቢቢሲ የሀገሪቱን የበሽታ መቆጣጠሪያ ማዕከል ጠቅሶ ዘግቧል።

በቫይረሱ ምክንያት ሕይወቱ ያለፈው እንግሊዝ ውስጥ የሕክምና ክትትል ሲያደርግ ቆይቶ ወደ ሀገሪቱ የተመለሰ አንድ የ67 ዓመት ግለሰብ መሆኑ ነው የተነገረው።

#BBC #WHO #ETV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮቪድ-19 ህይወቱ ያለፈው የ30 ዓመቱ ጋዜጠኛ!

ዚምባቡዌ ውስጥ ሕይወቱን ያጣው የሰላሳ (30) ዓመቱ የብሮድካስት ጋዜጠኛ ዞሮሮ ማካምባ ይባላል። በኮሮና ቫይረስ ወጣት ሊሞት አይችልም ተብሎ የሚነገረውን ሐሰት ያደረገው ይኸው ሞት ዚምባቡዌያውያንን አስደንግጧል።

ጋዜጠኛው በአገሩ የታወቀ እንደነበር እና የሀብታም ቤተሰብ ልጅም እንደሆነ ተዘግቧል። ቅዳሜ በቫይረሱ እንደተጠቃ በምርመራ የተረጋገጠው ዞሮሮ የጤናው ሁኔታ በፍጥነት ስላሽቆለቆለ በአገሪቱ መዲና ሀራሬ በጽኑ ሕሙማን ማቆያ ገብቶ ነበር።

#BBC #ETV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኮሮና ቫይረስ የተያዘ 1 ተጨማሪ ሰው መገኘቱ ተገለፀ!

መጋቢት 3/2012 ዓ.ም የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ በሀገራችን ከተገኘ ወዲህ በኮሮና ቫይረስ የተያዘ አንድ (1) ተጨማሪ ሰው በመገኘቱ በአጠቃላይ ቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል።

ታማሚው የ34 ዓመት ኢትዮጵያዊ ሲሆን ከዱባይ ወደ ሀገር ውስጥ መጋቢት 10 ቀን 2012 ዓ.ም የገባ ነው።

ግለሰቡ የሕመም ምልክት የነበረው በመሆኑ በመጋቢት 13 ቀን 2012 ዓ.ም ወደ ጤና ተቋም የሄደ ሲሆን ተቋሙም ለኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ሪፖረት በማደረግ በተደረገለት የላብራቶሪ ምርመራ በቫይረሱ መያዙ ተረጋግጧል።

ታማሚውም በለይቶ ማከሚያ ውስጥ የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን ጤንነቱ በመልካም ሁኔታ ላይ ይገኛል፤ ከዚሁ ጋር በተያያዘ ከታማሚው ግንኙነት የነበራቸው 15 ሰዎች በክትትል ላይ እንደሚገኙ የኢትዮጵያ ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል።

#etv
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia