TIKVAH-ETHIOPIA
1.53M subscribers
59.3K photos
1.51K videos
212 files
4.11K links
ይህ የቲክቫህ (ተስፋ) ኢትዮጵያ ቤተሰብ አባላት መሰባሰቢያ እንዲሁም የመረጃ እና የመልዕክት መለዋወጫ መድረክ ነው።

@tikvahuniversity
@tikvahethAfaanOromoo
@tikvahethmagazine
@tikvahethsport
@tikvahethiopiatigrigna

#ኢትዮጵያ
Download Telegram
ወደ ሥራ ያልገቡ 1,178 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰረዘ...

• 26 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ተመዝግቧል

ባለፉት ስድስት ወራት ውስጥ ያለ በቂ ምክንያት ወደ ሥራ ያልገቡ 1ሺ178 ፕሮጀክቶች ፈቃድ መሰረዙን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽን አስታወቀ። በግማሽ ዓመት 26 ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት መመዝገቡ ተጠቁሟል።

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ኢንቨስትመንት ኮሚሽነር አቶ አብዱልፈታ የሱፍ በተለይም ለአዲስ ዘመን ጋዜጣ እንዳብራሩት፤ በግማሽ በጀት ዓመቱ ዘርፈ ብዙ የኢንቨትመንት ፕሮጀክቶች ፈቃድ ለመስጠት ታሳቢ ተደርጎ ሰፊ እንቅስቃሴ የተጀመረ ሲሆን ለ1ሺ500 ኢንቨስትመንቶች ፈቃድ ለመስጠት ታቅዶ ሲሰራ ቆይቷል።

ይሁንና በአሁኑ ወቅት ከእቅዱ በላይ ልቆ 1 ሺ 598 ፈቃድ ለመስጠት ተችሏል። የኢንቨስትመንት ፈቃድ ወስደው በተገቢው ጊዜ ወደ ሥራ ባልገቡት ላይ እርምጃ ተወስዷል። የኢንቨስትመንት አዋጁ በሁለት ዓመት ውስጥ ወደ ሥራ ካልገቡ ፈቃድ የሚሰረዝ መሆኑን ያስቀመጠ ሲሆን፤ በግማሽ ዓመቱ 1ሺ178 ፕሮጀክቶች ፈቃድ ተሰርዟል።

(አዲስ ዘመን ጋዜጣ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
#Election2012

"ብልፅግና ፓርቲ ምርጫ (2012 ዓ/ም) በዚህ አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም አለው" - አቶ ብናልፍ አንዷለም

የብልፅግና ፓርቲ የ 2012 ብሄራዊ ምርጫ በያዝነው አመት እንዲካሄድ ጠንካራ አቋም መያዙን አስታውቋል። የፓርቲው የስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ ትናንት በወቅታዊ ሀገራዊ ሁኔታ እና በሀገራዊ ምርጫው ዙሪያ ተወያይቶ የተለያዩ ውሳኔዎችን ማሳለፉንም ነው የፓርቲው ፅህፈት ቤት ሀላፊ አቶ ብናልፍ አንዷለም በዛሬው እለት በሰጡት መግለጫ የጠቆሙት።

ብልፅግና ፓርቲ በምርጫው ዙሪያ የአቋም ለውጥ አላደረገም ያሉት ሀላፊው፤ ፓርቲው ምርጫው በዚህ አመት መካሄድ አለበት የሚል እምነት እንዳለው አብራርተዋል። ይህ ማለት ግን ፈታኝ ነገሮች የሉም ማለት አለመሆኑን ጠቅሰው፥ ስራ አስፈፃሚው በስብሰባው የምርጫው ስጋቶች እና መልካም እድሎች ዙሪያ በስፋት መክሮ የመፍትሄ ውሳኔዎችን ማሳለፉን ነው አቶ ብናልፍ ያነሱት።

ብልፅግና ፓርቲ ተፎካካሪ የፖለቲካ ፓርቲዎችም ሆነ ህብረተሰቡ ከምርጫው መካሄድ ጋር ተያይዞ የሚያነሷቸው ስጋቶችን እንደተወያየባቸው የጠቀሱት ሀላፊው፤ የምርጫው መካሄድ አልያም መራዘም የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እና ጉዳቶች ላይ በስፋት መምከሩን ተናግረዋል።

https://telegra.ph/PP-01-04

(ኤፍ ቢ ሲ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የትግራይ ክልል ምክትል ርዕሰ መስተዳድርና የህወሃት ሊቀመንበር ዶ/ር ደብረጽዮን ገ/ሚካኤል...

"ጉባዔው ቀጣይ የህወሃትን ህልውና የሚወስን ልዩና ታሪካዊ ጉባዔ ነው። ጉባኤው በህወሃት ፍላጎት የተጠራ ሳይሆን፤ በአገሪቷ ያለው ሁኔታ አስገድዶ የተጠራ አስቸኳይ ጉባዔ ነው።"

#BBC
@tikvahethiopia @tikvahethiopiaBot
የህወሓት አስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ...

"ኢህኣዴግ በህወሓትና ብኣዴን ተመስርቶ በብኣዴን ኣዴፓ ፈረሰ።" ዶክተር ደብረፅዮን ገ/ሚካኤል /የትግራይ ክልል ምክትል ርእሰ መስተዳድር/

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Election2012

«በመድረክ የሚመራ መንግሥት እንዲቋቋም እንሰራለን» - የኦፌኮ ሊቀ-መንበር መረራ ጉዲና

የኦሮሞ ፌደራላዊ ኮንግረስ ( ኦፌኮ ) በቀጣዩ ምርጫ (ምርጫ 2012) ስልጣን ለመጋራት እና ጥምር መንግስት መመስረት የሚያስችል ድምጽ ለማግኘት፣ ከተሳካም መድረክ የሚመራው መንግስት እንዲዋቀር እየሰራ መሆኑን ሊቀመንበሩ ፕሮፌሰር መረራ ለጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ ተናግረዋል።

ፓርቲው በቅርቡ ወደ ፓርቲው ለተቀላቀለው ጀዋር መሃመድ እና ሌሎች ግለሰቦች ዛሬ አቀባበል ያደረገ ሲሆን ፣መንግስት ከክራይ ቤቶች ሜክሲኮ አደባባይ አካባቢ የሰጠውን ቢሮውንም አስመርቋል።

(የጀርመን ድምፅ ሬድዮ ጣቢያ)
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
#Election2012

መኢአድ በባህር ዳር...

የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት/መኢአድ/በፖለቲካዊ  መስመሩን እና ወቅታዊ የሀገሪቱን ጉዳይ ዙሪያ ዛሬ ከአባላቱና ደጋፊዎቹ ጋር ዛሬ በባህርዳር ከተማ ውይይት አካሂዷል።

https://telegra.ph/ETH-01-04

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
Recep Tayyip Erdoğan... የቱርክ ምክር ቤት ራቺብ ጣይብ ኤርዶኻን ወደ ሊቢያ ወታደር ለማዝመት ያቀረቡትን ጥያቄ አጽድቋል። የግብጽ ውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤት ከተ.መ.ድ የጸጥታ ምክር ቤት የውሳኔ ሐሳብ የሚቃረን ተቀባይነትም የሌለው ሲል የምክር ቤቱን ውሳኔ ተቃውሟል። (ጋዜጠኛ እሸት በቀለ) @tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ሊቢያ ከቱርክ ጋር ያላትን ግንኙነት አቋረጠች...

የሊቢያ ምክር ቤት በዛሬው ዕለት ሀገሪቱ ከቱርክ ጋር ያላት ግንኙነት እንዲቋረጥ መወሰኑን አል-አረቢያ ዘግቧል። ምክር ቤቱ ከዚህ በተጨማሪም በቱርክ የሊቢያ ኤምባሲና በሊቢያ የቱርክ ኤምባሲ እንዲዘጉ ወስኗል።

#AlAin
@tikvahethiopia @tikvahethiopia
በ440 የተማሪዎች እርምጃ ተወሰደ...

በመንግስት ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በተከሰቱ ግጭቶች ውስጥ ተሳትፈዋል በተባሉ 440 ተማሪዎች ላይ ህጋዊና አስተዳደራዊ እርምጃ መወሰዱን የሳይንስ ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አስታወቀ።

ሚኒስቴሩ ከፌዴራል ፖሊስ ኮሚሽን ጋር በመሆን በከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች ለመፍታት አየተከናወኑ ባሉ ስራዎችና ቀጣይ እርምጃዎች ላይ መግለጫ ሰጥቷል።

እርምጃው ከማስጠንቀቂያ ጀምሮ ከትምህርት ገበታቸው እሰከማገድ የሚደርስ ቅጣት የሚደርስ መሆኑም ተመልክቷል። በዚህ መሰረት እርምጃ ከተወሰደባቸው ተማሪዎች ውሰጥ ከ170 በላይ የሚሆኑት የአንድ ዓመት እገዳና ሙሉ በሙሉ ከተቋማቱ ማባረርን ያካትታል።

ከ270 በላይ ተማሪዎች ደግሞ የመጨረሻ ማስጠንቀቂያ እንደተሰጣቸው ሚኒስትር ዴኤታው ዶክተር ሳሙሄል ክፍሌ ተናግረዋል። ከዚህም በተጨማሪ በ10 መምህራንና የአስተዳደር ሰራተኞች ላይም እርምጃ መወሰዱን ጠቁመዋል።

ባለፈው ጥቅምት ወር በወልዲያ ዩኒቨርስቲ በተማሪዎች መካከል በተከሰተ ግጭት የተማሪዎች መሞትን ተከትሎ በሌሎች የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች አለመረጋጋቶች እየተስተዋሉ መሆኑ ይገለጻል።

(ኢዜአ)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የሴራ በዓል በአዲስ አበባ...

የሀላባ ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ የሴራ በዓል በአዲስ አበባ ተከብሯል፡፡ ኢ/ር ታከለ ኡማ በበዓሉ ላይ ተገኝተው በአዲስ አበባ ለሚኖሩ የሃላባ ብሔረሰብ ተወላጆች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡

በአዲስ አበባ የሚኖሩ የሃላባ ብሔረሰብ ተወላጆች የከተማ አስተዳደሩ የሚሰራቸውን ስራዎች በቀጣይነት እንደሚደግፉ ተናግረዋል፡፡

በበዓሉ ላይ ኢ/ር ታከለ ኡማን ጨምሮ የመንግስት ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎች ፣ የብሔረሰቡ ተወላጆች እንዲሁም ሌሎች ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታዳሚ ሆነዋል፡፡ የሴራ በዓል በየዓመቱ በታህሳስ ወር ወይም በብሄረሰቡ አጠራር መንገሳ በሚባለው ወር የሚከበር በዓል ነው፡፡

(Mayor Office AA)
@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
በነገራችን ላይ...

ዛሬ ጠዋት በአዲስ አበባ ከተማ 6ኛው የብዙሃን ስፖርት መርሃ ግብር ተካሂዶ ነበር። የከተማ አስረዳደሩ በፌስቡክ ገፁ እንዳሰራጨው መረጃ ከሆነ የማስ ስፖርቱ ብዙ ሰው በማሳተፍ በአፍሪካ የመጀመሪያ የማስ ስፖርት ሆኖ መመዝገቡን ይጠቁማል፡፡ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ስፖርት ኮሚሽን አዲስ አበባ ከተማ በማስ ስፖርት ላስመዘገበችው ድል የእውቅና የምስክር ወረቀት እንዳበረከተም ተገልጿል፡፡ የከተማ አስተዳደሩ አዲስ አበባ ይህን ድል እንድትቀዳጅ ለሰሩ ፣ ላስተባበሩ እና ለተሳተፉ ሁሉ ምስጋናውን አቅርቧል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የቲክቫህ ኢትዮጵያ 5ኛው ዓመት የመማሪያ መፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ (ሀዋሳ እና አካባቢዋ)...

- ከአለን ኢትዮጵያ እና ከኢትዮጵያዊነት የበጎ አድራጎት ማህበራት ጋር በመተባባር በተሰራው የመፅሃፍት ማሰባሰብ ዘመቻ ከ1,000 በላይ የመማሪ የመፅሃፍት ማሰባሰብ ተችሏል።

- መፅሃፉ የተሰባሰበው ከሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች፣ የግል ትምህርት ቤት ተማሪዎች ነው።

- ከተሰበሰበው መፅሃፍ ውስጥ 300 የሚደርሰውን በትላንትናው ዕለት በሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ስር ለሚገኝ ቤተ መፅሃፍት ገቢ አድርገናል።

በቀጣይ፦

- ቡሌ ሆራ እና ሶዶ ከተማ ውስጥ ለሚገኙ ቤተ መፅሃፍት ተመሳሳይ እገዛ የምናደርግ ይሆናል።

- እገዛችን ምንም ትንሽ ብትሆንም ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ ስራ መጠቀም እንደምንችል ለማስታወስ ያህል ነው።

#ቲክቫህቤተሰቦች #አለንኢትዮጵያ

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
የምስጋና ወረቀት ለቲክቫህ ቤተሰቦች...

- በ5ኛው ዓመት የመፅሃፍ ማሰባሰብ ዘመቻ ለተሳተፋችሁ የቲክቫህ ቤተሰቦች ከሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምስጋና ቀርቦላችኃል።

- ባለፈው ዓመት ከአለን ኢትዮጵያ ጋር በመተባበር 1000 መፅሃፍት በማሰባሰብ አርቤጎና እና ወንዶገነት ለሚገኙ ቤተ መፅሃፍት እገዛ መደረጉ አይዘነጋም። ቀደም ብሎም 2007,2008,2009,2010 ለሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ቤተ መፅሃፍ እገዛ ለማድረግ ጥረት አድርገናል።

- እንዲሁም በዘንድሮው ዓመት ሰበታ ለሚገኝ ቤተ መፅሃፍ ከቅን ድል ኢትዮጵያ ጋር በመሆን 700 መፅሃፍ እገዛ አድርገናል።

- በሌሎች በርካታ ከተሞች በቀጣይነት ከወጣቶች እና ከወጣት ማህበራት ጋር የምንሰራ ይሆናል። ትውልዱ የማያልቅ፣ የማይጠፋ ሀብት ለማውረስ ነው የምንሰራው። እገዛችን ትንሽ ብትሆንም ማህበራዊ ሚዲያን ለበጎ አላማ መጠቀም እንደምንችል ለማስታወስ ነው።

በዘንድሮ ዓመት ከፍተኛው ድርሻ ለተጫወቱት የአዲስ አበባ ነዋሪዎች እና የሀዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ምስጋና እናቀርባለን!

የቲክቫህ ቤተሰቦች!

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
ለ120 ነዋሪዎች የተገነቡ 25 ቤቶች ተሰጡ...

የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለ120 የአዲስ አበባ ነዋሪዎች የተገነቡ 25 ቤቶችን የአዲስ አበባ ከተማ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ ለነዋሪዎች ተሰጥተዋል፡፡

ቤቶቹ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ጨርቆስ በሚባለው አከባቢ ለመኖር አስቸጋሪ በሆነ ሁኔታ ውስጥ ለነበሩ አቅመ ደካማ ነዋሪዎች ኮንትራክተሮችን በማስተባበር የተገነቡ ናቸው፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
TIKVAH-ETHIOPIA
#CNNHero2019 #FreweiniMebrahtu በአዲስ አበባ ከተማ በመንግስት ትምህርት ቤት ለሚማሩ ሴት ተማሪዎች ሞዲስ እና ሌሎች የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን በነጻ ለማቅረብ የከተማ አስተዳደሩ ከተለያዩ አካላት ጋር በቅንጅት እየሰራ ይገኛል። በዚሁ መሰረት የፊታችን ታህሳስ 28 ቀን 2012. ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ መርሃ ግብር መዘጋጀቱን አስተባባሪዎቹ በሰጡት መግለጫ ተናግረዋል።…
ፍሬወይኒ መብርሃቱ...

ታህሳስ 28 በሚሊየም አዳራሻ ሊደረግ የነበረው የ2019 የCNN የዓመቱ ጀግና ፍሬወይኒ መብርሃቱ የክብር አቀባበል እና የቁሳቁስ ማሰባሰቢያ ስነ ስርዓት የቀን እና የቦታ ለውጥ ተድርጎ ዛሬ በኤሊያና ሆቴል እጅግ በደማቅ ስነ ስርዓት እየተከናወነ ይገኛል።

ቆይት ብለን ዝርዝር መረጃዎችን እንሰጣችኃለን!

PHOTO : TIKVAH-ETH

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጠ/ሚ ዶ/ር አብይ አህመድ...

በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለው ኤክሳይስ ታክስ በሲጋራ እና በመጠጥ እንዲሁም ባገለገሉ መኪኖች ላይ ያስቀመጠው ታክስ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር መቅርፍ በዋናነት ታሳቢ ያደረገ መሆኑን ጠቅላይ ሚስትር ዶክተር አብይ አህመድ ገልፀዋል፡፡ ጠቅላይ ሚኒስትሩ የኤሌክትሮኒክስ አንድ መስኮት የአገልግሎት ስርአት መርሃ ግብርን በይፋ ባስጀመሩበት ወቅት እንዳሉት በረቂቅ ደረጃ ላይ ያለው ኤክሳይስ ታክስ በሲጋራና በመጠጥ በዜጎች ላይ እየደረሰ ያለውን ችግር ለመቅረፍ ያለመ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia
"...ጉባኤው በድል ተጠናቋል" - ህወሓት

የህወሓት የአስቸኳይ ድርጅታዊ ጉባኤ፣ "ጉባኤ ፅናትና መኸተ" በድል ተጠናቋል ሲል ድርጅቱ አስታውቋል። ዝርዝር ጉዳዮች ከደቂቃዎች በኃላ ለህዝብ እንደሚያሰራጭ ገልጿል።

@tikvahethiopiaBot @tikvahethiopia