TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.5K photos
1.51K videos
215 files
4.12K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
የጌዴኦ ህዝብ ክልልነት ጥያቄ...

የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት 4ኛ መደበኛ 4ኛ ዙር አስቸኳይ ጉባኤ የሥራ ዘመን አንደኛ አስቸኳይ ጉባኤ ዛሬ ባካሄደው አስቸኳይ ጉባኤ የጌዴኦ ህዝብ በክልል የመደራጀት ጥያቄን ገምግሞ በሙሉ ድምጽ አጽድቋል።

በሙሉ ድምፅ ውሳኔውን ያሳለፈው ምክር ቤቱ የጌዴኦን ዞን ክልል ለመሆን የሚያስችሉ ዘርፈ ብዙ ሁኔታዎች ያሉ መሆናቸውንም የምክር ቤቱ አባላት ገልጸዋል።

የጌዴኦ ዞን ምክር ቤት አባላት የጌዴኦ ህዝብ በክልልነት ቢደራጅ ለህብረተሰቡ የሚኖረውን ማህበራዊ ፣ ኢኮኖሚያዊ እና ፖለቲካዊ ፋይዳዎች ላይም ሰፊ ውይይት አድርገዋል ተብሏል።

[የጌዴኦ ዞን ብልጽግና ፓርቲ ህዝብ ግንኙነት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"መንግሥት ጥያቄዎችን ለመመለስ ባለው አቅም ሁሉ ይሰራል" - ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከስልጤ ዞን ነዋሪዎች ጋር ባደረጉት ውይይት በርካታ ጥያቄዎች ቀርበውላቸው ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

የመሠረተ ልማት፣ የመልካም አስተዳደር እንዲሁም ወቅታዊ አገራዊ ሁኔታዎች ላይ ያተኮሩ ጥያቄዎች ተነስተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይም መንግሥት ባለው አቅም ጥያቄዎችን ለመመለስ መሠራት ያለበትን ሁሉ እንደሚሠራና ኅብረተሰቡም በሚችለው ሁሉ አስተዋጽኦ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

በደቡብ የሚነሱ የክልልነት ጥያቄዎችን በተመለከተ ቀደም ብሎ ከክልሉ የተለያዩ አካባቢዎች ከተውጣጡ የህብረተሰብ ተወካዮች ጋር መወያየታቸውን አስታውሰው፣ ጥያቄዎችን በጥናት ላይ በተመሠረተ መንገድ እንደሚመለከቱ ገልፀዋል፡፡

በብሄር ብሔረሰቦች ቁጥር ክልል እንደማይመሠረት ፣ ነገር ግን ሕዝቡ ራሱን በራሱ የማስተዳደር መብቱ እንደሚከበርም ተሰምሮበታል፡፡

ምንጭ፡- የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የካቲት 12 የሰማእታት ቀን በአዲስ አበባ እየተከበረ ነው!

83ኛው የሰማእታት ቀን በአዲስ አበባ የ6 ኪሎ የሰማእታት መታሰቢያ ሀውልት አደባባይ አባት አርበኞችና ሌሎች የከተማዋ ነዋሪዎች በተገኙበት በመከበር ላይ ነው፡፡

የሀገር መከላከያና የፌደራል ፖሊስ መርሽ ባንድ በቦታው በመገኘት የሰማእታት ቀኑን በተለያዩ ጣእመ ዜማዎች እያሰቡ ይገኛሉ፡፡

የአባት አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ እለቱን አስመልከቶ በሰጡት አስተያየት ቀኑ የዛሬ 83 አመት በፋሺስት ኢጣሊን መሪ በሆነው በግራዚያኒ አማካኝነት ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት እለት ነው፡፡

አሁን ያለው ወጣት እለቱን ሲያስብ አባቶቹ በመሰዋትነት ያቆዩለትን ሀገር በአንድነት በመሆን በማበልጸግና ሰላሟን በመጠበቅ ወደፊት ለማስቀጠል መሆን እንዳለበት ልጅ ዳንኤል ጆቴ መልእክት አስተላልፈዋል።

#ኢዜአ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት12

"አሁን ያለው ትውልድ ይቅር መባባልን ከታሪካችን ሊማር ይገባል" - የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዝዳንት

83ኛው የሰማዕታት ቀን አዲስ አበባ 6ኪሎ በሚገኘው የሰማዕታት መታሰቢያ ሐውልት እየተከበረ ይገኛል።

በበዓሉ ላይ የጥንታዊት ኢትዮጵያ አርበኞች ፕሬዚዳንት ልጅ ዳንኤል ጆቴ ዕለቱን አስመልክቶ ባስተላለፉት መልእክት፣ ቀኑ የዛሬ 83 ዓመት በፋሺስት ጣሊያን ወራሪ ጦር መሪ በሆነው ግራዚያኒ ከ30 ሺህ በላይ ኢትዮጵያውያን በግፍ የተገደሉበት ዕለት ነው ሲሉ አስታውሰዋል።

ሆኖም ይህንን ጭፍጨፋ በይቅርታ ዘግተን ወደፊት በመጓዝ እዚህ ደርሰናል፤ አሁን ያለው ትውልድም ይቅር መባባልን ከዚህ ሊማር ይገባል ብለዋል።

አክለውም፣ ወጣቱ ዕለቱን ሲያስብ አባቶቹ በመሥዋትነት ያቆዩለትን አገር በጋራ ለማሳደግ እና ሰላሟን ለመጠበቅ መነሣት ይገባል ሲሉ ተናግረዋል።

ዕለቱ አባት አርበኞች ፣ የአዲስ አበባ ምክትል ከንቲባ የማኅበራዊ ጉዳዮች አስተባባሪ ኢንጂነር እንዳወቅ አብጤ ፣ ሌሎች የክብር እንግዶች፣ የከተማዋ ነዋሪዎች እና የውጭ አገራት ቆንስላ ተወካዮች በተገኙበት ነው እየተከበረ የሚገኘው።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#UPDATE - የሟቾች ቁጥር 2,012 ደርሷል - በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,307 በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,012 የደረሰ ሲሆን 75,307 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 14,942 መድረሳቸውን ተመልክተናል። @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

- የሟቾች ቁጥር 2,120 ደርሷል
- በቫይረሱ የተጠቁ ሰዎች ቁጥር 75,730

በኮሮና ቫይረስ [#COVID19] የሞቱ ሰዎች ቁጥር 2,120 የደረሰ ሲሆን 75,730 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተጠቅተዋል። ከበሽታው አገግመው ከሆስፒታል የወጡ ሰዎች ቁጥር ደግሞ 16,155 መድረሳቸውን ተመልክተናል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#የካቲት12

የካቲት 12 ቀን ጣልያን ኢትዮጵያን በወረረችበት ወቅት በጀነራል ግራዚያኒ ትዕዛዝ የተጨፈጨፉ ኢትዮጵያዉያን የሚታሰቡበት ነዉ። የዛሬ 83 ዓመት ግራዚያኒ የተባለዉ የጣሊያን ጀነራል ከሀገሩ ኢጣሊያ ንጉሳዊያን ቤተሰቦች ዘንድ አንድ ልዑል መወለዱን አስመልክቶ ደስታዉን ለማክበር የአዲስ አበባ ነዋሪዎችን በአሁኑ 6 ኪሎ ዩንቨርሲቲ በቀድሞዉ ገነተ ልሎል ቤተመንግሥት ሰበሰበ።

በዚህ ወቅት የፋሽሽት ኢጣሊያ ወረራ ያስቆጫቸዉ ሞገስ አስገዶም እና አብርሃ ደቦጭ የተባሉ ሁለት ወጣቶች ከተሰበሰበዉ ሕዝብ መሀል ወጥተዉ ወደ ግራዚያኒ ቦንብ ወረወሩ። በዚህም ግራዚያን እና በርካታ ባለስልጣናቱ ቆሰሉ። ይህ ያበሳጨዉ የፋሽስት ኢጣሊያ ጀነራል ግራዚያኒ ያለርህራሄ ኢትዮጵያዉያን እንዲጨፈጨፉ አዘዘ።

ኢትዮጵያውያኑ ሰማዕታት በፋሽሽት ኢጣሊያ የተጨረጨፉት በ1929 ዓ/ም የካቲት 12 ቀን ልክ የዛሬ 83 ዓመት ነበር። ወጣት አብርሃ ደቦጭ እና ሞገስ አስገዶምን ጨምሮ በሦስት ቀናት ብቻ 30 ሺህ ኢትዮጵያዉያን በዕለቱ ተሰውተዋል።

የሰማዕታቱ መታሰቢያ ሀውልት በአዲስ አበባ ከተማ በስድስት ኪሎ አደባባይ ላይ ቆሟል። በሀውልቱ ሥር በየዓመቱ የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ የመታሰቢያ ስነስርዓት ይካሄዳል። ዛሬም በስፍራው ህዝብ በተገኘበት የአበባ ጉንጉን በማስቀመጥ እና በተለያዩ ስነስርዓቶች ዕለቱ ታስቧል።

#DW2011የካቲት12 #ENA2012የካቲት12
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#UPDATE

ዛሬ ማለዳ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ የ18ኛ ክፍለ ዘመን ዘውድ ለመመለስ ከመጡት የደች የውጪ ንግድ እና የልማት ትብብር ሚኒስትሯ ሲግሪድ ካግ ጋር ተገናኝተዋል።

ዘውዱ ከ1985 ዓ/ም አንስቶ ጠፍቶ የቆየ ሲሆን፣ በጥቅምት 2011 ዓ.ም. በኔዘርላንዷ ሮተርዳም ተገኝቷል።

የኔዘርላንድ መንግሥት ይህንን ቅርስ ለኢትዮጵያ መመለስ ጠቃሚ እንደ ሆነ በማመን ዘውዱ ወደ ኢትዮጵያ እንዲመለስ ሁኔታዎችን አመቻችቷል።

#PMOEthiopia
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ ተዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ቀረበ!

የኢፌዴሪ ሲቪል ሰርቪስ ኮሚሽን አዲስ የመንግሥት ሠራተኞች ውሎ አበል ደንብ አዘጋጅቶ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት ማቅረቡን አስታውቋል።

በኮሚሽኑ የኮሙዩኒኬሽን ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አለባቸው ዓለሙ፣ ረቂቅ ደንቡ ካለው ነባራዊ ሁኔታ በመነሣት በጥናት ላይ ተመሥርቶ መዘጋጀቱን አመልክተዋል።

ደንቡ በሚኒስትሮች ምክር ቤት ተመርምሮ ማስተካከያ ከተደረገበት በኋላ፣ ወደ ሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ተመርቶ ተግባር ላይ እንዲውል የሚደረግ መሆኑም ተጠቁሟል።

#ኢቢሲ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ከሐምሌ 1 ቀን 2004 ዓ/ም ጀምሮ ስራ ላይ የዋለው የመንግስት ሠራተኞች የቀን ውሎ አበል መመሪያ፦

የመንግሥት ሠራተኛ በየትኛውም ክልል ሄዶ ቢሰራ ከፍተኛ ደመወዝ አለው የሚባለው 225 ብር የሚታሰብለት ሲሆን፤ አነስተኛ ደመወዝ ተከፋይ ነው የሚባለው ደግሞ በቀን የሚያገኘው 111 ብር ነው።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ዛሬም የድጋፍ ሰልፎች ዛሬም እየተደረጉ ነው...

በዛሬው ዕለት የካቲት 12 ዓ/ም በበደሌ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐብይ አህመድን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። የሰልፉ ተሳታፊዎች እንደነገሩን ሀገር በጥላቻ፣ በስድብ እና የሰዎችን ስራ በማሳነስ አይገነባም፤ የተለያዩ አካላት ከስድብ እና ከማንቋሸሽ ይልቅ ለህዝብ ያላቸውን ሀሳብ ያቅርቡ ህዝቡ የሚሆነውን ይመርጣል የሚል መልዕክት በሰልፉ ተላልፏል።

በተመሳሳይ፦

በሻሸመኔ ከተማ የጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይን የለውጥ አመራር የሚደግፍ ሰልፍ እየተደረገ ይገኛል። በስለፉ የከተማው ነዋሪዎች የትኛውም ወገን ከስድብና ከጥላቻ እንዲቆጠብ መልዕክት ተላልፏል።

በሌላ መረጃ፦

ትላንት ምሽት ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ኮሚኒኬሽን ቢሮ ይፋዊ የፌስቡክ ገፅ እንደተመለከትነው ነገ ዓርብ የካቲት 13 የጠቅላይ ሚኒስትሩን ስራ የሚያበረታታ፣ የለውጥ ኃይሉንም የሚደግፍ ሰልፍ ይደረጋል ተብሏል።

[ፎቶ : በደሌ እና ሻሸመኔ ቲክቫህ ቤተሰቦች]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ግንባታ...

በሜድሮክ እህት ኩባንያ ‹‹ሆራይዘን ፕላንቴሽን›› እየተገነባ ያለው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ ተጠናቆ ሥራ ሊጀምር የመጨረሻ ምዕራፍ ላይ እንደደረሰ የፕሮጀክቱ ሥራ አስኪያጅ አስታወቁ።

በሆራይዘን ፕላንቴሽን የእቅድ ቢዝነስ ልማትና ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ አቶ ይበልጣል ሽመልስ በተለይ ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንደገለጹት ግንባታው ከተጀመረ ወራትን ያስቆጠረው የሸገር ዳቦ ማምረቻ ፋብሪካ የመጨረሻው ምዕራፍ ላይ ደርሷል።

የመሰረት ድንጋይ ከተጣለ ጀምሮ ሥራው በጥብቅ ክትትልና ቁጥጥር እየተመራ እንደነበር የተናገሩት ሥራ አስኪያጁ በቀን 18 ሰዓት በመስራት ግንባታውን ማፋጠን እንደተቻለና ጎን ለጎንም የማሽነሪዎችንና የሌሎች ግብዓቶችን ግዢ ተፈፅሞ ሀገር ውስጥ መግባታቸውን ገልጸዋል።

ምንጭ፦ አዲስ ዘመን ጋዜጣ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት ተመረቀ!

የታላቁ ኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ ፕሮጀክት ስራ አስኪያጅ የነበሩት የኢንጅነር ስመኘው በቀለ የመታሰቢያ ሐውልት በዛሬው ዕለት ተመረቀ፡፡

በመታሰቢያ ሐውልቱ የምርቃት ሥነ ስርዓት ላይ በኦርቶዶክስ እምነት ስርዓት መሰረት የፍትሃትና የፀሎት ሥነ - ስርዓት ተካሂዷል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም በሐውልቱ ምርቃት ስነ ስርዓት ላይ የተገኙ የተለያዩ ድርጅቶ፣ ቤተሰቦችና ወዳጅ ዘመዶች የአበባ ጉንጉን አስቀምጠዋል፡፡

[የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#SolveITAccelerator

Icog Labs ከJICA ጋር በመተባበር ከኩዱ ቬንቸር በተገኘ ድጋፍ Solve IT Accelerator በተሰኘ ፕሮግራማቸው ለሥራ ፈጣሪዎችን ለማብቃት ፣ የገንዘብ ድጋፍ እንዲሁም የተለያዩ ስልጠናዎችንና ድጋፎችን ለማድረግ መጨረሳቸውን አዘጋጆቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

Solve IT Accelerator በቅርቡ በይፋ ለሚዲያዎች ጋዜጣዊ መግለጫ የሚሰጥ ሲሆን ወጣት ሥራ ፈጣሪዎችን የሚመዘግብበትና ስለ ፕሮግራሙ የሚገልጽበትን ድረ ገጽ ይፋ አድርጓል፡፡ ቲክቫህ ኢትዮጵያም ቤተሰቦቻችን ይህንን እድል እንዲትጠቀሙ እየጠቆምን ተከታታይ መረጃዎችንም የምናደርሳችሁ ይሆናል፡፡

More https://www.icog-sa.com

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopiaB
TIKVAH-ETHIOPIA
መንግስት ንብረታችንን እየነጠቀን ነው... መኪና የተነጠቀባቸው የቤተሰባችን አባላት፦ "መንግስት የህዝብ ንብረት መንጠቅ ተያይዞታል። ኮድ 2 ኦሮ VAN መኪኖች የሰጠን ኦሮሚያ መንገድ ትራንስፖርት ስህተት ካለበት የሰጠ አካል ነው መጠየቅ ያለበት ህዝብ ያለጥፋቱ እየተገላታ ነው። ኮድ 2 ኦሮ van መኪኖች እየቀሙ ቃሊቲ ግምሩክ መጋዘን እያስቀምጡ ነው እነሱ የሚሉት ኮድ 3 መሆን ነበረባቸው፤ ኮድ 2…
ከቲክቫህ ቤተሰቦች፦

መኪናቸውን ተይዞ ጉምሩክ እንዲያስገቡ የተጠየቁ ባለንብረቶች የተፈፀመባቸውን አግባብ ያልሆነ ድርጊት በተመለከተ ለሚመለከታቸው አካላት ቅሬታ አሰምተዋል።

ከጥዋት ጀምሮ ስንከራተት ነበር ያሉት የቲክቫህ ቤተሰቦች ወ/ሮ አዳነች አቤቤን ለማግኘት ሞክረን ነበር ግን ሚኒስትሯ ሰኞ ነው የሚገቡት ተብለን ተመልሰናል ብለዋል። ሌሎች በስፍራው ያገኘናቸው አካላት ደግሞ እየሆነ ያለውን ነገር እውቅና የሌለው ነው ብለውናል ሲሉ ለቲክቫህ መልእክታቸውን ልከዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia