TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሰበር ዜና!

ወደ ኳታር የሚደረጉ ማንኛውም የጉዞ በረራዎች [ከትራንዚት እና ከካርጎ በስተቀር] ከፊታችን ረቡዕ ጀምሮ ለ14 ቀናት ያክል ተከልክለዋል። የቀጠር ዜጎች ከየትኛውም አገር ወደ ዶሃ መግባት ይችላሉ ተብሏል።

መንግስት ማንኛውም የአገሪቱ ዜጋ እንዲሁም የአገሪቱ ነዋሪ ወደ ውጭ አገር ጉዞ እንዳያደርጉ አሳስቧል። እድሜያቸው ከ 55 በላይ የሆኑ፣ ነፍሰ ጡሮች እና ከባድ ህመም ያለባቸው ሰዎች ሥራቸውን በርቀት እንዲሰሩ ተወስኗል።

የሕዝብ ትራንስፖርት አገልግሎቶች ከዛሬ ምሽት ጀምሮ እንዲቆሙ ተወስኗል። የመንግስት ትምህርት ቤት ተማሪዎች ከሚቀጥለው እሁድ ጀምሮ ትምህርታቸውን በርቀት መማር ይጀምራሉ።

ምንጭ፦ የኢትዮጵያ ኤምባሲ -ዶሃ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
ጤና ሚኒስቴር! የአምቡላንስ መኪና መስታወት ሰብሮ ያመለጠው ከሳውዲ አረቢያ የመጣው ግለሰብ በአሁኑ ወቅት በደቡብ ወሎ ዞን ለጋምቦ ወረዳ በቁጥጥር ስር ውሎ እንደሚገኝ ያታወቃል። ጤና ሚኒስቴር ከግለሰቡ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸውን ግለሰቦች የመለየት ስራ እየሰራ እንደሚገኝ የገለፀ ሲሆን ግለሰቡን በቁጥጥር ስር ለማዋል ከፌዴራል እና ከለጋምቦ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽ/ቤት እንዲሁም የፀጥታ መዋቅሩ የጋር…
#UPDATE

የለጋምቦ ወረዳ ዋና አስተዳዳሪ ለቪኦኤ በሰጡት መረጃ ከአምቡላንስ አምልጦ የጠፋው የኮሮና ቫይረስ ተጠርጣሪ ግለሰብ ተሳፍሮበት በነበረው አውቶብስ ውስጥ የነበሩ 74 የሚደርሱ ሰዎች ቦሩሜዳ ወደሚገኘው የማቆያ ስፍራ ተወስደዋል።

በሌላ በኩል የደቡብ ወሎ ዞን ጤና መምሪያ ፥ ግለሰቡ ምልክቶች ታዩበት እንጂ በበሽታው መያዙ አልተረገጠም፤ ማኅበራዊ ድረ ገፆችና አንዳንድ የመንግሥት ተቋማት በገፆቻቸው ይዘውት የወጡት ዘገባ ኃላፊነት የጎደለው ነው ሲል ተችቷል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር ዓለም አቀፍ መረጃዎች፦

- አውስትራሊያ ከዛሬ ጀምሮ ማንኛውም ወደ ግዛቷ የሚገባ ሰው ራሱን ለ14 ቀናት ለይቶ እንዲያቆይ አዛለች። ኒውዚላንድም ቀደም ሲል ተመሳሳይ ርምጃ ወስዳለች።

- አየርላንድና ታላቋ ብሪታኒያን ጨምሮ የአውሮፓ ኅብረት የኮሮናቫይረስ እገዳን ከመጪው ማክሰኞ ጀምረው ሊተገብሩ ነው።

- ብሪታኒያ በ24 ሰዓታት ውስጥ በቫይረሱ የሞቱ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ በመጨመሩ 21 ደርሷል። ይህንንም ተከትሎ ከ200 በላይ የሚሆኑ ሳይንቲስቶች ጠንካራ እርምጃ እንዲወሰድ ደብዳቤ ጽፈዋል።

- ታላቋ ብሪታኒያ ወሳኝ ጉዞዎች ካልሆኑ በስተቀር ወደ ስፔን የሚደረገውን ማንኛውንም ጉዞ እንድታቋርጥ ተነግሯታል።

- ካናዳ በውጭ የሚኖሩ ዜጎቿ ወደ አገራቸው እንዲመለሱ ጥሪ አቅርባለች። ቺሊ ደግሞ በመርከብ ተጉዘው የመጡ 1300 ዜጎቿን በለይቶ ማቆያ አስቀምጣለች። በሌላ በኩል በእስራኤል ከዛሬ ጀምሮ የንግድ ተቋማት በከፊል እንዲዘጉ ተዳርጓል።

[በቢቢሲ አማርኛ ጋዜጠኞች]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አጫጭር መረጃዎች ከአፍሪካ፦

- በደቡብ አፍሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠቂዎች ቁጥር 61 ደርሷል። በ24 ሰዓት ውስጥ ብቻ 23 አዲስ ኬዞች ተመዝግበዋል።

- በሞሮኮ 10 ተጨማሪ አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ተመዝግበዋል። በሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች 28 ደርሰዋል።

- በቱሪዝያ 2 አዲስ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዞች ዛሬ ተመዝግበዋል። የቫይረሱ ተጠቂዎች 20 ደርሰዋል።

- ጋና በ24 ሰዓት ውስጥ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው በመረጋገጡ የተጠቂዎች ቁጥር ወደ 6 ከፍ ብሏል።

- በአይቮሪኮስት 2 የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ተጠቂዎች ዛሬ ተገኝተዋል። አጠቃላይ ተጠቂዎች 4 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
'ምህላ ታውጇል'

ዛሬ 3 በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች መገኘታቸውን ተከትሎ ምእመናን በጤና ሚኒስቴር በኩል የሚሰጡ መመሪያዎችን እንዲተገብሩ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ አሳስበዋል።

የቤተክርስትያኗ ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ በቀሪው የዐቢይ ፆም ጊዜያት በሁሉም የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን አድባራት እና ገዳማት የምህላ ጸሎት እንዲደረግም አውጀዋል፡፡

#EOTCTV
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ማጠቃለያ!

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 6,492 የደረሰ ሲሆን 168,834 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 76,598 ደርሰዋል።

ውድ የቲክቫህ ቤተሰቦች፦

- በፍፁም እርጋት እራሳችሁን ጠብቁ። ከጤና ሚንስቴር እና የጤና ባለሞያዎች የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ሳትሰለቹ ተግብሩ።

- ህዝብ የሚበዛባቸው ቦታዎች ላይ በፍፁም እንዳትገኙ፣ የቫይረሱ ስርጭት ወዳለባቸው ሀገራትም ጉዞ ካላችሁ ሰርዙ።

- የእጃችሁን ንፅህና መጠበቅ እንዳትረሱ፣ ከኮቪድ-19 ጋር የሚመሳሰሉ ምልክቶች ከተሰማችሁ በአስቸኳይ ለህክምና ተቋም ጥቆማ ስጡ፣ በሶሻል ሚዲያ ወሬዎች አትሸበሩ።

More 8335

ሰላም እደሩ!
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጉዳዩ ፦ ማስታወቂያዎች ለጥቂት ቀናት ማቆማችንን ስለማሳወቅ!

ለድርጅት ባለቤቶች ለሆናችሁ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት!

በእንዲህ ያለ ወቅት በተለይም የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እየተፈጠሩ ባሉ ክስተቶች ዙሪያ በቂ የሆነ ግንዛቤ እንዲያገኙ ፣ በተለያዩ ሚዲያዎችም የሚሰራጩ መረጃዎች በፍጥነት ይደርሳቸው ዘንድ እንደምንሰራ ይታወቃል።

እንዲህ ያለሁ ክስተቶች ሲፈጠሩ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ተመልካች ቁጥር በሰዓታት ውስጥ በመቶ ሺህ የሚቆጠር እንደሆነም ይታወቃል፤ ይህን መሰል ወቅት ወቅታዊ ጉዳዮች አሳስቧቸው መረጃ በሚከታተሉ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት ስልኮች ላይ ምንም አይነት የድርጅት ማስታወቂያ አናሰራጭም።

ይህ አሁን የጀመርነው እንዳልሆ እና ከዚህ ቀደምም ለበርካታ ጊዜያት ስናደርግ የቆየነው እንደሆነም ለማስታወስ እንወዳለን። ረጅም ጊዜ ከቲክቫህ ጋር አብራችሁ የቆያችሁ ድርጅቶችም አሰራራችን እና የምንከተለውን መንገድም እንደምታውቁት ተስፋ እናደርጋለን።

የቲክቫህ አባል የሆናችሁ የድርጅት ባለቤቶች ማስታወቂያ የማስነገር ሙሉ መብት እንዳላችሁ ብናውቅም፤ በእንዲህ ያሉ ወቅቶች ግን የድርጅቶቻችሁን ማስታወቂያ ማስተናገድ አንችልም! ለዚህም ይቅርታ እንጠይቃለን።

ከጥቂት ቀናት በኃላ ማስታወቂያዎች ይቀጥላሉ!

[email protected]
0919743630
@tsegabwolde

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ኬንያ የኮሮና ቫይረስ ከተመዘገበባቸው አገራት የሚመጡ ስዎች ወደ ግዛቷ እንዳይገቡ እገዳ የጣለች ሲሆን ኬንያዊያንና የመኖሪያ ፍቃድ ያላቸው ብቻ መግባት የተፈቀደላቸው ሲሆን ለ14 ቀናት እራሳችውን አግልለው መቆየት ይጠበቅባቸዋል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጃፓናዊው ኦሮሚያ ክልል የተንቀሳቀሰው 1 ቀን ነው!

የኦሮሚያ ጤና ቢሮ ምክትል ኃላፊ አብዱልቃድር ገልገሎ በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ከሆነው ጃፓናዊው ግለሰብ ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሰዎች በተጨማሪ ክትትል እየተደረገባቸው መሆኑን ትላንት ምሽት ለቪኦኤ ተናግረዋል።

ዶክተር አብዱልቃድር ገልገሎ ፥ 'ማን የት ነበር? ማን ጋር ነበር? ተብሎ እየተፈለገ መሆኑን የተናገሩ ሲሆን ጃፓናዊው ግለሰብ አንድ ቀን ብቻ ወደ ኦሮሚያ ክልል እንደሄደ ጠቁመዋል።

ግለሰቡ በአዳማ አቋርጦ ወደ ዴራ አርሲ ሄዶበት የነበረው ዋነኛው ምክንያት ከሚሰራበት የተርአድኦ ድርጅት ስራ ጋር በተያያዘ የትምህርት ጉዳይ ለመከታተለ እንደሆነ ነው ዶ/ር አብዱልቃድር የተናገሩት።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መዘናጋቱ ሀገሪቱን ዋጋ እንዳያስከፍላት!" - ቲክቫህ ቤተሰብ አባላት

የኢትዮጵያ መንግስት ውሳኔዎች ላይ መዘግየት ይታይበታል ሲሉ መልዕክቶቻቸውን እየላኩ የሚገኙ የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት ቅሬታ አሰምተዋል።

ጎረቤት ሀገራት እንኳን የወሰዱትን ፈጣን የጥንቃቄ እርምጃ የኢትዮጵያ መንግስት እንዴት ሊወስድ እንዳልቻልም ጠይቀዋል። የቫይረሱ በፍጥንነት መስፋፋት እየታወቀ እንዲህ ያለ መዘንጋት መታየቱ እንዳሳዘናቸውም ተናግረዋል።

ሩዋንዳ ፣ ሱዳን ፣ ኬንያ ሌሌችም ሀገራት ከወዲሁ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ለመግታት ድንበራቸውን መዝጋት፣ የትምህርት ተቋማትን መዝጋት ፣ ስፖርታዊ ክንውኖችን መሰረዝ፣ የአደባባይ ሃይማኖታዊ ስነ ስርዓቶችን መሰረዝ ፣ ከዚህ አለፍ ሲልም ከቫይረሱ ተጠቂ ሀገራት ማንኛውም ዜጋ እንዳይገባ እስከማገድ ደርሰዋል።

4 የቫይረሱ ተጠቂዎች የሚገኙባት ኢትዮጵያ መንግስት እስካሁን ጠንካራ እርምጃ አለመውሰዱን የቲክቫህ ቤተሰብ አባላት አምርረው ተችተዋል። ይህ መዘናጋት ሀገሪቱን ዋጋ እንዳያስከፍላትም አስጠንቅቀዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ 4 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በሩዋንዳ!

በሩዋንዳ ተጨማሪ 4 ሰዎች በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መጠቃታቸውን የሀገሪቱ የጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል። በሀገሪቱ የሚገኙ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ቁጥር 5 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ጣሊያን በትናንትናው ዕለት 368 ዜጎቿን ስታጣ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር ወደ 1 ሺህ 809 አሻቅቧል።

ስፔን 97 ዜጎቿ የሞቱባት ሲሆን አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 288 ደርሷል። በፈረንሳይም በትናንትናው ዕለት 29 ሰዎች ሲሞቱ በአጠቃላይ 120 ዜጎቿን በኮሮናቫይረስ ተነጥቃለች።

የዩናይትድ ኪንግደምም ትናንት ብቻ 14 ሰዎች የሞቱባት ሲሆን በአጠቃላይ ደግሞ የሟቾች ቁጥር ወደ 35 አድጓል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ መከላከያ ክትባት!

አሜሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] መከላከያ ክትባትን በሙከራ ደረጃ ዛሬ መስጠት እንደምትጀምር አስታውቃለች፡፡

የአሜሪካ ባለስልጣናት እንዳስታወቁት፣ ዛሬ የሚሰጠዉ የሙከራ ክትባት በ45 ፈቃደኛ ሰዎች ላይ የሚከናወን ሲሆን ክትባቱ ምንም አይነት የጎንዮሽ ጉዳት እንደማያደርስ ነዉ የተነገረዉ፡፡

ምርምሩን የሀገሪቱ ታላላቅ የጤና ተቋማት /የአሜሪካ ብሄራዊ ጤና ተቋም፣ ዋሽንግተን ሄልዝ ሪዘርች ኢንስቲትዩት፣ NIH and Moderna Inc እና ሌሎችም በጋራ ሲያካሂዱ መቆየታቸዉን ኤ ፒ ጽፏል፡፡

ሀገራት የመከላከያ ክትባቱን በእጃቸዉ ለማስገባት ከፍተኛ እሽቅድምድም ላይ በሆኑበት በዚህ ሰዓት አሜሪካ ወደ ማረጋገጫ ሙከራ ተሸጋግራለች፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች ጉዳይ! በከተማ አስተዳደሩ ቤቶች ልማትና አስተዳደር ቢሮ የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ዋና ዳይሬክተር በአቶ ደሳለኝ ተረፈ ፊርማ ሰሞኑን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች የተላከው ደብዳቤ እንደሚያስረዳው፣ ዕጣ የወጣባቸው የጋራ መኖሪያ ቤቶች በተያዘው ወር ዕጣ ለወጣላቸው ሰዎች ይተላለፋሉ፡፡ ነገር ግን በኦሮሚያና በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ወሰን ላይ የተገነቡ ቤቶች ዕጣ ፈንታ…
የ20/80 የኮንዶሚኒየም ዕጣ የደረሳቸው ዕድለኞች ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ ተደርጎላቸዋል!

ከአንድ ዓመት በፊት የካቲት 27/2011 ዓ.ም. ለ13ኛ ጊዜ ዕጣ የወጣባቸውና 20/80 የጋራ መኖሪያ ቤቶች የደረሳቸው ዕድለኞች፣ በየወረዳቸው ቀርበው ውል እንዲዋዋሉ ጥሪ እንደተደረገላቸው ሪፖርተር ጋዜጣ ዘግቧል፡፡

በከተማ አስተዳደሩ በቤቶች ልማት እና አስተዳደር የቤቶች ልማት ኮርፖሬሽን ለአሥሩም ክፍላተ ከተሞች ባስተላለፈው መመርያ መሠረት ፣ ክፍላተ ከተሞቹ ከዕድለኞቹ ጋር ውል እንዲዋዋሉ ለወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች መመርያውን ማስተላልፋቸውን ነው ጋዜጣው የጠቆመው፡፡

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
መሟላት ስለሚገባቸው መስፈርቶች፦

ከክፍላተ ከተሞቹ መመርያ የተላለፈላቸው የወረዳ ቤቶች አስተዳደር ጽሕፈት ቤቶች ፣ የጋራ መኖሪያ ቤት የደረሳቸው ዕድለኞች ውል ለመዋዋል ወደ ጽሕፈት ቤቶቹ ሲሄዱ ማሟላት የሚገባቸውን መሥፈርቶች በዝርዝር አሳውቀዋል።

ዕጣው የደረሳቸው ዕድለኞች የታደሰ መታወቂያ ፣ ያገባ (ች) ከሆኑ የጋብቻ ሰርተፊኬት ፣ ባልና ሚስት ከሚኖሩበት ወረዳ በስማቸው የግልም ሆነ የመንግሥት ቤት እንዳላቸው ወይም እንደሌላቸው የሚገልጽ ደብዳቤ ይዘው መቅረብ አለባቸው።

ያላገባ (ች) ከሆነ በስድስት ወራት ውስጥ የታደሰ ሰርተፊኬት ፣ የባንክ ደብተር፣ የተመዘገበው ዕድለኛ ከሌለ (ች) ሕጋዊ ውክልና ያለው(ላት) መሆን አለበት(ባት)።

ምንጭ፦ ሪፖርተር ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከኮሮና ቫይረስ ጋር በተያያዘ ሰራተኞቹ ለዛሬ ከቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ አድርጓል። መስሪያ ቤቱ ከውሳኔው ላይ የደረሰው ለቦርዱ ቴክኒካዊ ድጋፍ ከሚሰጡ የውጭ ሀገር ባለሙያዎች መካከል አንድ ግለሰብ የቫይረሱ ምልክቶች ስለታዩበት ነው።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ግለሰቡ በቫይረሱ መያዙ አልተረጋገጠም!

ምርጫ ቦርድ ሰራተኞቹ ቤታቸው ሆነው እንዲሰሩ ያደረገው ለቅድመ ጥንቃቄ እንደሆነ ሰምተናል። በግለሰቡ ላይ የታየው ምልክት ቫይረሱ ይሁን፣ አይሁን ገና አልተረጋገጠም። በማህበራዊ ሚዲያዎች ላይ እየተሳጩ ያሉት መረጃዎች ግነት ያለባቸው ናቸውም ተብለናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

"ትምህርት ቤቶችን መዝጋት የሚያስገድድ ሁኔታ የለም!" - ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ

በትምህርት ሚኒስቴር የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ የሆኑት ወይዘሮ ሐረጓ ማሞ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንደተናገሩት ቫይረሱ በትምህርት ቤቶች እንዳይስፋፋ ትምህርት ቤቶች ከጤና ተቋማት ጋር በትብብር እየሰሩ መሆኑን ገልፀዋል።

እስካሁን ባለው መረጃ ኮሮና ቫይረስ ከአዲስ አበባ ውጪ አልተከሰተም ያሉን ሲሆን ተማሪዎች እና መምህራን ከቫይረሱ እራሳቸውን እንዲጠብቁ በትምህርት ሚኒስቴር ቴሌዥን እና በትምህርት በሬድዮ ፕሮግራሞች እያስተማርን ነው ብለዋል።

በቫይረሱ ስርጭት ሳቢያ ትምህርት ቤቶች ሊዘጉ ይችላሉ? በሚል ለተነሳላቸው ጥያቄም አሁን ላይ ትምህርት ቤቶችን መዝጋት የሚያስገድድ ሁኔታ የለም ይሁንና መንግስት በቀጣይ ውሳኔ ይሰጥበታል ሲሉ ምላሽ ሰጥተዋል።

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትምህርት ቤትን መዝጋት በተመለት!

የአዲስ አበባ ትምህርት ቢሮ ትምህርት ቤትን መዝጋት በተመለከተ ለጊዜው የተወሰነ ውሳኔ የለም፤ በሁሉም ትምህርት ቤቶች የመማር ማስተማሩ ስራ ይቀጥላል ሲል ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ተናግሯል።

የቢሮው ኃላፊ አቶ ዘላለም ሙላቱ ወላጆች ፣ የትምህርት ቤት ባለቤቶች ፣ የትምህርት አመራሩም በዚህ ጉዳይ ጥያቄ እያቀረበ መሆኑን አንስተው ወላጆች፣ ተማሪዎችም እርሳቸውን በማረጋጋት የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲቀጥሉ ጥሪ አቅርበዋል።

የተለየና እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ላይ በሚደረስበት ወቅት እና ስጋቱ መጠን ከፍተኛ ሲሆን ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመነጋገር መግለጫ እንደሚሰጥ ጠቁመዋል፤ ለጊዜው የትምህርት ቤት አመራሮች፣ መምህራንና ተማሪዎች በከፍተኛ ጥንቃቄ የመማር ማስተማር ሂደቱን እንዲመሩና እንዲሳተፉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ ትምህርት አቋረጠ!

ናይሮቢ ዩኒቨርሲቲ ከኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስርጭት ስጋት ጋር በተያያዘ የመማር ማስተማር ስራውን አቋርጧል። በዚህ ሳምንት ሊሰጡ የነበሩ ፈተናዎችም ተሰርዘዋል። ትምህርት በኦንላይ እንዲቀጥል ተብሏል። በአሁን ሰዓት በኬንያ በኮሮና ቫይረስ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 3 ናቸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia