TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
211 files
4.1K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
መንግስትን የሚደግፍ ሰልፍ በጎባ ተካሂዷል!

በኢትዮጵያ መንግስት በሀገር ደረጃ የተጀመረው የለውጥ እንቅስቃሴ በመደገፍ የባሌ ዞን የጎባ ከተማ እና አካባቢው ነዋሪዎች በጎባ ከተማ ሰልፍ ማካሄዳወቸውን የባሌ ዞን መንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የፒክ ፒክ ታክሲ ተሽከርካሪዎች ለምን ታገዱ?

[ሸገር ኤፍ ኤም 102.1]

የፒክ ፒክ ታክሲ ከባንክ የተበደረውን ገንዘብ መክፈል ባለመቻሉ ተሽከርካሪዎቹ በባንክ ታግደዋል። የፒክ ፒክ ታክሲ ከህብረት ባንክ የወሰደውን ብድር መክፈል ባለመቻሉ ነው ባንኩ ተሽከርካሪዎቹን አግዶ ያቆመው፡፡

በዚህም ምክንያት 266 የፒክ ፒክ ታክሲ ተሽከርካሪዎች ከስራ ወጥተው ቆመዋል። በቁጥር የበዙ የፒክ ፒክ አሽከርካሪዎችም ከስራ ተሰናብተዋል።

ሾፌሮቹ በድንገት ከስራ መባረራችን ትክክል አይደለም ሲሉ ቅሬታ አሰምተዋል። የፒክ ፒክ የስራ ሀላፊ እንደተናገሩት ፦ ኩባንያው የባንክ እዳውን መክፈል ባለመቻሉ ሰራተኞቹን አላሰናበተም ለአንድ ወር ከስራ አግጃለሁ ብሏል።

ምንጭ፦ ሸገር ኤፍ ኤም 102.1
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
65 የጉሙሩክና ገቢዎች ሰራተኞች እርምጃ ተወሰደባቸው!

በአማራ ክልል በጥቅም ትስስር የቀን ገቢ ጥናትን በመሰረዝ ፣ ዝቅ አድርጎ በመገመትና ተያያዥ የስነ ምግባር ጉድለት በተገኘባቸው 65 የጉምሩክና ገቢዎች ሰራተኞች ላይ ህጋዊ እርምጃ መውሰዱን የክልሉ ገቢዎች ቢሮ ገለፀ።

የቢሮው ሃላፊ ወይዘሮ ብዙአየሁ ቢያዝን በባህርዳር ከተማ እየተካሔደ ባለው የቢሮው የስድስት ወራት የስራ አፈፃፀም የግምገማ መድረክ ላይ እንደ ተናገሩት የክልሉ የገቢ አቅም እንዳያድግ እንቅፋት የሆኑ ሰራተኞችን በጥናት በመለየት የማስተካከያ እርምጃ ተወስዷል ብለዋል።

በሰራተኞቹ ላይ እርምጃው የተወሰደው የተጣለባቸውን ሃላፊነት ወደ ጎን በመተው ከግብር ከፋይ ነጋዴዎች ጋር ያልተገባ ግንኙነት በመፍጠር ለግል ጥቅማቸው ሲሰሩ በተጨባጭ በመገኘታቸው እርምጃው እንዲወሰድ ሆኖአል ሲሉ ገልፀዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Election2012

የጨፌ ኦሮሚያ አፈ ጉባኤ ወ/ሮ ሎሚ በዶ የክልሉ ምክር ቤት ስብሰባን ሲከፍቱ እንደተናገሩት፤ ቀጣዩ ምርጫ "ዴሞክራሲያዊ፣ ፍትሃዊ እና ነጻ" እንዲሆን፤ በቀጣይ ወራት የመንግስት ቀዳሚ እና ዋነኛ ስራው መሆን የሚገባው "ሰላምን ማረጋገጥ ነው" ብለዋል።

#EthiopiaElection
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"አንዳንድ ከቻይና ወደ ሀገር ውስጥ የሚገቡ መንገደኞች ለምርመራ ፍቃደኛ ባለመሆናቸው የፀጥታው ሀይል ድጋፍ ሊያደርግ" - ዶክተር ኤባ አባተ
.
.
የኮሮና ቫይረስ ወደ ኢትዮጵያ እንዳይገባ ባለድርሻ አካላት እና የክልል መስተዳድሮች አስፈላጊውን ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ የኢትዮጵያ ማህበረሰብ ጤና ኢንስቲትዩት አስታውቋል፡፡

የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የሴቶች ፣ ወጣቶች እና ማሕበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የኢንስቲትዩቱን የድንገተኛ አደጋዎች ምላሽ ማስተባበሪያ ማዕከል ዛሬ ጎብኝተዋል፡፡

የኮሮና ቫይረስ በሽታ [COVID19] ወደ ሀገር እንዳይገባ እየተደረገ ያለውን የመከላከል ስራን አስመልክቶ የኢንስቲትዩቱ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ኤባ አባተ ገለፃ አድርገዋል። በዚህ ወቅትም ባለድርሻ አካላትና የክልል መስተዳድሮች አስፈላጊውን ድጋፍና ጥንቃቄ ሊያደርጉ እንደሚገባ ጠቁመዋል፡፡

በሽታው ከጉንፋን ቫይረስ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሲሆን በ14 ቀናት ውስጥ ሳል፣ ንጥሻ፣ የትንፋሽ ማጠርና የጉረሮ ህመም ምልክቶችን የሚያሳይ ሲሆን ÷ይህም በሽታው በፍጥነት እንዲዛመት ያደርጋል ሲሉ ሃላፊው ገልጸዋል፡፡

More https://telegra.ph/COVID19-02-18-2

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

በቻይናዋ ሁዋን ግዛት የሚኖሩ 276 ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ እስከ 300 ዶላር የሚደርስ ገንዘብ አንደሚሰጣቸው የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።

በቻይናዋ ቾንቺ የኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ፅ/ቤት ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 እንዳስታወቀዉ በኮሮና ቫይረስ ምክንያት ችግር ዉስጥ ለሚገኙ ኢትዮጵያዉያን ተማሪዎች ከነገ ጀምሮ የገንዘብ ድጋፉ ይሰራጫል ብሏል፡፡

የኮሮና ቫይረስን ስርጭት ለመከላከል ሲባል ተማሪዎቹ በመኖሪያ ቤታቸዉ በመቀመጣቸዉ የምግብ እና በሽታዉን ለመከላከል የሚረዱ ቁሳቁሶችን ለማግኘት መቸገራቸዉም ተነግሯል፡፡

[ETHIO FM 107.8]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በኢትዮጵያ ቆንስላ ጀነራል ፅህፈት ቤት ተጠባባቂ አቶ አንተነህ ታሪኩ ለኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 የተናገሩት፦

- የኢትዮጵያ መንግስት ለተማሪዎቹ የመደበዉን የገንዘብ ድጋፍ ለማከፋፈል የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ተጠናቀዋልም

- ለተማሪዎቹ ከነገ ጀምሮ ጀምሮም 276 ተማሪዎች ወጪያቸዉን እንዲሸፍኑ የሚረዳቸዉን ገንዘብ ለእያንዳንዳቸዉ ገቢ ይደረጋል።

- በከተማዋ የባንክ እና ሌሎች የፋይናንስ ተቋማት በቫይረሱ ምክንያት በመዘጋቱ ድጋፉ በእያንዳንዳቸዉ የሞባይል ስልክ እንዲደርስ ይደረጋል።

- መንግስት የተማሪዎች ደህንነት እንዲጠበቅ አስፈላጊዉን ድጋፍ ያደርጋል።

- ተማሪዎቹ በሚገኙበት የትምህርት ተቋም 24 ሰዓት የሚያገልግሉ ማዕከሎች እንደሚገኙና ተማሪዎችም ምርመራቸዉን እንደሚያደርጉ ይደረጋል።

[ETHIO FM 107.8]

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለፈረስ ደንበኞች በሙሉ!

የፈረስን አገልግሎት ሲጠቀሙ ከእያንዳንዱ ጉዞ 10% የማይልስ ስጦታ ያገኛሉ። በሰበሰቡት ማይልስ ካርድ መሙላት፣ገንዘብ ወጭ ማድረግ፣ማስተላለፍ እንዲሁም ነፃ ጉዞ ማድረግ እንደሚችሉ ስናበስርዎ በታላቅ ደስታ ነው። አሁኑኑ መተግበሪያውን በማውረድ በፈረስ ይሂዱ ተጠቃሚ ይሁኑ https://play.google.com/store/apps/details?id=com.feres.user

#ፈረስ #Feres @feresapps
በድሬዳዋ የጅብ መንጋ ለማባረር ስራዎች እየተሰሩ ነው...

ድሬዳዋ ከተማ ገንደ ሮቃ በተባለው ስፍራ የሚርመሰመሰው የጅብ መንጋ ከአካባቢው ለማባረር የተቀናጀ ስራ እየተካሔደ መሆኑን ባለድርሻ አካላትና የአካባቢው ወጣቶች ገልፀዋል።

ከሁለት ሳምንት በፊት አንድ የሶስት (3) ዓመት ህፃን አንጠልጥሎ የወሰደው የጅብ መንጋ የሚኖርበትንና በብዛት የሚንቀሳቀስበትን አካባቢ በድሬዳዋና በፌደራል መንግስት ተቋማት ቅንጅት በማሽነሪና በሰው ሃይል እንዲፀዳ እየተደረገ መሆኑን የሚመለከታቸው አካላት ተናግረዋል።

በገንደ ሮቃ እየተባለው በሚሳጠራው ሰፈር የቀበሌ 03 መስተዳድር ስራ አስፈጻሚ አቶ ቢንያም ግርማ እንደገለጹት ጅቦቹ የሚደበቁበትን ጥሻዎች በጥናት በመለየት እንዲፀዱና ጅቦቹ አካባቢውን ለቀው እንዲሔዱ እየተደረገ ነው ብለዋል።

#ENA
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Diredawa

በድሬዳዋ ከተማ ሰባተኛ እየተባለ በሚጠራው አከባቢ በሚገኘው አየር ኃይል ጊቢ የጅቦች መኖሪያ እና መደበቂያ የነበሩት ስፍራዎች በዘመቻ እንዲፀዱ ተደርጓል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#Diredawa

የኢትዮጵያ አየር ኃይል የምስራቅ አየር ኃይል ምድብ ተወካይ ሻምበል መጎስ መኮንን ለኢዜአ የተናገሩት፦

ጅቦቹ በቀን በአየር ሃይል ጊቢ ውስጥ በመዘዋወር በሰውና በእንስሳት ላይ ጉዳት ሲያደርሱ ቆይተዋል።

በአንድ የሠራዊት አባል ቤት ድረስ ዘልቆ በመግባት ትንቅንቅ ገጥመው አባላችንንና በሌላ የሶስት ዓመት ህፃን ላይ ጉዳት አድርሶ ነበር።

አሁን የተጀመረውን ስራ በማጠናከር ጅቦቹን ከአካባቢው የማስወጣት የተቀናጀ ሥራ ተጠናክሮ ይቀጥላል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
#UPDATE

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ ለስድስት (6) የፖለቲካ ፓርቲዎች የምዝገባ እና የሀጋዊ ሰውነት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት ሰጥቷል።

ፓርቲዎቹ፦

• ሕብር ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ
• መላው አማራ ህዝብ ፓርቲ
• ነጻነትና ሰላም ለኢትዮጵያ ህብረት ፓርቲ
• የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ ( ኢዜማ)
• አፋር ነጻ አውጪ ግንባር ፓርቲ ( አነግፓ)
• የቦሮ ዴሞክራቲክ ፓርቲ

ምንጭ፡- ምርጫ ቦርድ
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ተቋርጦ የቆየው ኔትዎርክ ሙሉ በሙሉ ተመልሷል!

ዛሬ አመሻሹን ጀምሮ በበርካታ የሀገሪቱ ከተሞች የዳታ ኢንተርኔት እና የስልክ አገልግሎት ተቋርጦ ነበር። በአሁን ሰዓት አገልግሎቱ መመለሱን ቤተሰቦቻችን ገልፀዋል። በምን ምክንያት ኔትዎርክ ሊቋረጥ እንደቻለ ለማጣራት ጥረት እያደረግን ነው ፤ የምናገኛቸውን መረጃዎች እንድታነቡት እናደርጋለን።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ነገ ወራቤ ይገባሉ...

የስልጤ ዞን ርዕሰ መዲና የሆነችው ወራቤ ጠቅላይ ሚኒስተር አብይ አህመድን ለመቀበል ዝግጅቷን አጠናቃለች።

በነገው እለት ማለትም የካቲት 11/2012 የኢፌዴሪ ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ከስልጤ ዞን ልዩ ልዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ለመወያየት ፕሮግራም ተይዟል።

ይህን ፕሮግራም በተሟላ መልኩ ለማስኬድና እንግዶችንም በተገቢው ክብር ለመቀበል የዞኑ ርዕሰ መዲና ወራቤ ዝግጅቷን አጠናቃለች።

ውይይቱ የሚደረግባቸው ቦታዎች ማለትም የስልጤ ባህል አደራሽና የወራቤ ስታድየም አስፈላጊው ዝግጅት ተጠናቋል።

የዞኑ ህዝብ ለጠቅላይ ሚኒስተሩና እሳቸውን ተከትለው ለሚመጡ እንግዶች የተለመደውን የእንግዳ አቀባበል እንዲያደርግና ለውይይቱ ውጤታማነትም የበኩሉን እንዲወጣ ጥሪ ቀርቧል።

[ስ/ዞ/ህ/ግ/ጽ/ቤት]
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ብልፅግና ፓርቲ...

ከለውጡ በኋላ በተለያዩ አካባቢዎች በወንጀል ተጠርጥረው የታሰሩትን የፖለቲካ ምህዳሩን ለማስፋት ሲባል ጉዳያቸው በአግባቡ በህግ ታይቶ እንዲለቀቁ አቅጣጫ ተቀምጧል ሲሉ ጠ/ሚር ዶክተር ዐቢይ አህመድ ተናገሩ።

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ከትግራይ ተወላጅ የብልፅግና ፓርቲ አባላት ጋር ውይይት አድርገዋል።

የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ ተወካዮች ከትግራይ ተወላጅ ወታደራዊ እና ሲቪል ባለስልጣናት እስር ጋር በተያያዘ ጥያቄ አቅረበዋል።

እነዚህ አባላት ከለውጡ በኋላ በርካታ አመራሮች ከሁሉም አካባቢዎች መታሰራቸውን በመጥቀስ፤ አብዛኞቹ ግን የትግራይ ተወላጆች መሆናቸው በህዝብ ዘንድ ቅሬታ እና የመጠቃት ስሜት እንዲፈጠር አድርጓል ብለዋል።

ታሳሪ ግለሰቦቹ ወንጀል ይስሩ ወይም አይስሩ የፍርድ ቤት ጉዳይ መሆኑ ሳይዘነጋ ለህዝብ ሰላምና መረጋጋት ሲባል ከለውጡ በኋላ የታሰሩ ዜጎች ክስ ቢቋረጥ እና ጉዳዩ የእርቅ እና የይቅር ባይነት ማሳያ ተደርጎ ቢወሰድ ሲሉ ጠይቀዋል።

More https://telegra.ph/FBC-02-18

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል" - ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ

የኢህአዴግ የጥልቅ ተኃድሶ ግምገማ በተለያዩ ወንጀሎች የተከሰሱ የመንግስት ባለስልጣናት እንዳሉና አብዛኞቹ የትግራይ ክልል ተወላጆች መሆናቸውን በማስታወስ ጉዳያቸው በእርቅ እና በይቅርታ እንዲታይ የትግራይ ክልል የብልፅግና ፓርቲ አመራሮች ለጠ/ሚ ዶ/ር አብይ ጥያቄ አቅርበው ነበር።

ጠቅላይ ሚንስትሩም ከዚህ ቀደም በተለያየ ምክንያት ተጠርጥረው በእስር ላይ የሚገኙ ዜጎች ህግን በተከተለ መልኩ እልባት እንዲያገኙ እንደሚደረግ ገልፀዋል፡፡ ወንጀለኝነትን ከብሄር ጋር ማያያዝ አይገባም ያሉት ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ ማንኛውም ሰው በሰራው ወንጀል በህግ ይዳኛል የሚል ምላሽ ሰጥተዋል፡፡

#EBC
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ጠቅላይ ሚኒስትሩ ስለትግራይ ክልል የፀጥታ ሁኔታ..

በትግራይ ክልል ላይ የሚቃጣ ማንኛውም ጥቃት የክልሉ ብቻ ሳይሆን የኢትዮጵያ ጉዳይ መሆኑን ጠቅላይ ሚንስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ገልፀዋል። ኢትዮጵያ በዚህ ደረጃ የሚያሰጋት ምንም አይነት የውጭ ጥቃት አለመኖሩን ተናግረዋል።

የፌዴራል መንግስት የትግራይ ክልልን የመጠበቅ ግዴታ እንጂ በተቃራኒው የማጥቃት ህጋዊ አግባብም ሆነ ፍላጎት የለውም ያሉት ዶ/ር አብይ በክልሉ የሚገኘውን የአገር መከላከያ ሰራዊት ይህን ተልዕኮ እየፈጸመ መሆኑን ለአብነት አንስተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ትግራይ ክልልን በኢኮኖሚና ልማት አሻጥር ለማዳከም እየተሰራ ነው?

የበጀት ቀመርን የሚያወጣውና የሚደለድለው የፌዴራል መንግስት ሳይሆን የፌዴሬሽን ምክር ቤት መሆኑን ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በዛሬው ውይይት ተናግረዋል።

ከዚህ አንጻር ትግራይ በተያዘው በጀት ዓመት 8 ነጥብ 2 ቢሊዮን ብር ለቀጥተኛ በጀት፤ 400 ሚሊዮን ብር ደግሞ ለዘላቂ የልማት ግቦች የሚውል በጀት ተመድቦለታል ብለዋል። የተመደበው በጀት በፌዴራል መንግስት የሚሰሩ ፕሮጀክቶችን እንደማያካትት ተናግረዋል።

ለትግራይ ክልል በዘንድሮው ዓመት የተያዘው በጀት ከዚህ ቀደም ከነበሩት በእጅጉ እንደሚበልጥ ጠቅሰዋል።

የትግራይ ክልል ምክር ቤት በጀቱ ለተያዘለት ዓላማ ብቻ እንዲውል መቆጣጠር እንደሚገባውም ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ አውስተዋል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia