TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
57K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#NAMA

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን)ከክልሉ መንግስት ጋር ያለን ትብብር እስከ ውህደት ሊደርስ ይችላል አለ፡፡ የድርጅቱ ሊቀ መንበር ዶክተር ደሳለኝ ጫኔ ለኢትዮ ኤፍ ኤም ራድዮ እንደገለጹት ክልሉ በዚህ ሰአት በትብብር መስራትን ይፈልጋል፡፡

የአማራ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ አዴፓ የክልሉን ሰላም ለማስጠበቅ የሚያደርገው እንቅስቃሴ በቂ አለመሆኑን የሚያነሱት ዶ/ር ደሳለኝ "የክልሉን ሰላም የማይፈልጉ አካላት የሚፈጥሩት ብጥብጥ የፖለቲካ ፓርቲዎቹ ተለያይተን ሳይሆን ተቀራርበን እንድንሰራ የሚያስገድደን ሁኔታን ፈጥሯል" ብለዋል፡፡

"ከአዴፓ ጋር የፖለቲካ ርእዮተ አለም ልዩነት ቢኖረንም የህዝባችንን ደህንነት ለማረጋገጥ ግን መቅረብ ያለብን ደረጃ ድረስ ቀርበን እንሰራለን" ነው ያሉት፡፡ ከመንግስት ጋር የመስራታችሁ ደረጃ እስከ ውህደት አሊያም ጥምረት ድረስ ሊሆን ይችላል ወይ ተብለው የተጠየቁት ዶ/ር ደሳለኝ ፦ "እኛ ለጊዜው ከአዴፓ ጋር የመዋሃድ ሃሳብ የለንም፤ ነገር ግን የህዝባችን ፍላጎት ከሆነና ጠቃሚ ሆኖ ካገኘነው ልንዋሃድ እንችላለን" ብለዋል፡፡

ምንጭ፦ ኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NAMA

አዲስ አበባ በእስር ላይ ያሉ የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ (አብን) አመራሮችና አባላት በርሀብ አድማ ላይ መሆናቸው ተገለጸ፡፡ አንዳንዱቹ ባጋጠማቸው የከፋ የጤና ችግር ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸውን የድርጅቱ ሊቀመንበር ዶ/ር ደሳለኝ ጫኔ ለኤትዩ ኤፍ ኤም 107.8 ተናግረዋል፡፡ ከሰኔ 15ቱ ግድያ ጋር በተያያዘ በመፈንቅለ መንግስት እና በጸረ ሽብር ክስ ተጠርጥረው የተያዙት 23 አባላቱ ካለፉት አራት ቀናት ጀምሮ በርሀብ አድማ ላይ መሆናቸውን ዶ/ር ደሳለኝ ተናግረዋል፡፡ በርሀብ አድማው ከተካፈሉት አብዛኞዎቹ የጤና ችግር ገጥሟዋል፡፡

የእስሩ ሁኔታ ከፍተኛ ዛቻ እና ማስፈራሪያ አለበት የሚሉት ታሳሪዎቹ ከፓሊስ አባላት እንግልት ይደርሰብናል በማለት አድማ ማደረጋቸውን ዶ/ር ደሳለኝ ገልጸዋል፡፡ በአባሎቻችን ላይ ስለሚደርሰው በደልና ግፍ ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት አንስቶ እስከ አለም አቀፍ የሰብአዊ መብት ተቆርቋሪዎች ድረስ ድምጻችንን ብናሰማም ጠብ የሚል ለውጥ እንዳላገኙም ዶክተር ደሳለኝ ተናግረዋል። ዶ/ር ደሳለኝ መንግስት ለጉዳዩ በቂ ትኩረት እንዲሰጥም አሳስበዋል፡፡

Via ETHIO FM 107.8
@tsegabwolde @tikvahethiopia
#NAMA

ላለፉት አራት ቀናት በርኃብ አድማ ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ በለጠ ካሳን ጨምሮ ሌሎች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትንና አመራሮች ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ።

ላለፉት 4 ቀናት የተፈፀመባቸውን ፓለቲካዊ እስር እና መንግሥታዊ እገታ በመቃወም የርኅብ አድማ በማድረግ ላይ ያሉት እና ከ6 ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት በሃምሳ አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ስር ክስ ከተመሰረተባቸው 13 ተጠርጣሪዎች መካከል የተካተቱት:-

1ኛ) ክርስቲያን ታደለ፦ የአብን የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ (12ኛ ተከሳሽ)
2ኛ) በለጠ ካሳ፦ የአብን ፅሕፈት ቤት ኃላፊ (13ኛ ተከሳሽ)
3ኛ) ሲሳይ አልታሰብ፦ የአብን ብሔራዊ ም/ቤት አባል (3ኛ ተከሳሽ)
4ኛ) አማረ ካሴ፦ የአብን የአዲስ አበባ የሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ (10ኛ ተከሳሽ)
5ኛ) ፋንታሁን ሞላ፦ የአብን አባል (11ኛ ተከሳሽ)
6ኛ) አስጠራው ከበደ፦ የአብን አባል (2ኛ ተከሳሽ)
7ኛ) አየለ አስማረ፦ የአብን አባል (9ኛ ተከሳሽ)

የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ሕግ የሽብር ሕጉን ተጠቅሞ ከ4 ወራት በላይ ምርመራ ሲያካሂድ ከቆየ በኃላ ከእድሜ ልክ እስከ ሞት የሚያስቀጣውን በ1996 ዓ.ም የወጣውን የኢፌዲሪ የወንጀል ሕግ አንቀፅ 32/1/ሀ//ለ/፣ 35፣ 38 እና 238/2/ ጠቅሶ “ሕገ-መንግስትንና ሕገ-መንግስታዊ ሥርዓቱን በኃይል ለመናድ ተንቀሳቅሰዋል" በሚል ኅዳር 12 ቀን 2012 ዓ.ም ክስ የመሰረተባቸው ሲሆን ተከሳሾችም ታኅሳስ 1 ቀን 2012 ዓ.ም በጋራ እና እያንዳንዳቸው በተናጥልም የክስ መቃወሚያቸውን ማቅረባቸው ይታወሳል፡፡

https://telegra.ph/NAMA-12-30

(የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ-አብን)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#NAMA ላለፉት አራት ቀናት በርኃብ አድማ ላይ የሚገኙት አቶ ክርስቲያን ታደለ እና አቶ በለጠ ካሳን ጨምሮ ሌሎች የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) አባላትንና አመራሮች ነገ ፍርድ ቤት ይቀርባሉ። ላለፉት 4 ቀናት የተፈፀመባቸውን ፓለቲካዊ እስር እና መንግሥታዊ እገታ በመቃወም የርኅብ አድማ በማድረግ ላይ ያሉት እና ከ6 ወራት በላይ በእስር ላይ የሚገኙት በሃምሳ አለቃ መሳፍንት ጥጋቡ መዝገብ ስር ክስ…
#NAMA

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ (አብን) ቃል አቀባይ አቶ ክርስቲያን ታደለን ጨምሮ በከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት ግድያ የተጠረጠሩ ግለሰቦች ዛሬ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን፣ ለጥር 08/2012 ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቶባቸዋል፡፡ችሎት ለመታደም የተገኙ ቤተሰብና ደጋፊዎቻቸው የተቃውሞ ድምጽ አሰምተዋል፡፡

(ELU)
PHOTO : BelayM.
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

አብን በዋግ ኽምራ ዞን ጋዝጊብላ ወረዳ...

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ የዋግ ኽምራ ዞን ማስተባበሪያ ፅሕፈት ቤት በጋዝጊብላ ወረዳ ከአባላቱ ጋር በተለያዩ ጉዳዮች ዙሪያ ከአባላቱ ጋር ከትላንት በስቲያ ጥር 3 ቀን 2012 ዓ.ም ውይይት አድርጓል።

#NAMA
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ItsMyDam #NAMA #GERD

ታላቁ የህዳሴ ግድብ የዓለም አቀፍ ድጋፍ እና እርዳታን ለማግኘት ማስያዣ መሆን እንደሌለበት አብን አስታወቀ።

የአማራ ብሄራዊ ንቅናቄ አብን የህዝብ ግንኙነት ሃላፊ አቶ ጣሂር መሃመድ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳሉት ግብጽ እስካሁንም የ1929ኙና የ1959ኙ ኢትዮጵያን ያገለለዉ ስምምነት እንዲመለስ ነዉ የምትፈልገዉ ያሉ ሲሆን የኢትዮጵያ መንግስት ጠንካራ አቋም ሊኖረዉ ይገባል ብለዋል።

ይህ የሉዓላዊነት ጉዳይ በመሆኑ መንግስት ከህዝቡ ጋር መምከርና ቀደም ሲል በነበረበት አቋም ጸንቶ ነዉ መቀጠል ያለበት ብለዋል፡፡

ንቅናቄዉ አሁን ላይ በተለይም ከአረቡ ዓለም ጋር መስመር የሳቱ የሚመስሉ ግንኙነቶች አሉ ብሎ እንደሚያምን ገልጾ በፖለቲካ ዓለም ዉስጥ ፍጹም ታማኝ ወዳጅ ባለመኖሩ ግንኙነታችን ግልጽ መስመር ሊኖረዉ ይገባል ብሏል፡፡

#ኢትዮኤፍኤም #ሙሉቀንአሰፋ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia