TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን በዋና ከተማዋ መጠቀም ጀምራለች።

ሩዋንዳ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ካልተመዘገበባቸው የሰብ ሳህራን አፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነች።

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ወረርሺኙን ቀድሞ ለመከላከል በዋና ከተማ ኪጋሊ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን ዜጎቿ እንዲጠቀሙ ተግባራዊ አድርጋለች።

በሩዳንዳ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮቹ የተተከሉት ባንኮች ፣ በገበያ ማዕከላት ፣ በባስ ስቴሽኖች እና በሬስቶራንቶች ውስጥ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

#ሮይተርስ #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መንግስት ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወደሀገር እንዳይገባ ጠበቅ ያለ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚገባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አስገንዝበዋል።

መልዕክቶቻቸውን በ @tikvahethiopiaBot የላኩ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን አባላት አየር መንገዱ ቫይረሱ ወደተስፋፋባቸው ሀገራት በረራውን እንዲያቋርጥ በድጋሚ ጠይቀዋል።

እንዲሁም መንግስት የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ውጭ ሀገራት የሚያደርጉት ጉዞ እንዲያግድ፣ ቫይረሱ ካለባቸው ሀገራትም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ለጊዜው ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ በድንበር አካባቢዎች በተለይም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አስፈላጊው እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ከህዝብ ደህንነት የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ድንበሩን መዝጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል!

"ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤ በተደረገው ምርመራ አንድ (1) ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች እንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" - ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጤና ሚኒስቴር ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በተመለከተ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ስለተያዘው ግለሰብ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ፦

- ቫይረሱ የተገኘበት ጃፓናዊው ግለሰብ 48 ዓመቱ ነው።

- የካቲት 25 ነው ከቡርኪነፋሶ ወደ አዲስ አበባ የመጣው።

- በሽታው የጀመረው ከ 3 ቀን በፊት ነው።

- ዛሬ ለሊት በሽታው እንዳለበት ተረጋግጧል።

- እስካሁን የከፋ የሚባል የጤና እክል አላጋጠመውም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በኮሮና ቫይረስ ከተጠቃው 'ጃፓናዊ ግለሰብ' ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦች የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል፡፡ ታማሚው ፣ አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ፣ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ሚኒስትር ዶክተር ሊያ ታደሰ፦

"በኮሮና ቫይረስ የተያዘ ግለሰብ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱን አረጋግጠናል፡፡ ግለሰቡ፣ የ48 አመት የጃፓን ዜጋ ሲሆን፣ የካቲት 25/ 2012 ዓ/ም ከቡርኪና ፋሶ ወደ አዲስ አበባ መምጣቱ ታውቋል፡፡ ከበሽተኛው ጋር የቅርብ ንክኪ የነበራቸው ግለሰቦችም የመለየትና ክትትል የማድረግ ስራ ተጀምሯል፡፡ ታማሚው፣ አስቀድሞ በተዘጋጀው የለይቶ ማከሚያ፣ ተገቢው የሕክምና ክትትል እየተደረገለት ሲሆን፣ እስካሁን ባለው ሁኔታ የከፋ የጤና እክል አልገጠመውም፡፡"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ፦

- ትላንት Positive ሆኖ የተገኘው ጃፓናዊው ግለሰብ የመጀመሪያው የጉዞ ታሪክ የሚያሳየው ከጃፓን እንደተነሳ ነው።

- FEBRUARY 23 ቡርኪነፋሶ ገብቷል። MARCH 4 ደግሞ አዲስ አበባ ገብቷል።

- አዲስ አበባ ከገባ በኃላ በMARCH 9 ከ5 ቀን በኃላ ምልክት ማሳየት ስለጀመረ ጤና ተቋም ይሄዳል፤ በዚህም ወቅት ለህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ጥቆማ ይደርሰዋል።

- የፈጣንሽ ምላሽ የሚሰጠው ግብረ ኃይል ለጃፓናዊው የሚያስፈልገውን ምርመራና ክትትል ካደረገ በኃላ በለይቶ ማቆያ ጣቢያ ውስጥ እንዲቆይ ተደርጓል።

- በትላንትናው ዕለት እዛው የለይቶ ማቆያ ጣቢያ እያለ ናሙናው ተሰርቶ ቫይረሱ እንዳለበት ተረጋግጧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለጊዜው ሊደረጉ የሚገባቸው ጥንቃቄዎች፦

- በጣም የሚጨናነቅ ቦታዎች ላይ አለመገኘት ይመከራል።

- አውቶብሶች ፣ የህዝብ ትራንስፖርት ላይ መስኮቶች እንዲከፈቱ እና አየር እንዲገባ ማድረግ ተገቢ ነው።

- በተቻለ መጠን የተጨናነቀ አውቶብስ ፣ ሌሎችም የትራንስፖርት አማራጮችን ከመጠቀም መቆጠብ ያስፈልጋል።

- በተጨናነቁ የህዝብ ትራንስፖርቶች ከመጠቀም ይልቅ ከተቻለ በእግር መሄድ ይመከራል።

- የጉንፋን ስሜት፣ ትኩሳት፣ ህመም የሚሰማችሁ ሰዎች ትልልቅ ስብሰባዎች ላይ ከመገኘት ተቆጠቡ። በተጨማሪ ወደስራም፣ ወደ ትምህርት ቤትም ባይሄዱ ይመከራል።

#ሼር #SHARE

#DrLiaTadesse
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የማስክ ጉዳይን በሚመለከት፦

- ይሄ በሽታ ተከሰተ ማለት ሁሉም ማስክ ያድርግ ማለት አይደለም።

- አሁን ባለው ሁኔታ ማስክ ማደረግ የሚጠበቅባቸው ሰዎች ዋነኛዎቹ በኮሮና ቫይረስ በሽታ የተያዙ ፣ የጉንፋን መሰል ምልክቶች የሚታይባቸው ፣ የማሳል ፣ ትኩሳት ያለባቸው ሰዎች ወደሌላ እንዳያስተላልፉ ማስክ እንዲያደርጉ ያስፈልጋል።

- በኮሮና ቫይረስ ለሚጠረጠሩ ሰዎች የህክምና ድጋፍ እና ክትትል የሚያደርጉ የጤና ባለሞያዎችም ማስክ መጠቀም አለባቸው።

#DrLiaTadesse

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቃሚ ምክሮች፦

- ሳል ወይም ትኩሳት ካለው ግለሰብ ቢያንስ ሁለት የአዋቂ እርምጃ ርቀት ያህል መራቅ
- እጅዎን በአግባቡ ሳይታጠቡ አይንና አፍንጫዎን አይንኩ
- ከሰዎችጋር አይጨባበጡ፣
- እጅን በንጹህ ውሃና ሳሙና አዘውትረው ይታጠቡ፣
- ሰዎች ወደ በሚበዙባቸው ቦታዎች በተለይም የህመም ስሜት ካልዎት አይሂዱ፣
- በሚያነጥሱበት እና በሚያስሉበት ጊዜ አፍና አፍንጫዎን በሶፍት ወይም ክርንዎን አጥፈው በመጠቀም ወደ ሌሎች እንዳያስተላልፉ ይጠንቀቁ፣ የተጠቀሙበትን ሶፍትና ተመሳሳይ ነገሮች በቆሻሻ ክዳን ባላቸው ማጠራቀሚያ ያስወግዱ፣
- በስራ ቦታ፣በትራንስፖርት እና መኖሪያ ወይም የመኝታ ክፍል መስኮት በመክፈት በቂ አየር እንዲኖር ያድርጉ፣
- መረጃዎችን ከአስተማማኝ ምንጮች ብቻ በመቀበል፣ የተሳሳቱ መረጃዎች የሚያስከትሉትን መደናገር እና ፍርሀት እርሶም ይከላከሉ!

#ሼር #SHARE

#ጤናሚኒስቴር
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19ETHIOPIA

የኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘቱ ይፋ ከተደረገ በኃላ በአዲስ አበባ ከተማ የሚኖሩ ነዋሪዎች የፊት ማስክ እና ጓንት ለመግዛት አንዳንድ ፋርማሲዎች ተሰልፈው ታይተዋል።

በአዲስ አበባ ከሚኖሩ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት እንደተነገረን ከሆነ የፊት ማስክ ላይ ከፍተኛ የሆነ የዋጋ ጭማሪም አድርገው የሚሸጡ አካላት እንዳሉ አስተውለዋል።

አንዳንድ ፋርማሲዎች ደግሞ ሰሞኑን ሲሸጡ የነበረውን የፊት ማስክ፣ የእጅ ማፅጃ አልኮል እና የመሳሰሉት ነገሮችን የለም፣ ጨርሰናል የማለትም ነገር እየታየባቸው እንደሆነ ተነግሮናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19ETHIOPIA

መደናገጥ እና አጉል ፍራቻዎች ከበሽታው እኩል አደገኛ መሆናቸውን ሁሉም አውቆ በተረጋጋ ሁኔታ የሚተላለፉትን የጥንቃቄ መልዕክቶች ተግባራዊ ሊያደርግ ይገባል።

አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያ ተጠቃሚዎች በምንም ሁኔታ ለህዝቡ የሚራሩ አይመስሉምና ከዩትዩብ ገንዘብ ለማግኘት ሲባል እየተሰራጩ የሚገኙ ሀሰተኛ መረጃዎች እንዳያሸብሯቹ ተጠንቀቁ።

ከጤና ሚኒስቴርና ከኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ውጪ የሚሰራጩ በርካታ ሀሰተኛ መረጃዎች አሉና ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድታደርጉ እንመክራለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ትላንት ጎረቤታችን ሱዳን ውስጥ አንድ ግለሰብ ህይወቱ አልፏል ፤ ይህ ግለሰብ በኮሮና ቫይረስ ተይዞ እንደነበረ ሀገሪቱ አስታውቃለች፡፡

ህይወቱ ያለፈው ግለሰብ በዚህ ወር የተባበሩት አረብ ኢሚሬትስን ጎብኝቶ እንደነበረ ነበረና ሀሙስ እለት ህይወቱ ማለፉ ነው የታወቀው፡፡

በ50ዎቹ ዕድሜ ውስጥ የነበረው ግለሰብ በሱዳን ዋና ከተማ ካርቱም ውስጥ መሞቱን የአገሪቱ የጤና ጥበቃ ሚኒስትር በሰጠው መግለጫ አስታውቋል፡፡

#ሮይተርስ #ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
በአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሰዎች ቁጥር፦ • ግብፅ - 80 ሰዎች • አልጄሪያ - 26 ሰዎች • ደቡብ አፍሪካ - 16 ሰዎች • ቱኒዝያ - 13 ሰዎች • ሞሮኮ - 6 ሰዎች • ሴኔጋል - 10 ሰዎች • ካሜሮን - 2 ሰዎች • ናይጄሪያ - 2 ሰዎች • ቡርኪነፋሶ - 2 ሰዎች • ጋና - 2 ሰዎች • ቶጎ - 1 ሰው • ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ - 1 ሰው • አይቮሪኮስት - 1 ሰው •…
አጫጭር መረጃዎች፦

- ኢትዮጵያና ሱዳን የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ኬዝን ሪፖርት ማድረጋቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ አፍሪካ ውስጥ የኮሮና ቫይረስ የሚግኝባቸው ሀገራት 17 ደርሰዋል።

- በዛሬው ዕለት በደቡብ አፍሪካ ተጨማሪ 8 ሰዎች በቫይረሱ መጠቃታቸው ሪፖርት በመደረጉ በሀገሪቱ የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር ወደ 24 ከፍ ብሏል።

- በDRC ደግሞ ዛሬ ተጨማሪ 1 የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ሪፖርት ተደርጓል። በዚህም DRC ውስጥ ያሉ የኮሮና ተጠቂዎች 2 ሆነዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከባህር ዳር - ጎንደር የሚታየው አቧራማ ጭጋግ!

ከዛሬ ከባሕር ዳር እስከ ጎንደር አካባቢ የሚታዬው አቧራማ ጭጋግ የተነሳው ከሱዳን መሆኑን የምዕራብ አማራ ሚትዮሮሎጂ አገልግሎት ማዕከል ለአብመድ አስታውቋል።

አቧራማው ጭጋግ የአየር ሁኔታ መንስኤው ሱዳን አካባቢ የሚስተዋለው ከፍተኛ ደረቃማና ሞቃታማ የአየር ሁኔታ የፈጠረው ነው፡፡

እንደዚህ ዓይነት የአየር ሁኔታ መለዋወጥ ሲያጋጥም የማጅራት ገትር በሽታ መንስኤ ሊሆን ስለሚችል ንጽሕናን በመጠበቅ ሕብረተሰቡ ቅድመ ጥንቃቄ እንዲያደርግም አቶ ጥላሁን መክረዋል፡፡

ምንጭ፦ አብመድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በተጨማሪ የትግራይ ምዕራባዊ ፣ ሰሜናዊ ምዕራብ እና ማዕከላዊ ዞኖች ዛሬ በኣቧራ አውሎንፋስ ተሸፍነው ነበር።

PHOTO : ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ መንገዶች፦

- የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክት ከሚያሳዩ ሰዎች መራቅ

- ባልታጠበ እጅ አይን፣ አፍንጫ እና አፍን አለመንካት

- እጅን በንፁህ ውሃ እና ሳሙና በደንብ መታጠብ

ይህን መልዕክት ለምታውቁት ሁሉ አጋሩ!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ በአዲስ አበባ የኮሮና ቫይረስ ከተገኘባቸው ጃፓናዊ ጋር የቅርብ ግንኙነት የነበራቸው 25 ሰዎች ክትትል እየተደረገላቸው ይገኛል።

ምንም እንኳን በዚህ 25 ሰዎች ጉዳይ ላይ በጤና ሚኒስቴር ምንም አይነት መረጃ ባይሰጥም አንዳንድ የማህበራዊ ሚዲያዎች ሀሰተኛ መረጃዎችን እያሰራጩ ስለሆነ ጥንቃቄ ይደረግ።

በዚህ አጋጣሚ 'ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ከሚገለገሉባቸው ይፋዊ የማህበራዊ ገፆች ውጭ ሌሎች 'Corona Virus Update'፣ ኮሮና ቫይረስ መረጃ' እየተባሉ እየተከፈቱ ያሉት አዳዲስ ገፆች በመንግስት እውቅና የሌላቸው እንደሆኑ እንጠቁማለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia