TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
58.4K photos
1.47K videos
209 files
4.04K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
አቶ ንዋይ ገብረዓብ ማረፋቸው ተሰማ!

የቀድሞዎቹ የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች መለስ ዜናዊ እና ሃይለማርያም ደሳለኝ የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ አረፉ።

የትግራይ ክልል የመንግስት ኮሙንኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንዳስታወቀው የቀድሞዎቹን የኢትዮጵያ ጠቅላይ ሚኒስትሮች የኢኮኖሚ አማካሪ የነበሩት አቶ ንዋይ ገብረዓብ ዛሬ ረፋድ ባደረባቸው ህመም ምክንያት አርፈዋል።

አቶ ንዋይ ኢትዮጵያ ከተለያዩ ዓለም አቀፍ የገንዘብ ተቋማት ጋር ጥሩ ግንኙነት አንዲኖራት፣ኢትዮጵያ ከአገራት ጋር የምታደርጋቸውን ኢኮኖሚያዊ ስምምነቶችን እና ሌሎች አገራዊ ጉዳዮች ላይ መሪዎቹን ሲያማክሩ ቆይተዋል።

አቶ ንዋይ ከሁለት ዓመት በፊት የአፍሪካ ህብረት የኢኮኖሚ ኮሚሽነር ለመሆን የኢትዮጵያ እጩ ተወዳዳሪ ሆነው ቢቀርቡም በመጨረሻው ዙር በካሜሩን እጩ መሸነፋቸው አይዘነጋም።

#ኢትዮኤፍኤም107.8 #ሳሙኤልአባተ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#EZEMA

ብልጽግና ፓርቲ የህዝብና የመንግስት ሃብትን ለምርጫ ቅስቀሳ እየተጠቀመ መሆኑን የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ኢዜማ አስታወቀ። የፓርቲው መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ በወቅታዊ እና ሌሎች ጉዳዮች ዙሪያ በአዲስ አበባ መግለጫ በመስጠት ላይ ናቸው።

ፕሮፌሰር ብርሃኑ በዚህ ጊዜ እንደተናገሩት ብልጽግና ፓርቲ የህዝብን እና የመንግስትን ገንዘብ ለምርጫ ቅስቀሳ እያዋለ ነው ብለዋል።

በመሆኑም የብልጽግና ፓርቲ ድርጊት ሌሎች ፓርቲዎችን ወደ አላስፈላጊ መንገድ የሚመራ ከማድረጉ በተጨማሪ የአገሪቱን የዲሞክራሲ ግንባታ ስለሚጎዳ ከዚህ ድርጊቱ እንዲታቀብ አሳስቧል። ምርጫ ቦርድም ይሄንን ህገወጥ እንቅስቃሴ እንዲያስቆም ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ ጠይቀዋል።

#ኢትዮኤፍኤም107.8 #ሔኖክአስራት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia