TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
214 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
#UPDATE

በኮንጎ የአንበጣ መንጋ መከሰቱ ተነገረ። የተመድ የምግብና የእርሻ ድርጅት ዛሬ እንዳስታወቀዉ የአንበጣ መንጋ በኮንጎ ሲታይ ከጎርጎረሳዉያኑ 1944 ዓ,ም ማለትም ከ 70 ዓመት ወዲህ ይሄ ለመጀመርያ ጊዜ ነዉ።

የዜና ምንጮች ከኮንጎ እንደዘገቡት በምራዕራባዊ አልበርት ባህር ዳርቻ ኮንጎዉስጥ የታየዉ የአንበጣ መንጋ አካባቢዉ ላይ በከፊል የደረሰዉ በንፋስ ታግዞ ነዉ።

የበረሃ አንበጣ መንጋን በመዋጋት ላይ የሚገኙት የምስራቅ አፍሪቃ ሃገራት ማለትም ኢትዮጵያ ሱዳን ሶማልያ ኬንያ እና ዩጋንዳ በሃገራቱ አንበጣዉ በተለይ በሰብል ላይ ከፍተኛ ጉዳት ማስከተሉ ን የመንግሥታቱ የምግብእና የእርሻ ድርጅት ዛሬ ይፋ ባደረገዉ ዘገባ አመልክቶአል።

Via DW
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የነጭ ሣር ብሄራዊ ፓርክ እሳት ቃጠሎ...

በነጭ ሣር ብሔራዊ ፓርክ ላይ ዛሬ የተነሳው የእሳት ቃጠሎ የከፋ ጉዳት ሳያደርስ መቆጣጠር መቻሉን የፓርኩ ስራ አስኪያጅ አስታውቀዋል። ስራ አስኪያጁ አቶ ሽመልስ ዘነበ እንደገለጹት የእሳት ቃጠሎው የተነሳው ዘጠኝ ሰዓት አካባቢ በፓርኩ ሰንጎ ሜዳ በሚባለው ስፍራ ነው።

በቃጠሎም 40 ሄክታር ያህል የፓርኩ አካል መጎዳቱን ጠቅሰው በዚህም ከኤሊ በስተቀር በሌሎች የዱር እንስሳት ላይ ጉዳት አለመድረሱን አመልክተዋል።

አቶ ሽመልስ የቃጠሎው መንስኤ በጫሞ ሀይቅ ዳርቻ የሚገኙ ህገ-ወጥ አሣ አስጋሪዎችን ጠርጥረዋል፡፡ ሆኖም የቃጠሎው ከተነሳበት አንድ ሰዓት ቆይታ በኋላ በህብረተሰብ ተሳትፎ በተደረገው ርብርብር መቆጣጠር መቻሉን አስታውቀዋል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት እሰራለሁ" - ፖሊስ

የጋሞ ዞን ፖሊስ አዛዥ የሆኑት ኮማንደር ሬታ ተክሉ በነጭ ሣር ብርሄራዊ ፓርክ የደረሰውን እሳት ለመቆጣጠር ፖሊስ፣ መከላከያ ሠራዊትና የፓርኩ ጥበቃዎች ወድያውኑ በመሰማራት ድጋፍ ማድረጋቸወን ገልጸዋል።

በቃጠሎው ከፓርኩ ሣሮችና ዛፎች ውጭ በእንስሳት ላይ የከፋ አደጋ ሳያስከትል መግታት መቻሉን ተናግረዋል። የአደጋውን መንስኤ ለማጣራት የዞኑ ፖሊስ እንደሚሠራም ጠቁመዋል፡፡ ባለፈው ዓመትን በተመሳሳይ በዚሁ ወርና ቦታ ላይ የእሳት ቃጠሎ ተነስቶ ከ600 ሄክታር በላይ የፓርኩ አካል መጉዳቱ ይታወሳል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከዱራሜ ቲክቫህ ቤተሰቦች፦

"የከምባታ ጠምባሮ ዞኖ ዋና ከተማ ዱራሜ ክቡር ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድን የካቲት 18 በድምቀት ለመቀበል ሙሉ ዝግጅቷን አጠናቃ በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በዱራሜ ከተማ ዝግጅት ተጠናቋል...

ነገ የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ/ም ጧት በዱራሜ ሁለገብ ስታዲየም ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አቀባበል ይደረጋል። እሳቸውም ንግግር ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የስታዲየም ዝግጅት እንዳለቀ በከምባታ ጠምባሮ ዞን ምክር ቤት መሰብሰቢያ አዳራሽ ከተለያዩ የኅብረተሰብ ተወካዮች ጋር ውይይት ያደርጋሉ።

ምንጭ፦ የከምባታ ጠምባሮ ዞን
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

ዕሮብ የካቲት 18 ቀን 2012 ዓ/ም ለትራፊክ ዝግ የሚሆኑ መንገዶችን ዝርዝር የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ፦

- ለደህንነት ጥንቃቄ ሲባል በ18/06/2012 ዓ/ም ከጧቱ 12፡00 ጀምሮ እስከ ቀን 8፡00 ባለሁለትና ባለ ሦስት እግር ተሸከርካሪዎች በዱራሜ ከተማ እንዳይንቀሳቀሱ ተወስኗል፡፡

- ከዬትኛውም አቅጣጫ ከላይ የተጠቀሱት ተሸከርካሪዎች ወደ ዱራሜ ከተማ ክልል መግባት አይችሉም።

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ካቢኔዎቻቸው የሚንቀሳቀሱባቸውን አካባቢዎች ተገቢ ጥንቃቄ ማድረግ በማስፈለጉ ከዚህ የሚከተሉት መንገዶች ለተወሰኑ ሰዓታት ለትራፊክ ዝግ ይሆናሉ፦

- የሀላባ ሻሸመኔ ዋናዉ መንገድ ከዞኑ ከተማ ልማት መምሪያ እስከ ፒፒ ከረጢት ፋብሪካ ድረስ

- የዱራሜ ስታዲየም ዙሪያና ሁሉም መጋቢ መንገዶች

- የከምባታ ጠምባሮ ዞን አስተዳደር ም/ቤት ዙሪያ ያሉ ሁሉም መጋቢ መንገዶች

More https://telegra.ph/TIKVAH-02-25

[የከምባታ ጠምባሮ ዞን ፖሊስ መምሪያ]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በሌላ መረጃ፦

በነገው እለት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐብይ አህመድ በሀላባ ዞን 'ቁሊቶ ከተማ' ተገኝተው ከዞኑ ህዝብ ጋር ውይይት ያደርጋሉ። ጠቅላይ ሚኒስትሩን ለመቀበል ዝግጅት መጠናቀቁ ተገልጿል።

ምንጭ፦ ሃላባ ዞን ኮሚኒኬሽን
PHOTO : ሀዋሳ የክልሉ ማርሽ ባንድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የ8 ሰዎችን ህይወት የቀጠፈው የትራፊክ አደጋ፦

- አደጋው የደረሰው ከገረሴ ወረዳ ወደ አርባምንጭ ከተማ ሲጓዝ የነበረ ኮድ 3-14167 ሚኒባስ መኪና በመገልበጡ ነው። ሾፌሩንና ረዳቱን ጨምሮ 8 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።

- 13 ሰዎች ከባድ እና ቀላል የአካል ጉዳት ደርሶባቸው በአርባምንጭ አጠቃላይ ሆስፒታል በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

- ከገረሴ ወረዳ መንገደኞችን ጭኖ ወደ አርባምንጭ ሲጓዝ የነበረው ሚኒባስ መኪና በአርባምንጭ ዙሪያ ወረዳ ቆላ ሼሌ መግቢያ ሲደርስ ነው የተገለበጠው።

- ከጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ የተገኘው መረጃ እንደሚያመለክተው አደጋው ከቀኑ 9፡00 ሰዓት አካባቢ ነው የደረሰው። የአደጋው መንስዔ እየተጣራ ነው።

ምንጭ፦ የጋሞ ዞን ፖሊስ መምሪያ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#attention

የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰቦች፦

ዛሬ አመሻሹን በአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ አካባቢ የአንበጣ መንጋ መመልከታቸው ለቲክቫህ ቤተሰቦች ጠቁመዋል።

ቦሌ አራብሳ ፣ የካባዶ፣ ለገጣፎ የሚገኙ ቤተሰቦቻችንም በተመሳሳይ የአንበጣ መንጋ መመልከታቸውን ጠቁመዋል።

በተመሳሳይ በሻሸመኔ ከተማ ዙሪያ የሚገኙ ቤተሰቦቻችን የአንበጣ መንጋ መመልከታቸው አሳውቀዋል። ሁሉም አካል መንጋው ጉዳት እንዳያደርስ ጥንቃቄ እንዲያደርግ መክረዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Attention

ከቲክቫህ መተከል ዞን ማንቡክ ቤተሰቦች፦

"መተከል ማንቡክ ከተማ ሰሞኑን እየተፈጠረ ያለው ነገር እጅግ አደገኛ እና አስፈሪ ነው። መንግስት ለአካባቢው ልዩ ትኩረት እንዲሰጠው መልዕክታችን ይድረስ። ሰው በፍርሃት እና በስጋት ላይ ነው ያለው። ዛሬም በጣም ሰው በፍርሃት እና በስጋት ውስጥ ሆኖ ነው የዋለው።"

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#attention

አሁንም በአንዳድን የማንቡክ አካባቢዎች የተኩስ ድምፅ እንደሚሰማ እየተገለፀልን ከቤተሰቦቻችን እየተገለፅልን ነው።

በአካባቢው የተፈጠረውንና እየተፈጠረው ያለውን ዝርዝር ጉዳይ ከቤተሰቦቻችን ጠይቀን፤ ተጨማሪ መረጃዎችን አካተን እንድታነቡት እናደርጋለን።

ለሁሉም ግን የሚመለከታችሁ አካላት [የፀጥታ ኃይሉ] የአካባቢውን ደህንነት እንድታስጠብቁ የቲክቫህ ማንቡክ ቤተሰቦች አሳስበዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሜ/ጄነራል ክንፈ ዳኘውና የአብዲ ኢሌ ጉዳይ...

ከዚህ ቀደም በተለያዩ ወንጀሎች ተጠርጥረው የነበሩ 63 ተጠርጣሪዎች ክሳቸው እንዲቋረጥ መደረጉን ዛሬ የፌደራል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ማስታወቁ፤ ክሳቸው የተቋረጠ ተጠርጣሪዎችን የስም ዝርዝር ይፋ መደረጉ ይታወቃል።

በማህበራዊ ሚዲያ [በተለይ በፌስቡክ] በስፋት ሲነገር የነበረው የሜ/ጄነራል ክንፈ ዳኘውና አብዲ ኢሌ ክስ ተቋርጧል እየተባለ የሚሰራጨው መረጃ ሀሰተኛ ነው።

የቀድሞው የሜቴክ ዳይሬክተር ሜጀር ጀኔራል ክንፈ ዳኘው እና የሱማሌ ክልል የቀድሞው ርዕሰ መስተዳድር አብዲ ኢሌ በዛሬው ስም ዝርዝር ውስጥ የሉበትም፡፡ ክሳቸውም አልተቋረጠም።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ወጣቶች ጥያቄ ቀጥሏል፦

ከተለያዩ የሀገራችን ክፍሎች ከሚገኙ የቲክቫህ ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት የሚመጡት መልዕክቶች ዛሬም ቀጥለዋል። የአብዛኛው ወጣቶች ሀሳብ የሚያመሳስላቸው ወጣቶቹ በእጅጉ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮችን መተቸታቸው ነው። ወጣቶቹ የገዢውን እንዲሁም የተቃዋሚ ኃይሎችን በእጅጉ ኮንነዋል፤ ስለ ወጣቶች የስራ ፈጠራ፣ ከኢኮኖሚ መሻሻል የሚሉት ነገር የለም ሲሉ ወቅሰዋል።

ከመጡት መልዕክቶች መካከል ለዛሬ፦

የፖሎቲካ ፖርቲዎች ለወጣቱ ትኩረት አልሰጡም። በብዙ ፓርትዎች ውስጥ ወጣት አመራሮች እምብዛም አይታዩም። ለሀገራችን ወጣቶች ትኩረት የሚሰጥና በስራ ፈጠራ ላይ የሚያተኩሩ፣ ለወጣቶች ኑሮ መሻሻል የሚታገሉ ፖርቲዎች ያስፈልጉናል።

ሁሉም በሚባል ደረጃ ፖለቲከኞች ወጣቶችን የራሳቸው የፖለቲካ መጠቀሚያ ከማድረግ በቀር አንዳቸውም ስለ ኢኮኖሚ እና ስራ ፈጠራ ሲያወሩ እንኳን አይሰማም።

ወጣቱን ሁሌም ስለተበዳይነት ነዉ የሚሰብኩት። የስራ እድል፣ የወጣቶች ህይወት በሚሻሻልበት ጉዳይ የሚከራከር የሚያወራ የለም፤ ነገሮች እየተባባሱ ወጣቶችን ተስፋ ወደማስቆረጥ እየከተቱ ነውና ይታሰብበት።

መልዕክት መቀበያ : @tikvahethiopiaBot

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#NewsAlert

በአፍሪካዊቷ ሀገር አልጀሪያ በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የተያዘ ግለሰብ መኖሩ ተረጋገጠ። የሀገሪቱ ብሄራዊ የቴሌቪዥን ጣቢያ እንደዘገበው ቫይረሱ የተገኘበት የካቲት 17/2020 ወደ አልጄሪያ የገባ የጣልያን ዜግነት ያለው ግለሰብ ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
- ል'ዩ ቅ'ና.ሽ፤ ፈጣ.ን JI.O W'I.FI 4.G LT.E P.OD ፤ 0911284606 ወይም 0913979706

- ከነ'ፃ ማድረ'ሻ ጋ'ር fr'ee deliv'ery 🚚 #JI.O 4G WIFI ፍጥነት በመጠቀም et.hiotel network ጋር ተስማሚ እና ፈጣን፤ ዋጋ 3000ብር የነበረውን 2500ብር
ከ1 ዓመት ዋስትና ጋር፤ አንድ ጊዜ ከ 32 ሰው በላይ ማስጠቀም የሚያስችል

- ቻርጅ ተደርጎ ረጀም ሰአት የሚቆይ፤ 4G ሲም ካርድ የሚሰራ፤ በጣም ፈጣን እና አስተማማኝ፤ ያዞ ለመንቀሳቀስ በጣም አመቺ፤ አድራሻ> ቦሌ መዳሃንያለም ቤዛ ህንፃ 2ኛ ፎቅ #208 ይጫኑት https://t.iss.one/joinchat/AAAAAEVlN7CGVU5yac-DFA
#NewsAlert

ኢትዮጵያ የታላቁ የህዳሴ ግድብን አስመልክቶ ከሱዳን እና ግብጽ ጋር በአሜሪካ ሊካሄድ የታሰበው ድርድር ላይ እንደማትገኝ አስታወቀች።

የታላቁ የህዳሴ ግድብን የተመለከተ ውይይት በኢትዮጵያ፣ ግብጽ እና ሱዳን መካከል በአሜሪካ ግምጃ ቤት ሃላፊ እና የዓለም ባንክ ፕሬዚዳንት በታዛቢነት የተገኙበት የሶስትዮሽ ድርድር በአሜሪካ ሲካሄድ መቆየቱ ይታወሳል።

ሆኖም የኢትዮጵያ ተደራዳሪ ቡድን በሃገር ውስጥ ከባለድርሻ አካላት ጋር የሚያደርገውን ውይይት ባላማጠናቀቁ የካቲት 19 እና 20 ቀን 2012 በዋሺንግተን ዲሲ ከተማ ሊካሄድ በታሰበው የሶስትዮሽ ድርድር ላይ እንደማይሳተፍ የውሃ ፣ መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር አስታውቋል።

ሚኒስቴሩ በተጠቀሰው ጊዜ አሜሪካ በመገኘት ድርድሩን ማድረግ እንዳልታቻለ ጥሪውን ላደረገው የአሜሪካ ግምጃ ቤት ቢሮ ማስታወቁንም ጠቅሷል።

ምንጭ፦ ኤፍ ቢ ሲ
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#ASTU

በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ /ASTU/ ቅጥር ግቢ ዉስጥ በሁለት ጓደኛሞች ተማሪዎች መካከል በተፈጠረ አለመግባባት የካቲት 17/2012 ከምሽቱ ሁለት ሰዓት አካባቢ የ4ኛ ዓመት ተማሪ የሆነዉ ተማሪ ዘሪሁን መንግስቱ ህይወት ያለፈ ሲሆን በግድያዉ የተጠረጠረዉ ተማሪ እጁን ለፖሊስ ሰጥቷል፡፡

በተባባሪነት የተጠረጠረዉ ተማሪ በፖሊስ ቁጥጥር ስር ሆኖ ጉዳዩ በአዳማ ከተማ ወንጀል ምርመራ አካላት እየተጣራ ይገኛል ሲል ዩኒቨርሲቲው አስታውቋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው እንደገለጸው በቀጣይም የተማሪዉን አሟሟት የሚገልፅ የፖሊስና የህክምና ምርመራ ዉጤት እንደደረሰ ለሚመለከተዉ አካል የሚገልጽ መሆኑን አስታውቋል፡፡

[Tikvah-family፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርሲቲ]

@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot