TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
"በአገሪቱ ምንም አይነት የነዳጅ እጥረት የለም፤ ማደያዎቹ የፈጠሩት ነው!" - የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት

በአዲስ አበባ ባለፉት ሦስት ቀናት ባጋጠመው የቤንዝን እጥረት ለእንግልት መዳረጋቸውን አሽከርካሪዎች እየተናገሩ ነው።

የኢትዮጵያ ነዳጅ አቅራቢ ድርጅት ዋና ዳይሬክተር አቶ ታደሰ ኃይለማርያም በአገሪቷ ምንም አይነት የነዳጅ እጥረት አለመኖሩን ገልጸዋል።

ችግሩ በየወሩ መጨረሻ የሚደረግን የነዳጅ ዋጋ ተመን ማሻሻያ ተከትሎ ማደያዎች የገንዘብ ጭማሪ ይኖራል በሚል እሳቤ በራሳቸው የፈጠሩት መሆኑን ተናግረዋል።

“በመላ አገሪቷ በቀን 2 ሚሊዮን ሊትር ነዳጅ ያስፈልጋል” ያሉት አቶ ታደሰ ድርጅቱ ከፍላጎቱ ጋር ተመጣጣኝ ነዳጅ ለማቅረብ እየሰራ መሆኑንም ገልጸዋል።

የነዳጅ አስፈጻሚ አካላት ኃላፊነታቸውን በሚገባ እየተወጡ ባለመሆኑ የነዳጅ እጥረቱ የሚከሰትበት ሁኔታ መኖሩን ጠቁመው ባለድርሻ አካላት ተቀናጅተው እንዲሰሩ አስገንዝበዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ባለፈው ዓመት በተከሰከሰው የኢትዮጵያ አየር መንገድ አውሮፕላን ሰለቦች አንደኛ ዓመት መታሰብያ ነገ ይከናወናል።

መቀመጫውን አሜሪካ አድርጎ በዚህና ሌሎች አደጋዎች ለተጎዱት ጥብቅና የሚቆም የህግ ተቋም ዛሬ አዲስ አበባ ላይ በሰጠው መግለጫ ቦይንግ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦች የሚያደርገውን ድጋፍ እንዲያጠናክር ግፊት እያደረኩ ነው ብሏል።

በዩናይትድ ስቴትስ ፍርድ ቤት እየታየ ያለው ጉዳይ ምን ደረጃ ላይ እንደደረሰም ለደንበኞቼ በየጊዜው መረጃ አደርሳለሁ ብሏል ድርጅቱ።

ከደቡብ አፍሪካ የመጣውና በአደጋው ሴት ልጁን ያጣው ተጎጂ ቤተሰቦች ሃዘናቸውን ተሰባስበው በጋራ መታደማቸው እንዳስደሰተው ገልጾ፣ ዓለም ለሰው ልጅ ቅድሚ እንድትሰጥ ጠይቋል።

ምንጭ፦ DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE ዓለም አቀፍ መረጃ፦ ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 3,462 የደረሰ ሲሆን 101,861 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 56,108 ደርሰዋል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዓለም አቀፍ መረጃ፦

ዛሬ ባገኘነው ሪፖርት በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 4,000 የደረሰ ሲሆን 114,010 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 62,832 ደርሰዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኮሮና ቫይረስ በሽታ ምልክቶች፦

- ትኩሳት
- ለመተንፈስ መቸገር
- ሳል

ውድ ቤተሰቦቻችን በኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ዙሪያ የበለጠ መረጃ ለማግኘት በነፃ የስልክ መስመር 8335 ላይ መደወል ትችላላችሁ ብለዋችኃል የጤና ሚኒስቴር እና የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት።

#share #ሼር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከዩጋንዳ [ካምፓላ] ቲክቫህ ቤተሰብ፦

በዩጋንዳ ካምፓላ የሚገኝ የቲክቫህ ቤተሰብ አባል በዛሬው ዕለት ሀገሪቱ ኮሮና ቫይረስን በቅድሚያ ለመከላከል የምታደርገውን ዝግጅት ምን እንደሚመስል አጋርቶናል።

ዩጋንዳ እንደኛው ሀገር በኮሮና ቫይረስ የተያያዘ ሰው የለም። ሆኖም ግን የሚወስዱት ጥንቃቄና ዝግጅት የሚደነቅ እንደሆነ ነው የቤተሰባችን አባል የገለፀልን።

ለምሳሌ ካምፓላ ውስጥ አንድ ሰው ወደ ማንኛውም ሆቴል ወይም የመንግስት መስሪያ ቤት እና ሌሎችም ቦታዎች ከመግባቱ በፊት እጁን በአልኮል ማፅዳት ግዴታው ነው። ከዚህ በተጨማሪ በሀገሪቱ ሊካሄዱ የነበሩ ዓለም አቀፍ ስብሰባዎች መሰረዛቸውን የሀገሪቱ ጋዜጣዎችን እያስነበቡ ነው።

በካምፓላ የተለያዩ ቦታዎች ላይ መረጃዎች ተለጥፈውም ይታያሉ። ይህ የሀገሪቱ ዝግጅት ጠቃሚ ተሞክሮ ይሆናልና አሁን በኢትዮጵያ እየተደረገ ከሚገኘው ዝግጅት በተጨማሪ ይህ ተሞክሮ ቢወሰድ መልካም ነው።

#ጌታነህገብሬ #ካምፓላ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#OMN

ከሰሞኑን ኦ ኤም ኤን በተባለ መቀመጫነቱን አዲስ አበባ ባደረገ የቴሌቪዥን ጣቢያ የዓለም አቀፍ የሴቶች ቀንን ምክንያት ባደረገ ዝግጅት ዙሪያ እየተሰራጨ በሚገኝ የቀጥታ ስርጭት ወቅት አንዲት ሴት የተናገረችው ንግግር ከፍተኛ ቅሬታን ፈጥሮ፣ ብዙዎችን አስቆጥቶ በመንግስት ደረጃም ግብረ መልስ ተሰጥቶበታል።

ንግግሩ በተላለፈ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ የቴሌቪዥን ጣቢያው ቪድዮውን ከማህበራዊ ገፁ ላይ ያነሳ ሲሆን በእንስቷ ያልተገባ ንግግር ለተከፉ የቴሌቪዥኑ ተመልካቾች በይፋ ይቅርታ ጠይቋል።

መንግስት በበኩሉ በህዝባዊ መድረኮችና መገናኛ ብዙሃን በኩል የሚተላለፉ የጥላቻ ንግግሮች በሃገር አንድነትና አብሮነት ላይ አደጋ እንደሚደቅኑ ገልጾ በመሰል ድርጊት በሚሳተፉ የፖለቲካ ፓርቲዎች እና የመገናኛ ብዙሃን ላይ ከኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለስልጣንና ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ጋር በመሆን ተገቢና ተመጣጣኝ ዕርምጃ ለመውሰድ እንደሚገደድ አስታውቀዋል።

More https://telegra.ph/OMN-03-10

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሰሞኑን በኦሮሚያ ሚዲያ ኔትዎርክ OMN የተላለፈውን አንድ መልዕክት ሰምተናል
<unknown>
#OMN

ሰሞኑን በOMN በተላልፈው መልዕክት በቀጥታ ሲከታተሉ የነበሩት የኦሮሚያ ፌዴራሊስት ኮንግረስ ፓርቲ ኦፌኮ ሊቀመንበሩር ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና እንዴት እንደተረዱት እንዲያስረዱ በሸገር ኤፍ ኤም ተጠይቀው ነበር።

ፕሮፌሰር መረራ ጉዲና የንግግሩ ችግር አይታየኝም፣ ማንኛውም ዜጋ የሚናገረውን ለመቆጣጠር ፍላጎቱ የለንም ብለዋል፡፡

ሬድዮ ጣቢያው ከዚሁ ጉዳይ ጋር በተያያዘ የሕግ ምሁር እና የብሮድካስት ባለስልጣንንም ጠይቋል፡፡ የጥላቻ ንግግር እና የሀሰተኛ መረጃ ስርጭት ለመከላከል በቅርቡ በጥቁር እና በነጭ ተፅፎ የፀደቀው ሕግስ እንዴት እየተተረጎመ ነው፡፡

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ከኢትዮጵያ ወደሀገሩ አሜሪካ እንደተመለሰ የተነገረለት አንድ የአሜሪካ የባሕር ኃይል ወታደር በኮሮና ቫይረስ መያዙን Talk Media News ዘግቧል። ለጊዜው ወታደሩ ከኢትዮጵያ መቼ እንደተመለሰ የሰጠው ፍንጭ የለም።

የኢትዮጵያ ጤና ሚኒስቴር እንዲሁም የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት በጉዳዩ ዙሪያ እስካሁን የሰጡት መረጃ የለም። በጉዳዩ ላይ የሚሰጡ መረጃዎች ሲኖሩ እንድታነቡት የምናደርግ ይሆናል።

https://www.talkmedianews.com/featured/2020/03/09/marine-back-from-ethiopia-tests-positive-from-covid-19-at-ft-belvoir-virginia/

#TalkMediaNews #EthioFM
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ ተይዘዋል ተባለ!

በፈረንሳይ መንግስት እርዳታ እየተዳሰ የነበረውን የላሊበላ ውቅር ቤተክርስቲያንን ለመገምገም ባለፈው መስከረም ኢትዮጵያ የመጡትና ከጠ/ሚ አብይ አህመድ ጋር ውይይት ያረጉት የፈረንሳይ የባህል ሚኒስትር ፍራንክ ራይስተር በኮሮና ቫይረስ መያዛቸው ተነግሯል።

የፈረንሳይ የጤና ሚኒስትር ኦሊቨር ቬራን ቢ ኤፍ ኤም ቴሌቭዥን ላይ ቀርበው እንደተናገሩት ”ሬይሰተር አሁን እቤቱ አረፍ ብሏል። ደህና ነው።” በማለት ሚኒስትሩ እቤታቸው ሆነው ህክምና እያገኙ መሆናቸውን ገልፀዋል።

የ46 አመቱ ሬይስተር በቅርቡ በኮሮና ቫይረስ ከተጠቁት አምስት የፈረንሳይ የፓርላማ አባላት ከአንዱ ጋር በመገናኘታቸው ቫይረሱ ሊይዛቸው እንደቻለም ተነግሯል።

ራይስተር ከፈረንሳይ ባለስልጣኖች መሀከል ግብረሰዶማዊ ነኝ በማለት በ2010 ዓ.ም መናገራቸው የሚታወስ ሲሆን የተመሳሳይ ፆታ ጋብቻን አጥብቀው ይደግፋሉ።

ራይስተር ዛሬ ማክሰኞ ከፊልም ኢንደስትሪ ሰዎች ጋር እና ከአርቲስቶች ጋር በኮሮና ቫይረስ መከላከል ዙርያ ዉይይት ለማድረግ ቀጠሮ ይዘው ነበር። በፈረንሳይ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት 25 ሰዎች ሲሞቱ 1,412 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል።

ምንጭ፦ fidelpost.com
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"ቤታቹ ሁኑ ሁሉም ነገር ይስተካከላል" - ካፑቱ

የሳሱሎው የፊት መስመር ተጫዋች ፍራንቼስኮ ካፑቱ ለክለቡ ግብ ካስቆጠረ በውሃላ በጣልያን በርካታ ሰዎችን እየጨረሰ ስለሚገኘው ኮሮርና ቫይረስ "ቤታቹ ሁኑ ሁሉም ነገር ይስተካከላል" በማለት ለጣሊያናውያን መልዕክቱን አስተላልፏል።

በጣልያን በፍጥነት እየተስፋፋ ከመጣው የኮሮና ቫይረሱ ስርጭት አንፃር የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር በመላው ሀገሩቱ እንቅስቃሴ አግደዋል። ሁኔታዎች እስኪረጋጉም የትኛውም ስፓርታዊ ውድድር እንዳይካሄድ የሚል መመሪያ ማስተላለፋቸው ተነግሯል።

የኮሮና ቫይረስ በስፖርቱ ዓለም ከፍተኛ ተፅእኖ እያሳደረ ይገኛል። በስፖርቱ ዓለም የሚፈጠሩትን ጉዳዮች በቲክቫህ ስፖርት መከታተል ትችላላችሁ @tikvahethsport

@tikvahethsport @tikvahethiopia
ኮሮና ቫይረስ የዓለምን ኢኮኖሚ ክፉኛ እያናጋ ነው!

ኮሮና ቫይረስ ኢኮኖሚውን ክፉኛ እያናጋው ነው የአውሮፓ ዋነኞቹ የንግድ ተቋማት የበርሊኑ DAX እና የለንደኑ ዋነኛው FTSE 100 ትላንት ጠዋት ላይ ኪሳራ እንደገጠማቸው የጀርመኑ ዜና ምንጭ DPA ጠቅሶ የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በቻይና በኮሮና ቫይረስ የሚጠቁ ሰዎች ቁጥር ከቀን ወደ ቀን እየቀነሰ እየመጣ ነው። በ24 ሰዓት ውስጥ በቻይና በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 20 ብቻ ነው። በአጠቃላይ በአሁን ሰዓት በቻይና በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 80,755 ይደርሳሉ።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የጤና ባለሙያ የቅጥር ማስታወቂያ!

የጤና ሚኒስቴር የኮሮና ቫይረስ [COVID-19] ወረርሽኝ ለመከላከልና ለመቆጣጠር ዜሮ ዓመት የስራ ልምድ ያላቸው፦

· ጠቅላላ ሀኪም
· ቢኤስ ሲ ነርስ
· ጤና መኮነን
· አከባቢ ጤና አጠባበቅ እና
· ጤና አጠባበቅ ትምህርት

ባለሙያዎችን ለ6 ወራት በኮንትራት በመቅጠርና አስፈላጊውን ስልጠና በመስጠት በአዲስ አበባና በተለያዩ ክልሎች ስር ባሉ የጤና ተቋማት ለማሰራት አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል፡፡

በመሆኑም ከላይ በተዘረዘሩ የሙያ ዓይነቶች ከተለያዩ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪ ድግር ተመርቃችሁ ወደ ስራ ያልተሰማራችሁ ባለሙያዎች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ከመጋቢት 02 ቀን 2012 ዓ. ም ጀምሮ ለተከታታይ 7 ቀናት ቅዳሜና እሁድን ጨምሮ ኦርጅናል የትምህርት ማስረጃ እና የሙያ ፍቃድ የማይመለስ አንድ ኮፒ ይዛችሁ ጤና ሚኒስቴር አንደኛ ፎቅ የሰው ሀብት አስተዳደር ዳይሬክቶሬት በመምጣት እንድትመዘገቡ እናሳስባለን፡፡

#ጤናሚኒስቴር

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19

ማንኛውም ወደ እስራኤል የሚያቀና መንገደኛ ለ14 ቀን ራሱን ለይቶ እንዲያቆይ መወሰኑ ተሰምቷል። ይህ ውሳኔ የመጣው የኮሮናቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል ሲሆን ውሳኔውንም የተናገሩት የአገሪቱ ጠቅላይ ሚኒስትር ቤንያሚን ኔታንያሁ ናቸው።

በሌላ በኩል ትናንት የጣልያኑ ጠቅላይ ሚኒስትር ጁሴፔ ኮንቴ ጣልያናዊያን ቤታቸው እንዲቀመጡና የግድ አስፈላጊ ነው የሚሉት ጉዞ ካላቸው ደግሞ የመንግሥትን ፍቃድ እንዲጠይቁ ትእዛዝ አስተላልፈዋል።

እርምጃው የተወሰደው በጣም ተጋላጭ የሆኑ ሰዎችን ለመጠበቅ እንደሆነ በቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት ባደረጉት ንግግራቸው የገለፁት ጠቅላይ ሚኒስትሩ "ምንም ጊዜ የለም" በማለት ችግሩ አሳሳቢ እንደሆነ አስረድተዋል።

#BBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የዛሬ ዓመት በET302 የአውሮፕላን አደጋ 157 ውድ ሕይወቶችን አጥተናል። ቤተሰቦችና ጓደኞች ያጧቸውን ለመዘከር በኢትዮጵያ በሚሰበሰቡበት በዚህ ጊዜ፣ ለአደጋው ሰለባ ቤተሰቦችና ወዳጆች ብርታትና ጽናቱን እንዲሰጣቸው እመኛለሁ።" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ የምርጫ ክልሎች ካርታ ይፋ ማድረጊያ ቀንን ከመጋቢት 01 ቀን 2012 ወደ መጋቢት 5 ቀን 2012 ዓ.ም ማዘዋወሩን አስታወቀ።

ምርጫ ቦርዱ የምርጫ ክልሎች ካርታ ዝግጅትን ያጠናቀቀ ቢሆንም ሂደቱ መከናወን ያለበት የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት በተገኙበት መሆን ስላለበት እና በጉዳዩ ላይ ባለሞያዎች ማብራሪያ መስጠት ስላለባቸው ቀኑን መቀየር ማስፈለጉን አስታውቋል።

በዚሁ መሠረት የምርጫ ክልሎች ካርታ የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 05 ቀን 2012 ዓ.ም የሚመለከታቸው አካላት በተገኙበት ይፋ የሚደረግ መሆኑን ቦርዱ ገልጿል።

ምንጭ፡- የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መሰረታችን ጋሞ ፤ ወላይታ ፤ ጉራጌ ፤ ኦሮሞ ፤ አማራ ፤ ትግራይ ቢሆንም ከፍታችን ግን ኢትዮጵያዊነት ነው" - ኢ/ር ታከለ ኡማ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክትል ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ትላንት በአዲስ አበባ በተካሄደው የጋሞ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም ላይ ባደረጉት ንግግር መሰረታችን ጋሞ ፤ ወላይታ ፤ ጉራጌ ፤ ኦሮሞ ፤ አማራ ፤ ትግራይ ቢሆንም ከፍታችን ግን ኢትዮጵያዊነት ነው ሲሉ ተደምጠዋል።

የጋሞ ባህልና ቋንቋ ሲምፖዚየም 'የጋሞ አባቶች የሰላም ተምሳሌት ለሀገር ግንባታ' በሚል መሪ ቃል ነበር የተካሄደው። በወቅቱ የጋሞ የሰላም አባቶች፣ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች፣ ታዋቂ ሰዎች ፣ በርካታ ጥሪ የተደረገላቸው እንግዳዶች ተገኝተው ነበር።

ምክትል ምከንቲባው የጋሞ የልማት ማህበር በአዲስ አበባ ለሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች የከተማ አስተዳደሩ ከጎናቸው እንደሚሆን ገልፀዋል። የልማት ማህበሩ በሚያከናውናቸው የልማት ስራዎች መልካም ጎዳናን በመከተል የአዲስ አበባን ብልፅግና እውን እናደርጋለን ሲሉም ተደምጠዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#HumanRightsWatch

የኢትዮጵያ መንግሥት በምዕራብ ኦሮሚያ ዘግቶ የቆየውን የኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ገደብ በፍጥነት እንዲያነሳ ዓለማቀፉ የሰብአዊ መብት ተሟጋቹ ድርጅት ሒውማን ራይትስ ዎች ጠይቋል።

ድርጅቱ ባወጣው መግለጫው እንዳስታወቀው ለሁለት ወራት የተዘጋው የስልክ እና የኢንተርኔት አገልግሎት ቤተሰብ እንዳይገናኝ አድርጓል፤ በአካባቢው የነፍስ አድን ሥራ በአግባቡ እንዳይከናወን አደናቅፏል ሲል ወቅሷል።

መንግስት በአካባቢው እየወሰደ ያለው ወታደራዊ ርምጃም መረጃ እንዳይወጣ አስተዋጽዖ ማድረጉንም መግለጫው አመልክቷል።

ከታኅሣስ 24 ቀን፤ 2020 ጀምሮ አንስቶ በምዕራብ ኦሮሚያ በቄለም ወለጋ፣ ምዕራብ ወለጋ፣ ሆሮ ጉዱሩ ወለጋ እና ምሥራቅ ወለጋ ዞኖች የኢንተርኔት እና የማሕበራዊ መገናኛ ዘዴዎች አገልግሎት መቋረጡን ነዋሪዎች ማመልከታቸውን ያተተው መግለጫው በጥቂት ዋና ዋና ከተሞች ብቻ የስልክ እና የመልዕክት አገልግሎት ብቻ እንደነበር አስታውቋል።

More https://telegra.ph/HRW-03-10

#HumanRightsWatch #DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#AddisAbaba

በአዲስ አበባ ከተማ የነዋሪዎችን የትራንስፖርት ችግር ለመፍታት በተያዘው በጀት ዓመት አንድ ሺ የሚሆኑ የግል ታክሲዎችን ለማስገባት መታቀዱን የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን አስታውቋል። በመንግሥት ሦስት ሺ የህዝብ ማመላለሻ አውቶብሶችን ለማስገባት እየተሠራ መሆኑንም ተሰምቷል።

#EPA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተጨማሪ መረጃዎች ይገባሉ ስለተባሉት ታክሲዎች፦

- በአዲስ አበባ ከተማ ታክሲዎቹን ለማስገባት የታቀደው በግለሰቦች ሲሆን፣ ታክሲዎቹም አራት እና ሰባት ሰዎች የሚጭኑ ላዳዎች ናቸው።

- የእነዚህ ታክሲዎች መግባት የከተማዋን የትራንስፖርት ችግር ለመቅረፍና ለበርካታ ዓመታት ባገለገሉ ታክሲዎች ሲሰጥ የቆየውን የትራንስፓርት አገልግሎት ለማዘመን ያስችላሉ ነው የተባለው።

- ከታክሲዎቹ 80 % አራት ሰዎች የሚጭኑ መሆናቸውን ጠቅሰው፣ የተቀሩት ደግሞ ሰባት ሰው የሚጭኑ ናቸው። ታክሲዎቹን ለማስገባት የሚያስችለውን ብድር ለማግኘት ለንግድ ባንክ ፕሮፖዛል ተልኳል።

- በአንድ ተሽከርካሪ ታክስን ጨምሮ ወደ 800 ሺህ ብር ብድር ግምት ተይዟል። ከላዳ ኩባንያ ጋር ድርድር ተጀምሯል።

- ታክሲዎቹን ለመግዛት ገዥዎቹ እንደ ቤቶች ልማት የባንክ ሂሳብ ከፍተው እንዲቆጥቡ እየተደረገ ነው። ከ10 ሺ 300 በላይ የሚሆኑ ተሽከርካሪዎችን ለማስመጣት ታቅዶ የነበረ ሲሆን፣ ለእዚህም ወደ 184 ማኅበራት ተደራጅት ተመዝግበዋል።

- በየክፍለ ከተማው ማኅበራቱን የሚወክሉ ሁለት ሁለት ሰዎች እንዲመርጡ ተደርጎ ከሃያ ተወካዮች ጋር ውይይት እየተደረገ ነው።

[የአዲስ አበባ ከተማ ትራንስፖርት ባለሥልጣን]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia