#BURAYUU
ዛሬ ማምሻውን በቡራዩ በነበረ የሆቴል ምርቃ ላይ የተገኙ ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል። በፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ከተፈፀመባቸው ሰዎች መካከል እውቋ አርቲስት ሀዊ ቀነኒ እና ሌሎች ይገኙበታል።
አርቲስት ሀዊ በተፈፀመባት ድብደባ ሆስፒታል ገብታ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው። የፀጥታ ኃይሎች ድምፃዊ ደሳለኝ ቤከማ እና አርቲስት ልጅ ያሬድን በቁጥጥር አውለው ነበር የተባለ ሲሆን ከሰዓታት በፊት ልጅ ያሬድ መለቀቁን ሰምተናል።
ልጅ ያሬድ በፌስቡክ ገፁ "የኦነግ ሸኔ ደጋፊ ነህ ተብዬ መሬት ላይ አከባለውኛል፤ ጭስ ቦንብም ወርውረዋል" ብሏል።
በቡራዩ ከተማ ስለተፈጠረው ክስተት OMN [ኦ ኤም ኤን] ከከተማው ከንቲባ ምላሽ ለማግኘት ጥረት ቢያደርግም ሊሳካለት እንዳልቻለ አሳውቋል።
በቡራዩ ከተማ የተፈጠረው ምንድነው? ለምን ሰዎች ተደበደቡ? ስለጉዳዩ የፖሊስ ምላሽ ምንድነው? ዘርዘር ያለና የመንግስት ምላሽ የተካተተበት መረጃ ስንመለከት እንድታነቡት እናደርጋለን።
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia

TIKVAH-ETHIOPIA
#BURAYUU ዛሬ ማምሻውን በቡራዩ በነበረ የሆቴል ምርቃ ላይ የተገኙ ሰዎች በመንግስት የፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ተፈፅሞባቸዋል ተብሏል። በፀጥታ ኃይሎች ድብደባ ከተፈፀመባቸው ሰዎች መካከል እውቋ አርቲስት ሀዊ ቀነኒ እና ሌሎች ይገኙበታል። አርቲስት ሀዊ በተፈፀመባት ድብደባ ሆስፒታል ገብታ የህክምና እርዳታ እየተደረገላት ነው። የፀጥታ ኃይሎች ድምፃዊ ደሳለኝ ቤከማ እና አርቲስት ልጅ ያሬድን በቁጥጥር…
#BURAYUU
የቡራዩ ከተማ አስተዳደር የመንግስት ኮሙዩኒኬሽን ጉዳዮች ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ አብደላ ጤቤሶ ለFBC የተናገሩት፦
ትናንት [የካቲት 7/2012 ዓ/ም] በከተማዋ የአንድ ሆቴል ምረቃት ላይ የነበረው ግጭት መንስኤ ስነ ስርዓቱን ለማድመቅ የተጋበዙ አርቲስቶች መካከል የዘፈን ምርጫን በተመለከተ የነበረ አለመግባባት ነው።
ያንንም አለመግባባት በመያዝ ምረቃው ተከናውኖ ምሽት ላይ ከውስጥም ከውጭም የነበሩ ልዩነቱን ይዘው ወደ መጣላት እና ግጭት አምርተዋል፤ በዚህም ወቅት በሁለት አርቲስቶች ላይ መጠነኛ ጉዳት ድርሷል።
በሰዓቱም ፖሊስ በስፍራው በመድረስ ግጭቱን በማሰቆም ተጨማሪ ጉዳት እንዳይደርስ አድርጓል። ጉዳቱን ማን እንዳደረሰ የፖሊስ ቡድን ተዋቅሮ እየመረመረ ነው።
ከዚህ ውጭ በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ስለ ጉዳቱ፣ ሰዎች ታስረዋል እና ፖሊስ ጉዳት አደረሰ ተብሎ የሚወራው ሀሰት መሆኑን እና የታሰረ ሰው እንደሌለ፤ የፖሊስም ሚና ግጭቱን የማስቆም እና ጉዳት እንዳይደርስ የማድረግ ብቻ ነበር። አሁን ላይ ከተማዋ ፍፁም ሰላማዊ ሁኔታ ላይ ትገኛለች።
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot