TIKVAH-ETHIOPIA
1.52M subscribers
57.5K photos
1.43K videos
206 files
3.95K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#update አዲስ አበባ⬇️

በአዲስ አበባ 6ኪሎ በሚገኘው አንበሳ ጊቢ ውስጥ አምስት አንበሶች መሞታቸዉ ተረጋገጠ።

ለእድሳት በሚል ተዘግቶ የቆየዉ የ6ኪሎ አንበሳ ግቢ መስከረም 2009 ዓ.ም የተጀመረ ቢሆንም 28 ሚሊዮን ብር ወጪ የተደረገበት ግንባታዉ ከ22 በመቶ በላይ ማለፍ አለመቻሉን ማወቅ ተችሏል፡፡

በአንድ አመት ዉስጥ ይጠናቀቃል ተብሎ የተጀመረዉ ግንባታዉ በመንጓተቱ ምክንያትና በእንክብካቤ ማነስ ምክንያት በቅጥር ግቢ ዉስጥ ይኖሩ የነበሩ 15 አንበሶች መካከል አምስቱ መሞታቸዉን #ኢቢሲ አረጋግጫለሁ ብሏል፡፡

📌የአዲስ ዙ ፓርክ ማእከል ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሙሴ ክፍሌ በበኩላቸዉ በመካነ እንስሳዉ የሞተ አንበሳ የለም ብለዋል፡፡

©ዘሪሁን ግርማ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NEBE

ለሐረሪ ክልል፣ ለድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር፣ ለጋምቤላ ክልል እና ለአማራ ክልል የምርጫ ክልል ኃላፊነት በቂ አመልካቾች አለመቅረባቸውን የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ገለፀ፡፡

ቦርዱ ለ9ኙ ክልሎችና ለ2ቱ ከተማ አስተዳደሮች የምርጫ ክልል ኃላፊነት ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለመመደብ የስራ ማስታወቂያ ማውጣቱ ይታወሳል።

መስፈርቱን ለሚያሟሉ እና በሶስቱ ክልሎች እና በድሬዳዋ ከተማ መስተዳድር መስራት ለሚፈልጉ ባለሙያዎች የማመልከቻ ጊዜው መራዘሙን ቦርዱ ገልጿል፡፡ የማመልከቻ ጊዜው በአንድ ሳምንት በመራዘሙ አመልካቾች ከዛሬ መስከረም 26 ቀን 2012 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት 7 ተከታታይ ቀናት ማመልከቻቸውን ማስገባት እንደሚችሉም ቦርዱ አስታውቋል፡፡

Via #ኢቢሲ
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#UPDATE

በ4 ነጥብ 5 ቢሊዮን ብር ወጪ በመቐለ ከተማ አስተዳደር እየተገነቡ ካሉ በድምሩ 93 ኪሎ ሜትር ከሚሸፍኑ መንገዶች መካከል 32 ኪሎ ሜትር የሚሸፍኑት 11 መንገዶች ዛሬ ተመርቀው ለአገልግሎት ክፍት ተደርገዋል። መንገዶቹን የመረቁት የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳደር ዶ/ር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል ናቸው። የፌዴሬሽን ም/ቤት አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ኬሪያ ኢብራሂም፣ የክልሉ ካቢኔ አባላት እንዲሁም የመቀሌ ከተማ አስተዳደር ም/ከንቲባ ኢንጅነር ኣርአያ ግርማይም በምረቃ ሥነ-ሥርዓቱ ላይ ተገኝተዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት12

"አሁን ያለው ትውልድ ይቅር መባባልን ከታሪካችን ሊማር ይገባል" - የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዝዳንት

83ኛው የሰማዕታት ቀን አዲስ አበባ 6ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ዕለቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት፣ ቀኑ የዛሬ 83 ዓመት በፋሺስት ጣሊያን ወራሪ ጦር መሪ በሆነው ግራዚያኒ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት ዕለት ነው ሲሉ አስታውሰዋል።

ሆኖም ይህንን ጭፍጨፋ በይቅርታ ዘግተን ወደፊት በመጓዝ እዚህ ደርሰናል፤ አሁን ያለው ትውልድም ይቅር መባባልን ከዚህ ሊማር ይገባል ብለዋል።

አክለውም፣ ወጣቱ ዕለቱን ሲያስብ አባቶቹ በመሥዋትነት ያቆዩለትን አገር በጋራ ለማሳደግ እና ሰላሟን ለመጠበቅ መነሣት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ዕለቱ አባት አርበኞች ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የማኅበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ፣ ሌሎች የክብር እንግዶች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የውጭ አገራት ቆንስላ ተወካዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ!

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በተደራጀ ሁኔታ የኢትዮ-ቴሌኮምን ጨምሮ በሌሎች መንግሥታዊ ተቋማት መሠረተ ልማት ላይ ዝርፊያ ሲፈጽሙ ነበሩ የተባሉ ተጠርጣሪዎች መያዙን የንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ፖሊስ ገለጸ።

ፖሊስ ተጠርጣሪዎቹን የያዘው ከንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ፣ አልማዝየ ሜዳ አካባቢ በደረሰው የኅብረተሰቡ ጥቆማ መሆኑንም አስታውቋል።

ኅብረተሰቡ መሰል የወንጀል ድርጊቶችን ሲመለከት ለፖሊስ ጥቆማ በመስጠት የበኩሉን እንዲወጣ ፖሊስ አሳስቧል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር ተፈፀመ!

የቀድሞ የግብጽ ፕሬዚዳንት ሆስኒ ሙባረክ ስርዓተ ቀብር በወታደራዊ ስነስርአት በክብር ተፈፀመ፡፡

የቀብር ስነ-ስርዓቱ በካይሮ ከተማ በፊልድ ማርሻል ታንታዊ መስጂድ ሲፈፀም በስፍራው የወቅቱ ግብጽ ፕሬዝዳንት አብዲል ፈታ አልሲሲ፣ ከፍተኛ የመንግስት የስራ ሀላፊዎች፣ የሟች ቤተሰቦች እና ደጋፊዎቻቸው ተገኝተዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ አስከሬን የቤተሰባቸው የመቃብር ቦታ ላይ እንደሚያርፍ የተገለፀ ሲሆን የግብጽ መንግስትም የሶስት ቀን ብሔራዊ የሀዘን ቀን አውጇል፡፡

[#ቢቢሲ #ሮይተርስ #ኢቢሲ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#ExciseTax

ከኤክሳይዝ ታክስ ጋር ተያይዞ ያልተገባ የኑሮ ጫና ለመፍጠር በሚሞክሩ አካላት ላይ ተገቢ ክትትል አንደሚያደርግ የገቢዎች ሚኒስቴር አስታወቀ።

የገቢዎች ሚኒስቴር ዛሬ በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ፣ በኤክሳዝ ታክስ ምክንያት በመሰረታዊ የምግብ ፍጆታ ላይ የተጨመረ ዋጋ የለም ብሏል።

ሲሲያቸው 1 ሺህ 3 መቶ የሆኑ አዳዲስ ተሽከርካሪዎች ላይ የኤክሳይስ ታክስ እንዲቀንስ ከመደረጉ በተጨማሪ የግብርና ግብአቶችና ምርቶች፣ የቆዳ እና ሌጦ ምርቶች እንዲሁም የቴሌኮሙኒኬሽን እቃዎች ከቀረጥ ነፃ እንዲሆኑ መደረጉ ተገልጿል።

እንዲያም ሆኖ ግን አሁን በገበያ ላይ ያልተገባ የዋጋ ጭማሪ እየተደረገ በመሆኑ ይህንን ለመፍታት ከባለድርሻ አካላት ጋር የጋራ ግብረ ኃይል ተቋቁሞ እየተሰራ እንደሆነ የገቢዎች ሚኒስትር አዳነች አቤቤ ገልጸዋል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#COVID19 #ETHIOPIA

በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ የኮሮና ቫይረስ አለመከሰቱን የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩት ዛሬ በሰጠው መግለጫ ገልጻል፡፡

የኢንስቲትዩቱ ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ አባተ ዛሬ በሰጡት መግለጫ በሽታው ወደ አገሪቱ እንዳይገባ በመግቢያ በሮች ያሉ የቁጥጥር ስራዎች ተጠናክሮ መቀጠሉን አስታውቀዋል፡፡

አየር መንገዱን ጨምሮ በ29 የየብስ መንገዶች ላይ በሽታውን የመለየት ስራ ተጠናክሮ መቀጠሉ የተነገረ ሲሆን፣ በቅርቡም በአፋር በኩል የሙቀት መጠን ልየታ ተጀምሯል ተብሏል፡፡

በትላንትናው ዕለት የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር ውይይት እንደተደረገ ነው የተገለፀው፡፡ህብረተሰቡም በአሁኑ ሰዓት በተለያዩ ወሬዎች ሽብር ውስጥ እንዳይገባ ዶ/ር ኤባ አሳስበዋል፡፡

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia