TIKVAH-ETHIOPIA
1.51M subscribers
56.9K photos
1.42K videos
205 files
3.9K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#COVID19 #ETHIOPIA #AMHARA_REGION

የኮሮና ቫይረስ ወደ አማራ ክልል መግባት የሚችልባቸው አጋጣሚዎች መኖራቸውን በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት የቅድመ ማስጠንቀቂያ ባለሙያ አቶ አሞኘ በላይ ለአብመድ ተናገሩ፡፡ አማራ ክልል ሰፊ የቱሪዝም እንቅስቃሴ ያሉበት በመሆኑ በርካታ የውጪ ሀገር ቱሪስቶች ወደ ክልሉ ይገባሉ፡፡

ምንም እንኳን በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ የቫይረሱ ምርመራ ቢደረግም በባሕር ዳር፣ ጎንደር፣ ላልይበላ እና ኮምቦልቻ የአውሮፕላን ማረፊያዎች በኩል የመግባት ዕድል ሊኖረው እንደሚችል በኢንስቲቲዩቱ ታሳቢ ተደርጓል፡፡

የተለያዩ የውጪ ሀገር ዜጎች የሚሠሩባቸው ካምፖች ፣ ኢንዱስትሪዎች እና ክልሉን በሚያዋስነው የሱዳን ድንበር ያለው የምድር ትራንስፖርት ኮሮና ቫይረስን [COVID-19] ወደ ክልሉ እንዲገባ ምክንያት ሊሆኑ እንደሚችሉ በስጋትነት ተለይተዋል፡፡

ይህንን ታሳቢ በማድረግ ኢንስቲቲዩቱ የቅድመ ዝግጅት ሥራዎችን እያከናወነ እንደሚገኝ ባለሙያው አስታውቀዋል። በተለዩት ቦታዎች የቫይረሱን ምንነት እና ቢከሰት መከናወን ያለባቸውን ተግባራት አስመልክቶ ለባለሙያዎች ሥልጠና እየተሰጠ እንደሚገኝም አቶ አሞኘ አስታውቀዋል፡፡

#AMMA

[በአማራ ክልል ኅብረተሰብ ጤና ኢንስቲቲዩት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia