TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የመርካቶ የአውቶብስ ተርሚናል!

የመርካቶ የአውቶቡስ ተርሚናል ግንባታ በመፋጠን ላይ መሆኑን የትራንስፖርት ቢሮ አስታውቋል። የተርሚናሉ ግንባታ 84 በመቶ ላይ የደረሰ ሲሆን፥ በ2012 በጀት አመት ሙሉ በሙሉ ለማጠናቀቅ ርብርብ በመደረግ ላይ ነው፡፡

የአውቶቡስ ተርሚናሉ የተሳፋሪዎችን ምቾት በመጠበቀ በርካታ አገልግሎቶችን መስጠት ያስችላል፡፡ ተርሚናሉ በአንዴ ለ20 አውቶቡሶች አገልግሎት መስጠት የሚያስችል፤ የራሳቸው መግቢያ እና መውጫ ያላቸው ሁለት ወለሎችን አካቷል፡፡

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃ ስለ መርካቶ የአውቶብስ ተርሚናል፦

- የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል የአውቶቡስ መጠበቂያ ቦታ ፣ የትኬት ሽያጭና የተሳፋሪ መጫኛና የማራገፊያ ቦታ አሉት።

- ዘመናዊ ስምሪት አገልግሎትን ጨምሮ የአውቶቡስ መርሃ-ግብርና የአስተዳደር ቢሮዎችን አካቷል፡፡

- ተርሚናሉ በ4,125 ካሬ ሜትር ቦታ ላይ ያረፈው ሲሆን፥ በአንድ ሰዓት 6,000 ለሚጠጉ የብዙሃን ትራንስፖርት ተጠቃሚዎች አገልግሎት መስጠት ያስችላል፡፡

- በቀን ከ50,000 እስከ 80,000 ገበያተኛ የትራንስፖርት ተጠቃሚዎችን አገልግሎት እንደሚሰጥ ታሳቢ ተደርጎ ነው ተርሚናሉ እየተገነባ ያለው።

- የመርካቶ አውቶብስ ተርሚናል ግንባታ በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተመደበ 200 ሚሊዮን ብር በመከናወን ላይ ይገኛል።

[የትራንስፖርት ቢሮ ኮሙዩኒኬሽን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ባለቤት ሶፊ ግሪጎሪ በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው መረጋገጡን ቢቢሲ ዘግቧል።

ሶፊ ግሪጎሪ ዩናይትድ ኪንግደም ውስጥ ንግግር አድርገው ከተመለሱ በኋላ የተወሰነ የሕመም ምልክት ማሳየታቸውን ተከትሎ በተደረገ ምርመራ ነው በቫይረሱ መያዛቸው የተረጋገጠው።

በዚህም ጠቅላይ ሚኒስትሩ በቫይረሱ ስጋት ምክንያት ለ14 ቀናት ብቻቸውን ለመቆየት መወሰናቸውን የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽ/ቤት አስታውቋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ የጤናቸውን ሁኔታ በከፍተኛ ጥንቃቄ እየተከታተሉ የዕለት ተዕለት ሥራቸውን ቤታቸው ሆነው እንደሚሠሩ ጽ/ቤቱ በመግለጫው አመልክቷል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቀለም አይለይም፤ ሁሉንም የሰው ዘር ያጠቃል!

የኮሮና ቫይረስ በሽታ [#COVID19] ነጭ ጥቁር የቆዳ ቀለም ሳይለይ ሁሉንም የሰው ዘር የሚያጠቃ በሽታ ነው፡፡

ኮሮና ቫይረስ አስካሁን የተረጋገጠ መድሐኒት ወይም ክትባት የለውም፤ ይህንን በመረዳት እና የጥንቃቄ መንገዶችን በማወቅ እንዲሁም በመተግበር በሽታውን መከላከል ያስፈልጋል።

በማህበራዊ ሚዲያዎች ኮሮና ቫይረስ ጥቁር አፍሪካውያን አያጠቃም በሚል የሚሰራጩት መረጃዎች ሀሰተኛ ናቸውና ውድ ቤተሰቦቻችን ጥንቃቄ አይለያችሁ።

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#COVID19

በኖርዌይ በኮሮና ቫይረስ የመጀመሪያው ሞት መመዝገቡን ጠቅላይ ሚኒስትር ኤርና ሳበርግ ለNRK ተናግረዋል።

ሀገሪቱ የቫይረሱን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ትምህርት ቤቶች እና ዩኒቨርሲቲዎች እንዲዘጉ አድርጋለች።

በአሁን ሰዓት 800 የሚደርሱ የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች በኖርዌይ እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ጋቦን እና ጋና በሀገራቸው በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የተጠቁ ግለሰቦች መኖራቸውን አረጋገጡ።

በጋቦን መንግስት ይፋ በተደረገው መረጃ ቫይረሱ የተገኘበት MARCH 8 ከፈረንሳይ በተመለሰ የ27 ዓመት ወጣት ጋቦናዊ ላይ ነው።

ከጋና የጤና ሚኒስቴር እንደተሰማው ደግሞ ከኖርዌይ እና ከቱርክ የተመለሱ ሁለት ግለሰቦች ላይ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቷል።

በጋቦ እና በጋና የኮሮና ቫይረስ ኬዞች ሪፖርት መደረጋቸውን ተከትሎ በአፍሪካ ቫይረሱ የሚገኝባቸው ሀገራት ቁጥር 14 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#HumanRightsWatch የኢትዮጵያ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ዘግቶ የቆየውን የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ገደብ በፍጥነት እንዲያነሳ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሒውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል። ድርጅቱ ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው ለሁለት ወራት የተዘጋው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቤተሰብ እንዳይገናኝ አድርጓል፤ በአካባቢው የነፍስ አድን ሥራ በአግባቡ እንዳይከናወን…
#UPDATE

ከሰሞኑ ሒውማን ራይትስ ዎች [HumanRightsWatch] በኦሮሚያ የተቋረጠው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት በአስቸኳይ እንዲቀጥል መግለጫ ማውጣቱ አይዘነጋም።

በዚህ ጉዳይ ላይ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ አቶ ጌታቸው ባልቻ ለሸገር ኤፍ ኤም 102.1 አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

አቶ ጌታቸው አገልግሎቱ የተቋረጠው በአካባቢው ያለውን የፀጥታ ችግር ለመፍታት እርምጃ በተወሰደባቸው የመጀመሪያዎቹ ጥቂት ቀናት እንደነበር ገልፀው ይህንንም ጉዳይ መንግስት ለህዝቡ ማሳወቁን አስታውሰዋል።

አሁን ግን መሰረተ ልማቱ በማበላሸት አገልግሎቱ እንዲቋረጥ ያደረጉት በአከባቢው የሚንቀሳቀሱ ህገወጥ ቡድኖች ናቸው ብለዋል። ጉዳት የደረሰበትን መሰረተ ልማት ኢትዮ ቴሌኮም እየጠገነው ይገኛል ሲሉ ገልፀዋል።

ሸገር ኤፍ ኤም 102.1 ይዞት በወጣው ተጨማሪ መረጃ የኦሮሚያ ፖሊስ ከፌደራል የፀጥታ ኃይሎች ጋር በመቀናጀት በክልሉ ምዕራብ ክፍል እየወሰደ ባለው ህግን የማስከበር እርምጃ በምስራቅ ወለጋ እና ሆሮ ጉድሩ ወለጋ የተሻለ ፀጥታ መስፈኑን አቶ ጌታቸው ባልቻ መናገራቸውን ዘግቧል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#BREAKING

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የመጀመሪያው በኮሮና ቫይረስ የተጠቃ ግለሰብ መኖሩን ይፋ አድርጓል። ቫይረሱ የተገኘባት ግለሰብ ከUSA ወደ ናይሮቢ የመጣች ሴት እንደሆነች ተነግሯል። ግለሰቧ ከአሜሪካ በለንደን አድርጋ ናይሮቢ እንደገባች ነው የተገለጸው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኬንያ በሀገሯ የኮሮና ቫይረስ መገኘቱን ይፋ ማድረጓን ተከትሎ በአፍሪካ የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] የሚገኝባቸው ሀገራት ቁጥር 15 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#COVID19

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር በሀገሪቱ የመጀመሪያውን የኮሮና ቫይረስ ኬዝ ይፋ አድርጓል። ኬንያ ቫይረሱ የተገኘባት የመጀመሪያዋ የምስራቅ አፍሪካ ሀገርም ሆና ተመዝግባለች።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

በመጪው ሚያዝያ ወር ላይ በቶጎ ሎሜ ሊካሄድ የታቀደው 6ኛው የአፍሪካ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ለመጪው አመት መተላለፉን የአፍሪካ አትሌቲከስ ኮንፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

ለሻምፒዮናው ተመልምለው በ6ኛው የአፍሪካ አትሌቲክስ አገር አቋራጭ ሻምፒዮና ለመሳተፍ በኦሮሚያ ክልል፣ዱከም ከተማ ካምፕ ገብተው የነበሩ አትሌቶችን እንደሚያሰናብትም የኢትዮጵያ አትሌቲከስ ፌዴሬሽን አስታውቋል፡፡

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ የሚገኝባቸው የአፍሪካ ሀገራት፦

- ግብፅ
- አልጄሪያ
- ደቡብ አፍሪካ
- ቱኒዝያ
- ሞሮኮ
- ሴኔጋል
- ካሜሮን
- ናይጄሪያ
- ቡርኪነፋሶ
- ጋና
- ቶጎ
- ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ
- አይቮሪኮስት
- ጋቦን
- ኬንያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኬንያው ጤና ሚኒስትር ሙታይ ካግዌ የተናገሩት፦

- በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው የተረጋገጠው ሴት ከሳምንት በፊት ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጡ ናቸው።

- እዚህ ግለሰብ ከአሜሪካ ወደ ኬንያ የመጡት በለንደን አድርገው ነው። መጀመሪያ ኬንያ ጆሞ ኬንያታ አውሮፕላን ማረፊያ እንደደረሱ ምርመራ ተደርጎላቸው ነበር፤ በወቅቱ የተገኘባቸው ነገር አልነበረም።

- ግለሰቧ አውሮፕላን ማረፊያ ውስጥ በሚገኝ የለይቶ ማቆያ እንዲቀመጡ ተደርጎ ከቀናት በኋላ በትናንትናው እለት ቫይረሱ ተገኝቶባቸዋል።

- ህመምተኛዋ አሁን ያሉበት የጤና ሁኔታ ደህና የሚባል ሲሆን ምግብም ይበላሉ ፤ ትኩሳታቸውም እየወረደ ነው።

- በህመምተኛዋ ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸው በኬንያ ብሄራዊ የኢንፈሉዬንዛ ላብራቶሪ እስኪረጋገጥ ድረስም በለይቶ ማከሚያው ተገልለው ይቆያሉ።

ምንጭ፦ BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ሱዳን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ስጋት ከግብፅ ጋር ያላትን ድንበር መዝጋቷን ይፋ አድርጋለች። ሀገሪቱ ከ8 ሀገራት ጋር የምታደርገውን በረራም ማቋረጧን አስታውቃለች። የሲቪል አቬዬሽን ባለስልጣን ዳይሬክተር ጄነራል ኢብራሂም አድላን ለሱዳን ትሪቡን እንደገለፁት ወደ ኮሪያ፣ ቻይና፣ ጃፓን፣ ጣልያን፣ ኢራን፣ ስፔን፣ ግብፅና ፈረንሳይ እንዲሁም ከነዚህ ሀገራት ወደሱዳን የሚደረጉ በረራዎች እንዲቋረጡ ተወስኗል።

ምንጭ፦ አል ዓይን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በአፍሪካ ሀገራት የኮሮና ቫይረስ ተጠቂ ሰዎች ቁጥር፦

• ግብፅ - 80 ሰዎች
• አልጄሪያ - 26 ሰዎች
• ደቡብ አፍሪካ - 16 ሰዎች
• ቱኒዝያ - 13 ሰዎች
• ሞሮኮ - 6 ሰዎች
• ሴኔጋል - 10 ሰዎች
• ካሜሮን - 2 ሰዎች
• ናይጄሪያ - 2 ሰዎች
• ቡርኪነፋሶ - 2 ሰዎች
• ጋና - 2 ሰዎች
• ቶጎ - 1 ሰው
• ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ - 1 ሰው
• አይቮሪኮስት - 1 ሰው
• ጋቦን - 1 ሰው
• ኬንያ - 1 ሰው

በአጠቃላይ በ15 የአፍሪካ ሀገራት 164 ሰዎች በቫይረሱ የተጠቁ ሲሆን ፤ በግብፅ ሁለት እንዲሁም በሞሮኮ ሁለት ሰው ሞቷል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ETHIOPIA

በአዲስ አበባ ያሉ የተለያዩ ሀገራት ኤንባሲዎች የኮንሱላር አገልግሎቶቻቸውን ከዛሬ መጋቢት 4/2012 ዓ/ም ጀምሮ ማቋረጥ የጀመሩ ሲሆን ከተያዘው ሳምንት መጀመሪያ ጀምሮም አንዳንድ ስብሰባዎቻቸውን መሰረዛቸው ተነግሯል፡፡

አዲስ ማለዳ ጋዜጣ አረጋግጫለሁ እንዳለው የአውሮፓ አገር ኤንባሲዎች አገልግሎቱን መስጠት ካቆሙት መካከል ናቸው፡፡ የአሜሪካ ኤንባሲ ለጋዜጣው እንዳስታወቀው ግን መደበኛ የኮንሱላር አገልገሎቶቹን እያካሄደ ነው፡፡

የጤና ሚኒስቴር የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ ዮርዳኖስ አለባቸው እደገለጹት በኢትዮጵያ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ያለበት ሰው ያለመገኘቱን ገልፀው ኤንባሲዎቹ ለምን አገልግሎት እንዳቁሙ የሚያውቁት ነገር እንደሌለ ገልፀዋል፡፡

ምንጭ፦ አዲስ ማለዳ ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሩዋንዳ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን በዋና ከተማዋ መጠቀም ጀምራለች።

ሩዋንዳ እስካሁን የኮሮና ቫይረስ ካልተመዘገበባቸው የሰብ ሳህራን አፍሪካ ሀገሮች አንዷ ነች።

ይሁን እንጂ ሀገሪቱ ወረርሺኙን ቀድሞ ለመከላከል በዋና ከተማ ኪጋሊ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮችን ዜጎቿ እንዲጠቀሙ ተግባራዊ አድርጋለች።

በሩዳንዳ ተንቀሳቃሽ የእጅ መታጠቢያ ሲንኮቹ የተተከሉት ባንኮች ፣ በገበያ ማዕከላት ፣ በባስ ስቴሽኖች እና በሬስቶራንቶች ውስጥ እንደሆነ ሮይተርስ ዘግቧል።

#ሮይተርስ #ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢትዮጵያ መንግስት ኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወደሀገር እንዳይገባ ጠበቅ ያለ እርምጃዎችን ሊወስድ እንደሚገባ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት አስገንዝበዋል።

መልዕክቶቻቸውን በ @tikvahethiopiaBot የላኩ የተለያዩ ከተማ ነዋሪዎች የሆኑ የቤተሰባችን አባላት አየር መንገዱ ቫይረሱ ወደተስፋፋባቸው ሀገራት በረራውን እንዲያቋርጥ በድጋሚ ጠይቀዋል።

እንዲሁም መንግስት የኢትዮጵያ ዜጎች ወደ ውጭ ሀገራት የሚያደርጉት ጉዞ እንዲያግድ፣ ቫይረሱ ካለባቸው ሀገራትም ወደ ኢትዮጵያ የሚደረጉ ጉዞዎች ለጊዜው ሙሉ በሙሉ እንዲቆሙም ጥሪ አቅርበዋል።

በተጨማሪ በድንበር አካባቢዎች በተለይም በኢትዮጵያና ኬንያ ድንበር አስፈላጊው እና ጥብቅ ቁጥጥር እንዲደረግ፤ አስፈላጊ ሆኖ ሲገኝም ከህዝብ ደህንነት የሚበልጥ ነገር ባለመኖሩ ድንበሩን መዝጋት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ ኢትዮጵያ ገብቷል!

"ለአዲስ አበባ ከተማ ነዋሪዎች፤ በተደረገው ምርመራ አንድ (1) ጃፓናዊ የኮሮና ቫይረስ ተገኝቶበታል። ሁላችንም ከእጅ ንክኪዎች እና አላስፈላጊ ስብሰባዎች እንቆጠብ ለማለት እፈልጋለሁ።" - ኢንጂነር ታከለ ኡማ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ጤና ሚኒስቴር ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] በተመለከተ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል። ሚኒስቴሩ ኢትዮጵያ ውስጥ በኮሮና ስለተያዘው ግለሰብ ዝርዝር መረጃ ይሰጣል። በኢትዮጵያ ቴሌቪዥን በቀጥታ መከታተል ትችላላችሁ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia